ብልፅግና ሆይ ከፖለቲካ ቁማር /Political Conspiracy/ ና ከፖለቲካ አስመሳይነት /Political Correctness/ አባዜ ውጣ

መንግስት የሚያዋጣውን እራሱ ቢያውቅም ሃገርን በሰላም ፣ በሕግና በአንፃራዊነት በተረጋጋ መንገድ ለመምራት ከብልጣብልጥነትና ከተንኮል በፀዳ  / far from Conspiracy/ መልኩ ሊያስተዳድር የግድ ይለዋል እንላለን።

ፈረንጆች አንድ የሚከውኑት አፀያፉ ና ተንኮል የበዛበት አካሄድ አላቸው እሱም የፖለቲካ ጂዋጂዌ(አስመሳይነት) / Political Correctness/ ይሉታል።

ይህ ማለት ፖለቲከኞች ወይም መንግስታት እውነቱን እያወቁና ትክክለኛ አደጋ የሚያስከትሉ ጉዳዮች እንዳሉ እየተገነዘቡ ለሚቃወሟቸው ፣ ለተፃራሪዎቻቸው፣ ለአደጋ ፈጣሪዎች እና ለአሸባሪዎች በመርዝ የተለወሰ ከለላ ፣ እሽሩሩ ማለትና ድጋፍ መስጠት የሚታይበት በሴራ የተተበተበ አካሄድ አላቸው።

ይህንም አካሄድ ብልፅግና እየተከተለና እየፈፀመ ይመስላል ። ኢትዮጵያዊነቱን ክዶ ልገንጠል ያለን ቡድን ፣ ወልቃይት ጠገዴን ቡጉልበት ይዞ ከሃገር ኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተጣምሮ ሃገርን ድምጥማጧን ሊያጠፋ ካሰብ ሕወሃት ጋር መለሳለስ ፣ አጥያቱን ማቅለል “የወገንን ቁስል ረስቶ “ ወያኔን “እመ አሰረ ዐጥያት ፣ እግዚአብሔር ይፍታችሁ” ብሎ በድፍረትና ሕዝብን ንቆ ከጠላት ጋር የመላላስ በፖለቲካ ሻጥር /Political Conspiracy/ና በፖለቲካ ሸለመጥማጥነት / Political correctness/ በሽታ ብልፅግና የተለከፈ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ እየታየበት ነው።

ለምሳሌ አሜሪካኖችና አውሮፖዊያን አሸባሪነትን በጣም ይጠየፋሉ ፣ ይከላከላሉ ፣ አሸባሪነት ይፈልቅበታል በሚባለው ሃገራት አፍጋኒስታን ፣ ኢራቅ ወዘተ ያለውን ቡድን ይፋለማሉ።

ነገር ግን በአሜሪካና በምዕራብ ሃገራት የሚኖሩ የአሸባሪ ቡድን ሰለባ ወይም ሰለባ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉትን ግለሰቦች ፣ ቡድኖችና ተቋማት መንከባከብ ፣ ተለሳልሶ ማቅረብ ፣ አስተሳሰባቸውን “ሙያ በልብ ነው ፣” በሚል ህሳቤ አለመጫን። ይህ ነው እንግዲህ የፖለቲካ አስመሳይነት / አልማጭነት/Political correctness / በአጭሩ ማለት።

ይህን ካልኩ ዘንዳ ሰሞኑን ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር በኢትዮጵያ ፓርላማ ተገኝተው በተለይ ስለወልቃይት የተናገሩትን ሃሳብ እንገመግማለን። አንድ ባንድ እንደሚከተለው ዘርዝረን የፖለቲካ ቁማሩንና የፖከቲካ አስመሳይነት እንተነትናለን;

 • ወልቃይት የወልቃይቴዎች ነው ለሚለው አገላለፅ፣

ወልቃይት የወልቃይቴዎች ነው የሚለው አገላለፅ ለወልቃይቴዎቹ የሚዋጥላቸው አገላለፅ አይደለም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሽታውን በአግባቡ ያላዎቀ በሽተኛ መጨረሻው አያምርም

ነገር ግን እኛ ወልቃይቴዎች አስረግጠን የምናስታውቀው ወልቃይት በቅድሚያ የኢትዮጵያዊያን አጥር ነው። ከዚያም አለፍ ሲል ፣ “የከለው ዘር” “የአኮኖ ወሳባ” ቅድመ አባታችን  ከዘር ግንድ የፈለቀ የመጀመሪያው አማረኛ ተናጋሪና አማራ ወልቃይቴ ነው።  ወልቃይት የአማራ ዐፅመ እርስትና ዋና ከተማው በዳባት ተሰይሞ በበጌምድር ጎንደር ለዘመናት ሲተዳደር የነበረ መሬት ነው። ከዚህ ባለፈ ሊታወቅ የሚገባው ወልቃይቴ የጎንደር መስራች አማራ እንጂ ወልቃይቴ የሚል የብሔር ማንነት ልንሰጠው ሞሞከር ነውር ነው።

 • የወልቃይት ሕዝብ የተጎላደፈ ትግረኛና አማረኛ ተናጋሪ ነው ለሚለው ታሪክን ያላጣቀስ ንግግር በተመልከተ ፣

እኛ የምንለው  ወልቃይት የአማራና የአማርኛ ቋንቋ መፍለቂያ እንደመሆኑ ወልቃይት ጥርት ያለ አማረኛ ተናጋሪ ነው። ወልቃይት ከሱዳን ፣ ከኤርትራና በተከዜ በኩል ከትግራይ ጋር ስለሚዋስን አብሮ በመኖር ዘየ የአረበኛ ፣ የተወላገደ ትግረኛና የግህዝ ቋንቋ ተናጋሪ ለመሆን አስችሎታል። ህውሃት በተወላገደ ፓሊሲው ወልቃይትን ያለሕግና አግባብ በትግራይ ክልል ለ27 ዓመታት አካሎ የወልቃይት የ30 ዓመታት ትውልደ ውጤቶችን አፈ ሙዝ ደቅኖ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አማረኛ ሳይሆን በትግረኛ እንዲማሩ ስላደረገ ልሳነ ንግግረ ዜያቸው (  Accents) የትግራይ ሊመስል ይችላል ። ነገር ግን ቋንቋ የመግባቢያ መሳሪያ እንጂ የማንነት መገለጫ ስላልሆነ ሳይንሱም ( Language is not a reliable reflection of once identity, but a mince of communication) ስለሚል ይህ አነጋገር ወንዝ አያሻግርም።

የወልቃይት ሕዝብ ትግረኛን ከሆነም የኤትራን የትግረ ቋንቋ ይወላገድበታል እንጂ የአማረኛ ቋንቋና የአማራ ቅድመ መሰረቱ ወልቃይት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

 • የወልቃይትና የትግራይ ሕዝብ የተጋባና የተዋለደ ሕዝብ ነው ለሚለው ።

ይህ አነጋገር ሊያስኬድ ቢችልም ታሪክና ቱፊት እንደሚያሳየው ወልቃይትና ትግራይ በየብስ /በመሬት/ ብዙም የደንብር ግንኙነት የላቸውም። በዚህም  ምክንያት ብዙም የጋብቻ ጥምረት አልነበራቸውም። ነገር ግን በ 27 ዓመታት የህውሃት ያገዛዝ ዘመን በኃይልና መሳሪያ በመደቀን በወልቃይት የትግራዮችን ቁጥር ለማብዛት ሲባል የለ ፈቃዳቸው የወልቃይት ልጃገረዶች የአስገድዶ ጋብቻ ሰላባ ሁነው ሊሆን ይችላል።

 • የወልቃትን ጉዳይ በደቡብ አፍሪካው ድርድር ሙድረክ የማቅረብ ሕጋዊ መሰረት የለንም፣ ይህን ካደረግን በአማራና ኦሮሞ በምስራቅ ሸዋና  በሲዳማና ወላይታ መካከል ያለውን የመሬት የይገባኛ ጥያቄን አብረን ይዘን መቅረብ አለብን ማለት ነው ?“ ለሚለው አመክንዮ መሰል ገልፃን በተመለከተ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ጎዶሎ ሃሳብ (በአዲሱ ሀይሉ)

 

አንዳንዴ “ኑሮውበት እንጂ ሰምቶ መናገር መልካም አይደለም ፣ያስተዛዝባልና። የወልቃይት ሕዝብ ከሕወሃት/ወያኔ/ ጋር ለ43 ዓመታት ተፋልሟል። ይህም የሆነው የወልቃይትና የሁመራን ለም መሬት ህወሃት ቡስግብግብነትና በመሰሬነት ለመውሰድ ያደርገው በነበረው ትንኮሳ ለ18 ዓመታት ፣ ከዚያም በወልቃይቴዎች ጣምራ ፍልሚያ ደርግን ካንበረከኩ በኋላ ከሃዲው ሕወሃት እንደዶለተው ከስልጣን ኮረቻው ከተፈናጠጠ በኋላ ወልቃይቴወችን ክዶ መሬታቸውን ወደ ትግራይ ሲያካልል ህውሃትን ለ27 ዓመታት ተፋልሞታል። ይህን የረጅም ዘመን የማንነት ፣ የነፃነትና የህልውና ጥያቄ በግጦሽ መገፋፋት የተነሳ የመሬት የይገባኛል ጥያቄን ከወልቃይትና ከእራያ ጥያቄ ጋር ማወዳደር የሆነ የፖለቲካ ብልጣብልጥነት / Political conspiracy/ እንዳለ ፍንትው ብሎ ያሳያል እንላለን።

 

 • የመሬት የይገባኛል ጥያቄ ያቀረቡ አካባቢዎች እራሳቸውን ያዘጋጁ የሚለውን ጉንጭ እልፍ  ንግግር በተመለከተ ፣

ታስቦበት ይሆን ወይም የምላስ መጎላደፍ / Sleep of the tonge/ ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ሃሳብ ደጋግመው ገልፀዋል።

ይህ አነጋገር ግልፅነት የጎደለው ሲሆን ፣ የወልቃይት ሕዝብ ጊዜው ደርሶና የግፉ ፅዋው ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ ሲፈስ ህውሃት በሕዝብ ኃይል ወደ ጎራው መቀሌና ደደቢት ሲፈነጠር ወልቃይቴዎች በመራር ትግላቸው ወልቃይትን በኃይል እንደተወሰደው በኃይል አስመልሰዋል። ያገኘቱን ነፃነት ለመሸራረፍ መሞክር “ከድጡ ወደ ማጡ” የሚያስገባ መሆኑን መግለፅ እንወዳለን።

የንግግሩ ውስጠ ወይራ የህዝብ ድምፀ ውሳኔ “Referondom” ይደረጋል ከሆነ ፣ የብልፅግና መንግስት ከአምና ጋሻ ዣግሬዎቹ ሊማር የሚገባው ኤርትራን ያለኢትዮጵያዊያን ፍቃድ በተንሸዋረረና አግባብ ባልሆነ ሪፈረደም ሕወሃት አስገንጥሎ የደረሰበትን ኪሳራ ፣ ጦርነትና ፀፀት ነው።  ብልፅግናም ይህን ታሪካዊ ስህተት ከደገመ የሃገር ክህደት እንደፈፀመ ይቆጠራል ፣ ዋጋም ይከፍላል።

ሊከናወን ከታሰበ የሕዝብ ድምፀ ውሳኔ /Referendum/ በወልቃይት ምድር ውጤቱ ምን ይሁን ምን ፣ ይህ አካሄድ መታሰብ የሌለበት ከመሆኑ ባሻገር አይበለውና ከሆነ ብልፅግና ታሪካዊ ቀርሾው ፣ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፣ ከአማራው ፣ ከጎንደሬውና ከወልቃይቴዎች ጋር ሲሆን ወደማይታረቅ የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ መግባት እንደሚያስከትል ግንዛቤ ሊወሰድቡት ይገባል እንላለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፖለቲካም እንደ ሳይንስና እንደ ሂሳብ መታየት ያለበት ወይስ ሳይንሰ-አልባ ! - ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

በፖለቲካ ውሳኔ የተወሰደን መሬት የቀደም አጋር ፓርቲን ለማስደሰት  ወይም ከላይ እንዳልነው “አካፋን አካፋ” ብሎ ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ካልከወኑ በፖለቲካ ቁማር /ሸብጥ/ (Political Correctness) በሕገ መንግስት ይፈታል ብሎ መወሰን የሕዝብን ድምፅ ፣ ዋይታና ፍላጎት አለማክበር ነው እንላለን።

ማጠቃ

ይህን ካልን ዘንዳ በኢትዮጵያ ታሪክ መንግስታት በጥሩም በመጥፎም ይነሳሉ። እንደ እኛ ግን እንደ ሕወሃት ታሪካዊ ስህተት የፈፀመ የለም እንላለን ። እሱም ኤርትራን በስመ ድምፀ ውሳኔ / Referondom/ ማእቀፍ አስገብቶ አስገንጥሏል፣ በፖለቲካ ውሳኔ ለኢኮኖሚ ጠቀሜታ ብሎ ወደ ክልሉ ወልቃይትና ራእያን በማነለብኝነት አካሏል። በየመንግስታቱ የግዛት ዘመን የአስተዳደር ስህተቶች ሊኖሩ ይችላሉ ፣ ይህ ዓይነት ዕፀፅ በጊዜ የሚፈታ ሊሆን ይችላል።

ስለዚህ “ ኋላ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” እንዲሉ ብልፅግና የሕውሃትን ዓይነት ስህተት በብልጣብልጥነት ፣ በማለብኝነት፣ እውነትን በመንሻፈፍ፣ ታሪክን በማወላገድ /Political correctness and conspiracy/ በመከተል በኢትዮጵያ ላይ ሕዝብ ይቅር የማይለው ስህተት  እንዳይፈፅም እንመክራለን።

የወልቃይትን ጉዳይ በአግባቡ ፣ የ 3000 ዓመታት ታሪካችን ፣ እውነታንና ለኢትዮጵያ ሰላም የሚበጀውን አስቦ ብልፅግና ወልቃይትን ሆነ እራያን በፖለቲካ ውሳኔ ለባለእርስቶቹ ከመለሰ ብልፅግና ያተርፋል ፣ አስተዳደሩ በአንፃራዊነት የተረጋጋ ይሆናል፣ ወዳጅም ያበዛልና ኢትዮጵያም በአንድነት የቆመች የተረጋጋች ሃገር ትሆናለች ። ብልፅግና ልቡና ይኑርህ “ እንደሸማኔ መወርወሪያ ወዲህ ወዲያ ካበዛህ” ሃሳርህና መከራህ ይበዛል ፣ መጨረሻህም አያምርም።

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።

 

 

1 Comment

 1. አይሆንም አትበሉ ሆኖ እንደሆንሳ
  ተቀብሮ ተቀብሮ የተኛው ሬሳ
  ድንጋዪን ፈንቅሎ ማን ያውቃል ቢነሳ
  ድንጋይ ተቆልሎ አፈር ተለውሶ
  በጸጥታ እሚኖር አፈር ቅጠል ለብሶ
  በድን ነው ተራራ አፍ የለውም ጀሮ
  አይሰማም አይለማም ግዑዝ ነው ደንቆሮ
  ብላቹሁ ስትንቁ የውስጡን ሳታውቁ
  ለእናንተ እኔ ፈራሁ ፈንድቶ እንዳታልቁ። (ግጥም ፑኒት ሃኒት)
  ይህ ግጥም የሃገራችን ጉዳይ ከሞላ ጎደል ፍንትው አርጎ ያሳያል። ያኔ በወያኔ መንግስት ሥር አብረው ሲዘርፉ ሲገሉ በዘራቸው ተሰልፈው ቋንቋውን እየተናገሩ የራሳቸውን ወገን እንደ ደሮ ብልት ሲገነጣጥሉ የነበሩ የደም ሰዎች ዛሬም በምድሪቱ ይራወጣሉ። በግፍ በመርዝ፤ በመኪና በመግጭት፤ በጥይት፤ ከፎቅ ላይ በመወርወር፤ በመሰወር፤ በእስር ቤት ሰቆቃና ግድያ የፈጸሙ የደም ሰዎች በሃገርና በውጭ ሃገር ይርመሰመሳሉ። የሚያሳዝነው የዘንድሮውም ከአምናና ከታች አምናው አለመሻሉ ነው። ውሃ በወንፊት ይሉሃል ለገባው ይሄ ነው። የኢትዮጵያ ፓለቲካ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል አይነት ነው። የወልቃይትን ጉዳይ ለመፍታት ሪፈረንደም ሲሉ አለማፈራቸው። እንዲህ አይነቱ የፓለቲካ ሻጥር በሌሎች ክልል ተብየዎች ላይ የሚያስከትለውን ግርግርና ለእኔም ላንቺም ሪፈረንደም የሚያስጠይቅ መሆኑን ጠ/ሚሩ ይገባዋል? የፓለቲካው አሻጥር ጊዜአዊ መተንፈሻ ለማግኘት የማይሆንና የማይባል ነገርን በይፋ እየደሰኮሩ ነገርን ማካረራቸው ለሃገርም ለራሳቸውም ጠቃሚነት የለውም። ሰው በአንዲት ሃገር ላይ ተቀምጦ የእኔ ድንበር ጠበበ የዚያኛው ሰፋ እያለ መነታረኩ የሚያሳየው የጠባብ ብሄርተኝነትን ፓለቲካ ነው። ወልቃይት መጀመሪያ የወልቃይቶች ብሎም ሃብትነቱ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። ማንም ኢትዮጵያዊ ከአራቱ ማዕዘን ወደ ወልቃይት ሂዶ ለመኖር የሚከለክለው አንዳች ነገር የለም። በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች መደረግና መሆን ያለበት የክልል ፓለቲካውን እሳት ውስጥ መክተትና ህገ መንግስቱን መቀየር ነው። ይህ ሌላውን የሚያገል የዝንጀሮ ፓለቲካ ለማንም አይጠቅምም።
  የሃበሻ ፓለቲከኞች ሳይጠጡ የሰከሩ ናቸው። በቃላት ጫወታና በጮሌ አፋቸው ሰውን እያማቱ ቀናቸውን የሚቆጥሩ የፓለቲካ ቀላዋጮች ለህዝባችን አስበው አያውቁም። ለኦሮሞ ህዝብ፤ ለትግራይ ህዝብ፤ ለአማራ ህዝብ ለአፋር ህዝብ ወዘተ የተባለውና የሚባለው ሁሉ ቢወቅጥ እምቦጭ ለመሆኑ ነገራችን ሁሉ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ ሲቀር እያየን ነው። በአለም ላይ ሪፈረንድም ያደረጉ ሃገሮችን በየተራ ለገመገመ ሰው ከጎረቤቶቻቸው ጋር የሚቆራቆሱ፤ እርስ በእርስ የሚባሉ፤ በፊት የነበረውን ሰላም የተቀሙ፤ ባጭሩ በአፈና ውስጥ ያሉ ለመሆኑ እማኝ መቁጠር አያስፈልግም። ሃርነት ብለው ባርነትን፤ ጥጋብና ብልጽግና ለፈው መታረዝን፤ ስደትና ሰቆቃ አበቃ ብለው እልፎች ሃገራቸውን እየተው በሞትና በህይወት መካከል ሆነው እግሬ አውጭኝ የሚሉባቸው እነዚህ በነጻነት ስም የእድሜ ልክ የህዝብ አሸባሪዎች በሚሰሩት መሰሪ ሥራ ነው። አውቃለሁ መሬት ላይ ያለውን እውነት ክደው እንዲህ ያለውን ነገር ሲያነቡ አካኪ ዘራፍ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉ የፓለቲካ ቁማርተኞች እንዳሉ። ጥሩ ነው ይዝለሉ። እውነታው ግን ትርፍ የለሽ ፓለቲካ ነው።
  አሁን እንሆ አለማችን በተለያዬ መልኩ ተወጥራ ተይዛለች። አንካራ ላይ አንድ ባለስልጣን ሲደነፋ ግሪክን አሸንፎ ለመቆጣጠር ቀናት ብቻ ይበቃል ብሎ ሲደነፋ ግሪኮች ደግሞ በዚህም በዚያም የቅርብና የሩቅ አጥቂ የጦር መሳሪያዎችን በመሸመት ላይ ይገኛሉ። አርሜኒያና አዘርባጃን አልፎ አልፎ እየተዳቆሱ ነው፤ ዪክሬን ላይ ራሽያ የምታደርገውን በዜና እየሰማን ነው። በዚህ የተነሳ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፈረሙት ስምምነት መሰረት ጦራቸው ከልክ እንዳያልፍ የተባሉት ጀርመኖች፤ ጃፓኖችና ጣሊያኖች እስከ አፍንጫቸው እየታጠቁ ነው።
  ባጭሩ አለማችን ተንጋዳለች። ጨርሳ ትገልበጥ አትገልበጥ የማውቀው ነገር የለም። የሚያሳዝነው ግን የራሺያ አለቅጥ ኢ – ሰብአዊነት ነው። ላስረዳ። በራሺያ ከዛምቢያ ሂዶ ተማሪ የነበረ አንድ ወጣት ከእጽ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ይታሰራል። ራሺያ ዪክሬንን ስትወር እስረኛው ሁሉ ወደ ግንባር ስለተባለ እሱም በዚያው ዘምቶ እንደሞተ ሉሳካ የደረሰው መረጃ ያስረዳል። ይህ አውሬነት ነው። ግን ለጥቁር ህዝብ ማን ገዶት። እንዲያውም ልብ ብሎ ለተመለከተ ራሺያኖች በዪክሬን ላይ ያደረጉትና የሚያደርጉት ድርጊት ወያኔ በሽዋ፤ በአፋርና አማራ ካደረገው ጋር እጅግ ተመሳሳይነት አለው። የድርቡሽ ሥራ ነው። አሁን ራሺያ ኢትዮጵያን ስለደገፈች ሁሌ ከጎን ትቆማለች ማለትም አይደለም። ያኔ ደርግ በስልጣን እያለ ጎርቫቾቭ ከመጣ በህዋላ ነው የጦር መሳሪያ ሁሉ መስጠት አቁማ ወያኔ በአዲስ አበባ፤ ሻቢያ በአስመራ አለቃ እንዲሆኑ የተደረገው። ነጩን ዓለም ማመን አይቻልም። አሁን ይህን እየጻፍኩ ዳግም ሊረጋገጥ ከሚገባው ምንጭ ወያኔ 4ኛ ዙር ጦርነት እንደከፈተ ተነገረኝ። ዝርዝሩን አላውቅም። ያው የብልጽግና ሙት መንግስት ስንቅና ትጥቅ እንዲሁም መድሃኒት አስገብቶላቸው የለ እስኪያልቅ ይዋጋሉ። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share