March 14, 2023
10 mins read

ዝናብን የተነበየቸው አህያና የአማራን ዘር ፍጅት መተንበይ የተሳናቸው ምሁራን!

Abiy ahmed 1 1 1 1

Abiy ahmed 1 1 1 1በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

መስማት የተሳነው የሰማ እለት ያብዳል ይባላል፡፡ የሙሴዎች የቀድሞ ተደማሪዎችና ካድሬዎች ሰሞኑን ሙሴው የሾማቸው የአዲስ አበባ ገዥዎች ተነሱ ዘሮች በቀር አማራም ሆነ ሌላው አዲስ አባባ እንዲገባ አይፈቀድም አሉ ብለው ማበድ ጀምረዋል፡፡ እነዚህ ተደማሪዎችና ካድሬዎች እንደ ብረት ድስት ቅቤ ቀልጠው እስተሚፈሱ ሙሴዎችን ያፈቀሩና ሙሴዎችን የተቹትን ሁሉ ሌተ ተቀን የሚያጥረገርጉ ጉዶች እንደነበሩ ይታወቃል፡፡  እነዚህ ከንቱ ካድሬዎችና ተደማሪዎች ክርስቶስን ያሳድዱት እንደነበሩት ፈሪሳውያን ሁሉ ይህ ግፍ እንዳይፈጠም አብክሮ ሲታገል የኖረውን እስክንድር ነጋን በመንጋጋቸው ነክሰው ለአምስት ዓመታት ሲያብጠለጥሉ እንደከረሙ ይታወቃል፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊትም በትግሬ ነጣ አውጪ አዛዥነትና በሙሴዎች ታዛዥነት እስክንደር ነጋ እስር ቤት በሚማቅቅበት ወቅት ፎቶውን እየሸጡ ብር እንደሰበሰቡበት አይተናል፤ ታሪክ ዘግቧል፡፡

እነዚህ ከንቱ ፈሪሳውያን ዛሬም ተዓይናቸው ጆሯቸውን ማመኑን ቀጥለዋል፡፡ በሙሴዎቻቸው የሚመራው ይህ አድግ ቁጥር ሁለትም ሆነ እንቃወመዋለን ይሉት የነበረው የፊቱ ይህ አድግ ቁጥር አንድ አማራን ከአዲስ አባባና ተሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች መንቀል የጀመረው ከሰላሳ ሁለት ዓመታት በፊት ጀምሮ እንደሆነ በዓይናቸው  በብረቷ አይተዋል፡፡ ነገር ግን ተዓይናቸው ጆሯቸውን ስለሚያምኑ የሙሴዎቹ የአዲስ አብባ ሹሞች ምን ታመጣላችሁ አማራም ሆነ ሌላው እነሱ ያልፈቀዱለት አዲስ አበባን አይረግጥም ብለው በገሀድ እስተሚናገሩ አላምን ብለው እስክንድርንና ሌሎችም ቁርጠኛ ጓዶቹን ተሙሴዎች ጋር ሆነው ሲያሳድዱ ከርመዋል፡፡ ወለጋም ሆነ ሌሎች ቦታዎች በአማራ የዘር ፍጅት ተፈጠመ አንልምም ብለው በሰው ነፍስ ቀልደዋል፡፡

እነዚህ ከንቱዎች ተዓይናቸው ጆሯቸውን ስለሚያምኑ ሙሴዎቻቸው ዛሬም እንደ ትናንትናው ወጥተው “ኢትዮጵያ እኮ ሱስ ናት! አትፈርስም፤ ሁላችንም እንኳን ቆመን ስንሞትም ኢትዮጵያዊ ነን፤ ተዋህዶ ቤተክርስትያንም አገር ናት” ቢሉ እንደገና በፍቅር ቀልጠውና ተሟዘው ተደምረናል፤ እስክንድር አብዝቶታል እያሉ ይከተሏቸዋል፡፡

ሰውን በታሪኩና በስራው መመዘን የማይችል ዱልዱም ሰው ዝናብን በደመ ነፍስ መተንበይ የቻለችውን አህያና ዝናብ መተንበይ ያቃተውን የአየር ጠባይ ባለሙያ ያስታውሳል፡፡ በልጅነቴ አህያ ዝናብ እንደሚዘንብና ተየት አቅጣጫ እንደሚመጣ በጆሮዋ ትጠቁማለች ሲባል እሰማ ነበር፡፡ እንደተነገረኝ ይኸንን የአህያን ጥበብ አጤ ሀይለ ስላሴም ያውቁ ነበር፡፡ አጤ ሀይለ ስላሴ አንድ ቀን ደብረ ዘይት ለሽርሽር ሲሄዱ የአየር ጠባይ ባለሙያውን ይዘንብ እንደ ሆነ ሲጠይቁት አይዘንብ ይሂዱ ይላቸዋል፡፡ እርሳቸውም በትንበያው ተማምነው ሲጓዙ አንድ አህያ ጆሮዋን ቀስራ ዝናብ ከወደ ምዕራብ እንደሚመጣ ስትተነብይ ያያሉ፡፡ ትንሽ እንደ ቆዩም እንደ ሰካራም ሽንት የሚወርድ ዝናብ ልብሳቸውን አረጠበውና “ተአየር ጠባይ ባለሙያዎችስ የአገሬ አህያ ትሻለለች” አሉ ይባላል፡፡

የአየር ጠባይ ባለሙያዎች በሙያችን ገብተህ አትፈትፍት አይበሉኝ እንጅ ዝናብ የሚተነብዩት ከመዝነቡ በፊት ያለውን የእርጥበት፣ የሙቀት፣ የአየር ግፊት፣ ነፋስና ሌሎችም ነገሮች ለክተውና በሚገባ አውጠንጥነው ነው፡፡ የሰውን የወደፊት ባህሪና ግብር መተንበይ የአየርን ጠባይ ከመተንበይ እጅግ በጣም የቀለለ ነው፡፡ እንኳን አዋቂ ልጅም መፈጠም የሚችለው ተግባር ነው፡፡ የሰውን የወደፊት ባህሪ መተንበይ የሚጠይቀው ንፁህ ህሊና አስተዋይነት ብቻ ነው፡፡ በቅድመ አያቶቻችን ጥበብ የሰውን የወደፊት ጠባይ ወይም ግብር ለመተንበይ የሚቀባጥረውን ሳይሆን  አሳዳጊዎቹን፣ አስተዳደጉን፣ ያደገበትን አካባቢና  ከዚህ በፊት የሰራውን ሥራ ማየት ነው፡፡ በፈረንጅ ጥበብ ደግሞ የሥራ ልምዱን (ሬዚዩሙን) ማየትና ማረጋገጥ ነው፡፡ ብዙ ከንቱ የአማራ ምሁራን የአማራ አጥፊ ሙሴዎች ካድሬ ሆነው ያረፉት “ሰልጥኛለሁ!” በሚል ጅል ፈሊጥ የቅድመ አያቶቻቸውን ወደር የለሽ ጥበብ አሽቀንጥረው ስለጣሉ የፈረንጁ ዘዴም ያልተዋሃዳቸው ገለዶዎች ስለሆኑ ነው፡፡

የአማራ ምሁራን ዛሬ በፍጥነት እየተካሄደ ያለውን የአማራ ዘር ፍጅት መተንበይ የነበረባቸው አማራን ለማጥፋት እቅድ የተለሙ ጭራቆች ዋለለኝ መኮነን የሚባለውን ጥሩንባ ተጠቅመው አማራ ጨቈኝ ነው የሚለውን መፈክር ማስማት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ነበር፡፡ የአማራ ምሁራን የአማራን ዘር ፍጅት መተንበይ የነበረባቸው ነጣ አውጪ ነን ባዮች ከተመሰረቱበት ከግማሽ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነበር፡፡ የአማራ ምሁራን አማራን ዘር ፍጅት ተንብየው መታገል የነበረባቸው ነቢዩን አስራት ወልደየስ ተከትለው አማራን በማደራጀት ራሱንና አገሩን እንዲጠብቅ በማድረግ ነበር፡፡ የአማራ ምሁራን በአዲስ አበባ የአማራን ዝር ፍጅት መከላከል የነበረቻቸው ለሁሉም ዜጋ የቆመውን የዘመኑን ኢዮብ እስክንድር ነጋን ማብጠልጠሉን ትተው ከአምስት አመት በፊት ከእርሱ ጋር በመቆም ነበር።

ብዙ የአማራ ምሁራን ዛሬ እንኳን ይኸንን የሚያህል የአማራ ዘር ፍጅት አይተው አማራ እንዳይደራጅና ራሱን ተሟጦ ተመጥፋት እንዳይከላክል ለማደናቀፍ “ዜጋ፣ አንድነት ቅብጥሶ” የሚል አማራን ያዘናጋና ያሳጨደ የአምሳ አመት የካድሬ መፈክር ያክላላሉ፡፡ በእውነቱ እነዚህ ይኸንን መፈክር የሚያክላሉ  “ምሁራን ነን! ታዋቂ ነን!” ባይ አዘናጊና አስፈጅ ከንቱዎች በደመ ነፍስ ዝናብን ከምትተነብየው የኢትዮጵያ አህያ እጅጉን ያንሳሉ፡፡ እንደ አህያዋ እንኳን ዝናብን ሊተነብዩ እንደ ወንዝ በመላ አገሪቱ የሚፈሰውን የአማራ ደምም አላዩ፡፡ መለኮት ዓይናቸውን አንደ ግልገል ድመት ታልገለጠው ተአይናቸው ጆሯቸውን እያመኑ  አማራ እጁን አጣጥፎ በጭራቆች እንዲያልቅ ማድረጉን እንደ ሰላሳ ዓመቱ ይቀጣላሉ፡፡

የካቲት ሶስት ቀን ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.

 

2 Comments

  1. ያልከው ሁሉ እውነት ሁኖ ጽሁፌ እንቆቅልሽ እንድ ይመስል ታማኝ በየነ፣ግርማ የሽጥላ፣አገኘሁ ተሻገር፣ብርሀኑ ነጋ፣ ዳንኤል ክብረት ።።።።።እያልክ ማጣቀሻ ብታክልበት መልካም ነበር። እነ ዳንኤል በቀለም ከምር ለመርህ ቁሙ ይህ ቀን ማለፉ አይቀርም በልልን የአቤል ደም ይጮሀል።

  2. ዱልዱሙ አብይ አህመድ፣ ተከታዩ የኦሮሙማ መንጋና ለሆዳቸው የተሸጡት የአማራ አሽከሮቹ ይህንን ወርቅ መልእክትህን እንዲያገኙት እመኛለሁ፡፤ ለነገሩ
    ከህዝብ ካዝናየህዝብ ብር እየተመዘዘ የሚከፈላቸውበውጭም በውስጥም ያሉት ቅጥረኞቻቸው የት ሄደው???
    ኦሮሙማ ምንም ቢሆን በድምር ዉጤቱ አላተረፈም፡፡ ህዝብብንና አገርን በእንርጥ በአያሌው ጎድቷል፡፡ ያሰበበትን ሊያሳካ ግን አልቻለም፡፡ ሁነቶች ቀድመውት ኣክሽፈውታል፡፡
    በህዝዝቡና በአገሪቱ ላይ ያደረሰው የዉድቀቱ ዉጤት ግን ለማገገም ብዙ አመታትን ይወስዳል፡፡ ቁስሎቹና ጉዳቶቹ በቶሎ አያገግሙም፡፡
    እመኑኝ!!! ሁሉም ከብቶችና ኩበቶች ስለሆኑ በህዝቡ ብሶት በመቀጣጠል ላይ ያለው የህዝቡ አመጽና የአልገዛም ባይነት አይምሬ ንቅናቄ ሁሉንም ጠራርጎ ይጥላቸዋል!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

abn
Previous Story

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ

180815
Next Story

የከንቲባ አዳነች አበቤ … አደገኛ ሴራ እና የመፈንቅለ መንግስት ስጋት

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop