March 29, 2022
2 mins read

የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚመለስ የፌዴሬሽን ም/ቤት ገለጸ

277471533 551681352980153 8907273255634613858 n
የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚመለስ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የራያ ሕዝብ ተወካዮች ላቀረቡት ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፥ የራያ ሕዝብ ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጠው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የራያ ሕዝብ ተወካዮች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የራያ ሕዝብ የማንነት እና የወሰን ጥያቄን በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ያቀረቡ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ ምላሽ ሳያገኝ እንደቆየ አውስተዋል፡፡
አያይዘውም÷ የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ሞትን ጨምሮ ሌሎች በደሎች በራያ ሕዝብ ላይ ሲፈፀም የቆየ እንደነበረና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የራያ ተወላጆች ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ እና ንብረታቸውም ሲወድም እንደነበረ ተወካዮቹ በአካል ቀርበው አስረድተዋል፡፡ ጥያቄያችን ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ሲሉም ተወካዮቹ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ጥያቄውን ላቀረበው ኮሚቴ በሰጡት ምላሽ÷ የራያ ሕዝብ ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ ይሰጠዋል ብለዋል፡፡
እንደ ከዚህ በፊቱ የሕዝብን ጥያቄ በኃይል ለማፈን የሚደረግ አላስፈላጊ ጫና ከሕገ መንግስቱ የሚቃረን ስለሆነ ተቀባይነት እንደሌለው የጠቆሙት አፈ ጉባዔው፥ የሕዝብ ጥያቄ ሕግን መሠረት በማድረግ ምላሽ በመስጠት ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል በማለት ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

3 Comments

  1. አገኘሁ ተሻገር ለቁራሽ እንጀራ ብለህ ብኩርናህን እንዳትሸጥ ብዙ እድል አስመልጠህ መስዋእት ተቀብለህ በክብር የምትሞትበት ጊዜ ላይ ደርሰሃል። የፖለቲካ መጠቀሚያ ሁነህ የመምቻ ዱላ እንዳትሆን። ካልጠፋ ቦታ እዚያ ላይ ሲያስቀምጡህ ምን እንዳሰቡ ቦታውን የሰጡህ ሰዎች ነው የሚያዉቁት አሁን ባለፈው ስታደርገው እንደነበር ነገር ካሳከርክ አንተም ሆነ ዘር ማንዘርህ የአባይን ድልድይ አልፎ ወደ ክልሉ ለመሄድ ይቸገራሉና እወቅበት። ያለፈውን ስራህንም እያነሱ ለማመንዠክ ይገደዳሉ።

  2. አገኘሁ ተሻገር ከብልፅግና የዘረፍከዉ 9 ሚሊዮን ብር ሸብቦህ የአማራን እርስት እናዳትሸጥ ህሊናህን መርምር። የአማራ መሬቶች የተወሰዱት የዘረኛው ህገ አራዊት(ሀገ መንግስት) በወያኔና ኦነግ ከመፃፉ በፊት ስለሆነ በህገ መንግሥቱ መሰረት ይፈታል የሚለውን ቀልድ ብታቆመዉ ይሻልሀል። ጨዉ ለራስህ ስትል ጣፍጥ የሚለውን ብሂል አስታዉስ።

  3. አገኘሁ ተሻገር ይህች ጥርስ የነቀልካበት ያረጀችና ያልሰራች ቀልድህን አሁን ቀይራት እንደ ሌሎች ጓደኞችህ በውርደት መጠናቀቅህን ልናሳስብህ እንወዳለን። ተከብረህ በምትወደው ስልጣን መቆየት የምትችለው ህዝብ ሲያቅፍህ ነው። ባለፈው የሰራኸው ስራ ዶሴው እንዳለ ነው። ዛሬም ይህ ነገር ባንተ መያዙ ሀሳብ ውስጥ ከትቶናል ብቃትህን እንጡራጠራለን የአላማና የጽናት ሰው መሆንህን ያየንበት ጊዜ የለም በዘመነ ሹመትህ ለአማራው የመከራ ዶፍ ነው ያዘነብክበት። ታሪክህን እንድታድስ አጋጣሚዎች እዚህ ቦታ ስላስቀመጡህ በድፍረት ኬሪያ ለትግሬ የሰራችውን ግማሹን እንኳን ለአማራ ዋልለት። ሽመልስ እኔ ነኝ አገጣጥሜ የሰራሁት ሲልህ ምን ይሰማሀል?። ህዝብ ብዙ ነው እጥፍተህ አትጨርሰውም። የትግሬን ታሪካዊ ቦታ ያላወቅኸው ከሆነ የወራሪው የትግሬ ሀይል ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት የነበረውን እልክልሀለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

170130
Previous Story

በድጋሜ መሰማት ያለበት: የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባዔ

234455eeee
Next Story

የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከሚሰጥ የአበል ክፍያ ጋር በተያያዘ ያላቸውን ቅሬታ ገለፁ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop