አማራ፡ ከማለቅህ በፊት የቀረህ አንድ አማራጭ ብቻ ነው (እውነቱ ቢሆን)       

እኛ አማራወች ሁሉንም አማራጮች ሞክረናቸው ሞክረናቸው አሁን ላይ የቀረን አንድ አማራጭ ብቻ ነው፡፡ ይህም ነጻ የሆነ ከህዝቡ ለህዝቡ በህዝቡ የሚመራ የ”አባት አገር የአማራ አገርና መንግስት” ምስረታ ነው፡፡ ወያኔወችና ኦሮሙማወች ልባቸው በሚያውቀው እነርሱ ግን ለጥቅማቸው ሲሉ በሚክዱትና በሚያወላግዱት ሀቅ ከተነሳን የአማራ ህዝብ ቁጥር ከተኛ ነው፡  ግምቱ በትንሹ ከ50 ሚሊዮን በላይ ነው፡፡ ተአማኒና ትክክለኛ የህዝብ ቆጠራ ቢደረግ ከዚህ በላይም ይሆናል፡፡ ይህ ያልተጋነነ እውነት ነው፡፡

አማራ እንደ ትውልድ ቀጣይነት እንዲኖረው የጎጠኞች ሰይፍ/ካራ/ ቢለዋ/በአማራው አንገት ላይ ተሰከቶበትም ቢሆን “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ”” እያለ የሚያላዝነውን ሞኝነት ከእንግዲህ ወዲያ ማቆም አለበት፡፡ ይህንን አማራ በመሆኑ ብቻ በጅምላ ያሳረደውን እምነቱን አንቅሮ መጥፋት አለበት፡፡ ይህ አስተሳሰቡ አስጨርሶታል፡፡ አስበልቶታል፡  አሁን መሬት ላይ ያለው እውነታና የሚታየውም የሚዳሰሰውም ተጨባጭ ሁኔታ አማራ የራሱን አገር መመስረትና ራሱን ተከላክሎ የአማራ ዘርና ትውልድ እንዲቀጥል የማድረጉ አስፈላጊነት ላይ መረባረብ አለበት፡፡ አሁን ለአማራው ይህንን ማድረግ ግዴታም፣ ወሳኝም፣ አስገዳጅምና አጣዳፊም ጉዳይ ነው፡፡

ከእንግዲህ ወዲያ አማራው “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚለውን አደንዛዥ እጽ” ከውስጡ አውጥቶ ጥሎ ሀገረ -አማራ ምስረታ ላይ ማተኮር ነው የሚያዋጣው፡  ኢትዮጵያ የሚል የሞኝ ዘፈን ለማስቀጠል አማራ እንደ እስካሁኑ ሲሞት ውሎ ሲሞት ቢያድር ያልቃታል እንጅ ኢትዮጵያ አትፀናም።

የኦሮሙማ ፖለቲካ ዋና ማጠንጠኛው በተለያዩ ስሞች የሚያሽሞነሙኑት ማንም የኦሮሙማ ብሄረተኛ እየመጣ አማራን እንዲያርድና ይህም የመንግስታዊ ድጋፍ ጭምር እንዲሰጠው በትጋትና በስሌት መስራት ነው፡  በኦሮሙማ አገዛዝ ውስጥ ሆነን በስካሁኑ አመታት የሞትንላት ኢትዮጵያ ወደፊትም እኛ በገፍ ብንሞትላትም ኢትዮጵያ ሆና አትጸናም፡፤ ኦሮሚያ በመቃብሯ ላይ እንዲያብብ እየተሰራ ነውና፡፡ በሞታችን ግን የአማራን መንግስት መስርተን የአማራን ትውልድ ማስቀጠል እንችላለን!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሞትን የመረጡ ወጣት ሴቶች የመጀመሪያውን ብቻኛ የነፃነት ተጋድሎ ምዕራፍ ከፈቱ። የምዕተ ዓመቱ ማህጸን ተስፋን ሰነቀ!

አማራውን ለዚህ ዉሳኔ ምን ገፋፋው ብሎ ለሚጠይቅ ማንኛውም ሰው መልሱ በአጭሩ ይህ ነው፡፡ከማኒፌስቶው ጀምሮ በአገሪቱ ውስጥ 27 አመታት ሙሉ ወያኔ የዘራው ጸረ አማራ መርዝና ተረኛው ኦሮሙማ ያስቀጠላቸው የአማራን ዘር የማጥፋት ሴራወች ናቸው፡፡

ወደፊት ለሁሉም እኩል የምትሆን ኢትዮጵያ እውን የምትሆንበት ሁኔታ በተአምር ከተፈጠረ ግን ያኔ በእኩልነት መርህ ኢትዮጵያዊ መሆን ይቻላል፡  አሁን ግን ከማንም አንሶና የበታች ሆኖ፣ በዚያ ላይ ተዋርዶና <ታ.ር.ዶ> ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያሉ መጃጃል፤ አማራው በቃኝ ብሏል፡፡ እውነትም በቃው!!

ኢትዮጵያዊነትን አጥፍተው በተናጠል መኖርን የናፈቁ መንደርተኞችና ጎጠኞች አገሪቱን ማጥፋቱ ይሳካላቸው እንበል፡  ከዚያ በኋላ ሁሉም ሲሰምርላቸው፣ሲደላቸውና ሲስማማቸው ወደፊት የምንታዘበው ይሆናል፡፡ እስከዚያው ግን ማን ሞኝ አለ? ማን ዝም ብሎስ ይታረ.ዳል?? እና አማራም በቃኝ ብሏል፡፡

በደማችን ታሪካዊ ምድራችንን እናስከበር! ሙሉ ጎጃም፡ ሙሉ ጎንደር፡ ሙሉ ወሎ፡ ሙሉ ሸዋ ታሪካዊ እርስቶቻችን ናቸው! ወልቃይት ጠገዴ፣ ሁመራ ጠለምት፣ ራያ ፣መተክልና ደራ በወያኔ አገዛዝ በተኮልና በሴራ ከአማራ ተነጥቀው የተወስዱበት የአማራ ርስቶችና የደም መሬቶች ናቸው፡፡

በጥቅሉ  አማራው እነዚህን ርስቶቹን አስከብሮ የአማራ ሀገረ መንግስትን ይመሰርታል፤፡፤ ያጸናልም፡፡ ለዚህም ብቃቱም ፣እውቀቱም፣ልምዱም፡ አለው፡፡ የሚጎድለው ዝግጁነት ነው ፤ ይህም አስፈላጊ ዝግጁነት በተቀላጠፈና በተጧጧፈ አካሄድ አስቀድሞ ሆዳም የአማራ ሹመኞችን በማጥራት በመላው አማራ ክልል ውስጥ በየወረዳውና በየዞኑ በየመንደሩና በየከተማው ወርዶ ይከናወናል፡፡

አዲስ አበባ የበፊት ስሟ በረራ ሲሆን ታሪካዊ ርስትነቷ የአማራ ቢሆንም በዋና ከተማነት የሁሉም የሆነች ራሷን በራሷ የምታስተዳድር የራሷ ቻርተር ያላት ከተማ መህኗን    አራው  ያምናል፡፤ ለዚህም ከአዲስ አበቤ ጎን በጽናት ይቆማል፡፡ኦሮሙማ ከተማዋን ለመጠቅለል የሚያደርግውን መሯሯጥ አጥብቆ ይቃወማል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል!” - ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደገና ወኔ የተሞላበት የትግል መንፈሱን በማደስ ጥንካሬውን አሳየ!

አማራ ሆይ ይህንን እውነት በማድረግ ሂደት ውስጥ ወያኔ፣ ሸኔ ኦሮሙማ ወዘተ ሊገድለኝ መጣ! መንግስት ምናምን ወዘተ አትበል። ገዳዩአሁን ያለው የተረኞች መንግስት ነው! ገዳዮቹ ውስጥህ ያሉት የአብይ አህመድ አሽከሮች ናቸው፡፡ ከሁሉ በፊት እነርሱን “”መቀጣጫ”” እስከሚሆኑ ድረስ አምርረህ አጽዳቸው፡  ከፖለቲካ እይታ አኳያም ገዳይህ አብይ አህመድ ነው እንጅ የኦሮሞ ህዝብ አይደለም፡፡ ገዳይህ የወያኔስብስብ ነው እንጅ የትግራይ ህዝብ አይደለም፡፡ ህዝብ ህዝብን አይገድልም፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ግን ህዝብ በጥቂት ፖለቲከኞች ይነዳል፡፤ ይህም በሁሉም አገሮች ፖለቲካ ክስተቶች ውስጥ የታየ ክስተት ነው፡፤ ሆኖም ግን እያንዳንዱ አገርና ህዝብ ከችግሮቹ መውጫውን እያበጀ ችግሮቹን እያቃለለ እዚህ ደርሷል፡፤ የእኛ ግን ትንሽ ለየት ያለ ይመስላል፡፡ ስር የሰደደና የገነገነ ድንቁርና፣ ኋላቀርነት፣ ከወለል በታች የወረደ ከባድ ድህነት፣ ምቀኝነትና ተንኮል ተገምደው ተገምደው ተመሰጣጥረው ችግሩን ማሰወገድ ቀርቶ ከመረዳት በላይ አክብደውታል፡፡ህዝቡም ደቋል፡፤ተኮላሽቷልም፡፡ ስለሆነም ለየወቅቱ የየወቅት መፍትሄ መሻት የግድ ነው፡፡

አገሪቱ ያሉባትን ፖለቲካዊ ችግሮች ከመፍታት ረገድ ችግሮቹ በተገቢው መንገድ ተፈትተው አገሪቱ የሰመረ እድገትና የተከበረ አንዲነት እንዳይኖራት ተግተው የሚሰሩት የው ወቹ ጠላቶቿ ተጽእኖ ቀላል አይደለም፡፡በዚህ ላይ አድርባይና ተንበርካኪ አመራር ሲያገኙ ምን ያህል ነገሩን እንዲወሳሰብ እንደሚያደርጉት የብዙ አገሮች አብነቶች አሉ፡፡ ብሎ ብሎ ህዝብ ነቅቶ ወደ ትክክለኛ መረዳቱ ሲመለስ ያኔ ብዙ ዋጋ የተከፈለበት ውጥንቅጥ፣ እልቂትና ውድመት በሚያሳዝን ሁኔታ በታሪክ ተመዝግቦ ያልፋል፡፤ ከዚያ በኋላ ትውልድም ህይወትም አገርም ይቀጥላሉ፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ አገሪቱ አሁን እቡይ በሆነ ሰው እጅ ወድቃለች፡፡ አብይ አህመድ ወደር የማይገኝለት እቡይ፣ አድርባይና አታላይ ሰው ነው፡  አገሪቱንም ወደባሰ ችግር እየወሰዳት ስለሆነ አማራ ግፉ በአንተ ላይ ስለበዛ ከማለቅህ በፊት በቶሎ ወስነህ ምርጫህን አስተካክል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጲያዊያን ላይ ሰቆቃ የሚፈጽመው የአብይ አህመድ ምንደኞች ይጋለጡ

ወያኔም ሆነ የአብይ አህመድ ኦሮሙማ በተናጠልም ሆነ በቅንጅት ሊገድልህ ሲመጣ በምትችለው ሁሉ ግጠመው! በነፍጥህ የሚገባውን በቦታው ላይ ስጠው፡  እንዳትምረው። ከአድዋ ድል አድራጊነትህ በፊትም ሆነ በአድዋ ላይ በሰራሀው ጀብድ አለም ያወቀው ታሪክህ ለዚህ ምስክር ነው፡፡

ወዳጅና ጠላትህን አበጥረህ ለይና ወዳጅህ ጋር ለጥቅምህ ተወዳጅ ጠላትህ ጋርም ለድልህና ለነጻነትህ ተፋለም፡  ለጊዜው ትጥቅ፣ ከባባድ መሳሪያ ስልጠና ወዘተ አስፈላጊወችህ ናቸው፡፤ በጊዜዊ ደረጃ ለዚሁ አጭሩ ስልት አማራ የሆንክ ሁሉ በቻልከው መጠን የውጭ የውስጥ ሳትል በቅንጅት ተናብበህ ስራ!!! ዞሮ ዞሮ መሳሪያ ልብ አይሆንም፡፡ተደራጅ፣ ታጠቅ!! ተነሳ!!

 

2 Comments

  1. አማራውም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ ማወቅ ያ፤ለበት አንድ ሀቅ አለ፡፡ አብይ አህመድ አሊ የአገሪቱ ነቀርሳ ነው፡፤ ነቀርሳ ደግሞ ተነቅሎ ወይንም ተቆርጦ ካልተጣለ(ካልተወገደ) በስተቀር ደህናውን ይበክላል፡፡ ቆይቶም ይገድላል፡፡
    ስለዚህ የሁሉም ኢትይዖፕያዊ ቀዳሚው አጀንዳ አብይ አህመድን ነቅሎ መጣሉ ላይ ነው፡፡

  2. አረ ከነቀርሳነቱ ብላይ ሳይጠራ አማራ ስብሰባ ላይ የሚገኝበት ምስጢሩ ምንድነው? ሰውዬው የፍርሀት ቆፈን ሳይጠፍረው አልቀረም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share