December 4, 2022
28 mins read

” የሚሰማ ጆሮ ያለው የሰማል ። የማይሰማም አይሰማም ። ዓዋቂ ሰውም  ጥፋትን  እያየ ” ዝም አይልም ! ” መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Atlantis was the ancient most continent of the earth, and civilization had reached the highest possible peaks. But whenever a civilization reaches a great peak there is a danger: the danger of falling apart, the danger of committing suicide.  Humanity is facing that same danger again. When man becomes powerful, he does not know what to do with that power. When the power is too much and the understanding is too little, power has always proved dangerous. Atlantis was not drowned in the ocean by any natural calamity. It was actually the same thing that is happening today: it was man’s own power over nature. It was through atomic energy that Atlantis was drowned — it was man’s own suicide. But all the scriptures and all the secrets of Atlantis were still preserved in Alexandria.

 

( Philosophia Perennis, Vol 1 Chapter #1 Chapter title: The Greatest Luxury 21 December 1978 in Buddha Hall ) እንግዲህ ሰውነት ተመልሶ አደጋ መሆኑ አይቀሬ ከሆነ ዘመናት መቆጠራቸውን የላይኛው የእንጊለዘኛ ፅሑፍ ይመሰክራል ። ሰው በጥበብ ተራቆ ኃይል በእጁ ሥትሆን የኃይልን አጠቃቀመሸ ወገኝነት ባለመገንዘቡ በራሱ ላይ አደጋ ማድረሱን ታሪኩ ያሥረዳል ። በጥበበኞች ጥበብ የገዘፈቺው ኃይል አውዳሚነቷን የሰው መረዳት ኮሳሳ ሆኖ መረዳት ሲሳነው ፣ ያቺን አውዳሚ ኃይል በቀላሉ ጥቅም ላይ ሰውየው ያውልና በምድሪቱ ላይ ማአትን ያወርዳል ። የመግቢያው ፅሑፍ እንደሚተርክልን ፣ አትላንቲስ በተፈጥሮ አደጋ ወይም በቁጣ አልወደመችም ። ዛሬ እያሥተዋልን ባለነው ከተፈጥሮ በተቃራኒ በቆመ የሰው የጥፋት አሥተሣሠብ እንጂ ። ብታምኑም ባታምኑም ፣ አትላንቲስ የጠፋቺው በአውቶሚክ ቦንብ ነው ።
( ነፃ ትርጉም _ ውርስ ትርጉም በሉት ከፈለጋችሁ ። )

እንግዲህ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ !  የሥልጣኔ ጫፍ ላይ የደረሱ አገራት እብድ መሪዎች ዓለም ካፈራች እና ለሥልጣን ያበቃቸው ህዝብ በፍርሐት ቆፈን ውሥጥ ያለ ከሆነ ፣ እነዚህ ኃያላን መሪዎች የዓለም ጦስ እንደሚሆኑ አትላንቲስ ያሳውቀናል ። የዛሬው ተጨባጭ እውነት የዓለም ፍፃሜ እንደአትላንቲስ እንደማያምር ያሳብቃል ። ሩሲያን ” እሥቲ ወንድነሽ !…እናይሻለን … ኒኩለር ተኩሽ እስቲ … ? ምላሹን እናሳይሻለን ። ” በማለት አሜሪካ በመሪዎቿ በኩል መፎከሯ ፣ የጤና ነው ትላላችሁ ? ። መሪዋ የዕድሜ ባለፀጋ በመሆናቸው ህይወትን እሥከ ጥግ ሥለኖሩ ፤ የዓለም ዜጎች ይበልጡንም ለህይወት የተራቡ ወጣቶችን ሞት ሊፈርዱባቸው የቻሉ ይመሥላል ። ደግሞስ የዩክሬን ጦርነት ሰበብ እና የአውሮፓ እና የአሜሪካ ግትር አቋም የጦርነቱ መንሥኤ እንደሆነ እያወቁ ለንፁሐን ዜጎች ማለቅ የሚረዳ ቢላ ማቀበል ነበረባቸውን ? ዩክሬን እኮ ጌቶቿን ተማምና ነበር እንደ በጊቱ ላቷን ውጪ ያሳደረችው ። በዚህ ሰበብም ” አጀብ ! ” ያሰኘ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ ውድመት ነው በዩክሬን ህዝብ ላይ የደረሰው ። … ያሳዝናል ።

 

ወዳጄ ፣ ጦርነት ፊልም እንደመሥራት እና ትያትር መድረክ ላይ እንደመሥራት የቀለለ አይደለም ። “ ዜለንስኪ “ ። ቀላል ነው ብለው ነበር ። በአውሮፖና አሜሪካ መንግሥታት ተማምነው የፊልም አክተሩ ህዝብና አገርን ለውድመት ዳረጉ ። በቡኩሌ የወገነ እና ለጥቅም የተቀመረ የኃያላን መንግሥታት ጦርነትን አጥብቄ እቃወማለሁ ። ትላንት እንጊሊዞች መቅደላ ድረስ በመዝመት የፈፀሙትን ግፍ አንረሳም ። የአፄ ቴዎድሮስን አስከሬን ሳይቀር አጎሳቅለዋል ። ዓፄ ቴዎድሮስ ፣ ራሳቸውን በጀግንነት የሰው ፣ ሽጉጣቸውን ጎርሰው ቃታውን ሥበው ጥይቱን በመጠጣት ፣ የተሰው ታላቅ መሪ ነበሩ ። የጀነራል ናፒየር ጦር ግን ጭካኔ በተሞላው ሁኔታ ሹሩባቸውን ሳይቀር ቆርጦ ወሰደ ። ልክ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ በልብሳቸው ላይ ወታደሮቺ ዕጣ ተጣጣሉ ። የቤተመንግሥቱን ሀብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያንን ሀብትና ንብረት ዘረፉ ። ከዛም የመቅደላና አካባቢዋን ቤት አቃጠሉ ።…የኢትዮጵያ አማፅያን መሪዎችም (ትህነግ ) አድራጎት በመሪውቹ ጨለምተኝነት የተከሰተ ነበር ። ከላይ በገለፅኩት የእሳት ጫወታ እና ” በመግደል ወደ ድል መዝለቅ “ይቻላል ብለው ያምኑ ነበር ። ግድሎ በጉልበት በልጦ ፣ ታላቅ ወይም ንጉሥ የመሆን የግለሰቦች እምነት ነገም ላለመቀጠሉ ምንም መተማመኛ የለም ።
ትርጉመ ቢሥ ጦርነት ፣ ዓለማና ግቡ ከህዝብ እውነት ጋር የሚጋጭ ፤ በጦርነት ተጠቅመው ሀብት ለማግበስበስ የሚሹ የውሥጥና የውጪ ኃይሎች ጦርነት ፤ በመቶሺ የሚቆጠሩ የአንድ አገር ዜጎች ከንቱ መሥዋትነት እንዲከፍሉ አድርጓቸዋል ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከሞቀ ጎጆቸው ተፈናቅለው የሥደት ኑሮ እንዲኖሩ ፣ በዚህ ጦርነት ተገደዋል ። ( ይኽ የሰሜኑ ቀፋፊ እውነት ዛሬ ወደ ምዕራብ ሸዋ እና ወለጋ ተሸጋግሯል ። )

 

ዛሬ ፣ ሠላም ሲወርድ ወደ ትግራይ ክልልም ሆነ ወደ አማራ ክልል ፤ ወደ ቀያቸው የተመለሱት ፣ ፍፁም ደይኽተው ነው ። እንዲህ ዓይነቱ መከራ በየትም አገር የሚከሰተው በእብድ የፖለቲካ መሪዎች ሰበብ ነው ። እነዚህ የሥልጣን አረቄ ናላቸውን ያዞራቸው መሪዎች ሥልጣን ከያዙ በኋላ መሪነታቸውን ያልወደደ ሁሉ እንዲሰቃይ የሚሹ ፣ መሪነታቸውን  ወዶ ላሸረገደ ደግሞ ወርቅ ይነጠፍለት የሚሉ ሆነው እናገኛቸዋለን ። በሰዎች ሥቃይ ዘላለማዊ ተፈሪነትን እናገኛለን ብለው የሚያሥቡ ፣ ከንቱዎች በመሆናቸውም m ለእነሱ ሥልጣን መራዘም እልፍ ሰው በየቀኑ መሰዋት ቢሆን ግድ የላቸውም ። …  በበኩሌ በሰዎች ሥቃይ የሚደሰቱ በፖለቲካ ዙሪያ ያሉ መሪዎች በሙሉ ጤነኞች ናቸው ብዬ አላስብም ። ” በመላው ዓለም ያሉ ፣ የአገር መሪዎችም ሆኑ ፖለቲከኞች የፈለጉትን ጥቅም ለማግኘት ከመግደል የዘለለ አማራጭ የላቸውም እንዴ ? ” ብዬም አንዳንዴ እጠይቃለሁ ። “ በሰዎች መከራ ፣ በሰዎች እልቂት ፣ ሥደትና ርሃብ መደሰት በእውነቱ እብደት እንጂ ጤነኝነት አይሆንም ። “ ብዬም እራሴው ጥያቄውን እመልሳለሁ ።

 

ፖለቲከኞቹ ምናልባት ለእውቀት ተግተው የአትላንቲሰን ፍፃሜ ከታሪክ በመረዳት ለሰው እና ለዓለም ሠላም ማሰብ የሚጠበቅባቸው ይመሥለኛል ። በዓለም ላይ የሥልጣኔ ጥግ ላይ የደረሰ ክፍለ ዓለም የወደመው እንደዛሬው ዓይነቱ የእሳት ጫወታ ተጀምሮ ነው ። ልዩ ፣ ልዩ ዘመናዊ መሣሪያ ሠርተው ፣ እሳት እየተወራወሩ መደባደብ የጀመሩት የአትላንቲስ ሰዎች ፣ በመጨረሻ የክፍለ ኀጉሩን ውድመት አዋልደዋል ። አጠቃላይ ውድመት ።

እውነታውን የዛሬ የታሪኩ ቅሪቶቹ ይናገራሉ ። ቅሪቶቹ ይመሠክራሉ ። ክፍለ ኀጉሩን ፣ በአንዳች ምትሃት አልጠፋም ። አትላንቲስ እና ከፍተውን አውደመው ራሳቸውም አብረው ያጠፉት በሥልጣኔ ከፍ ያሉት የዛን ዘመን ሰዎች ናቸው ። ዛሬ አሌክሳንደሪያ ውሥጥ ይህንን የታሪክ እውነት ታገኛላችሁ ( አሌክሳንደሪያ ሁለተኛዋ ትልቋ የግብፅ ከተማ ናት ። በአረቡ ዓለም አራተኛዋ ምርጥ ከተማ ሥትሆን ከአፍሪካም ዘጠነኛ ደረጃን ይዛለች ። የተሰየመችውም በታላቁ ጦረኛ አሌክሳንደር ነው ። የተቆረቆረችውም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 331 ነው ።  በነገሬ ላይ ? እንደ ምሥራቃዊያኑ አሳብያን እይታ “ ፖለቲከኛው ዝም ብሎ ዓለምን የግሉ ሊያደርጋት የሚሻ ፍጡር እንደሆነ ታውቃላችሁን ? አዎ ትልቅም ሆነ ትንሽ የሰው ኃይል አደራጅቶ የሚታገል የፖለቲካ ቡድን ሁሉ ለሥልጣን ወይም ለመሪነት ነው የሚታገለው ። መሸቱ ሥልጠን እና ሥልጣን የሚያጎናፅፈው ኃይል ነው ። በዚህ መሻቱም ፖለቲከኛው ከሁሉም በላይ አደገኛ ሆኖ እናገኘዋለን ። ምናልባትም ከፈላስፎች ይልቅ ፖለቲከኞች እጅግ አደገኞች ሆነው እናገኛቸዋለን ። ምክንያቱም ፖለቲከኛው ከፈላስፋው ይልቅ ሥልጣንን ይሻልና !! ይኽ ብርቱ የሥልጣን ኃይልን መሻትም የበለጠ ሁከተኛ ያደርገዋል ። በተግባር ። ፖለቲከኛው በህይወት ውስጥ ያለው መሻት ህይወት ራሷ ሳትሆን ሥልጣን የሚያጎናፅፈው ኃይል ነው ። ህይወትን በተፈጥሮዊ መልኳ እንደወረደች ማየት የማይችል ዕውር ቢኖር ፖለቲከኛ ነው ። ፕለቲከኛው ብዙን ጊዜ ግቡ ሥልጣን ሥለሆነ ፣ ለኃይል የተጠማ ንክ በመሆኑ አውዳሚ ተግባራትን ሲከውን እና ሲያስከውን እናሥተውላለን ። ፖለቲከኛው ፈፅሞ የህይወትን እውነት ወደ ማወቅ አይመጣም ።

 

እሥቲ ታሪክን ዳሱ ፣ ዓለም በመንግሥት መተዳደር ከጀመረች ጊዜ ጀምሮ ፣ ፈረኦን ፣ቄሣር፣ንጉሥ ፕሬዝዳንት፣ጠቅላይ ሚኒሥቴር የተባሉ ፣ የተደነቁ ፖለቲከኛ መሪዎች ዓለም ነበሯት ። ከፖለቲከኞች በተለየ መልኩ የህይወትን እውነት የተረዱ ። በተቃራኒው ደግሞ …. ሂትለር ፤ ሞሶልኒ ፣ እሥታሊን …ወደ አፍሪካ ሥትመጡ አፄ ቦካሣን ፣ፊልድ ማርሻል … ኢዲያሚን ዳዳን የመሣሠሉ ጨካኝ መሪዎችን ዓለም አሥተናግዳለች ። በጉልበት ፣ በኃይል የሚያምኑ ።… በጉልበት እና በኃይል የሚያምኑ የበዙ መሪዎች ዓለም ነበሯት ።እንደሚታወቀው ዛሬ በህይወት የሌሉ አብዘኞቹ የአገር መሪዎች ፖለቲካን ተገን አድርገው በህዝብ ይሁንታ ወይም በተወሰነ ህዝብ የኃይል ድጋፍ ለሥልጣን የበቁ ናቸው ። በአፍሪካ ደግሞ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ። ወይም በጠብ መንጃ ። … እናም በአፍሪካ ለሥልጣን የሚታገል ፖለቲከኛ ሁሉ አውዳሚ ኃይልን በጭፍን የሚጠቀም እና በሥሜት እርምጃ የሚወስድ ነው ። በአመዛኙ ።

ዓውዳሚ ና ያፈጠጡ እና ያገጠጡ እኩይ ተግባራትንም እንደ ሁለት የእግር ኳሥ ቡድኖች ጨዋታ የሚቆጥሩ እና ከአንዱ ቡድን ጋርም ወግነው ፣ ” በለው ! ቁረጠው ! ፍለጠው ! …” ሲሉ ከርመው ፣ ከአንድ እና ሁለት ዓመት እልቂት በኋላ የሚፀፀቱ ፖለቲከኞች እንዳሉም ዛሬ እያሥተዋልን ነው ።  መቼም ፀፀቱ ” የድመት መንኩሳ ዓመሎን አትረሳ ።” ተረት ባይሆን ደስ ይለናል ። … ዐይን እና አመዛዛኝ ህሊና ካላቸው የህይወትን እውነት ለማየት ይደፍራሉ ብዬ አሥባለሁ ። የህይወት እውነት ማለትም ደግሞ ፣ ሰው ሁሉ በትበብር ተደጋግፎ መቆሙን ፣ አመላካች ነው ። የአንዱ መኖር ለሌላው ህይወት መለምለም ግዙፍ አሥተዋፆ ያደርጋል ። ዓለም ራሷ እየተደጋገፈች ትቀጥላለች እንጂ ፤ በተናጥል የተሻለ ኑሮን መሥቀጠል ከቶም አትችልም ።

 

በአገራችን ዛሬ ጥቂት የማይባሉት ይህንን እውነት የተገነዘቡት ፣ እጅግ ብዙ ዜጎች ያለሃጢያታቸው እንደ ቅጠል ከረገፉ በኋላ ነው ። እጅግ ረፍዶ ፣በማይረባው የእርስ በእርስ ጦርነት ከተሰላቸን በኋላ ነው ፤ ይበቃል ። ጦርነቱ “ ለአገሪቱና ለህዝቧ የሚጠቅም አንዳችም ፋይዳ ፣ ቱርፋት ፣ ትርፍና ጥቅም የለውም ። “ የተባለው ። ። …
ይኽንኑ ለመሥከር ያህል ፣ የትህነግ መሪዎች ፣ የዕብደት ጉዞ እና ግብ አልባ እንደሆነና ፣ ረብ የለሽ ጦርነት እንደሆነ ተገልፆል ። የደቡብ አፍሪካ የጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ/ም የ ” ጦርነት ይበቃናል !! ” ንግግር በዋቢነት ማቅረብም ይቻላል ። ” ያለ ሐጢያታቸው የሚሞቱትን እንመልከት ። ሥለማፍረስ ሣይሆን ሥለመገንባት እንጨነቅ ። ለሰው ልማት እንጂ ጥፋትን አናሥብ ። ነገ ጠፊ ለሆነው አበባው ሰው ዛሬ መጨነቅ የእኛ ፖለቲከኞች ግዴታ ነው ። …” ተብሏል ። በገደምዳሜም ፣ ሥለ ወንዳዊ እኔነት ሆርሞን “ ቴስቴስትሮን “ በእንጊሊዘኛ ቅኔ ሲቀኝም ሰምተናል ።

የህይወት እውነት ምንድነው ? የምታየው የምትዳስሰው ፣ የምታሸተው ፣ የምታሥተውለው ፣ የምትመለከተው ፣ የምትሰማውና የምታዳምጠው ተፈጥሮ አይደለምን ? ተፈጥሮስ ሰው ለተባለ አለቃ የተፈጠረች አይደለችምን ? ከእምነት አንፃርም ሆነ ከሣይንሥ አኳያ በትፈትሽ ተፈጥሮ ለመለው ሰው ልጅ ጥቅም የተሰናዳች እና የተሰነደች አይደለችም እንዴ ! ? ታዲያ እሥከዛሬ ዩኒቨርሲቲ ለአሥተማረ መምህር ይህ ጥሬ እውነት እንዴት ሳይገባው ቀረ ? ይኽ ጥሬ እውነት ነው ። አንተ በፈለከው መንገድ አብስለው ። … አንተ ፣ አንቺ እና እኔ እሥከሞት በተፈጥሮ እየተገለገለን እንጓዛለን ። ከታደልን ፣ ከጨቅላነት እሥከ መጃጀት ባለው ሂደታችን ተፈጥሮን የሙጥኝ ብለን ፣ ከአንቀልባዋ ሣንወርድ ነው የምናቀለፋው ። ለዘላለሙ ።

 

የተፈጥሮን አየር እሥከ ህቅታችን ድረስ እየተነፈስን ። በከዋክብቱ ብርሃን እየተደሰትን። ፀሐይቱን እየሞቅን ። እፅዋቱን እና እንስሳቱን በየቀኑ እየተመገብን ። በውሃ ጥማችንን እያረካን ። በተፈጥሮ ድንገተኛ አደጋ ሥቃይዋን እያጣጣምን ። በሳቅና በኩርፊያ ፤ በደስታና በሐዘን ፤ በዳንኪራና ለቅሶ ፤ በማግኘትና በማጣት ፤ በፌሽታና በድብርት ፤ በመጥገብና መራብ ፤ በመነሳትና መውደቅ ፤ ወዘተ ።እውነት ነው ። ዘወትር ታቅፈን ፣ ተሳስረን ፤ እርስ በእርስ እንደ ሸማኔ ድር ተቆላልፈን ፣ ይህቺን ህይወት እሥከጊዜያችን እንኖራታለን ። እናም ህይወት በሥቃይዋ ና በደሥታዋ ውስጥ እያኖረቺን ሳናስበው ወደ ሞት ታዘልቀናለች ። መቼም የሥጋ መጨረሻው መበስበስ ነውና ! እየኖርን ሣለ ባላሰብነው ድንገተኛ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ ወይም በህመም እንሞታለን ። ሥጋችን ይበሰብሳል ። ” ይህ በሥባሽ ሥጋ ነው እንግዲህ የበዙ አላዋቂ ሰዎችን ብቻ ሣይሆን ሊሂቃኑን የሚያባለው ” ሁሉም ሰው መሞቱ እና ሥጋው መበሥበሱ ግን እርግጥ ነው ።

 

ይህንን እውነት ዘግይተው እንኳ የማይገነዘቡ ዛሬም ጥቂት አይባሉም ። ሞት በጉያቸው ውሥጥ እየኖረ ፈፅሞ የረሱት ሰዎች በቢሊዮን ቢቆጠሩ አይገርምም ። ሰው እኖራለሁ እያለ የሚሞት የዋህ ፍጥረት መሆኑ ያሳዝናል ።  ትላንት እንኖራለን ሺ ዓመት እንግሣለን ያሉ መሪዎች በየዋህነታቸው ባልጠበቁት መንገድ አልፈዋል ። የዩሊየስ ቄሣር እና የቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ኃይለሥላሤ ( የቀኃሥ ) ዓሟሟት አሳዛኝ ነው ። በዩሊያስ ቄሳር ግዲያ ሤራ እና ዘግናኝ አገዳደል የአጎቱ ልጅ ፣ ብሩተስ ተሳትፏል ። እያንዳንዱ የሤኔት ዓባል በዩሊያስ ቄሣር ሰውነት ላይ ጩቤውን አሣርፏል ። ሆኖም ዩሊያስ የተሰማው የብሩተሥ ጩቤ ነበር ። እናም ዩሊየስ ” አንተም ብሩተስ ? ” አለው ። ይሁንእንጂ ወዳጄ አንተ ከሮም አትበልጥብኝም ። ” አለው እና ጩቤውን አጥብቆ ዩሊያስ ልብ ላይ ሠነቀረው ። ቀኃሥም ምናልባት ያፈናቸው አንድ የሚያውቁት እና “ ይህን ከቶ አያደርግም ። “ ያሉት ሰው ሊሆን ይችላል ። እናም ” ጃንሆይ እርሶ ከኢትዮጵያ አትበልጡም ። ” የሚል መልሥ ሰጥቷቸው ይሆናል ። … ያም ሆነ ይህ ፣ ትላንት በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ያሉ ፣ ለሰማይና ለምድሩ የከበዱ ባለሥልጣናት ዛሬ የሉም ። በዓለም የታወቁ ሣይንቲሥቶች ፣ አቶሚክና ኒኩለር ቦንብን የፈለሰፉ ዛሬ የሉም ። በየትኛውም አገር የነበሩ እጅግ የተከበሩ እና የናጠጡ ሀብታሞች እና የአገር መሪዎች ዛሬ የሉም ። ተራ እና ተርታ ሰዎችም ገና እንኖራለን ብለው እየተመኙ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ፤ ዓለም ከተፈጠረች ጊዜ ጀምሮ ሞተዋል ። …

ዛሬም በቀን በመቶሺ የሚቆጠሩ ሰዎች በዓለም ላይ እየሞቱ ነው ። የእንግሊዝ ንግሥት በቅርቡ በየቀኑ ከሚሞቱት ከመቶ ሺ ሰዎች መካከል እንደ አንዱ ተቆጠረው ተቀብረዋል ። ማንም ከሞት አያመልጥም ። ይህንን የህይወት እውነት ተገንዝቦ ፣ ቆም ብሎ አሥቦ ከበዛ ግብዝነት እና ገደብ አልባ መሞላቀቅ በጊዜ መውጣት ብልህነት ነው ። በተለይም የአፍሪካ መሪዎች ትላንት የመጡበትን የድህነት መንገድ ዘንግተው ፣ በዛ ደሃ ወገናቸው ላይ እያንዳንዱ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መኪና እያንጋጉ የበቆሎ ቂጣ ብርቅ በሆነበት ደሃ ወንድምና እህታቸው ላይ መዘነጡ ሊያሳፍራቸው ይገባል ። ለደሃ አገር የማይመጥን መኪና በመግዛት የዓለም ቱጃሮችን የበለጠ ቱጃር በማድረግ ከሚያጠናክሯቸው ይልቅ ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊታቸውን ቢያጠናክሩ እና ደሃ ህዝባቸውን ቢያንሥ በቀን ሁለቴ ለማብላት የለሙሥና ቢሰሩ መልካም ይመሥለኛል ። የእነሱ ጥጋብ የደሃው ወገናቸው ፈንጠዚያን የሚያዋልድ አይደለም ና የተረጋጋች አገርን ለመገንባት ጠንካራ ዲሲፕሊን ያለው ፣ የፖለቲካ ወገንተኝነት የሌለው የአገር መከላከያ ሠራዊት ለአንድ አገር ሠላም ወሳኝ መሆኑንን መገንዘብም ለታሪክ መጨነቅ እንደሆነም መገንዘብ መልካም ነው ። ደሞም ይህ የገሃዱ ዓለም እውነት ነው ። ከአፍሪካ ግብፅን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል ። እውቀት ፣ ትዕግሥት ፣ አርቆ አሣቢነት ፣ ጠንካራ የቁጥጥር እና የውሳኔ ሰጪነት ማወቅር እሥካለ ጊዜ ድረሥ የአገርን ሠላም ጠባቂ እሥከ አፍንጫው የታጠቀ የጦር ሠራዊት መኖሩ ችግር አይሆንም ። ችግር የሚሆነው ” ዓለምን የሚያጠፋ አቶሚክ እና ኒኩለር ቦንብ ታጥቄለሁ እና ፍሩኝ ። አክብሩኝ ።

 

እንደ ፈለኩ አገራችሁ ገብቼ የደሃ መሶባችሁን እየገለበጥኩ ልብላ ። ” በማለት በደሃ አገር መሪዎች ላይ ማላገጥ ነው ። ችግር የሚሆነው ኒኩለር እና አቶሚክ ቦንብ እሥከ አፍንጫው ከታጠቀ ኃይል ጋራ ፤ ” እኔም አለኝ ! ” በማለት አጉል መሣፈጥ ወይም በእሣት መጫወት ነው ። አትላንቲስ የወደመው ምናልባት በእንዲህ ዓይነቱ ግብዝነት ነው ። ትላንት ዕውቀት ፣ ብሥለት ፣ ትዕግሥት ፣ እና ማስተዋል …በጎደላቸው የአትላቲሥ የፖለቲካ ሰዎችና መሪዎች ሰበብ አንድ ትልቅ ሥልጣኔ ላይ የደረሰ ክፍለ ሃገሩ መውደሙን ከላይ ጠቅሻለሁ ። እናም በያአንዳንዱ አገር ላይ ሠላም ይሰፍን ዘንድ ዓለም በአርቆ አሣቢ ፣ ለሰው ልጆች ሠላም ደንታ ባላቸው አሥተዋይ ፖለቲከኞችና የአገር መሪዎች እንድትሞላ በዓለም ላይ ያሉ ከራሥ በላይ ነፋስ የማይሉ አሳቢያን እና የፕሬስ ሰዎች የዓለምን ህዝብ በዕውቀት እንዲደረጅ መጎትጎት ይጠበቅባቸዋል ። ዕውቀት ከነገሠ ፤ ማለትም ሰው ሁሉ ተመጣጣኝ እውቀት ካለው ፤ በራሱ ኀይል ነውና ዓለምን ከጥፋት እንደሚታደጋት አምናለሁ ። ዕውቀት ጥቂቶች ጋር ተከማችቶ ብዙሃኑ በድንቁርና ውሥጥ ካለ ግን ፣ ዓለም በቀላሉ ትጠፋለች ። … ።

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Dr. Fekadu Bekele
Previous Story

ኢትዮጵያና የቴክኖሎጂ ዕድገት ፈለግ! – ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

FiBsfBgXoAAqoh1
Next Story

የዐማራ የህልውና ትግል መርህ የትግል ጥሪ

Latest from Blog

blank

አርበኛ አስረስ ማረ እና ምርኮኞቹ | ስለ ፋኖ የብሔራዊ ባንክ ገዥው ያልተጠበቀ ንግግር |

#ሰበር_ዜና #AmharaFano ➢መሰከረም 29/01/2017 ዓ.ምብዙ ድሎችን አግኝተናል፣➢1️⃣115 ምርኮኛ ➢2️⃣70 እስረኞችን አስለቅቀናል➢3️⃣ 7 ብሬን➢4️⃣2 ድሽቃ➢5️⃣ 4 ስናይፐሮችን➢ለትግል የሚጠቅሙ የነፍስ ወከፍ ክላሾችንተተኳሾችን መኪኖችም ገቢ… pic.twitter.com/GbYaOAtFtr — ትዝብቱ🔔 (@Geteriew1) October 12, 2024 በፋኖ የተማረኩት ኮሎኔል
blank

ትግሉ ይጥራ – ከጥሩነህ ግርማ

የህልውና ትግሉን ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለማሸጋገር የኦይዶሎጂ ብዥታን ማጥራትና በመሬት ላይ ያለውን ተንኮል መጋፈጥና ማፅዳት ያስፈልጋል የህልውና ትግሉ በአማራ ብሄርተኝነት ላይ ያጠነጠነ እንደመሆኑ የመኖር አለዚያም እንደ ህዝብ  የመጥፋት ትግል ነው: ሌላው ኢትዮዽያዊ ወገን
blank

የፋሽስቱ አብይ አህመድ አሊ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተካሄደ ስለሚገኘው ጦርነት ከመስከረም 13 እስከ 27/2017 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሰ የጉዳት !!!መረጃ:

ሸዋ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ኮሉ በተባለ አካባቢ ላይ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከኦሆዴዱ ጥምር ጦር ጋር ቅንጅት በመፈጠር መስከረም 22 ቀን 2017ዒ.ም ከለሊቱ
Go toTop