አባታችን “አዋቂ” ነው ያሉበት ንግግር አንድምታዎች* (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

February 3, 2023
10 mins read
179247

አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በመግለጫቸው በቤተክርስትያን ላይ የተፈጸመውን የተንኮል ጥቃት ያካሄደው “አዋቂ” ነው ብለዋል።  አዋቂ ነው ማለት ምን ማለት ነው?

አንድምታ አንድ

ክርስቶስ  ስለሰቀሉት አይሁድ አባቱን ሲማጸን “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ብሏል። “አዋቂ ነው” ቤተክርስትያኗ ላይ ጥቃት የሰነዘረው ማለት ወንጀለኛው ይቅርታ የሌለው፣ መንፈስ ቅዱስን የተዳፈረ፣ የሲዖል ተወካይ ነው ማለት ነው።  ይቅርታ የሚጠየቅለት ሰው ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ እንዳስተማረን የሚያደርገውን የማያውቅ አጥፊ ሲሆን ነው። አዋቂ አጥፊ ግን ይቅርታ የሚገባው አይደለም።

እሱ በዳይ ሆኖ እሱ ከሳሽ መሆኑ ያባቱን የሣጥናኤልን ባሕርይ መውረሱን የሚያሳይ ነው።እንደተለመደው ዲስኩሩን አቢይ አህመድ ኃላፊነቱ በሚጠይቀው መሠረት ሕግን ለማስከበር  ሳይሆን ይልቁንም ሁል ጊዜም እንደሚያደርገው ተደራራቢ የማታለያ ውሸቱን ከመንዛትም በላይ የማቃጠር፣ ክብሪት የመለኮስ፣ የማጋጨት ጄኖሳይዳዊ እልቂት የመጥሪያ የተመሠጠረ ኮድ የመርጨት ሥራን ለመሥራት ተጠቅሞበታል።

የጉዳዩ ባለቤት መሆኑንም ያለ እፍረትና ፍርሃት ግልጽ አርጎታል። አንደበተ ርቱዕ ቢሆንም የአማረኛ ቋንቋ ችሎታው ግን እስከዚህም እንደሆነ የማያጠራጥረው ጠ/ሚ  አዋቂ ነው ሲሉት  እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ተሸውደው ብልህ ነው፣ ባለ ምጡቅ አእምሮ ነው ያሉት ሊመስለው ይችላል። እያወቀ የሚያጠፋ ሰው የሠራው ሥራ ነው። በመንፈስ ቅዱስ የምትመራን ቤተ ክርስትያን ሆን ብሎ ለቄሣር እንድትሰግድ ለማስገደድ ሲል ሰይፍ መዝዞባታል ማለታቸው ነው።

እስክንድርን “ግልጽ ጦርነት እናውጃለን” እንዳለው በተዋሕዶ (በሀገርም ላይ)  ግልጽ ጦርነት አውጆ እያፋፋመው መሆኑን አመልክቷል። ሰሞኑን ከዓለም ዙሪያ ያሰባሰበው ቆርቆሮ  (የጦር መሣሪያ) ይሆን ለዚህ ድፍረት ልቡን ያተባው?

 

አንድምታ ሁለት 

አዋቂ ማለት የሚሠራውን የሚያውቅ፣ ለሚሠራው ሥራ በዘፈቀደ እና በይሁነኝ ሳይሆን በቂ ጥናትና በቂ ዝግጅት የሚያደርግ ማለት ነው። አቢይም ለዚህ የጥፋት ሥራ በቂ ዝግጅት**  ማድረጉን ሲያመለክቱ ነው። እዚህ  ላይ አቢይ አህመድ ራሱን ብቻ ሳይሆን ከመቶ አመት በላይ ተዋሕዶን ለማጥቃት ዝግጅት ሲያደርግ የኖረውን ኃይል በተግባርም  በመንፈስም  የሚወክል ነው።

አንድምታ ሦስት

አንድም ደግሞ አባታችን ሕገወጡን ሥራ የሠራው “አዋቂ” ነው ማለታቸው ቤተክርስትያንን የሚያውቃት አሳልፎ እንደሰጣት ሲያመላክቱ ነው። ክርስቶስን ለይተው መያዝ እንዲችሉ የውስጥ አዋቂ በመሆን ስሞ አሳልፎ የሰጣቸው ይሁዳ ነበር። ክርስቶስን የሚያውቀውና የሚለየው የውስጥ ባንዳ ማለት ነው ይሁዳ። በቤተክርስትያን ላይ ጥቃቱን የፈጸመው አዋቂ ነው ማለታቸው እንደ ይሁዳ አሳልፎ የሰጣት የውስጥ አዋቂ ባንዳ ነው ሲሉ የዳንኤል ክብረትን ሚና መግለጻቸው ነው። ይህ በሳጥናኤል ስብሐት ነጋ ተመልምሎ  በቤተክርስትያን ውስጥ የተመስገ ውስጥ አወቅ ለዚህ ለተፈጠረበት የክህደት ሰዐት ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል ማለት ነው።

 

*አንድምታ ማለት አንድ ቃል ወይም ንግግር በተለያየ አውድ፣ መቸት እና እሳቤ የተለያየ ትርጓሜ ሲኖረው አንድም እንደዚህ ተብሎ ይፈታል፣ አንድም ደግሞ እንደዚህ ተብሎ ይነበባል  እያሉ የሚያብራሩ ወይም የሚተነትኑበት ስልት ነው። አንዳንድ ተናጋሪዎች በተለምዶ አንድምታ እንደማለት የነገሩ “እንድምታ” ሲሉ ይደመጣሉ።  ይህ ግን ስህተት ነው።

**የአቢይ አህመድ ዝግጅት ከብዙ በጥቂቱ

 1. 40 አመትበተዋሕዶ ላይ የተደረገው ዘመቻ
 2. የተዘረጋውጸረ ተዋሕዶ መንግሥታዊና ተቋማዊ ሥርዓት
 3. ከ97 ጀምሮ ኢህአዴግ  በአዲስ አበባ የደህንነትና የፖሊስ መዋቅራት ውስጥ ኦርቶዶክስና ኢትዮጵያ ጠል የሆኑ አባላትን በከፍተኛ ቁጥር መሰግሰጉ።
 4. አዲስአበቤ ከከተማው የደህንነትና የፖሊስ ተቋማት ውጭ መደረጉ
 5. የጃርሶሱማሌ ጎሳ የሆኑ በዚያድ ባሬ ጸረ ኢትዮጵያ ስብከት ከተጠመቀው ምሥራቅ ሐረርጌ በኦህዴድና አብዲ ኢሌ ጥምረት ተፈናቅለው አዲስ አበባ ውስጥና ዙሪያ እንዲሠፍሩ የተደረጉ ተዋሕዶ ጠል  ኢስላሚክ ኦሮሞዎች (ለማ መገርሳ ባመነው አንድ ሚልዮን የሚደርሱ)
 6. ብልጽግናመንግሥታዊ ሚድያውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠርና ማፈኑ
 7. ተቋማትንመቆጣጠሩ
 8. በሚልዮንየሚቆጠር ከውጭ በጉምሩክ የገባ ገጀራ
 9. ከሩሲያናሌሎችም  ሀገራት የተገዙ ብረት ለበሶች፣  መትረየሶች፣  ጸረ ሰው ፈንጂዎች፣ መርዞች፣  ድሮኖች ወዘተ
 10. ልዩሥልጠናና ቅለባ ሲደረግለት የከረመ ከግማሽ ሚልዮን በላይ የኦሮሞ ልዩ ኃይል
 11. ልዩሥልጠና እና ቅለባ ሲደረግለት የከረመ የሪፐብሊካን ጋርድ
 12. በተለያየሽፋን የገቡ የባእዳን ሀገራት ሰላዮች፣ አልሞ ተኳሾችና ነፍሰ ገዳዮች
 13. ከተዋሕዶምእመናን ውጭ የተቋቋሙት (ወይም ተዋህዶዎች የጸዱባቸው) የደኅንነት፣ የፖሊስና የሕግ መዋቅሮች
 14. ተዋሕዶስትመታ እኛ እንጠቀማለን ብለው የሚያስቡ የተለያዩ የሃይማኖት ነጋዴዎች
 15. አለማቀፉሲዖላዊ ኃይል
 16. በተለያዩጥቅማ ጥቅሞች የተገዙ፣ በወንጀል ብላክ ሜይል የተደረጉ የውስጥ አርበኞች
 17. በምርጫናበሌሎች ሰበቦች ሲሰነድ የከረመ የተዋሕዶ ምእመናን ሙሉ መረጃ

ይሄ እንግዲህ በዋናነት ኦርቶዶክሳውያንን በጎራ ከፍሎ በጦርነት በማዳቀቁ ምክንያት (በአቢይና በሕወሃትም ጉልህ የፕሮፓጋንዳ ተሳትፎ ጭምር) በተለይ  በብዙ የትግራይ ክርስትያኖች  ላይ ከተፈጠረው  “የምናገባኝ ስሜት” በተጨማሪ ስለተደረጉ ዝግጅቶች ስንመለከት ነው።

በአጭሩ አቢይ አህመድ  ከሚገባው በላይ ተዘጋጅቶ፣  ከበሻሻው የተዋሕዶ ካህናት ጭፍጨፋ ዘመን ጀምሮ ከሃያ አመታት በላይ ልምምድ ወስዶ የገባበት ዘመቻ ነው። ሥልጣን ከመያዙ  አስቀድሞና ከያዘም እለት ጀምሮም ለዚች ቀን መሠረት ሲጥል፣ ወጥመዶቹን ሲዘረጋ የከረመ ነው። በዚህ ዝግጅቱ ምክንያት ከመጠን ያለፈ ስለሚታበይ እንደ ፈርዖን ባሕረ ኤርትራ በላዩ ላይ እስኪከደንበት ከዚህ የእብሪት መንገዱ የሚመለስ አይመስልም። እግዚአብሔር መከራውን ያቅልልን።

 

1 Comment

 1. የጥቃቱ ዓላማዎች (ፊታውራሪው አንድ ቢሆንም ጥቃቱ በጥምር ጦር የሚካሄድ ዘመቻ ስለሆነ)
  1. ሕዝብን በመከፋፈል፣ የተባበረ ተቃውሞን በማምከን የሥልጣን እድሜን ማራዘም
  2. ወረራና ዘረፋ (ኦነጋዊው ካድሬ* እንደ አንበጣ አዳዲስ የዘረፋ አድማሶች የሚያስስ ነው)
  3. ኢትዮጵያን ለባእዳን ዘረፋና ወረራ ለማመቻቸት
  4. የአጋንንትን ተልእኮ ለማስፋፋት
  5. የቤተክርስትያንን አድዋዊ ገድል ለመበቀል
  6. የሸዋ ኦሮሞን ከእምነት ወንድሞቹ ሙሉ በሙሉ ነጥሎ ለቀጣዩ ድፍጠጣ ለማመቻቸት
  7. አዲስ ሀገር በማዋለድ ስም ኢትዮጵያን ለመበታተን
  አቢይ የዚህ ዘመቻ ፊት አውራሪ እንጂ ደጃዝማቾችና ራሶቹ ሌሎች ናቸው።

  *የኦህዴድ/ኦነግ ኃይል ታሪካዊ መሠረት ያላቸው የወረራ ዘይቤዎችን ይከተላል።
  አንዱ ዘይቤ ጥንታዊው የቡታ ሥርዐት ነው። በቡታ ሥርዐት ለሳምንት ያህል አንዳንዴም ከዚያ በላይ በሬ እየታረደ ሙሉ ቀን ሲበላ ደም ሲጠጣ ይሰነበታል። በዚህ ጊዜ የሚያልቀው ከብት ቁጥር ሥፍር የለውም። ነባሩንም የከብት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ በመሆኑ በደም የሰከረውና በመብላት የከሠረው የጎደለበትን ለመሙላት እንደ ጎርፍ በአጎራባች ሕዝብ ላይ በድንገት በመዝመት ጭፍጨፋ፣ ዘረፋ እና ወረራ ያካሂዳል። ኦህዴድ/ኦነግም በታሪክ ታይቶ የማያውቅ ዝርፊያ ቢያካሂድም፣ በማሸሽ፣ በድግስና በብርቅርቅታ ያንን የተዘረፈ ሃብት እያወደመ የጎደለውን ለመተካት አዳዲስ የዘረፋ እቅድ እያወጣ የሚቀጥል አንበጣ ነው።
  አሁን ያለንበት ጊዜ ኦነጋዊው ኃይል ከወያኔ ያስጣለውን እና ሌላም የአዲስ አበባ መሬት፣ የወለጋና የመተከል መሬት ሰለቃቅጦ ምንም እንዳልቀመሰ በጠኔ እያገሳ ዘላለም ረሃብተኛ የሆነው ዓይኑ በቤተክርስትያን ላይ እያማተረ ያለበት ወቅት ነው። ቢሳካለትና የቤተክርስትያንን ሃብት ሁሉ ቢቆረጣጥም እንደልማዱ በቡታ አውድሞት ሌላ ተወራሪ ፍለጋ ስልት ሲያወጣ ያድራል እንጂ በጭራሽ በልቶ የሚጠረቃ አይደለም።

  ቤተክርስትያንን በሚመለከት ግን የተዋሕዶ ልጆች በቅድሚያ የሚያስፈልገን ንስሐ ነው። ሁላችንም በድለናልና። በበደላችን ምክንያት የመጣ መሆኑን አምነን ፈጣሪ ንሥሐችንን ተቀብሎ ምሕረቱን እንዲልክልን ልንማጸን ይገባል። ማድረግ ያለብንን ሳናደርግ ማድረግ የሌለብንን ስናደርግ ነው ለዚህ የበቃነው። ክርስቶስን አልመሰልንም። ክርስቶስን አልተከተልንም። ከሊቅ እስከደቂቅ። እያንዳንዳችን። በዝምታ፣ በይሁንታም ይሁን በሌላ ቤተክርስትያንን ለሚያጠፉ፣ ምእመናንን ለሚጨፈጭፉ ድጋፍ ስንሰጥ ቆይተናል። ለመልካም ሥራ የተነሱ ሰዎችን ባለመደግፍም ይሁን በመጥለፍ ክፋት እንድትነግሥ አስተዋጽኦ አድርገናል። አይተን እንዳላየን፣ ሰምተን እንዳልሰማን ኃላፊነታችንን ሳንወጣ ለሁለንተናዊ ውድቀት አስተዋጽኦ አድርገናል። መታገዝ የሚገባውን ሳናግዝ፣ መፋለም የሚገባንን ስናጎለብት ወገን አዳክመን፣ ጠላት አግዝፈናል።

  ዛሬ ቆም ብለን፣ ስላለፈው የጥፋት መንገዳችን ተጸጽተን፣ ለመልካም ክርስቶሳዊ ሕይወት፣ የፍቅርና የወንድማማችነት ጉዞ በእምነት የመጽናት፣ ሀገርን እና ወገንን የመታደግ ገድል እንዘጋጅ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

89020
Previous Story

አብይ አሕመድ እና ጌታቸው ረዳ ፊት ለፊት ተገናኝተው ተወያዩ- DW

94084
Next Story

“ሳውል፣ ሳውል [መንግሥት ሆይ፥] የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብኻል፤” የታሪክ አዙሪት

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop