ግልጽ ደብዳቤ፣ ለፕ/ት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ከልስጣን ይልቀቁ – ግርማ ካሳ

ወደዚህ ምድር ከመጡ 73 ዓመት ሆኖዎታል፡፡ ከደርግ ዘመን ጀምሮ፣ ፈረንሳይን ጨምሮ በበርካታ አገሮች የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ በተባበሩት መንግስት በተለያዩ ሃላፊነት ላይ ሰርተዋል፡፡ በባንኪ ሙን ጊዜ፣ በናይሮቢ የተባበሩት መንግስት የአፍሪካ ቀን ጽ/ቤት ሃላፊ የነበሩ ሲሆን፣ ባንኪ ሙንን በመተካት አንቶኒዮ ጉቴሪዝ ሲመጡ፣ በተባበሩት መንግስታት ረዳት ዋና ጸሃፊ ስልጣን ፣ በአፍሪካ ህብረት የተባበሩት መንግስታት ተጠሪ ሆነው፣ ያልዎትን ትልቅ ብቃት አሳይተዋል፡፡ በዚሁ ሁሉ ዘመን ለአገርዎት፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ላበረከቱት ትልቅ አስተዋጾ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ላመሰግንዎት እወዳለሁ፡፡

ከአምስት አመት በፊት ፣ በኦህዴድ/ብልጽግና ዘመን የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ሆኑ፡፡ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ኢዩ ቢለዩ ቤተ መንግስት እየኖሩ ነው፡፡

ከማንም በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለውን እጅግ በጣም ልብ የሚሰብሩ፣ አንገት የሚያስደፉ፣ አሳዛኝ ክስተቶች፣ እርስዎንም እያሳሰበ፣ እያሳዘነ እንዳለ አልፎ አልፎ ከሚናገሩት ንግግሮች ማወቅ ይቻላል፡፡ ሆኖም ይኸው አምስት አመት አደረጉ፣ ነገሮች እየተባባሱ እንጂ እየተሻሻሉ አይደለም፡፡

የሊሴ ገብረማሪያም ተማሪ ነበሩ፡፡በፈረንሳይ አገር ሞንትፐሊዬ ከተማ በሚገኘም ዩኒቨቨርሲቲ ከፍተኛ ትምህርት ተምረዋል፡፡ በመሆኑም ለፈረንሳይ ታሪክ እንግዳ ይሆናሉ ብዬ አላስብም፡፡ እስቲ በፈረንሳይ ስለነበሩ ሁለት ሰዎች ትንሽ ላስታውስዎት፡፡ በ18ኛ ክፍለ ዘመን የሉዊስ 16ኛ ባለቤት የነበረችው የፈረንሳይ ንግስት፣ ማሪ አንትዋኔትንና በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ወቅት፣ መቀመጫውን በቪሺ(Vichy) ከተማ አድርጎ፣ በግማሹ የፈረንሳይ ግዛት ሲገዛ የነበረው ፊሊፕ ፔተን፡፡

በማሪ አንቷኔት ጊዜ፣ የፈረንሳይ ህዝብ ለከፍተኛ ችግርና ረሃብ ተጋልጦ ነበር፡፡ ህዝቡከሽግሩ የተነሳ ተቃውሞ ማሰማት ጀመረ፡፡ እዚያ ቨርሳይን ቤተ መንግስት ድረስ በመሄድ፡፡ ተቃውሞዉን ማሪ አንቷኔት ሰማች፡፡ “ምንድን ነው የሚፈልጉት ?” ብላ ጠየቀች፡፡ “ዳቦ እያሉ ነው” የሚል መልስ ተሰጣት፡፡ ማሪ አንቲአኔትም፣ “ታዲያ ለምን ኬክ አትሰጧቸውም” አለች ይባላል፡፡ ንግስቲቱ በቤተ መንግስት ተቀምጣ፣ ከቤተ መንግስት ውጭ ካለው ሁኔታ ጋር የተለየች፣ out of touch ነበረች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አብን መከላከያ ሰራዊቱ ይቅርታ እንዲጠይቅ ጠየቀ

በሁለተኛ ዓለም ጦርነት የሂትለር ናዚዎች በመላው አውሮፓ ወረራ በፈጸሙ ጊዜ፣ ፈረንሳይም ቀድም ከተወረረችው አገር መካከል ነበረች፡፡ እነ ቻርልስ ደጎል ፣ በሽምቅ ውጊያ ናዚዎችን ሲዋጉ፣ ሌላው ፈረንሳዊው ፊሊፕን ፔተን ግን ከነ ሂትለር ጋር አብሮ መስራት ጀመረ፡፡ ለአጋረነቱም፣ ናዚዎች ፓሪስን ጨምሮ ሰሜናዊ ፈረንሳይ በቀጥታ ሲያስተዳድሩ፣ ደቡብን እርሱ እንዲያስተዳድር አደረጉት፡፡ የናዚዎች ተባባሪ ሆኖ ግማሹን ፈረንሳይ መግዛት ጀመረ፡፡ አገሩንና ህዝቡን ክዶ፡፡

ክብሩ ፕሬዘዳንት ሳህለ ወርቅ፣

ምን አልባት እንደ ማሪ አንቷኔት ቤተ መንግስት ውስጥ ስላሉ፣ በአገሪቷ እየተሰቃየ ያለው ህዝብ ስቃይና መከራ አልተሰማዎት ይሆን ? ናዚዛዊውና ዘረኛ የሆነውን የአብይ አህመድ ተረኛና ክፉ አገዛዝ እያዩ፣ የዚህ ስርዓት አካል መሆኗንዎ፣ ከሂትለር ጋር እንደ ተባበረው ፊሊፕ ፔተን ሆነው ይሆን?

በእድሜ ባለጠጋ ኖት፡ እግዚአብሄር ይመስገን፡፡ አገርዎትን በጥሩ ሁኔታ ለአስርተ አመታት አገልግለዋል፡፡

ታዲያ በመጨረሻው ሰዓታት ስምዎትን፣ ክብርዎትን ለምን ያበላሻሉ ? በታሪክስ፣ መጪው ትውልድ፣ “ከአብይ አህመድ ጋር ሲሰሩ የነበሩ ናቸው፣ ያ ሁሉ ጦርነት ሲደረግ፣ ያ ሁሉ ጄኖሳይዶች ሲፈጸሙ፣ አገር ስትተራመስ፣ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ቤተ መንግስት ነበሩ፣ የአገዛዙ አካል ነበሩ” ለምንስ ይባላሉ ? በዝምታዎት የተረኛው አገዛዝን እንደደገፉ ተድርጎስ ሊቆጠር አይችልም ወይ ? ማሪ አንቷኔት ከባሏ ሉዊስ 16ኛ ጋር በአደባባይ አንገቷ እንደተቆረጠው፣ እርስዎስ በህዝብ ቁጣ የማሪ አንቷኔት እጣ እንደማይደርስዎት ምን ማስተማመኛ አልዎት ? የሂትለር ጦር ሲሸነፍ፣ ከናዚዎች ጋር አብሮ ሲሰራ የነበረው የፊሊፕ ፔተን አይነት እጣስ፣ ተረኛው አገዛዝ በህዝብ ትግል ሲወገድ የርስዎም ሊሆን እንደሚችል አስበውታልን ?

ከትልቅ አክብሮት ጋር፣ “ታሪክዎትን በወርቅ ይጽፉ ዘንድ፣ ከህዝብ ወገን ይሆኑ ዘንድ እጠይቅዎታለሁ፡፡ “ስልጣንዎትን በመልቀቅ፣ ራስዎን በይፋ ከዘረኛው አገዛዝ በመለየት፣ የአገርዎንና የህዝብን ክብር ያስጠብቁ፡፡ ስምዎትን ያድሱ፡፡ ይሄን በማድረግዎ አገርን ለማዳን በሚደረገው ትግል ትልቅ አስተዋጾ ያደርጋሉ” እልዎታለሁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ጸጋዬ በርሄ ለሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ማስጠንቀቂያ ሰጡ

 

የአብይ አህመድ የግፍ እስረኞች

#image_title

2 Comments

  1. ግርማ ካሳ መልካም ብለሃል ለየትኛው ጊዜ ብለው ቢለቁ ይሻላቸዋል ሞዴሏ ጠቅላይ አቃቤ ህግ መአዛ አሸናፊ ከለቀቀች እሳቸው ምን ይሰራሉ በኋላ እኔ የለሁበትም አይሰራም ተጠያቂ መሆናቸውን እረስተውታል መሰል። አገኘሁ ተሻገርን ይልቃል ከፍያለውን ደመቀ መኮንን አንጠይቅም እነሱ ሮቦታይዝድ ሁነዋልና እሳቸው ግን ቢለቁ መልካም ነው

  2. እነዚህን እንቁ ዜጎች አሳስሮ አማራ ይተኛል በዴን እስኪያቀረሸው በየአረቄ ቤት ጠጥቶ የባህር ዳር ወጣት በሰላም ወደ ቤቱ ሸኝቶት ይመለሳል ቀደም ያሉት የኢትዮጵያ ተወርዋሪ ኮከቦችን ወኔ ይህንን ወጣት እንዴት እንጋተው …..ቢወጉት አይነሳም ያሉት ኮለኔል መንግስቱ እንዲህ አንጀታቸው በግኖ መሆን አለበት።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share