July 14, 2023
12 mins read

የፖለቲካ  ቁማርተኞች “ የእምቢ አላረጅም” አባዜ! – ተዘራ አሰጉ

part 10
#image_title
Oromo Tergnaw 1 1 1
#image_title

ፖለቲካ አቅም እስከፈቀደ ድረስ ለሃገር እምርታ ሲባል  በተለይ የፖለቲካ መርሁ /Manifesto/ አዋጭ ሁኖ በሕዝብ ሕይወት ላይ ሰላማዊ የእድገት ለውጥ ካመጣና ማህበረሰባዊ ቅቡልነት አግኝቶ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት እስካደረገ ድረስ የእሰየው ፣ የተስማምቶናል እና የይቀጥል ምላሽ በማግኘት በቅብብሎሽ የሚቀጥል ሂደት መሆን እዳለበት ታሪካዊ እስተምሮዎ ያሳያል ።

አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን ፖለቲከኞች ግን የፖለቲካ ቀመራችው አዋጭ ሆነ አልሆነ “ ስጋ እንደያዘ አንበሳ” በማናለብኝነት በሕዝብ ዘንድ ቅቡልነታቸው ‘እጂ – እጅ’ እያለም ቢሆን የወደቀ የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸውን ሟጭጨው ለረዥም ጊዜ ይገፉበታል ።

ይህን አጓጉል አካሄድ ተከትለው የተጓዙ አንዳንዶቹ በቂመኝነት የናወዙ መሰሬ ፖለቲከኞች ታሪክ እንዳሳየን በቁማቸው ሳያምርባቸው ፣ ሕዝብ አንቅሮ እንደተፋቸው እና የውርደት ማቅ እንደለበሱ እስከወዲያኛው እንዳሸለቡ ታሪክ አሳይቶናል።

በእነዚህ መሰሎቹ “የፖለቲካ አኞዎች እና ቆማሪ” የፖለቲካ መሪዎች እና አጨብጫቢዎቻቸው ምክንያት ህይወቱን ያጣው ወጣት ፣ የተዘረፈው መዋዕለ ንዋይ እንዳለ ሆኖ የአዲሱን ተተኪ ትውልድ የትግል ቀመር ፣ መርህ እና ፋና ወጊነት ለማኮሰስ እና ለማዋከብ የለመዱትን የደባ የፖለቲካ ቁማራቸውን አሁንም ስራየ ብለው ተያይዘውታል ፣ ቀጥለውበታል እንዲሁም ሰሞኑን ይህን ቅዥታችውን እያናፉ ይገኛሉ።

ይህ አካሄዳቸው ደግሞ ፅዩፍ እና “ የእኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” የለመዱት አባዜ  ከመሆኑ ባሻገር “እርጉም ከመአሪዎስ” የሚያሰኛቸው መሆኑን እነግራቸዋለን።

እነዚህ መሰል ፖለቲከኞች  እስከዛሬ ድረስ ያደረጉት ውሃ የማይቋጥር ሃገራዊ አስተዋፅዋቸው እንዳለ ሆኖ ለሰሩት የፖለቲካ ዕፀፅ እና ማህበራዊ ቀውስ ይቅርታ ጠይቀው እራሳቸውን ከትግሉ ገሸሽ ከማድረግ ይልቅ ስም እየቀያየሩ ሊወድቅ የሚንገዳገድን እንደ “ኦሮሞ ብልፅግና” ያለውን የደናቁርት ስብስብ ፓርቲ ከገባበት አረንቋ ጎትተው ለማውጣት ታች ላይ በማለት ላይ ይገኛሉ ።  ተደናግረው ሕዝብን እያደናገሩም ይገኛሉ ።

የሰው ልጅ ሕዝብን እና ሃገርን በተለያየ መልኩ ማገልገል ፣ መደገፍ ፣ መርዳት ከተቻለም መሬት ላይ የወረደ ስራ ሰርቶ ማለፍ ተፈጥሯዊ ኩነት እና ሂደት ነው ።

ይህን ተንተርሶ በዘመናት መካከል ለሃገራቸው ሆነ ለአፍሪካ የለውጥ አርሃያ ሆነው ያለፉ አንቱ የተባሉ ግለሰቦችንና ፖለቲከኞችን ሃገረ ኢትዮጵያ ያፈራች ቢሆንም እንዳንድ ተለጣፊ ፣ አፋጆ ፣ አጨብጫቢ ፣ ገዳይ እሰገዳይ እና ዘራፊ እና አዘራፊ ፕለቲከኞችንም በዘመናት መካከል ኢትዮጵያ  አፍርታለች።

የሃገር እድገት እና ለውጥ አበርክቶ ክዋኔ ያሳለጡ በእቡህ የሚታዩ አንቱ የተባሉና ማህበረሰቡ የሚያውቃቸው ግለሰቦች እና ፖለቲከኞች እንዳሉ ሁሉ “ አወድሱኝ ፣ እዩኝ ፣ እዩኝ ፣ አጨብጭቡልኝ እና አሞካሹኝ የማይሉ ለሃገር ታላላቅ አስታዋፅዎ አድርገው ያለፉ እና እያደረጉም ያሉ ግለሰቦችም እንዳሉም ሊታወቅ ይገባል።

የፖለቲካ አስተምሮው ደግሞ እንደሚያስተምረው እንደዚህ አይነቶችን ፖለቲከኞች “ምርጥ ፖለቲከኛ” ብሎ ያቆለጻጽሳቸዋል። ምክንያቱም የአስተዋፅዋቸውን መንዳ የሚጠብቁት ከለውጥ በሚገኘው የሕዝብ ሰላም ፣ እድገት እና የለውጥ ትሩፋት በመሆኑ ነው።

ታላቁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬነዲ ካለው “Ask not what your country do for you, ask what you can do for your country “ ካለው በተቃራኒ ደግሞ አንዳንድ የፖለቲካ ቁምርተኞች ሃገር ቀለብ እድትሰፍርላቸው ይዳዳሉ ፣ ይህ ደግም የነውር ነውርም ነው እንላለን።

ይህን ካልን ዘንዳ ከ30 ዓመታት ወዲህ ጀምሮ እና በተለይ በዚህ አምስት ዓመታት የሕዝብን አደራ ገሸሽ አድርገው “Some fulfill and some betrayed” እንዳሉት ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ሃገርን ከፍ ወደአለ ማማ አፈፍ ያደረጉ  ፖለቲከኞች እንዳሉ ሁሉ የርዕዮተ ዓለም መዕልቃቸው መስመሩን ስቶ ፣ ተዛብቶባቸው ፣ ተደናብሮባቸው እና “ፖለቲካችን አይነጥፍም ፣ ፖለቲከኛ አያረጅም” የሚል ነጠላ ዜማ እየለቀቁ ሃገርን “ከድጡ ወደ ማጡ” እንድትገባ ታላቁን ሚና የተጫወቱ እና እየተጫወቱ ያሉ የፖለቲካ ቅድመ አያቶች እንዳሉ ሃገር እና ሕዝብ እንዲገነዘብ እና “ ይበቃችኋል ” ሊላቸው እንደሚገባ እናስገነዝባለን  ።

እንደ እነ ኢንጂነር ስመኘው ፣ ጀነራል አሳምነው ፅጌ ወ.ዘ.ተ. ያሉትን ጀግና መሁራንን እና የጦር ፈላስፎችን ያፈራች ሃገር በተፃራሪው ከገዳይ ፣ ከከፋፋይ ፣ ከሃገር አጥፊ እና ኢትዮጵያ እና አማራ ጠል ከሆነው የኦሮሞ ብልፅግና ተብየ ቡድን ጋር እየተላላሱ  ፣ እያሸረገዱ ፣ እያሻጠሩ ፣ ተልዕኮ እየተቀበሉ ፣  “በእንቢ አላረጅም የፖለቲካ አባዜያቸው”  ሃገረ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን መቀመቅ ውስጥ የጣሉ እና “ከድጡ ወደማጡ” የከተቷት የፖለቲካ አትራፊዎች ፣ የሥልጣን ጥመኞች እና አልጠግብ ባይ ያረጁ ፣ ያፈጁ እና የጃጁ ሁሉነተናቸው ፉርሽ የሆነባቸው ፓለቲከኞች አሁንም እጃቸው እረጅም እንደሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊረዳ ይገባል እንላለን።

በአሁኑ ሰዓት ከኦነግ ብልፅግና አሸክሻኪዎቹ ፣ ከጥቅም ተካፋዮች እና ከስግብግብ የስልጣን አጋር ጡሮተኛ ፖለቲከኞች በስተቀር ግፉ ያንገበገበው መላ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም በተለይ የአማራ ሕዝብ ባልጌዎን ብልፅግናን ከስር መንግሎ ለመጣል ግብግብ በገጠሙበት ፣ መቃብሩን ለማቅረብ በተንሳሱበት እና የሕዝብ እምቢተኝነት ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ በተጧጧፈበት ወቅት ቀደም ያለውን ሻጥራቸውን በማጧጧፍ ትግሉን ለማጨናገፍ እነዚህ ከንቱዎች ታች ላይ እያሉ እንደሚገኙ ምልክቶች እየታዩ ነው።

በህውሃት ዘመነ መንግስት በኤርትራ በርሃ ያስፈጇቸው የአማራ ወገን ወንድሞች እና እህቶች ወደ ስልጣኑ ዕርካብ እንዳይመጡ ቀን ተሌት የሚኳትኑት የብልፅግና ወዳጆች እነ “ሲያልቅ አያምር” ጡረተኞቹ ፣ በሁለት ፖስፖርት ተጫዋቾች እና የፖለቲካ ቁማርተኛ ግንቦቴዎች ፣ አዜማዎች እና መሰሎቹ የአማራ ሕዝብ በቃኝ ብሎ መስሪያውን ወልውሎ እና አንግቦ ለለውጥ መነሳቱ ብርክ ብርክ አስብሏቸዋል ፣ የሚገቡበት ጠፍቶባቸዋል ከዚያም አልፎ ብልፅግናን ከሞት አፋፍ ለመመለስ መውክሸት እና ከአጨብጫቢዎቻቸው ጋር ሆነው የቋጡን የቧጡን የፍሬፈርስኪ ስብከታቸውን ተያይዘውታል።

አምና እና ታች አምና ከወያኔ ስር ተበርክከው አልሳካ ሲላቸው አንዴ ቅንጅት ፣ መድረክ ፣ ቀስተደመና ፣ ግንቦት ሰባት ወ.ዘ.ተ. እያሉ ስም በመቀያየር ሕዝብን እያደናብሩ ከገዳይ መንግስት ቁንጮዎች ምንዳ እየተሰፈረላቸው የሚኖሩ ምንደኞችን እና አደርባዮችን  “እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምስናል “ ከእንግዲህ በኋላ በእናንተ እንቶ ፈንቶ መዳፈቅ ፣ የፖለቲካ አጓጉል ትርክት እና ደባ የሚሸወድ የለም ፣ “ከቻላቻሁ አደብ ገዝታችሁ ተቀመጡ ፣ በቃችሁ እና የዘመናት ርዕዮተ ቀመራችሁ አልሰራም” ልንላቸው ይገባል።

ካልሆነ ግን የትግሉ ፍላፃ በእናንተ ላይ አርፎ ይበላችኋል እንላለን።

ተዘራ አሰጉ።

 

ከምድረ እንግሊዝ።

 

https://twitter.com/medhanitgg/status/1678900238256414720?s=20

Leave a Reply

Your email address will not be published.

184027
Previous Story

ልዩ ምረጃ!! “ክንዳችንን አልቻሉትም!” ፋ.ኖ አበበ ፈንታው!| የአማራ ድምጽ ዜና

Next Story

በአማራው ክልልና በሌሎችም ቦታዎች “የማይታወቁ ሰዎች”ን ያብዛልን!!

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop