መንግስት በዐማራ ፋኖ ላይ የሚያደረገውን ዘመቻና ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን!

June 14, 2022

ያንድን አገር ሉዐላዊነት መጠበቅ፤የህዝቡን  ሰላምና ደህንነቱን ማረጋገጥ፤ በተለይም ደግሞ አቅመ ደካሞችን (ህጻናትን፤ አረጋውያንን) መደገፍ ዋና ዋናዎቹ የመንግስት ግዴታ፤ ሃላፊነትና ተግባር ናቸው።

ይህንን ሃላፊነት ለመሸከምና ተግባራዊ ለማድረግ መንግስት ፍቃዱ ካልሆነ፤ ካልቻለ፤ህዝብ አፉን ሞልቶ መንግስት አለኝ ለማለት ይሳነዋል። መንግስት የህብረተሰቡና የሃገርን ፈቃድ ለመፈጸም ካልፈቀደ፤  የአገርንና የህዝብን አደራ እንዳልተወጣ ተቆጥሮ ለሥልጣን  ያበቃው ህዝብ ከሥልጣኑ ማግለል  ብቸኛው አማራጭ ይሆናል።ሌላ አማራጭ የለምና!!

ማንነቱን እንደሰው፤ ታሪኩን እንድ ማህበረሰብ፤ አገሩን ጭምር ዝቅ  አድርጎ ፤ጊዜ እስኪያልፍ ያለፋል በሚል ብሂል ለገዢዎች ምቹ ሆኖ መኖር ካልተፈቀደለት፤ከቀዬው  በመዝለቅ፤ከቤትንብረቱ ካፈናቀሉት፤ክልሉድረስ መጥተዉ፤ ስላሙን ከነሱት፤ንብረቱን ከዘረፉት፤ የዜግነት መብቱን ከገፈፉትና እስትንፋሱን ከነጠቁት፤ ይህ ድርጊት የተፈጸመበት  ህዝብ ሰለ እውነተኛ ነጻነቱ፤ተፈጥሮያዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱ ነቅቶና ተደራጅቶ ከመታገል ሌላ ምን አማራጭ አለው?

አሁን ባለንበት ወቅት በዐማራ ክልል ያለው እውነታ ይህ ከላይ የተገለጸው ነው። ዛሬ ዐብይ አህመድና በስልጣኑ ዙሪያ የተኮለኮሉት ጥቂት አድርባይ ቢሮክራቶች፤ የጦር መሪዎችና ምሁራን ነን ባዮች፤ የዐማራውን ሕብረተሰብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በማጋጨት እየሰሩ ያሉት ፀረ ዐማራ ሴራ፤ ማንገላታት፤ ዕስርና ግድያ የዐማራው ህዝብ ዕጣ ፈንታ እየሆነ የመጣ የትውልዱ አሳዛኝና አሰቃቂ ፈተና ነው። የዐማራውን ህብረተሰብ ነጥሎ በመምታት ብሎም ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚደረገውን ዕኩይ ሤራ፤ የኢትዮጵያ የውይይትና የመፍትሄ መድረክ /EDF/ አጥብቆ ያወግዛል።

ከታሪክና ከህዝብ ተሰውሮ መኖር አይቻልምና የብልጽግና ፓርቲ  ህዝብን ክህዝብ ጋር በማጋጨት የስልጣን ዘመኔን አራዝማለሁ በሚል ቀቢጸ ተስፋና ምኞት፤በህዝባችን ላይ እየፈጸመ የሚገኘው የጥፋት እርምጃ ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍለው መሆኑን ከወዲሁ ማስገንዘብ እንወዳለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Ethiopia to buy more than 200 T-72 tanks from Ukraine for $100 million

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፤ የኢትጵያ ህዝብ የሰጠህን ድጋፍ  በተከተልከዉ የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት የማፈራረስ ርምጃ ምክንያት ፤ታሪክና ህዝብ ጠልቶሀል!ድጋፉንም ነስቶሀል!!

የኢትዮጵያን ሕልውና ዘላቂነት የሚወድ ሀቀኛ ዜጋ ሁሉ በሰሜን፤ በደቡብ፤ በምስራቅም ሆነ በምእራብ የሚገኝ ሕዝባችን አብሮነቱን አጠናክሮ፤የዜጋነቱን ማተብ አጥብቆ  ሁሉም በጋራ በመነሳት የተወጠነበትን ጥቃት በማክሽፍ በአሸናፊነት መወጣት አለበት ብለን እናምናለን።

 

አገር ወዳድ የሆናችሁ የአንዲት እናት አገር የኢትዮጵያ ልጆች መልእክታችንን በአለም ዙርያ ሁሉ እንድታስተጋቡ ትብብራችሁን በአክብሮት EDF ይጠይቃል።

ኢትዮጵያ በሐቀኛ ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዐለም ትኖራለች!!!

 

 

 

 

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share