ሐረር በእሳት አደጋ፣ በጥይት ሩምታ፣ በሕዝባዊ ተቃውሞና በቆመጥ ድብደባ ስትታመስ ዋለች

March 10, 2014

(ዘ-ሐበሻ) በሐረር ትናንት ምሽት ከግምት ከሶስት ሰዓት ተኩል ጀምሮ ልዩ ስሙ መብራት ሃይል ተበሎ በሚታወቀው የገበያ ቦታ በተነሳ እሳት አደጋ የበርካታ ነጋዴዎች ንብረት ከወደመ በኋላ “የእሳት አደጋውን የክልሉ መንግስት ሆን ብሎ ያቀነባበረው ነው” በሚል የአካባቢው ነዋሪ በዛሬው ዕለት ተቃውሞን ለመግለጽ አደባባይ ወጥቶ እሳቱን ለማጥፋት ውሃ ያልነበረው የክልሉ የእሳት አደጋ ማጥፊያ የተቃውሞ ሰልፈኛውን ለመበተን ውሃና አስለቃሽ ጭስ ሲጠቀም ዋለ። የክልሉ ፖሊስም በጥይት ሩምታ በማውረድ፣ በቆመጥ በመደብደብ ሰልፈኛውን ሲበትን መዋሉን ለዘ-ሐበሻ ከስፍራው የደረሱ ዜናዎች አመልክተዋል።

የዘ-ሐበሻ ተባባሪ ዘጋቢዎች ከሐረር በትናንቱ የእሳት አደጋ ቃጠሎ ንብረታቸው ከወደመባቸው መካከል የተወሰኑትን በማነጋጋር ባጠናቀሩት መረጃ “የክልሉ መንግስት ነጋዴዎቹ ይሰሩበት የነበረውን ቦታ ይፈልገው ነበር። በተደጋጋሚም እንዲነሱ ጠይቋል። ነጋዴዎቹ ከዚህ ቀደም ከ3 ዓመታት በፊት ሸዋበር አካባቢ በተመሳሳይ ሴራ ንብረታቸው የተቃጠለባቸው መሆኑን እና በትናንቱ አደጋ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ለተቃውሞ አደባባይ እንዳስወጣቸው መረዳት ችለናል።

በመብራት ሃይል የገበያ ቦታ የተነሳው እሳትን ለማጥፋት የተደረገው ርብርቦሽ በጣም ደካማ እንደነበር የሚገልጹት እነዚሁ ነጋዴዎች ከድሬደዋ እና ከጅጅጋ የእሳት አደጋ ማጥፊያ ብርጌድ እስኪመጣ ድረስ ብዙ ንብረት ወድሟል። እሳቱ ሳይስፋፋ ነጋዴዎቹም የተወሰነ ንብረት እንኳ ከእሳቱ እንዲያተርፉት አለመደረጉን የገለጹት እነዚሁ ባለንብረቶች መንግስት ወዲያውኑ የተቃጠለውን አካባቢ በግሬደር ማረሱ አስገራሚ ሆኖባቸው ነጋዴዎቹ ዛሬ አደባባይ ወጥተው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነበር።

በብሶት የተወጠረው የሃረር ሕዝብ ባስነሳው ተቃውሞ የክልሉ ፖሊስ በአስለቃሽ ጭስ፣ በቆመጥ ድብደባ፣ በውሃ፣ በጥይት ሲበትን የዋለ መሆኑን የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በርካታ ሰዎች መታፈሳቸውንም ገልጸዋል።

በዚህ የተቃውሞ እንስቃሴ ላይ የሞተ ሰው እንዳለ ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ግን ተሰምቷል።

ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን እንመለሳለን።

2 Comments

  1. yemiasazinew negadewochu sebisibo ayizoachihu enidemalet bezaw mishit metaresu new. yeharer “yihudawoch” lelaw biher harar leko endiweta begilits biyasayum mengist minim alemaletu betam yasazinal.

Comments are closed.

Previous Story

ኢህአዴግ ዳግም በክፍፍል ጎዳና?… (ከተመስገን ደሳለኝ)

Next Story

የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ አሳሳች መረጃዎችና የተምታታ አስተያየት

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop