የታሪክ ተመራማሪው መምህር ታዬ ቦጋለ ተደበደበ!

March 20, 2023
1 min read
በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ሀገሬ ኢትዮጵያ ለሸለምሽኝ ሽልማት አመሰግናለሁ።” ብለዋል መምህር ታየ ቦጋለ
“ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።”
 አሻራ ሚዲያ

4 Comments

  1. ታየንም ደበደቡት ሰላማዊውን ሰው? የግፋችሁ ጽዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው እናንትን አያድርገን፡፡

  2. አቶ ታዬ ቦጋለን በቅርብ አላውቀውም ሆኖም እራሴ እንደ ኢትዮጵያዊነት የተደበደብኩ ይመስለኛል ሆኖም ኢትዮጵያዊነት ማሸነፍ አይችሉም? ማንስ ይፈራቸዋል መስሎአቸውል?

  3. በመግደል * በመደብደብ * በማሸማቀቅ * በማዋረድ * በማሰር * በመግረፍ *…ወዘተ ለመግዛት ማሰብ ለዛውም ኢትዮጵያዊን ፍጡር በፍጹም በፍጹም አይቻልም ! ልብ ያለው ልብ ይበል ! ዘመኑን ይዋጅ !!

  4. አፋኞቼ ትግርኛ ተናጋሪ ናቸው። የእስር ቤት ጠባቂዎቼም ትግርኛ የሚናገሩ ብቻ ነበሩ። ከእነርሱም መካከል መልካም ሰዎች ነበሩ – የታፋኙ ማስታወሻ – አንድ አርጋቸው ጽጌ። ከልጄ ፊት ሽጉጥ አውጥተው በአፈና ጫካ ወስደው የደበደቡኝ ሁሉም ኦሮምኛ ተናጋሪ ናቸው። ከእነርሱም መካከል በጎ ሰዎች ነበሩ ይለናል። የጠ/ሚሩ መንግስት ወያኔን በኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች ከተካ ወዲህ የተደረገውና የሚደረገው ግፍ ሁሉ ከወያኔ መጽሃፍ የተቀዳ አልፎ ተርፎም የከፋ እየሆነ መቷል። ግራ የገባው መንግስት ሌላውንም ግራ ያጋባል። በጠ/ሚሩ ዙሪያ አሸሸ ገዳሜ የሚሉ የፓለቲካ ዘፋኞች ማየት ያለባቸው የጠ/ሚሩን የጣፈጡ ቃሎች ሳይሆን በምድር ላይ የሚፈጸመውን በደል መሆን ይኖርበታል። መምህር ታየ የነገረን ከደረሰበት ግፍ በጣም ጥቂቱን ነው። ራሱ አይኑና ሰውነቱ እንዲሁም በአንደበቱ ሁሉን ላለመናገር ያደረገው ታቅቦ የተፈጸመበትን የመብት ረገጣና የግፈኞች ጡጫ ያለምንም ጥርጥር ይነግረናል።
    ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ አንድ ላይ ቡና ጨልጦና ጣፋጭ ቃሎችን ተናግሮ ወደ ሃገሩ የተመለሰው የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “አስመራንና አዲስ አበባን” በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ በሰው መብት ረገጣ ይከሳቸዋል። ግን አስተዋይ ለሆነ ሰው ይህን ክስ ወደ ፊት ለማራመድ አሁን ጊዜው ነውን? ለምን ይህን ጉዳይ አሜሪካኖች ያዝ ለቀቅ እያረጉ ሁሌ በኤርትራና በአማራ በማላከክ ያላዝናሉ? ሆን ተብሎ እኛ እርስ በእርሳችን እንድንተላለቅ እሳት ለማቀበል እንዲመቻቸው ነው። በቅርቡ ወደ ቻይና ለጉብኝት ይጓዛሉ ተብሎ የሚጠበቀው የኤርትራው መሪ ለይቶላቸው አሜሪካኖችንና አውሮፓውያንን አፍንጫችሁን ላሱ በማለት ወደ ቻይናና ራሽያ በጠነከረ መልኩ አይናቸውን ማዞራቸው የባሰ አሜሪካንና የአውሮፓን ህብረት አስቆትቷል። ስለዚህ ኤርትራን የጦር አውድማ ለማረግ ምዕራባዊያን የቀራቸው ተስፋ ወያኔ ጎን መሰለፍ ብቻ ነው። ያኔም ዛሬም የሚያፋጅን እነርሱ ናቸው። በቅርቡ የኤርትራው ፕሬዝደንት እንዳሉት ለ 80 ዓመታት ያገዳደሉን እነርሱ ናቸው። ይህ በዚህ እንዳለ ነው የጠ/ሚ አብይ መንግስት ሁሉን ነገር ኦሮሞ በማድረግ ለኦሮሞ ብሎ ለመብታቸው የሚታገሉ ጦማሪዎችን፤ ጋዜጠኞችን፤ መምህራንና ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖችን በኦሮሞ አፋኞች እያሳፈነ በመደብደብና በማስፈራራት ህሊናቸውን አቁስሎ የሚለቃቸው። መምህር ታዪ ያልነገረን ግን ጫፉን ጠቅሶ ያለፈው ጸጥ ብለህ ባትቀመጥ በልጆችህ፤ በቅርብና በሩቅ ዘመዶችህ ሁሉ በደል እናደርሳለን እንዳሉት ነው። ይህ በቀጥታ ከወያኔ የሰቆቃ መጽሃፍ የተቀዳ ነው። በጊዜ የጠ/ሚሩን እብደትና የኦሮሞ ፓለቲከኞችን ማን አለብኝነት በመረጃ በማጋለጥ ሰከን እንዲሉ ካልተደረገ በስተቀር ገና ብዙ ግፍ በህዝባችን ላይ እንደሚመጣ መገመት አያዳግትም። በ 21ኛው ክፍለ ዘመን በዘሩ የሰከረን፤ ቋንቋየን ካልተናገርክ እቃ አልሸጥም፤ የሥራ ማመልከቻህን አልቀበልም ከሚሉ የድንጋይ ዘመን አሳቢዎች ምን አይነት የመደመር ውጤት ነው የሚገኘው? መጨፍለቅ እንጂ መደመር የለም። የመደመሩ ታሪክ የማዘናጊያ ብልሃት እንጂ ለሃገርና ለወገን የሚጠቅም ቢሆን ኑሮ በኦሮሞ ህዝብ ስም የተፈጸመውንና በመፈጸም ላይ ያለውን ግፍ ለማስቆም በአደባባይ በግልጽ መመሪያ መስጠት ይቻል ነበር። እንደ መምህር ታዬ ያሉ ወገኖቻችንም በእነዚህ የዘር ጥማተኞች ጡቻ በየስርቻው እየተደበደቡ፤ ያለዚያም በስልት እየተገደሉ አንድ በአንድ የዘርና የቋንቋ ፓለቲካው ሰለባ ይሆናሉ። እናስብ ቢሮ ሰብሮ የጋዜጠኛ መገልገያ መሳሪያዎችን የሚሰርቅ፤ ሱቆችን በእሳት የሚያጋይ፤ የሰዎችን መኖሪያ ያለምንም ድጎማ በቡልዶዘር አፈራርሶ ሰው ጎርፍ ወሰደው የሚለው የአሁኑ የኦሮሞ መንግስት ከወያኔ ቢከፋ እንጂ የሚሻልበት ምንም መንገድ የለም። ሰው ግን ደንዝዟል። የዛሬው ካለፈው ይሻላል የምትሉ አፋር ላይ ሜዳ ላይ የወደቁትን ወገኖች፤ ደብረ ብርሃን ላይ ከኦሮሞ መሬት ውጡ ተብሎ ለብርድና ለበሽታ የተዳረጉትን፤ አዲስ አበባና ዙሪያዋ ላይ ቤታቸው ፈርሶ ማደሪያ ያጡትን አይታችሁ ፍረድ። የፕሪቶሪያውም ሆነ የናይሮቢው የሰላም ስምምነት ውሃ የማይቋጥር፤ የጊዜ መግዣ እንጂ በጭራሽ ወያኔ እሺ ብሎ ትጥቅ አውርዶ በሰላም ይኖራል ብሎ መገመት ቂል መሆን ነው። ግን በዚህ ሁሉ ሴራ ወያኔ ለ 4ኛ ወረራ ሲመጣ የሚጎዳው አማራና አፋር በመሆኑ የጠ/ሚሩ መንግስትም ከሩቅ እየተመለከተ ልክ አጠገቡ ሊደርሱ ሲሉ ኑ ሃገር ተወረረ በማለት ውጊያ ይከፍታል። ሰው ግን አሁን ነቅቶበታል። ማን እየሞተ ማን ይኖራል። የኦሮሞ መንግስት ከወያኔ መንግስት ሽርክና እንጂ ጥል የለውም። ይህን ቀን ፍንትው አርጎ ያሳየናል። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የመደመር አዙሪት ፍልስፍና ፌዝና ተረት ተረት! – ከተዘራ አሰጉ ከምድረ እንግሊዝ

Next Story

የአብይ መደመር ማለት ይሄ ነው – በቃ እንበል

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop