February 2, 2023
13 mins read

 ከትምህርት ሚኒስትር ፤ ከሱሪ በአንገት አውልቅ ውሳኔ እና ውጤቱ ፣ ምን ተማርን ? – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Ministry of Education e1634643601726 2የ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በየዩኒቨርስቲው መሰጠቱ ለተፈታኞቹ ” ሱሪ በአንገት አውልቅ ” እንደሆነባቸው ያገኙት ውጤት ይመሰክራል ። የመንግሥትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪወቻቸውን ለኩረጃ ከማዘጋጀት ባሻገር ፣ ፈተናውን በአስተማሪዎቻቸው አሰረተው በማሰራጨት ፣ አሰስ ገሰሱ ወደ ዩኒቨርስቲዎች  እንዲገባ ያደርጉ እንደነበር ይታወቃል ። ይኽንን ትውልድ ገዳይ የሥርቆት መንገድ በማስቀረት ረገድ የፈተና አሰጣጡ ከፍተኛ ሚና ከመጫወቱ ባሻገር ፣ ለአገሪቱ የትምህርት አሰጣጥ ጥራት ትልቅ ትኩረት እንዲደረግበት  ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የማንቂያ ደውል ከፍ አድርጎ  የደወለ ነው ።

በሚኒስትሩ እንደተገለጠው ” በመቶኛ ሲሰላ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ተፈታኞች ከ50 በመቶ  ባላይ ውጤት በማስመዝገብ ከማኅበራዊ ሳይንስ አቻዎቻቸው የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል። ከ339,642 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች መካከል 6.8 በመቶው እንዲሁም የማኅበራዊ ሳይንስ ፈተናን ከወሰዱት 556,878 ተማሪዎች መካከል ደግሞ 1.3 በመቶው ብቻ ከ50 በመቶ በላይ ነጥብ አስመዝግበዋል።

በዚህም መሠረት ከ50 በመቶ በላይ ነጥብ ያስመዘገቡ 30 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች በቀጥታ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማም ገብተው ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ይሆናል። ከዚህ  ባሻገር ደግሞ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅምን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት “የተሻለ ውጤት ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ የሚደረግ ቢሆንም እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ” የትምህርት  ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ከዚያ ይልቅ ግን ተማሪዎቹ ደካማ ውጤት ያስመዘገቡባቸውን የትምህርት ዓይነቶች ለአንድ ዓመት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንዲማሩ ተደርገው፤ የሚሰጣቸውን የመመዘኛ ፈተና የሚያልፉ ከሆነ የአንደኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ይጀምራሉ ። ” ይኽ ውሳኔ የትምህርት ሚኒስቴር ነው ።ፈተናው “ በሱሪ በአንገት አውልቅ “ መንገድ ነው ። የተሰጠው ። ጊዜውም አልነበረም ። ውጤቱ ይኽ እንደሚሆን የተረጋገጠ ነው ። ለሚቀጥሉት አምሥት አመታትም ከዚ የባሰ ውጤት ይጠበቃል ።  በየትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚቆጣጠር ገለልተኛ ተቋም ተምህርት ሚኒስቴር በመገንባት ተከታታይ ቁጥጥር እና የሞዴል ፈተና አሰጣጥ እስካልፈጠረ ጊዜ ድረስ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ከቶም አይቻልም ።

ተምህርት ሚኒስተር ፣ ውሳኔውን ይፋ ከማድረጉ በፊት ፣ 50% ካመጡት ውስጥ 300 እሰከ 350 ያመጡ ና ከዛ በላይ ውጤት ያገኙ ሥንት ናቸው ? በመቶኛ ። ከ100እሰከ 200 የመጡትስ ? ከ200 እሰከ 300 ያመጡትስ ? ምናልባት ከመቶ በታችስ  የሉም ወይ ? ይኽንን በዝርዝር ማየት ነበረበት  ።

በበኩሌ ከ200 እሰከ 300 የፈተና  ውጤት ያላቸው  በተመሳሳይ የዕውቀት ደረጃ ያሉ ናቸው ብዬ አምናለሁ ። ከ100 በታች ያሉትም እንደዛው ። ከ300 እስከ 400 ያመጡ ተቀራራቢ ዕውቀት አላቸው ብዬ እገምታለሁ ። ከ500 እስከ 600 ፤ ከ600 እሰከ 700 ደግሞ በአንድ ቅርጫት አስገባቸዋለሁ ።

ለምሳሌ ሚኪያስ አዳነ 666 በማግኘት የተፈታኞቹ ሁሉ አንደኛ ሆኗል ። ያውም ባለፉት አመታት ሰላም በደፈረሰበት በልዩ ትምህርት መከታተያ ” በቦርዲግ እስኩል ” እየተማረ ። 700 ያላገኘው 34 ጥያቄዎችን ብቻ ባለመመለሱ ነው ። ከዚህ ልጅ ውጤት ተነስተን የሌሎችን ተማሪዎች ውጤት መፈተሽ ይኖርብናል ። የውጤት ፍተሻው የሚማሩበትን ትምህርት ቤት የትምህርት አሰጣጥ ያገናዘበ መሆን ይኖርበታል ። እርግጥ የትምህርት ሚኒሥቴር ድንገት የወሰደው እርምጃ ያጋለጠው የየትምህርት ቤቶችቹን የትምህርት አሰጣጥ ደካማነትን ነው ።

ደካማ የትምህርት አሰጣጥ ና ፣ የመምህራኑ ብቃት ማነስ  ነው ። ተማሪው ደካማ ውጤት እንዲያገኝ ያደረገው ። ከዚህ በተጨማሪ ያለመረጋጋት ጭንቀትና እና  ሁከት በአንዳንድ ዩኒቨርስቲ መፈተኛ ጣቢያዎች ነበሩ ። በዚህ ላይ  አሉባልታ ነበር ። ” ፈተና ተሠረቀ ” የሚል ። በነገራችን ላይ ሥርቆት በመብዛቱ ነው ፣ ወደ ዩኒቨርስቲ ከልሎ ማስፈተን የተገባው ።በሌብነት ምክንያት ነው ፣ በገለልተኛ ፈተኛ መምህራን  ተማሪዎች የተፈተኑት ። እንደተገመተው ሥርቆት የትምህርት ጥራቱ ተጋድሮት እንደሆነ ተረጋግጧል ። ይኽ እውነት ቢረጋገጥም ፣  ዛሬም በየትምህርት ቤቱ ፣ ከፈተና በፊት ያውና ተመሳሳይ ትምህርት ነው የሚካሄደው ። በኩረጃ ነው አብዛኛው ተማሪ ለ12ኛ ክፍል  የደረሰው ። …ይኽ ከቀጠለ በመሠረቱ “ የታጠበ የለም ። ታጥቦ ጭቃ የሚሆንም የለም ። “ ማለት ይቻላል ።

በመንግሥትም ሆነ በግል ትምህርት ቤቶች ደካማ መምህራን ነፍ ናቸው ። ዲግሪና ማስትሬት እንደ ከረሜላ የሚያድሉ ኮሌጆች በሞሉበት አገር (ባይበዛም  አንዳንድ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችም ውስጥ  ይኸው ይስተዋላል  ። ) በያዘው ወረቀት ብቻ ችሎታው ሳይገመገም በየመንግስት መስሪያ ቤት ፣ በየህክምና ተቋሙ የተቀጠረ በለማስትሬትና ባለ ድግሪ ቁጥሩ ትንሽ ነው ፣ ብሎ መናገር አይቻልም ።

በትምህርት ዓለምም ውስጥ ፣ ከፈታኞች ጋር በመሞዳሞድ የሁለተኛ ደረጃ አሥተማሪ የሆኑ በአንዳንድ የመንግስትም ሆነ የግል  ትምህርት ቤት ውስጥ መኖራቸው  ይታወቃል ። እነዚህን በገለለተኛ አካል ፈታኝነት አበጥሩ ከየትምህርት ቤቱ ጠራርጎ ማውጣት ቢያስፈልግም የሚተኩ ምሁራንን ከህንድ ካልሆነ በያዝነው የሚያስታውክ የቆንቋ ፖለቲካ ከአገር ውስጥ ማግኘት አይሆንልንም ። ይኽን በቋንቋ መሞዘዝን ትተን ከሁሉም ክልሎች ለሁሉም ክልሎች ከልብ አሥተማሪ የሆኑ ፣ የበቁ መምህራንን አሥተማሪ ካልተደረገ  ግን በመጨው ዓመትም ሆነ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት በሚደረጉ ፈተናዎች  ከአሁኑ የተሻለ ውጤት ማምጣት አይቻልም ።

በተጨማሪ ፣ እንደመፍትሄ የሚሆነው ተማሪዎቹ የሙሉ ቀን ተማሪዎች የሚሆኑበተን መንገድ መቀየስ ፤ አልያም ዓመቱን በሙሉ ቅዳሜና እሁድ ሙሉ ቀን የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲማሩ በማድረግ የተሻለ ውጤት ከአምስት ዓመት በኋላ ማምጣት ይቻል ይሆናል ። ዛሬ ከ30ሺ ያልበለጠ ተማሪ 50% ፐርሰንት አግኝቷል ።  ይኽም ዩኒቨርስቲ ይገባል ማለት  ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመቀበል አቅም በላይ ያልሆነ ተማሪ አልፏል ማለት ነው ። እናም ሌሎች  የመቀበል አቅማቸው ከ20 ሺ በላይ የሆኑ ዩኒቨርስቲዎች እንዴት ነው እነዚህን ተማሪዎች የሚቀበሉት ። እንደተባለው “  በወደቁበት የትምህርት አይነት ላይ ያተኮረ ትምህርት በመስጠት በዓመቱ መጨረሻ ፈተና በመስጠት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያገኙት ሀ ብለው የዩኒቨርስቲ ትምህርት ይቀጥላሉ ። “ የሚለው ሃሳብ ከተማሪው ሞራል ግንባታ  አንፃር ትክክል አይመስለኝም ። ከ 200  እስከ 300 ያመጡ ተማሪዎች ፣ ለስድስት ወራት ተከታታይ የሆነ መሠረታዊ ዕውቀት በወደቁባቸው ትምህርቶች ሰጥቶ አጠቃላይ እውቀታቸውን በተግባራዊ ፈተና ገምግሞ ወደቀጣዩ ትምህርት ማሳለፍ ። እንዲሁም ከ200 በታች ያገኙትን በአንድ ምድብ መድቦ በዩኒቨርስቲውቹ  አቅም አስገብተው ፣ ለአንድ ዓመት ማወቅ በሚገባቸው ትምህርቶች ላይ ዕውቀት ሰጥቶ ፣ ያንን ዕውቀት የተረዱትን በፈተና ለይቶ ወደ ቀጣዩ መደበኛ ትምህርት ማሸጋገር ፍትሃዊ ነው ብዬ አምናለሁ  ።

ይኽ ለአሁኑ መፍትሄ ቢሆንም ፤ ለቀጣዩ በየትምህርት ቤቱ መሰራት ያለበት ምንድነው ? ዛሬም በአይን ጥራታቸው በመመካት፣  በኩረጃቸው የቀጠሉትን ፣ ኩረጃ አእምሮን  ገዳይ እንደሆነ እና ለመጨረሻው ፈተና መሰናክል እንደሚሆንባቸው ማነው በሚገባቸው ቋንቋ የሚያስረዳቸው ? እነዚህ እንቦቃቅላዎች በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናንን በየዩኒቨርስቲው ተፈተኑ ሲባሉ እንደ መጀመሪያዎቹ ተፈታኞች ሁኔታው ” ሱሪ በአንገት አውልቅ ። ” ሆነብን ይሉ ይሆን ??

Mekonen1
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop