ዛሬ ፋኖን ለመደቆስ የሚፈልጉ ባንድ በኩል ደግሞ አርጮሜ አድርገው ሊጠቀሙበት የሚፈልጉት በሌላ በኩል ተሰልፈው ከግራና ቀኝ ሲያዋክቡት ይታያል። የኦሮሞ መሪወችና ወያኔወች ተቀዳሚ ጠላታቸው ፋኖ እንደሆነ አይደብቁም። የትግሬው ወራሪ የፋኖን እጅ ስለቀመሰና ህልሙ ተኖ እንዲቅረ ስላደረገው ጥላቻው አያስደንቅም። የአማራ መሬት የምትታይ ፍሬ እንጅ በወራሪው የማትበላ መሆኗን ፋኖ በደሙ አስመስክሯል።
በሌላ በኩል ይህ ጀግንነትና ሃገር አፍቃሪነት የኦሮሞ መሪወች ባላቸው የተስፋፊነትና ሁሉ ኬኛ ስግብግበንት አመለካከታቸው ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም። ሰው ሲገድል፣ ሲያፈናቅል፤ ሃገር ሲያምስና ባንክ ሲዘርፍ የነበረውን የበኩር ልጃቸው ሸኔን አንድም ሳይናገሩ ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጀምሮ በፋኖ ላይ የማያወላዳ አቋም አላቸው። አይደብቁትም፣ አይሸማቀቁበትም። ፋኖን ጠላት ነው ብለው ሲፈርጁት ሽኔን የኦሮሞ ነጻነት ተዋጊ ብለው ኦሮማዊ ክርስትና ስም ስጠተውታል።
በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉትን የኦሮሞ ሊህቃን በአማራ አስተዳደር ውስጥ በተሰገሰጉ አሽርጋጆች እንደሚደገፉ ብዙ መረጃወች አሉ። ይህም ልክ በወያኔ ጊዜ ይደረግ የነበረው አጫፋሪነት መሆኑ ነው፣ ያኔም የከዱት የአማራውን ህዝብ ነው ዛሬም የሚያደርጉት ይህንኑ ነው። ልዩነቱ ወያኔ ከመድረኩ ሲገፈተር አዳዲስ አለቆች ማገልገላቸው ነው።
ፋኖን የማሪያም ጠላት ያሉት ወያኔወች፤ የኦሮሞ ሊህቃን( በመንግስትም ሆነ በተቃዋሚ ተሰልፈናል የሚሉት)እንዲሁም የአማራ ከዳተኞች ናቸው። በሌላ በኩል ከመንግስት/ብልጽግና ጋር የነበራቸው ግንኙነት የደበዘዘባቸው፣ጥላ የጣለባቸው ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ፋኖን የነሱው የፖሊቲካ ህልም ማሳኪያ፣ ማስፈራሪያ ሊያደርጉት ሲቋምጡ ይታያሉ። ትናንት የት ወደቅህ ያላሉት ዛሬ የነሱው መግረፊያ ጅራፍ ሊያደርጉት ሲሞክሩ በዝምታ ማየት ትክክል አይደለም።
ፋኖ ዛሬም እንደትናንቱ ሁሉ የህዝብ አለኝታ እንጂ የማንም ብረት አንጋች አይደለም፣ አይሆንምም። አጥብቀው የሚጠሉት እንዳለ ሁሉ መጠቀሚያና መደራደሪያ የሚይደርጉትንም መቃወም የሁላችንም ሃገራዊ ሃላፊነት ነው። ወራሪው በፈጸመው ግፍ ሲቀጣ ለወደፊቱ ለኛም አይተኛልንም ብለው የሚቃዡትን ገደብ የማስያዝ የሁሉም የሃገር ወዳድ በጎ ተግባር ነው።
እንዲሁም ፋኖን አርጩሜ ለማድረግ እንቅልፍ ያጡትንም ታገሱ ተመለሱ ማለት የግድ ነው። ፋኖ የማንም እይደለም ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለኢትዮጵያ አንድነት ነው። ይህን በተግባር አስመስክሮአል። ሌላ ዋቢ አያሰፈልገውም።
እንዲያውም መጠየቅ ያለብን ፋኖ በየሽንተረሩ ሲዋደቅ እናንት የፋኖ ጠላቶችም ሆናችሁ ልትጠቀሙበት ደፋ ቀና የምትሉት ሁሉ የት ነበራችሁ? ዝም ብለን ሆድ ይፍጀው ብለን ልናልፈው ነው?
የፋኖ ጠላቶች የኢትዮጵያ አንድነት ጠላቶች ናቸው፣ የህዝቧ ጠላቶች ናቸው፣ የኢትዮጵያ አንድነት ጠላቶች ፋኖንና ሸኔን በአንድ መድረክ ላይ የሚያስቀምጡ የሀገር ጠላቶች ኛቸው። ሀገር የሚገድልን ከሃሀር መከታ ጋር ማወዳደር ሌላ ትርጉም የለውም።
በአንጻሩ በፋኖ ተጠልለው የፖለቲካ ቁስላቸውን ለማከም የሚፈልጉም ጤነኛ አዕምሮ ያላቸው ሳይሆኑ ለራሳቸው ያደሩ የህዝብን ፍላጎት ያላማከለ የተሽናፊወች መፈራገጥ ነው።
ፋኖን አትንኩ፣ ፋኖም በውስጡ ጽንፈኞችም ሆነ ወሮበሎች ካሉ ከመካከሉ ነቅሎ ማስወጣት ይጠበቅበታል። የማንም ጥላቻ አያንበረክከውም መጠቀሚያም አይሆንም። ፋኖ ትልቅ ስዕል ከፊቱ አለው፣ እሱም ታላቋ ኢትዮጵያ እንጂ ነገ የሚያልፉ ምንደኞች አይደለም።
የፋኖ ስነልቦና ኢትዮጵያዊነት ነው፣ከዚህ ማንም ዝቅ ሊያደርገው አይችለም። ፋኖንና ኢትዮጵያዊነትን ለመለያየት እንቅልፍ ማጣት ከንቱ ድካም፣ ትልቅ ድንቁርና ነው።
በግራም በቀኝም የተሰለፋችሁ ጸረ ፋኖዎች እጆቻችሁን አንሱ፣
የራሳችሁን ፍላጎት ለማርካት ፋኖን መሰላል ለማደረግ የተሰላፋችሁም ሁሉ እጆቻቻሁን አንሱ። ያለየላችሁና አሸናፊ ወዳለበት የምታዝነብሉ የመንፈስ ጥንካሬ የጎደላችሁ መጥኔውን ይስጣችሁ ከማለት ሌላ ማለት አይቻልም፣ በጥቅሉ ግን የናንተ ግራና ቀኝ መርገጥ ፋኖናም ሆነ አማራን ለማዳካም ደፋቀና ከሚሉ አማራ ጠሎች ጋር ያሰልፋችኋል።
ፋኖ፣ አስመሳይ ያልሆነው ፋኖ በራሱና በህዝቡ መተማመን ይኖርበታል፣ ፋኖ የአማራ አለኝታ ነው፣ ፋኖ የኢትዮጵያ አለኝታ ነው። አማራን ለማውረድ የሚፈልጉ፣ ኢትዮጵያን ለማወረድ የሚፈልጉ ፋኖን ቢጠሉ አያስገርምም።
ፋኖ ጠላቱን ያውቃል
“Try not to stress over shady people who betrayed you.
I know it hurts but the truth is that they were always shady, they’re never going to change, and you’re actually much better off now because at least you know who yhey really are.”
ለወያኔ አገልጋይ የነበሩ ዛሬም ለአዲስ ጌታ ማገልገላቸው ከላይ እንደተባለው ድሮውንም ከሃዲወች እንደሆኑ የምታውቀው ነውና አትደነቅ።
የፋኖ ጠላቶች እጆቻችሁን ከፋኖ ላይ አንሱ
ወላውዮች(spineless) ብቅ ጥልቅ እያላችሁ አታወናብዱ እጆቻችሁን ከፋኖ ላይ አንሱ
የፖለቲካ ስንኩላን ፋኖን መጠቀሚያ ለመድረግ የምትባዝኑ እጆቻችሁን ከፋኖ ላይ አንሱ