January 2, 2023
7 mins read

ጭራቅ አሕመድ፤ እኩይ አዟሪት የገባ ኦነጋዊ አውሬ

abiy Asafariwያንድ ብሔር አባል አለመሆኑ የሚጠረጠር ግለሰብ የዚያ ብሔር ብሔርተኛ ከሆነ፣  ጥርጣሬውን ለማስወገድ ሲል ብቻ ማናቸውንም አረመኔያዊ ድርጊት ለመፈጸም ቅንጣት አያቅማማም፡፡  ሂትለር ይሁዳወችን ያለ ርኅራኄ የጨፈጨፈበት አንዱ ምክኒያት፣ የይሁዳ ደም አለበት የሚባለውን ጭምጭምታ ለማስተባበል ነበር፡፡  ምሥራቅ አውሮጳውያን (ቸኮች፣ ፖሊሾች፣ ዩክሬኖች፣ ክሮአቶች…) ካንግሎ ሳክሶኖች በከፋ ሁኔታ ዘረኛ መስለው ለመታየት የሚጥሩት፣  ከነጭ አይቆጥሩንም ለሚሏቸው ለምዕራብ አውሮጳውያን ነጮች መሆናቸውን ለማስመስክር ሲሉ ነው፡፡  ያሜሪቃ ጥቁር ፖሊስ ከነጭ ፖሊስ የበለጠ በጥቁር ላይ የሚጨክነው፣ ታማኝነቱን ለነጭ አለቆቹ ለማሳየት ነው፡፡  ባባቱ አማራ ነው የሚባለው ጌታቸው አሰፋ ያማራ ሳጥናኤል የሆነው፣ ትግሬነቱን ለማስመስከር ነበር፡፡

ጭራቅ አሕመድ ደግሞ በናቱ አማራ ነው ይባላል፡፡  አባቱ ደግሞ ኦሮሞ ናቸው ይባላሉ (ኤርትሬ ናቸው የሚሉም አሉ)፡፡  በዚያ ላይ ደግሞ የተጋባው ከጎንደሬ ጋር ነው፡፡  ስለዚህም በጎጠኝነት የሰከሩት የኦሮሞ ጽንፈኞች ጭራቅ አሕመድን ከአሮሞ አይቆጥሩትም፡፡  እንደማይቆጥሩት ደግሞ እሱ ራሱ በደንብ ማውቅ ብቻ ሳይሆን አልቅጥ ያስጭንቀዋል፡፡  ኦሮሞነቴን ማንም አይሰጠኝም አይነፍገኝም፣ እናቴ አማርኛ አትችልም እያለ ሳይጠይቁት የባጥ የቆጡን የሚቅባጥረው ይሄን ጭንቅቱን ለማለዘብ ነው፡፡

ጭራቅ አሕመድ፣ ፀጋየ አራርሳና የመሳሰሉት ግማሽ አማራ ናቸው የሚባሉ የኦሮሞ ጎጠኞች በኦሮሞነታቸው ስለሚጠረጠሩ፣ ባይነ ቁራኛ እንደሚጠበቁና እያንዳንዷ ድርጊታቸው በጢኖፓይፋ (microscope) እንደምትመረመር አሳምረው ያውቃሉ፡፡  ትንሽ ቢሳሳቱ ግዙፍ ውለታቸው መና ቀርቶ ከሃዲወች እንደሚባሉ ነጋሪ አያስፈልጋቸውም፡፡  እስከጣፈጡ ድረስ ተላምጠው የሚተፉ አገዳወች እንደሆኑ በደንብ ያውቃሉ፡፡  ስለዚህም እነዚህ ግማሽ አማራ ናቸው የሚባሉ ኦንጋውያን ለኦነግ ፀራማራ ዓላማ ሽንጣቸውን ገትረው የቆሙ መሆናቸው ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይገባ ሲሉ ብቻ ፣ ማናቸውንም ፀራማራ ድርጊት ለመፈጸም ቅንጣት አያቅማሙም፡፡   ከለማበት የተጋባበት እንዲሉ፡፡

“ግማሽኦሮሞ” ኦንጋውያን “ከሙሉኦሮሞ” ኦነጋውያን እጅግ የከፉ ጽንፈኞች ናቸው፣ መሆንም አለባቸው፣ ግዴታቸው ነውና፡፡  ለምሳሌ ያህል ለማ መገርሳና ጃዋር ሙሐመድ፣ “ሙሉኦሮሞ” ሆኑም አልሆኑም በኦሮሞነታቸው ስለማይጠርጥሩ፣ ጭራቅ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚጭክነውን ያህል እንደማይጭክኑ በርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡

ጭራቅ አሕመድ እጅግ አረመኔ በላዔ አማራ ጭራቅ መሆኑን በስካሁን ድርጊቱ በግልጽ ያስመሰከረ ቢሆንም፣ ግማሽኦሮሞ ስለሚባል ብቻ ኦነጋውያን መቸም ቢሆን በሙሉ ልብ አያምኑትም፡፡  ስለዚህም ኦነጋውያን ትናንት ከሚያምኑት የበለጠ ዛሬ እንዲያምኑት ከፈለገ ትናንት ካደረገው የከፋ ዛሬ ማድረግ አለበት፡፡    ስለዚህም የአማራን ሕዝብ በተመለከተ ጭራቅ አሕመድ የበለጠና የበለጠ ጭራቅ እየሆነ ይሄዳል፣ መሄድም አለበት፡፡

ጭራቅ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ ነገ የሚያደርገው ትናንት ካደረገው የክፋ እንደሚሆን ከስካሁን ድርጊቱ በመነሳት ብቻ በርግጥኝነት መናገር ይቻላል፡፡  ትናንት በሺወች አርዷል፣ ነገ ባስር ሺወች፣ ከነግ ወዲያ ደግሞ በመቶ ሺወች ያርዳል፡፡  ለዚህ ደግሞ በስልጣኔ ብትመጡብኝ መቶ ሺወች ባንድ ጀምበር ይታረዳሉ በማለት እሱ ራሱ፣ በራሱ አንደበት የተናገረውን መጥቀስ ብቻ ይበቃል፡፡  ትናንት ቶሌ ላይ ያማራን ሕጻናት ግዳይ ጥሏል፣ ነገ ጉለሌ ላይ፣ ከነገ ወዲያ ደግሞ ቦሌ ላይ ግዳይ ይጥላል፡፡

ባጭሩ ለመናገር ጭራቅ አሕመድ በማንነቱ ምክኒያት መቸም ከማይወጣበት እኩይ አዟሪት (vicious circle) ውስጥ የገባ ኦነጋዊ አውሬ ነው፡፡  ካዟሪቱ የሚያወጣው ደግሞ ሞቱ ብቻ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ መዳን የሚችለው ደግሞ ጭራቅ አሕመድን በማናችውም መንገድ ጨርቅ በማድርግ ብቻና ብቻ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ ካደረገ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡  ያሳ ግማቱ ካናቱ ነውና፣ አማራ ሆይ ሙሉ ትኩረትህን አራት ኪሎ ላይ አድርገህ፣ በማናቸውም መላ የግሙን አናት ቅላ፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop