August 8, 2023
3 mins read

ፋኖ በራሱ ስንቅ፣ በራሱ መሳሪያ፣ በራሱ ሕይወት ….ግን ለሀገሩ ለወገኑ

Fano2 2 1
ደሞዝ ሳትቆርጥለት፣ መሣሪያ ሳታዘጋጅለት፣ ሽልማት ሳታበረክትለት፣ ለወገኑና ለሀገሩ ክቡር ሕይወቱን በሰጠ ኢትዮጵያዊ መሥዋዕትነት የቆመ ሀገር ነው ያለን። ይህ በነጻ ለሀገር የሚከፈል፣ ለወገን የሚሰጥ የሕይወት መሥዕትነት ፍልስፍና አለው። በቅርቡ ታሪካችን እንኳን በአምስቱ የጠላት ወረራ ዘመን ያየነው እውነታ ነው፡፡ ይህ ገድል፣ ይህ አርበኝነት ሥያሜ አለው። “ፋኖነት” ይባላል። በፈቃዱ፣ በፍላጎቱ ራሱን ለዚህ መሥዋዕትነት ያዘጋጀው አርበኛም “ፋኖ” ይባላል።
ፋኖነት እና ሽፍትነት በምንም በምን አይገናኙም። ፋኖነት በራስ ፈቃድ፣ በራስ ወጪ፣ በግል መሳሪያ ለአንድ ታላቅ ዓላማ የሚፈጸም የጦር ሜዳ ውሎን የሚያመለክት ሲሆን ሽፍትነት ግን ሕገ ወጥነትን፣ ወንጀለኝነትን የሚያሳይ ሐሳብ ነው። የታሪክ ዕውቀት፣ ራስንና ማንነትን የማወቅ ጥበብ ጉድለት ባለበት በዚህ ዘመን ሁለቱን የሚያምታቱ ሰዎች ማግኘታችን የሚደንቅ አይደለም። ነገርን ነገር ካነሣው አይቀር ግን ሁለቱንም በሚገባቸው ቦታ ማስቀመጡ ተገቢ ይሆናል፡፡
365216364 707334518101240 501228974185273297 n 2 1
ፋኖነት ክቡር መሥዕትነት ነው። በታሪክ መዝገብም የተቀመጠው በክቡር ቀለም ተጽፎ ነው። ዛሬም ያ ክቡር ስም ጥላሸት እንዳይቀባ ሊጠበቅ ይገባል። ቅርስ ነው፣ የአንድ ሕዝብ የሕይወትና ራስን ከጠላት የመከላከል ፍልስፍና ነው፡፡ ፋኖነት በመላው ሀገራችን ባይኖር ኖሮ የነገሥታቱን የወታደር ብዛት ብቻ አይተው በንቀት የወረሩን ባዕዳን ባሪያዎች አድርገው ባስቀሩን ነበር። ግማሽ ቀን አርሶ፣ በሬዎችን ፈትቶ ቅዳሴ ገብቶ ቀድሶ፣ ቃለ እግዚአብሔር አስተምሮ ሃይማኖቱን ባቆየውና ጠላት ሲመጣበት የዕለት ኑሮውን ትቶ ፣ ፋኖነት ገብቶ ሀገሩን ከወራሪ በታደገው ወገናችን መሥዋዕትነት የቆመ ማንነት ነው ያለን።
Fanos 1 1 1
አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ::
ፋኖነት ቅርሳችን ነው።
 ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
Go toTop