ኢትዮጵያ የዓለም ፩ ክፍል አባል አገር ናት ፡፡ የአፍሪካ ክፍለ ዓለም ከራሳቸዉም ሆነ ከሌላዉ ዓለም ሠወ መማር የተሳናቸዉ ዞትር በሁሉም ትክክለኛ እኛ የሚሉ በአዕምሯቻዉ ሳይሆን በሆዳቸዉ የሚኖሩባት ምድር ናት ፡፡
በአፍሪካ ህዝብ ከመሪዎችም ከሚደርስበት መከራም አስቀድሞ ከሚመጣበት ችግር ለመከላከል ቀድሞ ይረዳል ነገር ግን ሰሚ ያጣ ጩኸት ሆኖበት እንደ ቁራ ሲቆጠር ባለንበት ዘመን ደርሷል፡፡
ህዝቡም የመሪዎችን በደል እና ግፍ ተሸክሞ የመከራ ዘመኑን መግፋት ሳይወድ በግድ ተጭኖበት ይገኛል ፡፡ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ከትናንቱ እ.ኤ.አ. 2010 የአረብ ህዝቦች የህዝባዊ መንግስጥ ጥያቄ አብዮት መማር አለመቻላቸዉ የማያዉቀዉትን እና የማይችሉትን ኃላፊነት ለፖለቲካ ስልጣን ሲባል ብቻ መሸከማቸዉ ህዝብን እና አገርን ለማገልገል ሳይሆን ለመገልገል መሆኑ ነዉ ፡፡
ለአብነት ከሊቢያ አስከ ተኒዚያ፣ ከሶርያ አስከ አልጀሪያ፣ ከየመን አስከ ባህሪን በነበረዉ ህዝባዊ ዕንቅስቃሴ ማዕበል ለዘመናት ፉፁም እና አይሰሳት አድርገዉ ያስቡ የነበሩ የዕድሜ ልክ የሀገር እና ህዝብ ሸክሞች አይናቸዉ እያየ ግፍ እና በደል የወለደዉ ህዝባዊ ማዕበል በትዉልድም በታሪክም እንዳይነሱ አድርጎ ላይመለሱ ጠርጓቸዋል ፡፡
በነሱ የግል ፍላጎት እና የስልጣን ጥም በተነሳ ህዝባዊ ማዕበል አገራቸዉን እና ህዝቡን ለማያባራ መከራ እና ሰቆቃ የግጭት ዕሳት ላይ ጥደዉት ወደ ማይቀረዉ መንገድ አልፈዋል ፡፡
ከአፍሪካም ምስራቅ አፍሪካ ከዚህ መማር አለመቻል በከፍተኛ አዚም እና ዕንቅልፍ ከሚገኙት ሱዳን እና ኢትዮጵያ ላይ የትክከለኛነት አባዜ ስር ሰዶ እና ተጋምዶ ቀጥሏል ፡፡
ይህም ለሁለቱ አገሮች በሽታ መድኃኒት የሆነዉ መነጋገር እና መግባባት እንዳይኖር የማይድን ፖለቲካም ሆነ ፖለቲከኛ የማይሰሳት አመለካከት ሰለባ ሆኖ መገኘት ነዉ ፡፡
የሱዳንን በአገሪቷ እንደ ሰደድ ዕሳት የተቀጣጠለዉን የጥፋት ዕሳት ትተን ወደ እኛ ስንመለስ በኢትዪጵያ የፖለቲካ ስርዓት ታሪክ ኢህአዴግ ስህተት የሚባል የማያዉቅ እና ተሳስቶ የማያዉቅ አድርጎ ይልቅ ህዝብ እና አገር ፣ታሪክ፣ ትዉልድ…..ይሰሳታል የሚል መሆኖ ላለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት በላይ አገሪቷን እና ህዝቧን እንደ ግል ዕቃ በመቁጠር ከሳሽ እና ወቃሽ ሆኖ የህዘቡን ጩኸት ሲቀማ አንድም ጊዜ ስህተቱን ተቀብሎም ሆነ አምኖ አያዉቅም ፡፡
ለዚህ ሌላኛዉ ድጋፍ ሰጪ ብአዴን በኢትዮጵያ እና ህዝቧ ላይ በተደጋጋሚ ለሆነዉ እና ለደረሰዉ መከራ ተባባሪ ከመሆን በላይ የሕዝብን የትግል እንቅስቃሴ አቅጣጫ በማስቀየር እና የሕዝብን መብት ፣ የአገሪቷን ብሄራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት የማያርፈዉ ሌላዉ የምንጊዜም ትክክለኛ ድርጂት ተቀፅላ ነዉ ፡፡
ብአዴን በህዝብ እና አገር ስም ተተንርሶ በህዝብ እና አገር ላይ ያደረሰዉ መከራ በቁጥር መግለፅ ቢሆንም አዞትሮ ትክክለኛነቱን የሚገልፅበትን እና ክህደቱን ከነድክመቱ የሚሸፋፍንበት ፡-
1ኛ) ቅድመ ሽግግር ጊዜ ፡
- በአብዛኛዉ ከበርኃ ትግል አስከ ኢህአዴግ ምስረታ ጊዜ ድረስ ትልቁን ድርሻ የነበረዉን የዓማራ ህዝብ ተጋድሎ ወደ ኋላ መጎተት፡
2ኛ) በሽግግር ምስረታ
- በሽግግር ምስረታ ጊዜ አብዛኛዉን ኢትዮጵያዊ በተለይም የዓማራዉን ማህበረሰብ በገዥ እና ተገዥ ፣ በጨቐኝ ተጨቋኝ፣ በነበሩት ስርዓተ መንግስት ወገናዊነት ፣ በትምክህትኝነት…..ወዘተ የዉሸት ትርክት በማግለል ፀረ- አንድነት እና ዓማራ አስተሳሰብ ያካተተ ሽግግር መንግስት እንዲቋቋም በማድረግ የነበረዉ ሚና ከፍተኛ የነበር መሆኑ ፡፡
- በሽግግር መንግስት ምስረታ የተደገፉ እና የተረሱ ፣ ጨቋጭ እና ተጨቋ ፤ያለፈዉ ስርዓት የቀደሙት ሥርዓት ተቀጥላ በማለት በህዝቦች እና በዜጎች መካከል ልዩነት የሚፈጥር ስምምነት ላይ መሳተፍ እና መስማማት ፡
- በዚህም የዓማራ ህዝብ በመራር ትግል ያስኘዉን ድል መንጠቅ እና መበደል በሚያስችል ሁኔታ መስማማት ይገኙበታል ፣
- ለረጂም ዘመናት የኢትዮጵያ ህዝብ አለኝታ እና መከታ የነበሩ ብሄራዊ እና ህዝባዊ ተቋማት ያለምንም በቂ እና አሳማኝ ምክነያት ኢትዮጵያዊ ስም ፣ምግባር እና ተግባር የነበራቸዉ በመሆናቸዉ ብቻ በጥላቻ እንደ ዕድር ድንኳን በአንድ ድምፅ እንዲነቀሉ በማድረግ ግንባር ቀደም ሚና በመጨዋት ከዚያ ዕለት ጀምሮ አስካሁን ኢትዮጵያዊ ስም እና ማንነት ያላቸዉን ሁሉ በማጥፋት ወደር የለሽ ትብብር ሲያደርግ መሰሳት የሚባል የማያዉቅ መሆኑ ፡፡
3) ድህረ ሽግግር መንግስት አስከ ዛሬ ፡
- በህገ ኢህአዴግ መሰረት ግንባር ቀደም ትግል ያደረጉት ታጋዮች በተለያየ ምክነያት እንዲገለሉ ሆኗል፣
- ኢትዮጵያዉያን ኢትዮጵያዊ በመሆናቸዉ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለአገር አንድነት በማገልገላቸዉ ብቻ ከዜግነት መብቶች በሙሉ እንዲታገዱ ፤ እንዲወገዱ ተደርጓል፣
- ክልሎች ሲመሰረቱም ሆነ ኤርትራ ከናት አገሯ ስትለይ የህዝብ ይሁንታ እና አስተያየት እንዲጠየቅ አልሆነም ፡
- ኢትዮጵያ በታሪኳ እና በተፈጥሯዋ የወደብ ባለቤት የነበረች አገር በቆየ ጥላቻ እና በሴራ የነበሩትን የኢትዮጵያ ዕሴቶች የማፈራረስ ዕኩይ ፍላጎት የተነሳ ወደብ አልባ እንድትሆን በማድረግ ብአዴን እና ኢህአዴግ ትልቁን ሚና ተጫዉተዋል ነገር ግን በዕነርሱ ቋንቋ ስህተት የለበትም ፣
- በኢትዮጵያ በሁሉም የአስተዳደር ክልልሎች አንድም ልዩ ዞን በቋንቋ ምክነያት ሳይኖር በዓማራ ክልል ልዩ ዞኖች በማቋቋም ኢትዮጵያዊነትን በማጥፋፋት ብአዴን ዓሜን ባይ መሆን ፣
- የዓማራ ክልል ስያሜ ብዙ አማራጮችን ማየት እተቻለ ብአዴን እንደ ስሙ ዓማራ ክልል ብሎ የሰየመዉን ትህነግ አሜን ብሎ በመቀበል እሱንም በላቲን ቋንቋ/ሆሄ Amhara ማለት በትክክለኛዉ “ AMARA ” ማለት ሲቻል ይህም ለአገር እና ህዝብ የሚረባ ነገር ከመከወን የማይሆነዉን ይሆናል፤ ስህተቱን ወይም ዉሸቱን ዕዉነት…በማለት ተመሳሳይ ማንነት፣ ወግ ፣ ባህል እና አገራዊ አንድነት የነበረዉን ህዝብ የሚለያይ አደረጃጀት መቀበል፣
- በተለያየ ጊዜ እና ዘመናት የዓማራ ህዝብ ለአገር ግንባታ እና ዕድገት የነበረዉን ጉልህ ድርሻ በማሳጣት የፖለቲካ ተሳትፎዉን በመገደብ ወደ ኋላ መጎተት ፣
- በራሱ አገር ዓማራ መጣተኛ እና ጥገኛ እንዲሆን እንዲሁም በጥላቻ እንዲሳደድ በማድረግ ከፍተኛዉን ድርሻ ብአዴን ይወስዳል፣
- በዘመነ ስቃይ /ኢህአዴግ በተካሄዱ ሁለት ዋና ዋና ጦርነቶች (በኤርትራ ፤ኢትዮጵያ ጦርነት ፣ በትግራይ የዓማራ ህዝብ ወረራ እና ምዝበራ የእብሪት ጦርነት ) ዓማራ ህዝብ ራሱን ፣አካባቢዉን እና አገሩን በመከላከል ረገድ የነበረዉን ታላቅ አበርክቶት የዘነጋ መሆን ፣
- ከትግራይ /ትህነግ ወረራ ማግስት ወረራዉን በመቀልበስ ከፍተኛ ድርሻ የነበረዉን የዓማራ ህዝብ ( ልዩ ኃይል፣ ህዝባዊ ተጋድሎ ዓርማ የሆነዉን የህዝብ አደረጃጀት /ፋኖ….) ትጥቅ ማስፈታት “በጥቁር ጠበንጃ ” ሰበብ ለደረሰበት እና እየደረሰበት ላለዉ ምስቅልቅል ቸልተኛ ከመሆን በላይ ህዝቡ እና አካባቢዉ ጦርነት እንዲታወጂበት ፈቃድ የሰጠዉ ብአዴን ይህ ለርሱ ስህተት ሳይሆን ከአገር እና ህዝብ ይልቅ ለጥቅም እና ለከንቱ ዉዳሴ እንዲኖር የተፈጠረ መሆኑን አረጋግጧል፣
- “ በጥቁር ጠብመንጃ አገሬ ሆነች እያደር ጥጃ ” ሲባልላት ብአዴን /ኢህአዴግ ዛሬም ትክክል ነዉ ፡፡
የኢትዮጵያ እና የዜጎች የማያባራ ሁለንተናዊ የዘመናት መከራ ( ባርነት፣ ድህነት ፣ግጭት፣ ስደት፣ ዉርደት፣ ሞት …) ይቆም ዘንድ ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት በሞት እና በስህተት ጎዳና እየነጎደ ለዚህ ሁሉ አገራዊ ምስቅልቅል ምክነያት ሌላዉን በመክሰስ እና በመዉቀስ ቀዳሚ የማይገኝለት ከአዉራ ፓርቲ ወደ ፍፁም ፓርቲ ራሱን ያበቃ በዚህች አገር ዕዉነተኛ እና ዘላቂ ፍትህ፣ ዕኩልነት እና አንድነት ይሰፍን ዘንድ ዓለም እና የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠይቀዉ “ፍጡር መሆኑን አዉቆ መሰሳቱን ተቀብሎ ኃላፊነት በዉሰድ ለአገር እና ለህዝብ በሚጠቅም ሁኔታ ላይ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስማማት እንዲዘጋጂ በቅን መንፈስ ሊያስብበት እና ሊቀበለዉ ይገባል ” ይህም ከምንም በላይ ለህዝብ እና አገር ባለዉለታነቱን በተግባር የሚያሳይበት እና የሚያረጋግጥበት ወርቃማ ታሪካዊ አጋጣሚ ይሆናል ፡፡
Allen
አንድነት ኃይል ነዉ !