August 19, 2023
6 mins read

የመጨረሻው ደወል !! ( አሥራደው ከካናዳ )

The Last bell 1 1 1ኳ ! ኳ ! ኳ ! ሲል፤

የመጨረሻው ደወል ሲደወል፤!

ያንዱ ፍፃሜ፤ የሌላው ጅማሬ ይሆናል !!

ኳ ! ኳ ! ኳ ! ሲል ሲደወል: የመጨረሻው ደወል፤ ከወዲያ ከሩቅ፤ ከሚካኤል ደጅ፤ ከማርያም ደብር፤ ከጊዮርጊስ ደጃፍ፤ ከተክልዬ ገዳም፤ ከእየሱስ ደጅ፤ ሲያስተጋባ የደወሉ ጥሪ፤ በዱር በገደሉ፤ በየመንደሩ በከተማ በገጠሩ፤በክፍላተ ሃገሩ፤ የግፍ አገዛዝ ፍጻሜ፤ የፍትሃዊ አስተዳደር ጅማሬ ይሆናል !!

በተራሮች አናት ተሻግሮ እንደገና፤ ግው! ግው! ግው! ብሎ ሲጣራ፤ ያልሰማው እንዲሰማ፤ የተኛው እንዲነቃ፤ ያልታጠቀው እንዲታጠቅ፤ የመጨረሻው ደወል ሲደወል፤ የመጀመሪያው ክብሪት ተጭሮ፤ የድል ችቦ ተለኩሶ፤ ደመራው ሲነድ: ሲንቦገቦግ፤ ምድር ተቀዳ ቀውጢ ስትሆን: አቧራው እንደ ጭስ ሲቦን፤ ሰማዩ ቀልቶ፤ ጨለማው ሲሸሽ፤ የማለዳው ጮራው ሊፈነጥቅ: የነፃነት ጠሃይ ፍንትው ብላ ልትወጣ ቀኑ ቀርቧል::

ያንዣበበው የፍርሃት ደመና ተገፎ: ጎህ ሲቀድ፤ ከአድማስ ባሻገር: በሚፈነጥቀው የጠሃይ ጮራ፤ በሃዘን የተሰበሩ ልቦች፤ በብርሃኗ ሙቀት እንደ ጽጊረዳ ተፈልቅቀው ይፈካሉ:: በቁጭት የከሰለ አንጀት: በሃሴት ያቆጠቁጣል፤ በግፍ የወደቁ ወንድሞቻችን ደም: የሚያስተጋባው የድል ጩኸት፤ ከአጥናፍ አጥናፍ ሲያስተጋባ ይደመጣል:: የእናት አገራችን ኢትዮጵያ ትንሳኤ: የመጨረሻው ደወል የሚሰማበት ቀኑ ቀርቧል ::

ክርፋት ክርፋት በሚሸት: የዘረኝነት፤ የጥላቻና የጎሣ ሽታ: የታፈኑ አፍንጮች፤ በጽጌረዳ ጣዕም የታወደ የነፃነት አየር በመተንፈስ፤ በጥላቻ የጠቆሩ ሳንባዎቻቸውን ይፈውሳሉ :: በዘረኞችና አምባ ገነኖች በትር: በዝምታ የተሸበቡ አፎች ተከፍተው፤ የእናት አገራቸው ኢትዮጵያን፤ ሕዝባዊ መዝሙር በአብሮነት ጮክ ብለው በመዘመር፤ የደስታ ዕንባ እየተናነቃቸው ተቃቅፈው፤ ዳግም በዘር፤ በሃይማኖትና በጎሣ ተከፋፈለው፤ አገራቸው በደም ላትርስ፤ በታንክ ላትታረስ፤ አረንጓዴ፤ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማቸውን፤ በኢትዮጵያ ተራሮች ላይ፤ ከፍ አድርገው በማውለብለብ፤ በአያት በቅድም አያቶቻቸው መቃብር ላይ ቆመው ቃል የሚገቡበት የመጨረሻው ቀን ቀርቧል::

ጉንጮቻቸው በሃዘን ዕንባ የተሸረሸሩ እናቶች፤ እድላቸውን የሚያማርሩበት፤ ጧሪ ልጁን በጠራራ ፀሐይ የተነጠቀ አባት፤የሚተክዝባት፤ በረሃብ ቆዳቸው ከአጥንታቸው የተጣበቀ ሕፃናት የሚያለቅሱበት፤ በገዛ አገሩ ተስፋ ቆርጦ የሚሰደድ ወጣት፤ ዳግም የማይኖሩባት ኢትዮጵያን የምንገነባበት ቀን ቀርብውል:: ክብሩን ማንነቱንና አገሩን ተሰርቆ፤ የድቀላ ስንዴና ቦቆሎ እየተመጸወተ፤ ዳግም ዲቃላ ሆና የሚፈጠር ትውልድ የሚያበቃበት ቀኑ ቀርቧል::

የስደት በሩ ተዘግቶ፤ የመመለሻው በር ወለል ብሎ ሲከፈት፤ ሁሉም ዜጋ የስደት ኑሮውን ትቶ፤ ወደ ጥቁሯ እየሩሳሌም፤ እናት አገሩ ኢትዮጵያ በመመለስ: በፍቅር፤ በወንዳማማችነት፤ በአንድነትና  በእኩልነት የምንኖርባት አገራችንን የምንገነባበት ቀኑ ቅርብ ነው::

የደወል ጥሪውን እናዳምጥ፤ የነፃነት ቀን ቀርቧል! ዳግም ሌቦች ድላችንን እንዳይነጥቁን፤ ሁላችንም ለመብታችን ዘብ እንቁም :: ትግል በውክልና፤ ድል በልመና መቋመጡ ያብቃ ! ሁሉም የበኩሉን የዜግነት ድርሻና ግዳጁን ይወጣ፤ ተጎልቶ በሌሎች ደም የተዋጀ ድልና ነፃነት መጠበቁ ያብቃ ! ::

የኢትዮጵያን ህዝብ ድል፤ በመጀመሪያ ወታደሩ ሲነጥቅ፤ ቀጥሎ ህወሃት ሁለት ጊዜ መንትፏል፤የኦህዴ/ ኦነግ እና የጃንደረባው ብአዴን ጥምር፤ ብልጽግና በሚል የዳቦ ስም ለአራተኛ ጊዜ ሰርቆናል ::

የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ከአሁን በኋላ የሚሰረቅ ድል ሊኖረው አይገባ፤ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን ለአገራችንና ለመብታችን ዘብ እንቁም፤ ይህ ካልሆነ ታሪክ በድጋሚ ይቅር አይለንም፤ እግዚአብሔርም በስንፍናችን ይጠየፈናል ::   

 

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

ነፃነት፤ እኩልነትና ወንድማማችነት ይለምልም !!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ !!

አላህ ከእኛ ጋር ይሁን !

ነሃሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ( 19/08/2023 ) እኤአ

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop