አብይ አህመድ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኛ ወይንስ የኦነግ ምርኮኛ? ……ከጥሩነህ

Abiy Ahymedኢትዮጵያዊነትን በተራብንበት ጊዜ ብቅ ብለው ኢትዮጵያዊነትን አጎረሱን፣ ጥጋብ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት አሰከሩን። አቅላችንን እስከምንስት ድረስ ጮቤ አስረገጡን፤ የኢትዮጵያው ሙሴ ስንልም አሞካሸን፣ ከሰማየ ሰማያት የውረዱ የፈጣሪ ስጦታ ብለን ዘመርን። ዳሩ ምን ያደረጋል የአነሳሱን፤ የፍቅሩን መዕራፎች ጽፈን ሳናገባድድ የአወዳደቅ፤ የመንጋዳገድ  ተቃራኒ ምዕራፍ ተጀመረ። ወጣወጣና ተንከባለለ እንደሙቀጫ እንዲሉ የደስታን ዳር ሳናይ የሃዘን ድባብ በኢትዮጵያዊነት ላይ ተንጣለለ፣ የመከራ ዳመና በሃገራችን ላይ አንዣበበ። አብይም ኢትዮጵያ አትፈርስም ከማለት ባሻገር አቅመ ቢስ ወይም ፍላጎተ ቢስ ሆነው ተከሰቱ። ብዙ ጥያቄዎችን የሚያጭር ክስተቶች በየቀኑ ይወጡ ጀመር።እምነታችን ይሸረሸር ይከስም ዘንድ አውነታዎች አፍጥጠው መጡብን። የሰው ልጆች እንደፋሲካ በግ እየታረዱ ነፍስ ይማር ብቻ ሆነ።

ሱማሊ ክልል ውስጥ የነበረውን እልቂት በአንድ ውሳኔ ያሰቆመ በኦነግ ሽብርተኞች ላይ አይን አፋር ሆነ ክንዱ ደከመ።  በየጎራው የአማረ ህዝብ ሲያልቅ መታደግ ቀርቶ ያ አንደበተ እርቱ ሰው ቃል ለመተንፈስ ተናነቀው።

ብዙ ሰው የሚጠይቀው ግን መልስ ያልተገኘለት ነው።

አብይ በአማራ ህዝብ ጉዳይ ላይ ደብቁኝ ደብቁኝ ጨዋታ የመጨረሻውን ውድቀት እውን የሚያደርጉበት ጉዞ ነው። ያለውን እውነታ ተደብቆ መኖር ግመል ሰርቆ አጎንብሶ መሄድ ነው። የዘመርንለት አብይ ወደ ሃዘን ቤት እየውሰደን ነው፣ ለእራሱ ሃዘን፤ ለኢትዮጵያ ሃዘን።  ይኸውና ያ ከልብ የነበረ ድጋፍ እንደጉም ተነነ።

የኦሮሞ ጽንፈኞች የሚያደርሱትን ግፍ እያዩ እንዳላዩ መሆን በሃገራችን ላይ የነበራቸውን ታላቅ ድጋፍ ወደ ገድል የወረወሩ መሪ ለመሆን ብዙም ጊዜ አልፈጀባቸውም። ከኦሮሞ ይልቅ መሪየ ብሎ ህይወቱን ሊሰጥላቸው የተሰለፈውን አማራ በኦሮሞ ሲጨፈጭፍ ከታዛቢነት አልፈው የተሰጣቸውን አደራ ለመወጣት ምን አሰራቸው? እምነታቸውን ያልተወጡት ለምን ይሆን?

የሁሉም ጥያቄ ነው።

ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር በስነልቦናቸው ውስጥ ያላነጋቧት ኦነጋውያንን እሸሩሩ እያሉ ስለኢትዮጵያ ትንሳኤና እድገት ማወራት ማታለል አይሆንምን? ባለተራ ናቸውና  ዛሬ እንደትናንትናው ደወያኔ ይዘርፏታል ነገ ሲያቅታቸው የኦሮሚያን መገንጠል ይጋብዙናል። ከፈጣሪያቸው ከወያኔ የተማሩት ይህን ብቻ ነው። ኦነጋውያን ከወያኔ የተማሩትን አይለቁም አዲስ መፍጠርም አይችሉም::  በእርግጥ ኢትዮጵያ ሲሞቅህ የምታውልቃት ሲበርድህ የምትልብሳት ጨርቅ አይደለችም: ይህ ለወያኔ ከሀዲዎች መገለጫ ሆኗል ዛሬ ደግሞ ለባለጊዜዎች ይሆናል።

ማለብ እስከቻሉ ኢትዮጵያን ያልቧታል ስትነጥፍ ሌላ አማራጫቸውን እውን ለማድርግ ይሯሯጣሉ:: ኢትዯጵያ ለኢትዯጵያውያን የህልውናቸው መገለጫ ናት: አያወልቋትም  ወያኔ በአንድ በኩል ውሃ አቅራቢው ኦነግ በሌላ በኩል ሃገራችንን እንደቆዳ ወጥረው ሲያለፏት የሁገሪቱ መንግስት በታዛቢነት የቆመበት ምክንያት ነው ግራ የሚያጋባው።

አቅም የለውም እንዳይባል በቂ የሰለጠነ መከላከያ ሃይልና ከፈለገም ሊጠቀምበት የሚችል እንዳሽን የተፈለፈለ ልዩ ሃይል አለው። ማዘዝ አይችልም እንዳይባል ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚታሙበት እንዲያውም ወደ አምባገነንነት እያመሩ ነው የሚል ነው። ስለዚህ ማዘዝ እንደሚችሉ ግልጽ ነው። ታዲያ ችግሩ በወያኔ ላይ በተለይ በኦነግ ላይ የሳሳ ልብ ስላላቸው ነው?

በአሜሪካ የርስበርስ ጦርነት ፕሬዜዳንት የነበሩት አብርሃም ሊንከን እየተልፈሰፈስ ባስቸገራቸው ጄኔራለቸው ላይ በመበሳጨት ይህን ብለው ነበር

“ If General McClellan does not want to use the Army, I would like to borrow it for a time..”

የጀነራሉ መልፈስፈስ የአቅም ማጣት አልነበረም ችግሩ ከልቡ የሁኒየኑን cause ከመደገፉ ላይ እንጂ :

ጦሩ ሰላም እንዳያስከብር እጅ ከወርች አስሮ የያዘው የአብይ እእህመድ መንግስት ከጄኔራል ማክክሌላን በምን ይለያል?

ህዝቡ እንዳይታጠቅ በፍርሃት የሚርበደብድ እንዲያውም በአንጡራ ሃብቱ የገዛውን ነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመንጠቅ ህዝቡን ቀኝና ግራ እጆቹን አስሮ ማስደብደብ የመንግስት ተግባር እየሆነ አይደለምን?

የኦነግ መንጋ ህዝብ ሲያርድ ከመንግስት እይታ ውጭ ሆኖ አይደለም፤ የመንጋው ድርጊት እርዳታ እንደልቡ ያገኛል ይህም ከኦሮሚያ መንግስት ከብልጽግና አባላት የሚቸረው መረጃ፤ ገንዘብና መሳሪያ ነው። ቀስበቀስ ሞትን አለማመዱን፤ ከንፈር ከመምጠት ባሻገር እጅ ከወርች አማራን አስረው ሲያስጨፈጭፉት እየሰማን ሞትን ለመድነው፤  አስደንጋጭ መሆኑ ተረሳ።

ሞትን ለመድኩት

በቆንጨራ እየተቀሉ

በሳት እየጋዩ የህሊና

እረፍት ቢነሳኝ

የሃሳብ ሜዳው ቢጠበኝ

ፈጣሪን ለመንኩት ተማፀንኩት

አልሰማ ቢል ግን የድሃ ጩኸት

ተስፋ ቆርጨ ሞትን ለመድኩት::

አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ ብዬ

ባልወደውም ተቀበልኩት:

ሞትን ለመድኩት

ባልወደውም ተቀበልኩት

የግፍ ሞትህን ሞቴ አደረኩት

ሞትሽን ሞቴ አደረኩት

ባልወደውም ተቀበልኩት::

ይህን ጭንቀቴን፤ የህዝቡን ጭንቀት ምነው መንግስት እንደሌለ ቆጠረው። ሟቹ አማራ ገዳዮ ኦነግ መሆኑ ለምን በአምሯቸው ውስጥ ጭንቀትን አልፈጠረም?

የሁሉም ጥያቄ ነው።

ስለኢትዮዽያ ታላቅነት እየዘመሩ ስለልጆቿ ብሶትና ስቃይ አልሰማም ማለት ኢትዮዽያዊነት ቀርቶ ሰው አያደርግም።

በየቀኑ የሰው ልጆችን ደም የሚያፈስ ስጋ የሚቆርስ ኦነጋውያን ቡድን ባለበት ለሀገሩና ለክብሩ የተዋደቀውን ፋኖ ላይ ዘመቻ መክፈቱ እውነት ኢትዮዽያን ከማዳን ወይንስ የአማራን ህልውና ከማዳከም ላይ የተመሰረተ እምነት? የትግሬው ወራሪ አማራን ማዳከም ብቻ ሳይሆን ቢችል ከምድረገፅ ማጥፋት ህልሙ ነው: ኦነጋውያንም ከዚህ የተለየ እምነት የላቸውም: ይህ የጠቅላይ ሚኒስትትሩም እምነት ይሆን? ለማሰብ ቢከብድም መሬት ላይ ከሚታዩ እውነታወች ስንነሳ  ጥያቄውም ሆነ የህዝቡ ጥርጣሬ መሰረት የለውም ማለት ያስቸግራል: የጦርነቱ አለመቋጨት አማራን እንደሚያዳክም ወራሪው ትግሬም ኦነጋውያንም ያውቁታል:: በመንግስት ውስጥ ያለው ኦነግ ከመረጃ ጀምሮ እስከ  መሳሪያ ማቀበል የክህደት አገልግሎቱን እየሰጠ ባለበትና የኢትዮዽያ ህዝብ በሚገባ በተረዳበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አያውቁም ማለት መሳደብ ይሆንብናል::

በወራሪው ትግሬ ስር ወድቀው ምድራዊ ሲዖልን የሚቀበሉት አማሮችና አፋሮች ከጠቅላዩ አይኖች እርቀው ይሆን? ወይንስ ለአማራና ለአፋርች ህዝብ የተጠነሰሰለት ጉድ ይኖር? ሲጀመር ጦርነቱ እንዲቆም የተደረገው የአማራና የአፋር መሬቶች እንደተያዙ መሆኑ ጥርጣሪይችንን በሁለት እጅ የማይነሳ ክብደት ይሰጠዋል:

እንድ እውነቱ ከሆነ ይህ መንግስት እኒህ ክፉ ወልቃይቶች፤ ራያዎች፤ አማሮች ጋሬጣ ባይሆኑበት ወልቃይትንም ራያንም  ከወራሪው ትግሬ ጋር መደራደሪያ አድርጎ ስልጣኑን ማደላደል አይፈልግም የሚል ደፋር ይኖራል ብየ አልገምትም:: ችግሩ የወልቃይትም ሆነ የራያ ድርድር አይኖርም  ከኖረም ይህች የሚሳሱላት መንግስት ከጃቸው ትወጣለች: መንግስትነትን ስለሚወዱ እንጂ የህዝብ ጥያቄ ከልባቸው ስለገባ አይደለም::

ወራሪው ትግሬም ሆነ ኦነግ የአማራ ማስፈራሪያ አርጩሜዎች ሆነው እያገለገሉ ነው: ለዚህ ነው ህይወቱን ገብሮ ወራሪውን የተፋለመውን ፋኖ አይንህን ላፈር የሚሉት፤ ለእቅድ አፈፃፀማቸው እንቅፋት ስለሆነባቸው የወራሪውን ብቻ ሳይሆን የኦነጋውያንን ተስፋፊነት ሀገር አፍራሽነት የብረት በር ሆኖ ስለሚዘጋባቸው ነው::

በሁለት ባላ ላይ ቆሞ የህዝብ መንግስት መሆን አይቻልም አንድም ሀገር ወዳድ የሁሉም ህዝብ ተጠያቂ መሆን አለዚያም የብሄርተኞች ምርኮኛ ሆኖ ክፉ አወደደቅን መቀበል ነው: ሁለቱንም መሆን ግን አይቻልም አይታሰብም በተቃራኒ የቆሙ አንዱን ሌላው የሚያጠፋበት ባህሪ አላቸውና::

የኦነግን ሀገር አፍራሽነት ደም አፍስሽነት በትዕግስት እየተመለከቱ ኢትዮዽያን መታደግ የቂላቂል እምነት አለዚያም ፊታችሁን አዙሩና ላሞኛችሁ ነው፤ ይህም ቂልነት ነው:: ኢትዮዽያ በታሪኳ ብዙ ውጣውረዶችን ያሳለፈች ዘለዓለማዊት ሃገር ናት ከናነተው ጋርም ሆነ ከናነተ ውጭ ዛሬም ነገም እስከዘለዓለሙም ትኖራለች: በየቢሮው በዘር የተመደቡና በነሱው ቋንቋ ብቻ ካልተናገርክ አገልግሎት የማታገኝባት ኢትዮዽያ የሁላችን ልትሆን አትችልም፤ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ የናንተም አይደለችም: ኢትዮዽያን ለምትሰጠው ጥቅም  ብቻ ከውጭ ልብስ የምታደርጋት ከልብህ ግን ፍቀህ ያወጣሃት ሀገር አትሆንህም:: ዛሬ አማራ ዙሪያውን ተከቦ እንደ ገና ዳቦ በእሳት በሚጋይበት ወቅት የመንግስትን ዝምታ ብቻ አይደለም  በትዝብት የምናየው፤ እኛ ጋ ችግር የለም ብለው አፋቸውን ዘግተው እጃቸውን አጣጥፈው በታዛቢነት የተቀመጡትን ሌሎችንም አካባቢዎች ጭምር  ነው: የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ በኦሮሞ ተስፋፊዎች መዳፍ ስር እንደሚገቡ የተገነዘቡት አይምስልም ወይም በአስቀድሞ ፍርሃት ተርበድብደው በድን ሆነዋል።

በአማራ ላይ ያነጣጠረው ጦር እነሱን ሳይደቁስ እንደማይመለስ ኦነጋውያን  አስቀድመው ግልፅ አድርገውታል: መቆሚያቸው ኬንያ ነውና:

የዛሬው የአማራ ሞት ነገ ለሌችም አካባቢዎች ነው። ሶማሌ ደቡብና ጋምቤላ ወዘተ ማነህ ባለተራ ውስጥ የሚገኙ የነገው ስለባዎች ናቸው: ዛሬ ጦሩ በአማራ ደረት እያረፈ ይህን እንጂ ተባብረው ለእውነተኛይቱ ኢትዮዽያና ሰላሟ ካልቆሙ ጦሩ ይወረወርባቸዋል እንደ አማራም ይደማሉ ይቆስላሉ ይሳደዳሉ ይሞታሉ::

ዛሬ ለአማራ ሰቆቃ ያልቆምክ ነገ ብቻህን ትሆናለህ

ዛሬ የአማራ ብሶት ያልገባህ ነገ ትሰቃያለህ

ዛሬ በሞቀ ቤትህ የተቀመጥህ ነገ የዛሬውን የአማራ ስደት ትከተላለህ:

መንግስት  ከአንተ ውጭ ለሆነ ዘር ብቻ ሲቆም አስቀድሞ እንደፈረደብህ ካላወቅህ ትልቅ ችግር አለብህና ነገ የዛሬው አማራ እጣ ይገጥምሃል:

አንድ ሰው ፈጣሪውን እባክህን ሳታስጠነቅቅ እንዳትገልኝ ይለዋል ተስፋም ያገኛል፤ታዲያ ከሩቅ ያሉ ሰዎች ይታመማሉ፤ይሞታሉ ቀስ እያለም ወደሰውየው አካባቢ ሞት እንደልቡ ሰዎችን ይቀጥፋል: በመጨረሻ ሰውየው ሲታመም ምነው ፈጣሪየ ልታስጠነቅቀኝ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን?  ይለዋል: እስካሁ ዙሪያህን ሳደርገው የነበረውን ምን ብለኸው ነው? አለው ይሉናል:

የዛሬው የአማራ ሞት ያልታየህ፤ እሩቅ ሆኖ የተሰማህ ነገ ከአንተ ሲደርስ ልትነቃ አትችልም አውቀህም ሆነ ሳታውቅ ያኔ ሞተሃልና::

የዛሬው የአማራ ሞት የአንተም ሞት ነው: ይህን ምንጊዜም አትርሳ::በተናጠል ከመሞት በጋራ መኖርን መምረጥ ብልህነት ነው:: የወራሪው ትግሬም ሆነ የኦነጋውያን ህልም ለአንተም ሆነ ለኢትዮዽያ የማይፈታ ቅዥት ነው: ቢያንስ በሁለት  ባላ ላይ የቆመመንግስትም ድጋፍ አላቸው::

ትጥቅ ተከልክሎ በመመንጠር ላይ ያለውአማራ የኦነግም ሆነ የወራሪው  ትግሬ ጠላት  ስለሆነ የመንግስት ምልምሎች ድጋፍ አይጓደልባቸውም:

ኢትዮጵያ ለሚጠሏት ሳይሆን ለሚሞቱላት የምትሆንበት ጊዜ አሩቅ አይሆንም።

ኢትዮጵያ ሃገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ

የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ

አባባል ለጥቅማቸው ሲሉ ተለጥፈው ባሉ ተውሳካት ሳይሆን ፍቅሯን በልባቸው በጽፉ ጀግኖኞቿ ይቀየራል። ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን ትሆናለች።

ለውጥ ይኖራል፤ የሚኖረውም ለተርኝነት  አይደለም ለእውነተኛ የትዮጵያ ትንሳዔ እንጂ።

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Dawit State Terrorism 1
Previous Story

ኢትዮጵያ በአብይ እጅ እየወደቀች ወይስ የሻለቃ ዳዊት ማስጠንቀቂያ ብቻ? | Hiber Radio

170207
Next Story

ከአጣዬ እስከ ሸንኮራ የወራሪዎች የዕብሪት እርምጃ ድንበር የት ነው? | Hiber Radio

Latest from Blog

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የውጪ ግንኙነት የቤተክርስቲያኒቱን የሺሕ ዘመናት ታሪክ እና እሤቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርባታል!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) (ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) እንደመንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ- ባሳለፍነው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአንድ ቀን የተካሄደው፤ ‹‹የአፍሪካ  መንፈሳዊ ቀን/The African Spiritual

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |
Go toTop