ከደረጀ ተፈራ (በግል የቀረበ)
- መግቢያ፣
እንደሚታወቀው አውሮፓውያን በተለያዩ ዘመናት በእምነት ሰባኪነት፣ በሃገር አሳሽነት (Exploration)፣ በጎብኚነት፣ በዲፕሎማት ማዕረግ እና በመሳሰሉት ሽፋን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ሃገራችንን በመሰለል ለቅኝ ገዥ መንግስቶቻቸው መረጃ ያስተላልፉ የእምነትና የታሪክ ቅርሶችንም በመስረቅ ወደሃገራቸው ያሻግሩ ነበር። ለምሳሌ በ 17 መ/ክ/ዘመን ጀምስ ብሩስ የተባለ እንግሊዛዊ (የስኮትላንድ ተወላጅ) የአባይን ምንጭ ፉለጋ በሚል ሰበብ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ታቦተ ፅዮንን ለማግኘት ብዙ ጥሮ ባይሳካለትም በመጨረሻ ግን በተሟላ ሁኔታ የሚገኙ ሁለት የመፅሀፈ ሄኖክ የግዕዝ ኮፒዎችን እና ሌሎች የብራና መፅሀፍትን ሰርቆ ሊወጣ ችሏል። ከእሱም በመቀጠል ሌሎችም ወደ ሃገራችን የመጡ ፈረንጆች በብራና የተጻፉ መጽሃፍትን፣ ታቦትን ጨምሮ በርካታ ነዋየ ቅዱሳትን እና የተለያዩ የታሪክ ቅርሶቻችን በመዝረፍ ወደ ሃገራቸው አግዘዋል። እስረኛ ለማስለቀቅ በሚል ሰበብ የእንግሊዝ መንግስት በፈጸመቸው ወረራ አጼ ቴዎድሮስ ባቋቋሙት ቤተ መዛግብት ይረኙ የነበሩ በርካታ የሃገራችን ቅርሶችና መጻህፍት ተዘርፈዋል፣ “የሰው ጌጥ አያደምቅ” እንደሚባለው ፋሽስት ጣሊያን የእነሱ ታሪክ ያልሆነውን የአክሱምን የድንጋይ ሃውልት ሳይቀር ወደ ሃገሩ ጭኖ በመውሰድ በኢትዮጵያ ቅርስ ሊያጌጥ በሮም ከተማ ማቆሙ ይታወሳል። እነዚህ ወደ ሃገራችን በተለያየ ምክንያት የሚመጡ አውሮፓውያን የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነቱን በማላላት ሃገራችንን ለመቆጣጠር በህዝቡ መሃል እየተሽለኮለኩ መርዛቸውን ይረጩ ነበር። ለምሳሌ የክርስቲያኑን መንግስት ለማገዝ ወደ ኢትዮጵያ መተው የነበሩ ፖርቹጋሎች የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስን በሮማ ካቶሊክ ለመቀየር በመሞከራቸው በእነሱ ጦስ በርካታ ህዝብ በርስ በርስ ጦርነት እንዳለቀ በታሪክ ይታወቃል። ህዝቡን የእጅ ሞያ ጥበብ (ተግባረ ዕድ) ለማስተማር ከአውሮፓ ወደ ሸዋ የመጣ ዮሐን ክራፕፍ (Johann Ludwig Krapf) የተባለ የጀርመን ሚሲዮናዊ ነበር። ዮሐን ክራፕፍ እ.አ.አ ከ1837 እስከ 1842 ኢትዮጵያ (ሸዋ) ውስጥ በቆየባቸው ጊዜያት ከመጣበት ዓላማ ውጭ በሸዋና አካባቢው በየገጠሩ በመዟዟር፣ እንዲሁም ከሸዋ ርቀው በሚገኙ እንደ እናርያ፣ ከፋ፣ ጎንደር እና በመሳሰሉት የሃገራችን ክፍሎች በንግድ እና በኑሮ ወደ ሸዋ የሚመጡ ሰዎችን በማናገር መረጃ ያሰባስብ ነበር። አንዱን ህዝብ በሌላው ላይ በማነሳሳት ግጭት ለመፍጠር ሞክሯል። ለምሳሌ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን የአፍሪካ ጀርመኖች ናችሁ (“The Germans of Africa”) ሌላ ጊዜ ደግሞ ሃገራችሁ “ዖርማኒያ (ORMANIA)” ናት፣ የአውሮፓን ባህልና ሃይማኖት ብትከተሉ መልካም በሆነ ነበር እያለ መርዛማ ቅስቀሳ ያደርግ ነበር። (በስተመጨረሻ ላይ በተገለጸው ምንጭ #1፡ ገጽ 52 /pdf ገጽ 2 ላይ ይመልከቱ)።
- የሉትራንፕሮቴስታንትአብዮት (በትንሹ)፣
የሮማን ኢምፓየር መንግስት ሃያል በነበረበት ጊዜ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ የአውሮፓ ጫፍ፣ ከሰሜን ብሪቴን እስከ ግብጽና የሜዲትራሊያን የባህር ዳርቻ ድረስ እንዲሁም የባልካን ሃገሮችን እና የመካከለኛውን ምስራቅን የሚያጠቃልል ሰፊ ግዛት ነበር። የሮማን ኢምፓየር መንግስት በየግዛቱ ለሚያሰማራቸው ወታደሮች የሚያወጣው ወጪ በየጊዜው እየጨመረ በመሄዱና ኢኮኖሚውም እየተዳከመ በመምጣቱ በተለይ በሮማን የጦር መኮንኖች መሃል በተፈጠረ የስልጣን ሽኩቻ የተነሳ ምስራቃዊና ምዕራባዊ የሮማን ኢምፓየር ተብሎ ለሁለት ተከፈለ። መቀመጫውን በጥንቷ የሮም ከተማ ያደረገው ምዕራባዊው የሮማን ኢምፓየር ሮማውያን ባርባሪያን (Barbarian) ብለው በሚጠሯቸው ከጀርመን ምድር የራይንን (Rhine) ወንዝ እየተሻገሩ ወደ ሮም በሚፈልሱ በጀርመን ጎሳዎች ከተማው ተጥለቀለቀ። በከተማው ህግና ስርዓት እየተፋለሰ፣ ቅሚያ፣ ዝርፊያና ስርዓት አልበኝነት እየተስፋፋ ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ እየሆነ መጣ። በመጨረሻም በ5ኛው ክ/ዘ ላይ ሮም ላይ የከተመው ምዕራባዊው የሮማን ኢምፓየር ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ ቻለ።
የጥንቱ የሮማን ኢምፓየር ከፈረሰ በኋላ በ8ኛው ክ/ዘ በካቶሊክ ፖፕ እና ሾለሜ (Charlemagne) በተባለ ንጉስ በፈጠሩት ጥምረት ምዕራባዊውን እና ማዕከላዊ አውሮፓን የሚያጠቃልል “ሆሊ ሮማን ኢምፓየር” የሚባል አዲስ መንግስት ተመሰረተ። በዚህ ጊዜ አብዛኛው በአምልኮ ባዕድ ተተብትቦ በመብረቅ፣ በተራራ፣ በባህር ማዕበል እና እመሳሰሉ ተፈጥሮዎች ያመልክ የነበረ፣ አስማትን፣ ዝርፊያን፣ ወረራን እና ጦርነትን ባህሉ ያደረገ አረማዊ (Pagan) የአውሮፓ ህዝብ በብዙ ድካምና ጥረት የካቶሊክ ክርስትናን የተቀበለበት ዘመን ነበር። በመቀጠል በ16ኛው ክ/ዘ ቀድሞ የካቶሊክ መነኩሴ የነበረ “ማርቲን ሉተር” (Martin Luther) የተባለ የጀርመን ተወላጅ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሮም የሚገኘውን የቫቲካንን ቤተክርስቲያን ህንፃ ለማስገንባት ሃጢያታችሁ ተደምስሶ ገነት ትገባላችሁ በማለት ገንዘብ ከህዝቡ የለአግባብ ትሰበስባለች (Indulgence ታስከፍላለች) የሚል ተቃውሞ አነሳ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ማርቲን ሉተር በካቶሊክ ቤ/ክ እምነትና እስተዳደር ላይ ባቀረበው 95 ዝርዝር ትችቶች የፕሮቴስታንት የለውጥ እንቅስቃሴን (Reformation) ጀመረ። በተለይ ከህትመት ማሽን መፈጠር ጋር ተያይዞ ሉተርና ደጋፊዎቹ መጽሃፍ ቅዱስን ከላቲን ወደ ጀርመንኛ ቋንቋ በመተርጎም ከእምነት ስብከቱ ጎን ለጎን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ማርቲን ሉተር በቤተመቅደስ ውስጥ የጀመረው እምቢተኝነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመሄድ በአመጽ፣ በነውጥ፣ በተቃውሞ እና በስርዓት አልበኞች የሚመራ የአደባባይ ትግል እየሆነ መጣ። በመሆኑም ለውጡን አንዳንዶች “የፕሮቴስታንት አብዮት” እያሉ ሲጠሩት ይሰማል። ሌላው ደግሞ በወቅቱ ጀርመንኛ ቋንቋ ተናጋሪ ማህበረሰቦች በተለያዩ የአካባቢ መሳፍንት ተበታትነው ይተዳደሩ የነበረ ና ጀርመን እንደ ሃገር የማትታወቅበት ጊዜ ነበር። ከሆሊ ሮማን ኢምፓየር ተገንጥለው ሃገር መስራት በሚፈልጉ ጀርመንኛ ቋንቋ ተናጋሪ ፓለቲከኞች እና የአካባቢ መሳፍንት ለውጡ ከሚያስገኝላቸው የግል የስልጣን ጥቅም አንጻር ይደግፉት ስለነበር የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ ጉድፍ እየፈለጉ የተጋነነ ፕሮፓጋንዳ በመክፈት ለውጡን አቀጣጠሉት። ባጠቃላይ የፕሮቴስታንት አብዮት ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊውን ህይወት በዓለማዊ ፍልስፍና በፖለቲካና ለግል ህይወት ከሚያስገኝ ልዩ ጥቅም አንጻር የተቃኘ ነበር። እነ ማርቲን ሉተር በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ ያደርጉት የነበረው ትችትና ነቀፋ ያሳደገቻቸው ቤተክርስቲያን የነበረባትን ችግር በቅንነት እንድትፈታ ለማገዝ ሳይሆን እንድትፈራርስ ያለመ ነበር።
በመሆኑም የካቶሊክ ምዕመናን በስርዓት አልበኞች በየሜዳው ተገደሉ፣ የእምነቱም አባቶቶች እና ምዕመናን በወከባና በማስፈራራት ጀርመንን ለቀው እንዲሰደዱ ተደረጉ፣ በፕሮቴስታንት ስም የተደራጁ አማጽያን እና ቀማኛ ወሮበሎች ቀድሞ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ንብረት የነበሩ የቤተክርስቲያን ህንጻዎችን እና የተለያዩ ንብረቶችን በጉልበት ነጠቁ፣ ከዝርፊያ የተረፈውንም አቃጠሉ። ቄስ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ሰው የክህነት ትምህርት ኖረውም አልኖረው በገባውና በተረዳው መጠን መጽሃፍ ቅዱስን መተርጎም ይችላል የሚል ስርዓትን እና ህግን የሚቃወም አስተሳሰብ በማርቲን ሉተር ይሰብክ ስለነበር እንደዘመናችን የፌስ ቡክ ተንታኝ አክቲቪስት ሁሉም እየተነሳ ሰባኪ በመሆን መንፈሳዊውን ህይወት ከዓለማዊ አስተሳሰብ እና ከግል ፍላጎቱ አንጻር እየደባለቀ በሚያደርገው ፍልስፍና በየጊዜው የተለያዩ የፕሮቲስታንት ቅርንጫፎች (denominations) ሊፈጠሩ ቻሉ። ለምሳሌ የእንግሊዙ ንጉስ ሄነሪ 8ኛ (Henry VIII) ዙፋኑን የሚተካ ወንድ ልጅ ስለሌለው ሚስቱን ፈትቶ ሌላ ሴት ለማግባት ቢጠይቅም የካቶሊክ ቤ ክ ከሚስቱ ጋር እንዲጸና እንጂ እንዲፈታት ስላልፈቀደችለት ተገንጥሎ የራሱን አዲስ Church of England የሚባል የፕሮቴስታንት ቤ/ክ አቋቋመ። እራሱን የአንግሊካን ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂም በማድረግም ለራሱ የፍች ወረቀት በመስጠ በተከታታይ ስድስት (6) ሚስቶች አግብቶ ፈታ። የተወሰኑትንም በላዬ ላይ ወሰለቱ፣ አሴሩ ወዘተ በማለት በግፍ ገደላቸው። ማርቲን ሉተርም በበኩሉ ጌታን ለማገልገል እምነት እንጂ ምንኩስና፣ ጾም፣ ምጽዋት፣ ቁርባን፣ ለካህን ንስሃ መግባት ወዘተ አያስፈልግም በሚል የግል ፍልስፍና የመነኩሴ ቆቡን ጥሎ ኑሮውን ከተማ በማድረግ ካትሪን የምትባል አንዲት የካቶሊክ ደናግል ከገዳም አስኮብልሎ በማግባ አምስት ልጆችን ወለደ።
በማርቲን ሉተር አብዮት በጀርመኛ ቋንቋ ተናጋሪው ማህበረሰብ ዘንድ የፕሮስታንታንት እምነት ከተስፋፋ በኋላ የምጣኔ ሃብት እና የማህበራዊ ሳይንስ ምሁር የሆነው ማክስ ዌበር (Max Weber) የተባለ የጀርመን (ፕረሺያ) ተወላጅ የፕሮቴስታንት ስነምግባርና ካፒታሊዝም (Protestant Ethic and Capitalism) በሚል ርዕስ የፕሮቴስታንት እምነት ለካፒታሊስት ስርዓት (ለኢምፔሪያሊዝም) ግንባታ እና ለግለሰቦች በሃብት መበልፀግ (Wealth and prosperity) አስፈላጊ መሆኑን እና በተቋማት ውስጥ ቢሮክራሲያዊ አደረጃጀት መከተል ለስራ ቅልጥፍና አጋዥነቱን የሚያትት መጽሃፍ አሳተመ። የማክስ ዌበር ጽሁፍ ከመንፈሳዊነቱ ይልቅ ዓለማዊ ይዘት ያለው ሲሆን፣ የጀርመን ህዝብን አዲሱን የፕሮቴስታንት እምነት ከኑሮው ጋር በማስተሳሰር አዲስ ለራስ ጥቅም ብቻ የቆመ፣ ለኔ ብቻ የሚል የግለኝነት ባህል እንዲያዳብር አደረገ። በመሆኑም በማርቲን ሉተር የተጀመረው እንቅስቃሴ እምነት ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ይዘት ያለው በመሆኑ የጀርመን ብሔርተኝነትን ለማቀጣጠልና ለሃገር ምስረታ እንደ ስልት (ታክቲክ) ያገለገለ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ የፈረንሳይ ተወላጅ የሆነው ጆን ካልቪን (John Calvin) የፕሮቴስታንት የለውጥ እንቅስቃሴ ያደርግ የነበረ ሲሆን በስዊዘርላንድ እና በአካባቢው ሃገሮች ፕሮቴስታንትን አስፋፋ። በመሆኑም የፕሮቴስታንት አብዮት ወደ ሌላውም የአውሮፓ ክፍል በመዛመት ከየአካባቢው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ጋር ተደማምሮ ከሆሊ ሮማን ኢምፓየር እየተለዩ እራሳቸውን የቻሉ በርካታ የአውሮፓ መንግስታት ሊፈጠሩ ቻሉ። በፕሮቴስታንት ስነምግባር እና በካፒታሊዝም (ኢምፔሪያሊዝም) ርዕዮት የተቃኙ እንደ እንግሊዝ፣ ጀርመን እና የመሳሰሉ የአውሮፓ ሃገራት በቀጣይ አፍሪካን በቅኝ ግዛት በመውረር፣ የሰሜን አሜሪካን እና የአውስትራሊያ ነባር ህዝቦች ጨፍጭፈው በሃገሩ ላይ በመስፈር ከፍተኛ የሰባዊ ጥሰትና የዘር ጭፍጨፋ የፈጸሙ ናቸው።
ሮማውያን “ባርባሪያን” እያሉ ይጠሯቸው የነበሩ ከጀርመን የፈለሱ ጎሳዎች ለጥንታዊው የሮማን ኢምፓየር መፍረስ እንደ አንድ ምክንያት የሚጠቀሱ ሲሆኑ፣ ዳግም የምዕራብ አውሮፓን የካቶሊክ ክርስትናን እና የሆሊ ሮማን ኢምፓየርን ያፈራረሰው ክዚሁ አካባቢ በፕሮቲስታንታዊ አብዮት በተነሳ ህዝባዊ ማዕበል ነው። ማርቲን ሉተር በህይወቱ መጨረሻ ዘመን በጀርመን ስለሚኖሩ የይሁዲ ማህበረሰብ በተመለከተ “On The Jews and their Lies” በሚል ርዕስ በ1543 ላይ አንድ ፅሁፍ ፅፎ አሰራጨ። በፅሁፉም ውስጥ የይሁዲዎችን መኖሪያ እና ማምለኪያ ሲነጎጋቸውን አቃጥሉ፣ የፀሎት መፅሃፋቸውን ቀሟቸው፣ የሃይማኖት አባቶቻቸው የሆኑት ራባዎች እንዳይሰብኩና እንዳያስተምሩ ከልክሏቸው፣ የፋይናንስና የቢዝነስ ተቋማትን እንዳይጠቀሙ አግዷቸው፣ ይሁዲዎች እንደ ድንጋይ እና ብረት የጠነከረ የማይለወጥ ልብ ያላቸው የሴጣን ልጆች ስለሆኑ የተረገሙ ናቸው ወዘተ በማለት ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ዘረኛና ፀረ ይሁዲ (Anti-Semitism) ፅሁፍ ፅፎ አሰራጨ። በዚህ በማርቲን ሉተር ፀረ ይሁዳ (ጸረ ህዝብ) ቅስቀሳ የተነሳሱ የሉተር ተከታዮች በመንጋ በመንቀሳቀስ በጀርመን የሚገኙ ሲነጎጎችን በእሳት አቃጠሉ፣ ንብረታቸውን አወደሙ፣ በርካታ ይሁዶች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ምስራቅ አውሮፓ ሃገራት ወደሆኑት ወደ ሩሲያ፣ ፖላንድና የመሳሰሉት ሃገራት ተሰደዱ። በመጨረሻም በተፈጠረው ምስቅልቅል ጭንቀት ውስጥ ገብቶ በ1546 በአዕምሮ ደዌ ተሰቃይቶ እንደሞተ የህይወት ታሪኩ ላይ ተፅፎ ይገኛል። በመቀጠልም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የሉተርን ክፉ ሃሳብ መነሻ በማድረግ በሂትለር የሚመራው የናዚ መንግስት በጀርመን ውስጥ ከማርቲን ሉተራ ዘረኛ ቅስቀሳ ተርፈው ከስደት የቀሩትን ይሁዲዎች በማንነታቸው እንዲገለሉና እንዲጠቁ ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፈተባቸው። የሉተራል ፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆኑ እነ አዶልፍ ሂትለር እና ተከታዮቻቸው ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል እንደሚባለው የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ ይሁዲዎችን ማጥቃት ጀመሩ። ለምሳሌ ጌታችንን የሰቀሉት ይሁዶች ናቸው፣ ሌላ ጊዜ ለአንደኛው የዓለም ጦርነት ሽንፈታችን መረጃ ለጠላቶቻችን አቀብለዋል፣ ከእኛ ጎን አልቆሙም፣ እንዲሁም በሃገራችን ላይ መጤ ሆነው ሳለ ከእኛ በላይ ሃብት አፈሩ፣ ጀርመን ለጀርመኖች እንጂ የመጤዎችና የስደተኞች መኖሪያ አይደለችም ወዘተ በማለት በጥላቻ ተሞልተው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ጀርመን ውስጥ ይኖሩ በነበሩ ወደ 6 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ይሁዲዎች ላይ የዘር ጭፍጨፋ ፈጽመዋል።
ወደራሳችን ጉዳይ ስንመጣ የማርቲን ሉተር ተከታዮችና ደጋፊዎች የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የነበረባትን ችግር በቅንነት እንድትፈታ ሳይሆን እንድትፈርስ ያቀርቡት እንደነበረው አሉታዊ ትችት እና አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ፣ እንዲሁም በይሁዲ ማህበረሰብ ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ያውጁ እንደነበረው ዓይነት የኛዎቹ ጉዶች የአውሮፓን አስቀያሚ ታሪክ ወደ ኢትዮጵያ ጎትተው ለማምጣት ትርክት መፈብረክ ጀመሩ። የአውሮፓ መንግስታት ባህር አቋርጠው ወደ አፍሪካ በመምጣት በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በጅምላ እየጨፈጨፉ ቅኝ ግዛት ያስፋፉበትን ታሪክ ገልብጠው የኦርቶዶክስን ከውጭ ባህር አቋርጣ የመጣች ይመስል በሃገሯና በምድሯ ላይ ይህንን ያንን አደረገች እያሉ ስሟን በአሉባልታ ወሬ አጠፉ፣ በመቀጠልም በተለያየ ጊዜ ተሃድሶዎችን አስነስተው ኦርቶዶክስን ሊያምሱ ሞከሩ፣ ይህ አልሳካም ሲላቸው የመስቀል ደመራ እና የጥምቀት ታቦት መውጫ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቦታዎቿን ከለከሉ፣ በተወሰኑትም ላይ ቤተ አምልኮታቸውን እና የባዕድ አምልኮ ማምለኪያ የእሬቻ የውሃ ኩሬ ገነቡበት፣ በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚሰሩ የኦርቶዶክስ ምዕመናን የአንገታችሁን ክር ካልበጠሳችሁ በሚል ብዙዎችን ከስራ አባረሩ። በመጨረሻም ለሁለት እንደሚከፍሏት በሃሰተኛ የፕሮቴስታንት ጠንቋይ ነብያቸው ሟርት አስነግረው ሲያበቁ የቤተክርስቲያኗን ቀኖና እና ዶግማ በመጣስ ለዚሁ የጥፋት ስራ ባስቀመጧቸው የበግ ለምድ በለበሱ ተኩላዎች ህገ ወጥ ሲኖዶስ አቋቋሙ። ህገወጦቹም ማርቲን ሉተር በካቶሊክ ቤ ክ ላይ እንዳደረገው እነሱም በተራቸው በኦርቶዶክስ እምነትና እስተዳደር ላይ በብሔር ካባ ተሸፍነው ፖለትካዊ ይዘት ያላቸው አሉታዊ ትችቶችን እና አሉባልታዎችን ማስወራት ጀመሩ። የብልጽግና ኦነግ ካድሬዎች ብሔራችንን ኦርቶዶክስ በሃይል ነው ክርስቲያን ያደረገችው በማለት ሲወነጅሉ፣ በተቃራኒው ደግሞ አፈንጋጭ ካህናቱ ኦርቶዶክስ ወደ ብሔራችን ክርስትናን አላስፋፋችም እያሉ ወቀሷት። ቅንነቱ ቢኖር ኖሮ ቤተክርስቲያኗን ለሁለት ሳይከፍሉ ውስጧ እያሉ ብሔራቸውን ማስተማር፣ ሐዋሪያዊ ስራ በመስራት የኦሮሚያ መንግስት በባህል ስም እያስፋፋ ካለው ከቃልቻና ከባዕድ አምልኮት ህዝቡን በማስተማር ማላቀቅ በቻሉ ነበር። ነገር ግን ከአጥፊዎቹ ጎን ቆመው ስንፍናቸውን በቤተክርስቲያኗ ላይ ማላከካቸው ድብቅ የስልጣን ፍላጎታቸውን እና የብሄር ፖለቲካ አቀንቃኝ ፖለቲከኛ መሆናቸውን ያሳያል። በመሆኑም የበግ ለምድ በለበሱ የኦነግ ብልጽግ ተላላኪ ተኩላዎች ለሺ ዓመታት ተተብቆ የመጣውን የቤተክርስቲያኗን መተዳደሪያ ቀኖና እና ዶግማ በመጣስ ምክንያት እየፈለጉ የ16ኛውን ክ/ዘ የማርቲን ሉተርን የፕሮቴስታንት Reformation በኢትዮጵያ ለመድገም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
- የኦነግብሔርተኝነት መነሻና መድረሻ፣
የኦሮሞ ጽንፈኛ ብሔርተኞች አንዱ መነሻ የኮሊያኒስት ጀርመን ሰላይ የነበረው የዮሐን ክራፕፍ የሉተራን ፕሮቴስታንት ስሁት አስተምህሮ ሲሆን ሌላው ደግሞ የኮሚኒስቶች የጨቋኝ ተጨቋኝ የብሔር ፖለቲካ ነው። መቀመጫቸውን ወለጋ ላይ አድርገው ይንቀሳቀሱ የነበሩ የሉተራን ሚሲዮናውያን የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ከመመስረት ጎን ለጎን ህዝቡን በመያዝ እምነታቸውን በአካባቢው ለማስፋፋት ያመቻቸው ዘንድ ት ት ቤቶችን፣ የህክምና ክሊንኮችን፣ የእርዳታ ሰጪ ተቋማትን በማቋቋም ለረጅም ጊዜ በአካባቢው በመቆየታቸው በትውልዱ ላይ ከእምነት እስከ ፖለቲካ አስተሳሰብ (ርዕዮት) ቀረጻ ድረስ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ መጫና ቱለማ የሚባል መረዳጃ ማህበር ነበር። መጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት እና የልማት ስራዎችን ለማከናወን በሚል በ1956 ዓ/ም ተመሰረተ። ይሁን እና የማህበሩ አመራሮች እንደ ልማት ማህበር ሳይሆን እንደ ፖለቲካ ድርጅት የሚንቀሳቀሱ ነበሩ። በየስብሰባዎች ላይ የሚያደርጉት ንግግር ከልማት ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው፣ ጊዜውን ባልዋጀ በተስፋፊ የብሄር ፖለቲካና ባህላዊ አስተሳሰብ የተቃኙ ነበሩ። በመሆኑም የሚሲዮናውያኑ ተማሪዎች የነበሩት እነ ሃይሌ ፊዳ፣ ዲማ ነግዎ፣ ሌንጮ ለታ፣ ባሮ ቱምሳ፣ ነጋሶ ጊዳዳ እና የመሳሰሉት በ60ዎቹ በተማሪው እንቅስቃሴ ወቅት የፖለቲካ ድርጅቶች ሲቋቋሙ አብዛኛዎቹ ኦነግ እና መኢሶን በሚባሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ መሳተፍ ጀመሩ። መኢሶን የኮሚኒዝም ርዕዮት የሚከተል የፖለቲካ ድርጅት ሲሆን ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ መኮንኖች ይደግፉት የነበረ ነው። መኢሶን ከደርግ ወታደራዊ መንግስት ጋር ለጊዜውም ቢሆን መሞዳሞድ ቢችልም እንኳን ደርግ ኢህአፓ የሚባል ትልቁን ጠላቱን ካጠፋና የእውቀት ድርቀቱን በመኢሶን ከተወጣ በኋላ በሁለት እግሩ መቆሙን ሲያረጋግጥ መጨረሻ ለስልጣኑ በመሰጋቱ ፊቱን ወደ መኢሶን አዞረ። በዚህ ጊዜ በርካታ የመኢሶን አባላት ህይወታቸን ለማትረፍ ለደርግ ወታደራዊ መንግስት በወዶ ገብነት እጃቸውን ሲሰጡ፣ ከፊሎቹ ደግሞ የጀርመንና የሌሎች የአውሮፓ የፕሮቴስታንት የእምነት ድርጅቶች ጋር በነበራቸው የቆየ ግንኙነት የሃይማኖት ሽፋን እየተሰጣቸው በመለኮታዊ ትምህርት (Theology Study) በሚል ሽፋን ወደ አውሮፓ እየሾለኩ ወጡ። የተወስውኑት ደግሞ በደርግ መንግስት ውስጥ ከነበሩ የኦሮሞ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ኔትዎርክ በወቅቱ ሶሻሊስት ሃገሮች የሚሰጡትን የነጻ ት/ት (free scholarship) በመተቀም ትምህርት ስም ወደ ውጭ ሃገር እየተሽለኮለኩ ከሃገር ወጡ።ለምሳሌ ከብዙ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል የመካነየሱስ (የሉተራን) ቄስ የሆኑት የቄስ ጊዳዳ ልጅ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በእምነት ስም ወደ ጀርመን ለትምህርት ከወጡት ውስጥ አንዱ ናቸው። ዶ/ርነጋሶ ጊዳዳ ጀርመን በትምህርት ሳሉ በኦነግ ስር ወጣቱን በማደራጀት የፖለቲካ ተሳትፎ ነበራቸው ሌላው አሰፋ ጃለታ የተባለ ሰው ነው፣ ይህ ግለሰብ ለደርግ መንግስት ያገለግል የነበረና ለአብዮቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ ደርግ ወደ ሶሻሊስት ቡልጋሪያ “Karl Marx Higher Institute of Economics” ለትምህርት የላከው ሲሆን “ከአርያን ዘር” የተገኘን ምርጥ የሰው ዘር ነን በማለት አውሮፓን ብሎም መላው ዓለምን በጦርነት እንዳተራመሰው የጀርመኑ ናዚ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ የኦሮሞ ህዝብ “ኦሮሙማ” ከሚባል ምርጥ የሰው ዘር የተገኘ ነው የሚል ናዚያዊ አስተሳሰብ የሚያራምድ ግለሰብ ነው። ይህ ሰው Journal of Oromo Studies በሚል ስም በርካታ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጭ የኖረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ኗሪነቱን ያደረገ የአንድ ዩኒቨርስቲ የሶሾሎጂ መምህር (ፕሮፌሰር) ነው። ሌላው ደግሞ በንቲ ቴሶ የተባለ ፓስተር ነው። በንቲ ቴሶ በአንድ የጀርመን የፕሮቴስታንት ተቋም ውስጥ መለኮታዊ ትምህርት የተማረና በጀርመን ሉተራን ካህናት የተቀባ የኦነግ ፓስተር (Reverend) ሲሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የኢትዮጵያ ስም በኩሽ መቀየር አለበት የሚል ዘመቻ ከፍቶ የነበረ ነው። ባጠቃላይ በትምህርት፣ በእምነት፣ በስራ እና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ውጭ ሃገር ወጥተው በአሜሪካና በአውሮፓ ኑሯቸውን ያደረጉ ለሞያቸው፣ ለዕምነታቸውና ለህሊናቸው ታማኝ ያልሆኑ፣ ዋሾ ኦነጋውያን የሚገኙ ሲሆኑ ያለ በቂ መረጃና ምሁራዊ ፍተሻ በጥናት (research) ስም ለርካሽ የፖለቲካ ዓላማቸው የሚያመቻቸውን ሃሰተኛ ትርክት እየፃፉ ህዝቡን ተሰድበሃል፣ ተንቀሃል ተነስ እያሉ በማሳመጽ ሲቀሰቅሱ ኖረዋል፣ መጸሃፍትና ምሁራን ለማለት ከተፈለጉት (context) ውጭ ሆን ብለው ቃላትን እና ታሪክን አጣመው በመተርጎም ብዙዎችን አሳስተዋል። በደርግ ዘመን የኦነግ አባላት የነጻ ስኮላር ሺፕ ትምህርት ይከታተሉ በነበረበት ሶሻሊስት ሃገራት የተማሩትን ወይም የሰሙትን የአውሮፓ ብሔረሰቦች የግጭት ታሪክ በሚያመቻቸው መልኩ የቦታና የስም ለውጥ በማድረግ በሃገራችን የተፈጸመ አስመስለው በማቅረብ በኦሮምያ ቋንቋ ለደጋፊዎቻቸው የፖለቲካ መቀስቀሻነት ተጠቅመውበታል።
በአውሮፓ በተደረገው በፕሮቴስታንት የለውጥ እንቅስቃሴ (አብዮት) ወቅት ከህትመት ማሽን መፈጠር ጋር ተያይዞ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን በማንሳት የካቶሊክን ቤተክርስቲያን ከህዝብ ለመነጠል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እንደክርፈቱ ሁሉ የእኛ ሃገር ጉዶችም ሚሲዮናውያኑ በእንግሊዘኛ (ላቲን) ፊደል በመጠቀም ወደ ኦሮምኛ የተረጎሙትን ወንጌል መነሻ በማድረግ በላቲን የቁቤ ፊደልን ቀርፀው ወጣቱን ክልል በሚባል በረት ውስጥ አፍነው በመያዝ በሚሰማው ቋንቋ ሃሰትና ጥላቻን አስተምረው፣ ሌላው ኢትዮጵዊ ወገኑ ሳይሆን ጠላቱ ሆኖ እንዲያስብ በማድረግ ተናካሽ አውሬ አደረጉት። ምርጥ የአርያን ዘር ነን በማለት የሉተራን ፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆኑ የሂትለር ናዚዎች በይሁዲ ማህበረሰብ ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ እንደፈፀሙ ሁሉ፣ የኦነግ/ ብልጽግና የፕሮቴስታንት ተከታዮች ደግሞ በአማራ ህዝብ እና በኦርቶዶክስ ምዕመናን ላይ በግልጽና በስውር የጅምላ ጭፍጨፋ ፈፅጸመዋል። ካህናቱን ቤተ መቅደስ ውስጥ አርደዋል፣ በመሃል ከተማ አዲስ አበባ ሳይቀር በታከለ ኡማ ትዕዛዝ የኦሮሚያ ታጣቂዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ በጥይት የአዲስ አበባን ልጆች ደም አፍሰዋል። ፖለቲካ የአስተዳደር ጥበብ (ሳይንስ) ሳይሆን ቁማር ነው ብሎ የሚያምነው እንጭጩ የኦህዴድ ብልጽግና መንግስት ሃላፊነት የሚሰማው ባለመሆኑ ኦነግን ከተኛበት አስመራ ድረስ ሄዶ ቀስቅሶ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ሽፋን እየሰጠ ባንክ እና የመሳሪያ መጋዘን ዘርፎ እንዲደራጅ አደረገው። መንግስት እጁ ባይኖርበት ወንጀለኞችን ለፍርድ ባቀረበ ነበር። በመሆኑም ለበርካታ ህዝብ ሞት፣ መፈናቀል፣ ንብረት ውድመት፣ ካህናትና ምዕመናን ግድያ፣ ለቤተክርስቲያን መቃጠል እና ለሃገራችን መመሰቃቀል ከኦነግ ሸኔና ከህወሃት እኩል የአብይ አህመድ የብልጽግና መንግስት ተጠያቂ ነው። የኢህአዴግ/ ብልጽግና መንግስት ሃገራችን የቆመችበት ዋልታዎች የሆኑትን የእምነት ተቋሞችን፣ የማህበራዊ እሴቶቻችን፣ በማህበረሰቡ ውስጥ የቆዩ የስነ ምግባር እና የስነ መንግስት ባህሎችን፣ በህግ አምላክ እያለ ለእውነት እና ለፍትህ ያለውን እሴቶች የህግ የበላይነትን በመጨፍለቅ በሃሰት ክስ ንፁሃንን እያሰረና ከመጋረጃ ጀርባ ተከፋዮቹን እያስመሰከረ አፈራርሶታል። የአብይ አህመድ የብል(ግ)ና መንግስት ተማሪዎች የሚታፈኑበትን፣ ተጓዦች መኪናቸው እየቆመ በመታወቂያ እየተለዩ የሚረሸኑበትን፣ ሰው በየመንገዱ ደሙ የሚፈስበት፣ ከተሞች በጽንፈኛ ወንበዴዎች የሚወድሙበትን ስርዓት አልበኛነትን በሃገሪቱ አስፋፋ። የኦህዴድ ኦነግ ካድሬዎች የሃሰት ትርክት ፈጥረው በማስጮህ የጥላቻ ሃውልት አቆሙ፣ በህዝቡ ውስጥ ፕሮፓጋንዳ አሰራጭተው፣ የትምህርት ስርዓቱን በአሉባልታ ወሬ አጭቀው የትውልዱን ጭንቅላት በዕውቀት ሳይሆን በበቀል እና በጥላቻ ሞሉት፣ በጀትና የሰው ሃይል መድበው፣ እቅድና ፍኖተ ካርታ ነድፈው፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በሚዲያ በት/ት፣ በዘፈን፣ በመዝሙር እና በመሳሰሉት በመንግስት ተቋማት የሚመራ የተቀነባበረ ፖለቲካዊ ጥቃት በኦርቶዶክስ እና በአማራ ህዝብ ላይ በመክፈት በርካታ ንፁሃን ዜጎች በጅምላ እንዲጨፈጨፉ፣ እንዲፈናቀሉ፣ ንብረታቸው እንዲወድም፣ ቤተክርስቲያናት እና ከተሞች እንዲቃጠሉ አደረጉ። አሁንም ቢሆን መፈንቅለ ሲኖዶስ ለማድረግ ሲታቀድ መረጃው የነበረው መንግስት ህግ እና ስርዓትን ማስከበር ያልፈለገው የሴራው አካል ስለሆነ መሆኑ ግልጽ ነው። የመንግስት ተቀዳሚና ዋና ስራ የሆነውን የህዝብን እና የተቋማትን ደህንነት (ሰላም) መጠበቅ ቢሆንም ህግ አስፈጻሚ የሆነው የመንግስት አካል ቀድሞ ያደርግ የነበረውን ጥበቃ በዚህ ጊዜ ከመንበረ ፓትርያርኩና ከቤተ ክህነቱ ማንሳቱ እራሱ መንግስት ትርምስን እና ስርዓት አልበኝነትን ስለሚደግፍ ነው። የግማሽ የኢትዮጵያ ህዝብ ዋና ጉዳይ የሆነውን መፈንቅለ ሲኖዶስ ህዝቡ ታክስ ከፍሎ ባቆመው ሚዲያው እንኳን የራሱ ጉዳይ እንዳይዘገብ ማድረጉ መንግስት ስራውን መስራት ያልቻለ ብቻ ሳይሆን ሃላፊነት የማይጣልበት በብሔር ስም ተጠራርተው የተሰባሰቡ ቀባጣሪ ቁማርተኞች እና በኦርቶዶክስ ላይ የተነሱ ዳግማዊ ሉተራናውያን መሆናቸውን ያሳያል።
የኦርቶዶክስን እና የአማራን አከርካሪ ሰበርን ያለው ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ የአድዋውን ተወላጅ አባ ጳውሎስን በፖለቲካዊ ጣልቃገብነት በቤተክርስቲያኗ ላይ ፓትርያርክ አድርገው ከሾሙ በኋላ ጵጵስናን በመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን እንደ ዓለማዊ ስልጣን በብሔረሰብ ኮታ እየተቆጠረ የሚሰጥ የፖለቲካ ሹመት ሆነ። የኢህአዴግም የጎሳ ፖለቲካ በቤት ክህነቱ ውስጥ በግልጽ መንጸባረቅ የጀመረው በዚሁ በወያኔ አገዛዝ ዘመን ነው። ወያኔ፣ ሻዕቢያና ኦነግ ወደትግል ገባን ካሉበት ጊዜ ጀምሮ በኦርቶዶክስና በአማራ ላይ ያልተቋረጠ ስም የማጠልሸት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አድርገዋል። በተለይ ከ1983 ዓ/ም ወያኔና ኦነግ የመንግስትን ስልጣን ከተቆጣጠሩ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ት/ት ቤቶች በተማሪው መጽሃፍ ባህር አቋርተው ወደ አፍሪካ የመጡ የአውሮፓ ሚሲዮናውያንን ታሪክ ገልብጠው ለኦርቶዶክስ ሰጡ። በተማሪው ላይ የአዕምሮ ዕጥበት ፈጸሙ፣ በጽሎትና በመንፈሳዊ ተጋድሎ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ያገለገሉ መነኮሳቱን እና ዘወትር በቅዳሴና በጸሎት መሃል ስለሃገራቸው ሰላምና ስለ ህዝቧ አንድነት የሚጸልዩ ካህናቱን አዋረዱ፣ በቤተ መቅደስ ውስጥ አረዱ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ሰብስባ የያዘቸውን ኦርቶዶክስን ባቆመችው በሃገሯ ላይ መጤ ናት ብለው ሰበኩ። አማራ ጠላትህ ነው በማለት ነፍጠኛ በማለት የማጥቂያ የኮድ ስም ሰጡት፣ በየገጠሩ ከተሞች እና ቀበሌዎች እንዲሁም በየገበሬ ማህበራቱ ያልተቋረጠ ቅስቀሳ በማድረግ ኦርቶዶክስና አማራ እንዲጠላ አድርገዋል፣ በባህል ስም አምልኮ ባዕድና አረማዊነትን አስፋፍተዋል፣ በነብይ ስም በርካታ የፕሮቴስታንት አንጋሽ ጠንቋዮች፣ ዘወትር ስለ ኦርቶዶክስ ክፉ የሚቃዡ ሟርተኞች፣ በእግዚአብሔር ቃል ሳይሆን በካራቴ እርኩስ መንፈስ የሚያስወጡ፣ ለአማኙ ዘይት ሸጠው የሚከብሩ ፓስትሮች፣ በሞባይል ከጌታ ጋር በስልክ እናገናኛለን የሚሉ ፌዘኞችን፣ የዋቃ ፈታ ቃልቻዎች በየአካባቢው ተስፋፍተዋል። የዘመናችን የብልጽግና ጴንጤዎች በመንግስት ስልጣን ላይ ተቀምጠው በሙስና ሃብት የተጨማለቁ፣ የከተማ መሬት ሸጠው በህግ መጠየቅ ሲገባቸው ሃይማኖትን መደበቂያ ዋሻ ያደረጉ፣ ከግል አዳኛችን ከሆነው ከጌታ ጋር በግል ተነጋግረናል እያሉ የሚያላግጡ ዓይናቸውን በጨው ያጠቡ ነፍሰገዳይ ሙሰኛ ሌቦች ናቸው።
- 4.ማጠቃለያ
ኦነግ ህሊና እና ሰባዊነት ያልፈጠረበት፣ የንፁሃንን ደም ሲያፈስ የኖረ፣ በርካታ የኦሮሞ ወገኖቻችንን በጥላቻ የመረዘ፣ ሃገራችንን በሃሰት ትርክት የበከለ ነው። ተጨቆንኩ ብሎ ሌላን ህዝብ የሚጨቁን በቀለኛ እንጂ የፍትህና የነጻነት ታጋይ ሊሆን አይችልም። ኦነግ ከ1982 ዓ/ም አሶሳ ላይ በንጹሃን አማራዎች ላይ ከፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ ጀምሮ ይኸው እስከዛሬ ድረስ ፋሽስታዊ ድርጊቱን እንደቀጠለ ይገኛል። አሁንም በህይወት ያሉት የኦነግ መስራቾች እኛ የታገልነው መብታችንን ለማስከበር እንጂ ሌላውን ህዝብ ለመጨቆን፣ ለመግደል፣ ለማፈናቀል፣ ከተማ ለማቃጠል አይደለም ሲሉ አለመሠማታቸው እስካሁን ድረስ ለሚፈሰው የንጹሃን ደም እና ለሚወድመው ንብረት ተጠያቂ መሆናቸውን ያረጋግጣል። ኦነጋውያን ወደ ትግል የገቡት በሚሲዮናውያን ስብከት፣ በአማራ ጥላቻ፣ ባልጠራ ድንግዝግዝ አስተሳሰብና በፕሮፓጋንዳ ተገፍተው እንጂ ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና መብታቸውን ለማስከበር አለመሆኑ ስራቸው ይመሰክርባቸዋል።
የህወሃት እና የኦነግ የጥላቻና የበቀል ፖለቲካ ህገ መንግስት ተቀርጾለት ሃገር እየተመራበት ይገኛል። ይህን የዘር ፖለቲካ (tribalism) የትምህርት ስርዓት (ፖሊሲ) ተቀርጾ በተማሪው መማሪያ መጽሃፍት ውስጥ በማስገባት ትውልዱን መርዘውበታል። የጥላቻ ሃውልት ቆሞለታል፣ ወያኔ ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት በኢትዮጵያ ታሪክ ቀድሞ ያልነበረን ክልል የአባቶችህ ሃገር ኦሮሚያ ይህች ናት በማለት ካርታና ወሰን አስምረው በመስጠት ከክልልህ ጠላትህን አማራ ንብረቱን እየቀማህ አባር፣ ግደል፣ አፈናቅል፣ የኦርቶዶክስ ክርስትና በሃይል በነፍጠኛ የተጫንችብህ ስለሆነ አቃጥለህ አውድማት፣ በማለት የሰበኩት ትውልድ፣ አድጌ ነፍጠኛን ተበቅዬ፣ ኦርቶዶክስን አፍርሼ፣ ኢትዮጵያን በትኜ፣ ባንዲራዋን ረግጬ፣ የአዲስ አበባን ህዝብ የምንሊክ ሰፋሪ እያልኩ አፈናቅዬ፣ ወዘተ ወዘተ በማለት ውድመትና ጄኖሳይድ ቢፈጽም ለዚሁ የተፈጠረ ማመዛዘኛ ህሊናውን የተቀማ መንጋ ትውልድ በመሆኑ ነው። ሃገር በመምራት ላይ የሚገኙ የኦህዴድ/ ብልጽግና ባለስልጣናት ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጀምሮ ከላይ እስከ ታች ድረስ የፖለቲካ እውቀታቸው የተቀረጸው ከዚሁ ከወያኔና ከኦነግ ስሁት አስተምህሮ ሲሆን፣ ወያኔ ስልጣን ላይ እያለ ከምልመላ ጀምሮ በስልጠና/ በግምገማ የአማራንና የኦርቶዶክስ ጥላቻን እየጋተ ያሳደጋቸው፣ በየመድረኩ ላይ ሲራገሙና ሲሳደቡ የኖሩ ናቸው። በመሆኑም ብልጽግና/ ኦህዴድ ጭንብል አድርጎ የመጣ ቫይረስ ተሸካሚ ቁጥር ሁለት ኢህአዴግ ነው፣ ባለስልጣናቱም በሴራና በበቀል የተሞሉ፣ የአማራ ጥላቻ ከውስጣቸው አልወታም ብሎ የሚሰቃዩ የወያኔና የኦነግ የበኩር ልጆች ናቸው። ከቀባጣሪው ከአብይ አህመድ መንግስት ሞትን እንጂ ፍትህ አገኛለሁ ብለህ አትጠብቅ። የኦህዴድ ብልጽግና መንግስት ለውጥ መጣ ሲባል አደባባይ ወጥቶ የደገፈውን፣ በወያኔ ጥይት የሚፈሰው የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው ያለውን የአማራን ህዝብ የካደ፣ በጨነቀው ጊዜ ከወያኔ መንጋጋ ያስጣለውን ፋኖን ቀን አይቶ ፊቱን ያዞረ ውለታ ቢስ፣ ይሁዳን የሚያስንቅ ከሃዲ ቁማርተኛ ነው። ስለሆነም የይሁዳው የአብይ አህመድ ኦነጋዊው የኦህዴድ/ ብልጽግና መንግስት ህዝብ የሰጠውን ሃላፊነት መወጣት ባለመቻሉ ከስልጣኑ ወርዶ በግልና በጋራ ለፈጸመው ወንጀል በህግ ሊጠየቁ ይገባል። ለዚህ ሁሉ ስርዓት አልበኝነት ላደረሰን ህገ መንግስት እና የጎሳ ፌዴራል ስርዓት እስከ ግሳንግሱ አስወግዶ በአዲስ ዘመኑን በዋጀ ስልጡን ስርዓት መተካት አማራጭ የሌለው ጉዳይ እየሆነ መጥቷል።
የኦነግ ብሄርተኝነት መነሻው ከላይ የተገለጸው ሲሆን መድረሻው ደግሞ የማርቲን ሉተር ደጋፊዎች እምነትን ሽፋን አድርገው በአመጽና በስርዓት አልበኝነት የጀርመንን ብሔርተኝነት በመቀስቀስ በጀርመን ይኖሩ የነበሩ በርካታ የካቶሊክ ቤተክርስቲያናትን ቀምተው፣ የእምነት አባቶቶችን እና ምዕመናንን ገድለውና ከሃገር አሰድደው በፕሮቴስታንት እምነት ዙሪያ ተሰባስበው ጀርመን የሚባል ሃገር እንደመሰረቱት ሁሉ የሚሲዮናውያን የመንፈስ ልጆች የሆኑት የኦነግ እና የብልጽግና ወንጌላውያን ከኦነግ ሸኔ ጋር እየተናበቡ በሽብር ስራ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ህንጻዎችን በመንጠቅ በኢትዮጵያና በኦርቶዶክስ ፍርስራሽ ላይ ኦሮሚያን እንደ ሃገር ለመመስረት እንደሆነ ግልጽ ነው። የኦሮሙማ ፖለቲካ ከኦሮሞ ውጭ ያለውን ህዝብ ጨፍጭፎና አፈናቅሎ በማርቲን ሉተር ተጀምሮ በአዶልፍ ሂትለር የተጠናቀቀውን የናዚን ርዕዮት በኢትዮጵያ ምድር ለመድገም ነው። ስለዚህ ኦነጋውያን የውሸት ታሪክ ፅፈው የኦሮሞን ወጣት አነሳስተውና ህዝቡን አሳስተው በጨበጣ ሃገራችንን ቀምተው ስር እንደሌለው እንጉዳይ ነቅለው ሳይጥሉን ወገባችንን ታጥቀን ከወዲሁ ማድረግ የሚገባንን ማድረግ አለብን። ጆሮ ያለህ ስማኝ! ታሪክ እንደሌለው፣ እምነት እንደሌለው ህዝብ ሃገራችንን አፈራርሰው ሊበትኑን ተነስተዋል። ይህንንም በወሬ ሳይሆን በተግባር በአሶሳ፣ በበደኖ፣ በአርባጉጉ፣ በጉራፈርዳ፣ በቤንሻንጉል፣ በቡራዮ፣ በአጣዬ፣ በወለጋና በመሳሰሉት የንጹሃንን ደም በግፍ አፍሰውና አፈናቅለው፣ ንብረታቸውን ቀምተው፣ ለዘመናት የተገነቡ ከተሞችን በአንድ ቀን አፈራርውና አቃጥለው በዓይናችን አሳይተውናል። መዘናጋቱን ትተህ፣ አዚም እንደተደገመበት ንፉዝ ሰው አብይ አብይ ማለቱን አቁመህ፣ ለሃገርህ፣ ለክርህ፣ ለሚስትህ፣ ለልጅህ፣ ለናትህ፣ ለማንነትህ፣ ለታሪክህ ዘብ ቁም!!!
ጆሮ ያለው ይስማ! የማውቀውን ተናግሬያለሁ። ያየሁትንና የሰማሁትን መስክሬያለሁ።
እግዚአብሔር የበቀል አምላክ ነው።
የበቀል አምላክ ተገለጠ።
የምድር ፈራጅ ሆይ፥ ከፍ ከፍ በል፤
ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው። . . .
አቤቱ፥ ሕዝብን አዋረዱ፥ ርስትህንም አስቸገሩ።
ባልቴቲቱንና ድሀ አደጉን ገደሉ፥ ስደተኛውንም ገደሉ።
እግዚአብሔር አያይም፥ የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም አሉ።..
እንደ በደላቸውም እንደ ክፋታቸውም ፍዳቸውን ይከፍላቸዋል፥
አምላካችን እግዚአብሔርም ያጠፋቸዋል።
አሜን! (ከመዝሙረ ዳዊት ምዕ. 94 የተወሰደ) -//-
ምንጭ፣
- L Krapf A Personal Portrait in Memory of His Entry to East Africa in 1844 (Africa Journal of Evangelical Theology) pdf.
- “The Story of the World” (W.B. Bartlett, 2014)
- “A Short History of Europe” (Simon Jenkins, 2018/ 2019)
- The Protestant Ethic and the sprit of Capitalism (Max Weber)
- Aspects of the Rise of Economic Individualism (A criticism of Max Weber and his school by H.M. Robertson, PhD)