September 12, 2023
6 mins read

ኢትዮጵያውያን ሊታገሉት የሚገባ ወንጀል ነው! – አንዳርጋቸው ጽጌ

የአማራ ሕዝብን በማንነት ማጥቃቱ ጦርነት ባልነበረበት ወቅትም ያልተቋረጠ ወንጀል ሆኖ ኗሯል። ከወለጋ፣ ከሸገር ከተማና ከአዲስ አበባ በጅምላ ተፈናቅሏል። በከተሞች ሳይቀር ቤቱ እየፈረሱ ተባርሯል። አማራው በማንነቱ እየተጠቃበት ያለውን ሁኔታ በምክር ቤት የተመሰከረ ጉዳይ ነው።

377881396 682584297228013 185565906492051971 nየአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ ዶክተር ካሳ ተሻገር ከመታሰሩ በፊት በነበረ የምክር ቤት ስብሰባ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎች በገፍ መታሰራቸውን በምክር ቤት ተናግሯል።

በተመሳሳይ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በፓርላማ ባደረገው ንግግር የኦሮሞን ህዝብ በአማራ ህዝብ ላይ የማነሳሳት ተግባር እየተፈፀመ መሆኑን ተናግሯል።

በመንግስት የሚተዳደረውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ጨምሮ የአገር ውስጥና የውጭ የሰብአዊ መብት ተቋማት የአማራ ተወላጆች በጅምላ እየታሰሩ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ጦርነቱ አማራ ክልል ላይ ሆኖ እያለ አስቸኳይ ጊዜያዊ አዋጁ ከአማራ ክልል ውጭ እንዲተገበር ተደንግጓል። ይህን ተከትሎም ቀደም ብሎ ከነበረው በከፋ የፓርላማ አባላትን የመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ፣ ምስኪን ሰርቶ አደሮችን በማያውቁት ጉዳይ እያፈሱ ማጎሪያ ውስጥ አስገብተዋቸዋል። በርካታ የአማራ ተወላጆች ኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባ፣ ደቡብ፣ ሲዲማ፣ አፋር ክልል ሰብአዊ ክብርን በሚነካ ሁኔታ ታስረው ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህል ዛሬ በተቆርቋሪዎች በኩል ወጥቶ ማህበራዊ መዲያ ላይ እየተዘዋወረ የሚገኝ ምስል ገላን አካባቢ የሚገኝ ካምፕ በጅምላ የታሰሩ አማራ ተወላጆችን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። የገላን ካምፕ አሰቃቂ ምስል ወጣ እንጅ ሌሎች ከዚህም የከፉ መኖራቸው ተሰምቷል።

የአማራ ተወላጆች በሌሎች ክልሎች ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ታፍሰው በብር ሸለቆ፣ በሸዋ ሮቢት እንዲሁም በየወረዳውና በየከተማው በሚገኙ ጣቢያዎች ታስረው መከራ እየተቀበሉ ይገኛሉ። ይደበደባሉ፥ ምግብ አያገኙም።

377447767 682584650561311 1123166842110772425 nከአማራ ክልል፣ ከኦሮሚያ ክልል እና ከአዲስ አበባ የታፈሱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የኮተቤ ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲ፣ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ፣ የአዳማ ዩኒቨርስቲ፣ የአርሲ ዩኒቨርስቲ መምህራንን እንዲሁም በአዲስ አበባ የተለያዩ ት/ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንን ጨምሮ፥ የአማራ ብልጽግና አባላት የሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ባለ ሀብቶች፣ የቀን ሠራተኞች፣ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት (የአብንና የኢዜማ አባላትን ጨምሮ) … በአጠቃላይ በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች በአዲስ አበባ በሁሉም እስር ቤቶች፣ በመንግሥት መጋዝኖች፣ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ መጋዝኖች፣ በገላን፣ ቡራዩ፣ ሰበታ፣ ገፈርሳ፣ ዓለም ገና ወዘተ… ከተሞች ማጎሪያ ጣቢያዎች እንዲሁም በፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋማት ታስረው እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ብዙዎቹን የማሰቃያ ጣቢያዎች የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እንዳይጎበኟቸው ተደርገዋል።

377447795 682584550561321 2994001384227234185 nአማራ በመሆናቸው ብቻ ከያሉበት እየታፈሱ የታሰሩትና አሁንም የሚታሰሩት ወገኖች ፍፁም ዘረኛ የሆነ ስድብ ይሰደባሉ፤ ይደበደባሉ፤ በረሃብ ይቀጣሉ ወዘተ…

“ማንም አይደርስልህም፤ ፋኖ ያስፈታህ፤ 4 ኪሎ ሲያምርህ ይቀራል” ወዘተ… እየተባሉ ይሰደባሉ። በምርመራ ወቅት ከፍተኛ ድብደባ ይፈጸምባቸዋል።

በሌላ በኩል የአማራ ባለሀብቶችን ገንዘብ ክፍሉና ትፈታላችሁ በማለት ገንዘብ እየተቀበሉ ነገር ግን እንኳን ሊፈቷቸው ፍርድ ቤትም አያቀርቧቸውም።

እስሩ በተጠቀሱት ቦታዎች ብቻ ሳይሆን በሐዋሳና በሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች እንዲሁም በቤንሻንጉል እና በአፋርም ጭምር የተከናወነ ነው።

ይህ የጅምላ እስርና ማሰቃያ ዜጎች በማንነታቸው ተለይተው የተጠቁበት፣ ነገ በማንም ላይ የሚደርስ፣ በንፁሃን ላይ እየተፈፀመ ያለን የጭካኔ ወንጀል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊታገለው የሚገባው ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop