ለማኝዋ ስትሞት አራት ሚሊየን ዶላር ተገኘባት

ክንፉ አሰፋ

አንዲት የተጎሳቆለች ወይዘሮ በሪያድ ጎዳናዎች ላይ ምጽዋት ትጠይቃለች። አላፊ አግዳሚው እቺን ወይዘሮ አይቶ አያልፋትም። ሰደቃ እየወረወረላት ያልፋል። በተለይ በበዓል ወራት ገቢዋ በእጥፍ ይጨምራል።

አይሻ ትባላለች። ነዋሪነትዋ ሪያድ ሳውዲ አረቢያ ነው። ላለፉት 50 አመታት በልመና ስራ ስትተዳደር ቆይታ በተወለደች በ100 አመትዋ በያዝነው ሳምንት እሁድ እለት ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። አማሟቷም ድነገት ነበር ይላል አረብ ኒውስ።

ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው እንዲሉ የአይሻ ህልፈት አለምን ያስደመመ ጉድ ይዞ መጣ። ለሃምሳ አመታት በልመና የተሰማራችው ወይዘሮ ሚሊየነር ኖራለች። የወርቅ ጌጣጌጦች እና የጥሬ ገንዘብ ሃብትዋ አራት ሚሊየን ዶላር ሲሆን በጂዳ ከተማ የአራት ትላልቅ ህንጻዎች ባለቤትም ነበረች።

የአይሻን ንብረት የሚወርስ ዘመድ የለም። አብሮ አደግ ነኝ የሚል አህመድ አል ሰይድ የሚባል ሰው ግን የውርስ መብት አለኝ ብሏል። በእርግጥ አይሻ ሌላ ዘመድ የላትም። እህትና እናትዋ ለማኞች ነበሩ። ወላጆችም በልመና ይተዳደሩ የነበሩ መሆናቸውን የጠቀሰው የአረብ ኒውስ፣ አይሻ ንብረታቸውን በከፊል ከነሱ በውርስ እንዳገኙም ዘግቧል። አሁን ሁለቱም ሞተዋል።

አህመድ አል ሰይድ ንብረቱን “አይሻ ለኔ አውርሳኝ ሞታለች እኔም ተቀብዬ ለድሆች እንዳከፋፍል ይፈቀድልኝ” ብሎ ነበር። ከመንግስት ያገኘው ምላሽም ግን የለም።

ልመናውን እንድትተው ቢወተውታትም አሻፈረኝ ማለቷን ለመገናኘ ብዙሃን ገልጿል።

ሌላው የሚገርመው ነገር አይሻ ህንጻዋ የሚኖሩትን ሰዎች የቤት ኪራይ አታስከፍላቸውም ነበር።

አይሻ ሚሊየነር ነበረች። አንድ ቀን ጥሩ ምግብ ሳትበላ፣ ጥሩ መኝታ ላይ ሳትተኛ፣ ጥሩ ቤት ውስጥ ሳትኖር፣ ጥሩ ልብስ ሳትለብስ ኖራ ለዘላለሙ አሸለበች። ግን ይህ ለምን ሆነ የሚለው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕብር ራድዮ ሙሉ ፕሮግራም: የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማሳፈን በሚሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ አውጥቷል የሚል ወቀሳ ቀረበበት.. እና ሌሎችም

አልፎ አልፎ የዚህ አይነት ክስተቶችን በአለም ላይ እናያለን። በሺዎች የሚቆጠሩ የኔብጤዎች ያሉባት ኢትዮጵያም በዚህ ስራ ከፍተኛ ሃብት እና ንብረት ያፈሩ ለማኞች አጋጥመውኛል።

እርግጥ የልመና ገንዘብ ስላልተለፋበት ይጣፍጥ ይሆናል። ልመናም እንደ አደንዛዥ እጽ ሱስ ያስይዝ ይሆን?

1 Comment

Comments are closed.

Share