May 16, 2023
8 mins read

አገር ሲፈርስ የማያለቅስ ቤቱ ሲፈርስ ቢያለቅስ ምን ይጠቅመዋል ?

abiy ahmed 2 1

ከረጂም ዓመታት በፊት የቀድሞዉ ኢትዮጵያ መሪ የነበሩት ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም እና እንዲሁም ኢሀአዴግ ሲመሰረት በሽግግር ምስረታዉ ዋዜማ የኢትዮጵያን ነባር እና ቀደምት ተቋማት አፍርሶ የራሱን የፖለቲካ ስልጣን ጠባቂ ድርጂታዊ ተቋም ሲያቋቁም ከጥቂት እና ቀድሞ አወቅ ልበ ብርኃን ኢትዮጵያዉያን በቀር የገባዉም ፤ያሳሰበዉም የለም ነበር ፡፡

በሽግግር ምስረታ ወቅት ምሁራንን ወክለዉ ከታደሙት ዉስጥ ፕ/ር አስራት ወልደ የስ እና ዶ/ር መኮንን ቢሻዉ ዉጭ ማንም ስለ ዕዉነት ብሎ በሆነዉ እና ወደፊት ሊሆን ስለሚችለዉ የተናገረ አልበረም ፡፡

ዓለም እንደሚያዉቀዉ ዕዉቁ እና ንቁ የጥበብ እና የማገናዘብ ባለፀጋ  የኢትዮጵያዉን የአገር ባለዉለታ የሊቃዉንት  ቀንድ ፤ የግንባር ስጋ፣ የአገር እና የትዉልድ የዕድሜ ልክ ባለዉለታ ፕ/ር አስራት በኢትዮጵያ እና በዜጎች ላይ  የዘመናት ጥላቻ  ወጥመድ እና ጉድጓድ  ጂምር ዕዉን ለማድረግ በሽግግር መንግስት ምስረታ ሀ ብሎ መድረክ ሲከፈት  የህወኃት ሊቀ መንበር እና በኋላም የኢህአዴግ ጠ/ሚኒስቴር  ለገሰ /መለስ ዜናዊ  ይመራዉ የነበረዉን መድረክ  “አገር ለማፍረስ ፍላጎትም እና ስልጣንም የለኝም ” በማለት ከምክትላቸዉ ጋር ያለምን ፍርኃት እና አድርባይነት በዉሳኔአቸዉ  ፀንተዉ ስብሰባዉን ረግጠዉ ወጥተዋል ፡፡

እንግዲህ ከዚህ በፊት ከነበረዉ ኢትዮጵያን ፣ኢትዮጵያዉያንን እና በተለይም ዓማራን በጥላቻ እና በበታችነት ስሜት በተነቀረ ማንነት ቀጣይ በኢህአዴግ ትህነግ ጥርስ ዉስጥ የገቡት ፡፡

ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ለማፍረስ አስቀድሞ ከዓመታት በፊት የተነሳበት ዓላማ ቢሆንም ትምክተኛ  ዓማራ የሚለዉን ምሁር ወደ ሚል ያዛመተዉ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነበር ፤ ነዉ ፡፡

የኢህአዴግ ጠ/ሚኒስቴር  የነበሩት  ስለ ኢትዮጵያ እና ዓማራ ህዝብ የተነቀሩበት አስተሳሰብ ፣ መገንዘብ ፣ ንግግር እና ተግባር ወደ ኋላ ማየት ኢትዮጵያዊነት ፣ዓማራ እና ኢትዮጵያ ጠርስ የገቡ  የኢህአዴግ መነሻ እና መዳራሻ  ዋልቶች ናቸዉ ፡፡

ኢህአዴግ እና ልሳኖች ኢትዮጵያ ሲባሉ፤ ፌደራል፤ ኢትዮጵያዊነት ሲሏቸዉ  ብሄር ብሄረሰቦች ፤ ዓማራ ሲሏቸዉ ጠላት እና ስጋት አድርገዉ የሚስሉት ባዶነታቸዉ በምንም የማይሞላ  “በጥላቻ እና በማይታረቅ  አቻ ”  ግምት እና ገደል ላይ መቆሙ ነዉ ፡፡

አዚህ ላይ የማይተረቅ አቻ ግምት ሲባል ዘይት እና ዉኃ ለመቀላቀል እንደመሞከር እንዲሁም ዕዉነትን  በሀሰት መቀየር እንደሚቻል በማሰብ የዓመታት የጥላቻ እና የማይሆን አቻ ፈጠራ ላይ በማተኮር በህዝብ እና አገር ላይ አስካሁን ድረስ በዘለቀ ቀዉስ እንዲፈራረቅ ማድረግ ነበር ፡፡

ለዘመናት የደም ፣ ዕንባ እና ፍጂት ምድር ስትሆን  ይህን አስቀድመዉ የተረዱት ፐ/ር አስራት የህዝብ ሞት እና መፈናቀል ይብቃ ብለዉ ዳግም በዕዉነት እና በልበ ሙሉነት የነበረዉን እና ያለዉን ስርዓት አደብ ለማስገዛት ለነፃነታችሁ እና ለአገራችሁ የምትሉ  ንቁ ለራሳችሁ እና ለአገራችሁ ዘብ ቁሙ ሲሉ የሰሟቸዉ ጥቂቶች እና አስተዋዮች ነበሩ ፡፡

ለአብነትም ከትናንት አስከዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ ላብ እና ደም መኖሪያቸዉ ያደረጉትን  እነ ጌታቸዉ ማሞን ሳይቀር የቀበሮ ባህታዊ እና ሆድ አደር ከርሳሞች ብለዋቸዋል ፡፡

በዚህ ከዚያ አስከ ዛሬ ቁጭት ያደረባቸዉ የርሳቸዉን ቃል የሰሙ ፤ፈላጋቸዉን የተከተሉ ጥቂቶች ለራሳቸዉ ፣ ለአገራቸዉ እና ለዘላለማዊ  ስማቸዉ መስዋዕት ሆነዉ ያለፉም ሆነበ በህይወት የሚገኙ አሉ ፡፡  አበዉ የያዘዉን…….እንዲሉ  ሩጫቸዉን ጀምረዉ የጨረሱ  በነርሱ ዕግር የተተኩ እና ለዛሬ በህይወት የደረሱ የማይረሱ አሉ ፡፡

ሌሎች ግን ከሆድ አደሮች ሆነዉ ሆዳቸዉ  አምላካቸዉ ያልሆነ ነገ ግን  ቁጭ ብለዉ በነፈሰበት ሊወድቁ ለነርሱ መኖር እና ነፃነት ሌላዉ እንዲሞትላቸዉ ይጠብቁ የነበሩት ሚሊዮናት ካለፉት ሶስት ስርተ ዓመታት ጀምሮ በቁማቸዉ የሞቱ ዛሬ ስለ ንብረት እና ቤት መፍረስ በችርቻሮ ሲያለቅሱ መስተዋሉ የሚያሳዝን ቢሆንም ሁሉም በአገር እና በወገን አለመሆኑን አለማወቅ ግን ማሳዘን ብቻ ሳይሆን ኃጢያት ነዉ ፡፡

አበዉ “ሞኝ የጨዉ ክምር ሲናድ ይስቃል ፤ ብልህ ግን ያለቅሳል ” እንዲሉ  አገር እና ህዝብ ላለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት ጀምሮ አገር ሲፈርስ ፤ ህዝብ ሲያለቅስ ፣ አገር ሲታመስ ፣ ዜጎች በማንነታቸዉ ተለይተዉ በሶስተኛ ደረጃነት ተፈርጀዉ በግፍ ሲገደሉ  እና ሲበደሉ ያየ ህዝብ  እና ሠዉ ዛሬ ላይ ቢያለቅስ ፣ ዐዉቃለሁ ስሙኝ ልናገር  ቢል….ትናንት የነበር እና ሲተባበር የነበር ዛሬ ስሙኝ ልንገራችሁ ፤ ስሙልኝ አመመኝ እያሉ ዕየሞቱ ማልቀስ ሊቆም ይገባል ፡፡

በራስ እና በአገር ጉዳይ ላይ ሌላዉ ዋጋ እየከፈሉ ለመኖር  የሚመኝ  እርሱ  ከርከሮዉን  ያየ ያየዋል ፡፡  እንግዲህ ስለ ቤት ፣ ንብረት ፣ ስለ ግለሰብ  እና ግዑዝ …..በችርቻሮ ማልቀስ በሶስት አሰርተ ዓመታት የታየ  የሞት እና ዕልቂት  ዉጤት  ከዚህ በለ፤ይ አገር ፣ ህዝብ እና ሠዉ የሚሉትን አንኳር የብሄራዊ ጉልቻዎች መርሳት አያስፈልግም ፡፡

ብቻ የኛ ነገር የሶስቱ እንስሶች  ተታሪክ  የሚገልጠን ስለሆነ  ይህንም  “አብላኝ ያለ በላ አዉጣኝ ያለ ወጣ በመኃል የተኛ  ዕንቅልፎ ተበላ !”

 

Allen Amber!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop