March 6, 2023
5 mins read

ላም ባልዋለበት… – ከመርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ

334476376 616109283712666 256688385386527955 n 1 2አይበገሬዎቹ አባቶቻችንና እናቶቻችን በዳግማዊ አጼ ምኒልክና በብልኋ ባለቤታቸው በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ግንባር-ቀደምት አዝማችነት ከዛሬ 127 ዓመት በፊት ከየኣካባቢው ተጠራርተው ዎረኢሉ ላይ የተሰባሰቡትና ወደአድዋ የተመሙት ሀገራችንን በግፍ ለመቆጣጠር ከሞከረው ወራሪ ሀይል ጋር በመፋለም ውድ ህይወታቸውን በቤዛነት አስይዘው ህዝባቸውን ከቅኝ አገዛዝ ለመከላከልና ሉኣላዊነቷን እስከወዲያኛው ለማስከበር እንደነበር ፈጽሞ ልንስተው አንችልም፡፡

እነሆ በተባበረ ክንዳቸው ጠላትን ድል ነስተው ከችግሮቿ ጋርም ቢሆን ይህችን አገር በነጻነት አስረክበዉናልና ከባድ አደራ አለብን፡፡

ሆኖም እኛ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ልብን ክፉኛ በሚያደማ አኳኋን በማይረባና በወደቀ የብሔር ፖለቲካ ተጠምደን እርስበርስ ስንበላላ ከያኔው ግዙፍ የአውሮፓ ወራሪ ሀይል ጋር ሲወዳደሩ የትንኝ ያህል ሊቆጠሩ ከሚገባቸው የሰሜንና የደቡብ ሱዳን ወራሪዎች እንኳ ራሳችንን ለመከላከል ተስኖን የምንገኝበት አሁናዊ አቋም በብርቱ ያሳስባል፡፡

በሌላ አነጋገር የትላንትናዎቹ ካርቱምና ጁባም አነስተኛና ጥቃቅን አገሮች ከመሆን አልፈው እነሆ ወደተለያዩ ግዛቶቻችን በመዝለቅ ሉኣላዊነታችንን በግፍ ከተዳፈሩና መሬታችንን በማናለብኝነት ከተቆጣጠሩ ውለው ማደራቸውን በግድ-የለሽነት እየተለማመድነው የመጣን ይመስለኛል፡፡

በርግጥ ይህንን ለማለት ያበቃኝ አንድ ክልስቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኀላፊ የደቡብ ሱዳን ወራሪ ሀይሎች አዲስ በተቋቋመው የደቡብ-ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል በኩል እስከ200 ኪሎ ሜትር ድረስ ዘልቀው በመግባት ዜጎቻችንን በግፍ ስለሚገድሉበትና የመአድን ማውጫ ስፍራዎችን ሳይቀር ስለተቆጣጠሩበት ሁኔታ ሰሞኑን በጋዜጠኞች ተጠይቆ እንዲህ ያለው ግጭትና ምልልስ በኛም ሆነ በነርሱ ወገን አሁን ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲልም ቢሆን ሲከሰት የነበረና የተለመደ ነው ሲል የችግሩን ክብደት አለቅጥ አቃሎ የሰጠውና ግድ-የለሽነት የተጠናወተው የተዳከመ ምላሽ ነው፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቁ የአድዋ ድል በአል በተከበረበት መስቀል አደባባይ አናት ላይ በእለቱ ወታደራዊ የጦር ጀቶችና ተዋጊ ሄሊኮፍተሮች የበረራ ትርኢት እንዲታይ ተደርጎ ነበር፡፡ እንደአየር ሀይሉ ሁሉ የምድር ጦሩም ቢሆን ቀላልና ከባድ መሳሪያዎችን በኩራት ሲያንቀሳቅስ ታዝበናል፡፡

እንዲህ ያለው የሀይል ማሳያ እንቅስቃሴ ያን ያህል ባልከፋ፡፡፡

ነገር ግን ተጠቂ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ከምድር ጦር እንቅስቃሴ ባሻገር ነጎድጓዳማ ጀቶቻችን በማስፈራሪያነት እንኳ ቢሆን በአሁኑ ወቅት ደጋግመው ሲያንዣብቡ ማየትና መመልከት የምንፈልገው እነሆ ጠላት በወረራ ከመያዝና ለጊዜው ከመቆጣጠር አልፎ ለተራዘመ ጊዜ በማንአህሎኝነት ተንሰራፍቶ በተቀመጠባቸውና ከዛሬ ነገ ይለቀቁልን ይሆናል ብለን በምንጠብቃቸው በርካታ ኪሎ ሜትሮችን በሚሸፍኑ የሰሜንና የደቡብ ግዛቶቻችን አየር ላይ እንጂ በሠላማዊቷ መዲናችን አናት ላይ አይደለም፡፡

 

በኔ አስተያየት ይህ ፈጽሞ የለየለት የግብዝነት እርምጃ ይመስለኛል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop