September 11, 2023
4 mins read

ለውድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ፥ የኢትዮጵያ 2016 አዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጭ

Moresh

Moresh 1September 10, 2023

ቁጥር: MW-00723

 

ለውድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ፥ የኢትዮጵያ 2016 አዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጭ፤ እንኳን ለእንቁጣጣሽ አውደዓመት በሰላም አደረሳችሁ!!!

በሞረሽ ወገኔ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና በራሴ ስም መጪው የኢትዮጵያ 2016 አዲስ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የብልጽግና፣ የደስታ፣ በተለይም የጤና እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታችንን እየገለጽን፤ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያም ለልጆቿ አንድነትንና ትብብርን ሰጥቶ፣ ከቤታቸው ወጥተው በሰላም የሚገቡበት፣ ከቤት ንብረታቸው ተገፍተው የወጡ እንዲሁም በማንነታቸውና በእምነታቸው ተለይተው የተፈጁ ፍትህ የሚያገኙበት፣ ያዘኑ የሚጽናኑበት፣ የተራቡ የሚመገቡበት፣ የታመሙ ፈውስን የሚያገኙበት ጊዜ እግዚአብሔር ያሰፍንልን ዘንድ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን።

በተለይ በሲቪክ ድርጅትነት ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ከቆመለት ራዕይ አንጻር፥ በኢትዮጵያ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ በሀገራችሁ የትኛውም ጥግ ተዘዋውራችሁ የመሥራት፣ የመበልጸግ፣ ቤተሰብ የመመስረትና፣ በሰላም የመኖር መብታቸችሁ ይከበር ዘንድ በአንድነት እንድትቆሙ፤ አንዱ ኢትዮጵያዊ የሌላው ኢትዮጵያዊ ጠባቂ መሆኑን በማሰብና ነባር እሴቶቻችሁን ተጠቅማችሁ ሁላችሁም የወገን አልኝታና መከታ በመሆን ይህን ፈታኝ ጊዜ በተለይም በኦሮሚማ / ብልጽግና የአብይ አህመድ አሊ አገዛዝ በአማራው ላይ እየፈጽመ ያለውን የጥፋት ወረራ ፋኖ በተባበረ ክንድ ሙሉ በሙሉ ቀልብሶ ይህን የፋሽስት አፓርታይድ ሥርአት ከኢትዮጵያ የምታስወግዱበት ወቅት ይፋጠን ዘንድ የእግዚአብሔር ፍቃዱ እንዲሆን ልባዊ ምኞታችን ነው።

በተለይ መጪው 2016 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት፣ በፋኖ ቀንዲልነት እየተካሄደ ያለው የአማራ የህልውና ትግል በፍጹም አሸናፊነት የሚጠናቀቅበት፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት የፋሽት አፓርታይድ አገዛዝ መዋቅራዊ አጣብቂኝ የምትወጣበት፤ መላው ዜጎቿ መሰረታዊ ሰብአዊ መብታቸው የሚከበርባት፣ በሰላም ከቤታቸው ወጥተው የሚመለሱባት፣ ፍትህ

የሚያገኙበት፣ ለእኩልነትና ዲሞክራሲ የሚያደርጉት ትግል ፍሬ የሚያፈራበት፣ በተለይም አማራው ወገናችን በተለያዩ አቅጣቻዎች ከሚደረገበት የጥፋት ወረራና በመንግስታዊ ፖሊሲ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳትን ጨምሮ ሰለባ ከሚፈጽምበት አሰቃቂ ወንጀሎች ለአንድዬና ለመጭረሻ ጊዜ ተላቆ፤ ለዘመናት እንደ ድርና ማግ በመሆን አብሮ ከኖራቸው ነገዶች ጋር ተባበሮ የኢትዮጵያን ትንሳኤ እውን የሚያደርግበት ዘመን እንዲሆን የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

በድጋሚ መልካም የ2016 አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ!!!

 

ከአክብሮት ጋር

Moresh

 

 

 

አረጋኸን ንጋቱ (ዶ/ር)

 

የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ሊቀመንበር

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

185661
Previous Story

የፋኖ የአዲስ ዓመት ጥሪ | ወታደሩን አሽመድምደነዋል |

Fz2WSkuaEAAhBI6
Next Story

አዲስ ዓመት

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop