አቶ ወርቁ አይተነው መልዕክት አስተላለፉ

March 13, 2022
275751643 3150703011914168 2960228920287557200 n
የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን በየአላችሁበት የከበረ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ!
* * * *
ጁንታው ኢትዮጵያን ለመበታተን የአማራን ህዝብ ዘሩን ለማጥፋት አላማ አድርጎ ወረራ በጀመረበት ወቅት፤ እኔም እንደ አንድ ዜጋ ለሀገሬና ለህዝቤ የሚጠበቅብኝን ለማድረግ ቀን ከሌሊት ያለ ድካም በትግሉ ጎራ ከተሰለፉት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሀይሎች፣ ሚሊሻና የአማራ ፋኖ እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ በሚያደርግበት ጊዜ እኔም ህዝቤን በመሰብሰብ የሞራል ግምባታን ስሰጥ፣ ያለኝን ሁሉ ያለ ስስት ሳበረክት ቆይቻለሁ።
ይሁንና ወራሪው ሀይል በአማራ ክልል ዘልቆ ጥፋትና ውድመት እየፈጸመ በመጣ ጊዜ “ሊበላህ የመጣውን ጅብ በልተኸው ተቀደስ” በሚል የአባቶቼ ብሒል በመነሳት ልዩ ስፍራው በጎጃም መርጡ ለማርያም አካባቢ ሚሊሻውን ሰብስቤ በማነጋግርበት ወቅት ወራሪው ጠላት ሀገርን ለብተና አማራን ጨርሶ ለማጥፋት በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰ መምጣቱን አስመልክቶ፤ ጨርሶ ሊያጠፋን የመጣውን ጠላት በማንኛውም መልኩ እስከ ህይዎት ፍጻሜ እንድንዋጋው ለማስገንዘብ የተናገርኳቸውን ንግግሮች በከፊል ቀነጫጭበው ከዋናው አውድ በራቀ መልኩ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨትና በኔ ላይም ያልተገባ የታሪክ ስሁት ለማስረጽ ወርቁ አይተነው “እንደ ፍዬል ጠብሳችሁ ብሉት” ብሏል በማለት ጥቂቷን ንግግር ለብቻ በመቀንጨብ የሰውን ልጅ አርዶ ስለመብላት ያስተማርኩና የሰበኩ አስመስለው ያወጡት ቪዲዮ ለሰፊው ህዝብ ለምወዳችሁና ለምትወዱኝ ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ሙሉ ንግግሬን ከታች ያስቀመጥኩ በመሆኑ የጠላትን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ስራና፤ በኔ ላይም የሚደረገውን የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ ከዚያም አለፍ ብሎ ከአባት አያቶቼ ያልተማርኩትን አረመኔአዊነት የተላበስኩ አስመስለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሰራጩት ቪዲዮ አውዱን የሳተ መሆኑን እንድትረዱልኝ ስል በአክብሮት እጠይቃለሁ።
ይህም ወራሪው ሀይል ህዝብን የማይወክል የተገነጠለ ጁንታ ሲሆን በህዝብ ለይ የፈጸማቸው ግፎች ቀላል የማይባሉ ታሪክ መዝግቦ ያስቀመጣቸው በደሎች በርካታ ናቸው።
ከእነሱም መካከ፦ ባልን አስቀምጦ ሚስቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ደፍሯል፣ ገና ምንም ያላወቁ ጨቅላ ህጻናትንና መነኮሳትን ከገዳም እያወጣ ሲደፍር የነበረ ጨካኝ ሀይል ነበረ።
ይሄን ጭካኔ የፈጸመን ሀይል መታኮስና ፊለፊት መጋፈጥ ሳይሆን በፉጭራም ሆነ እንደፍየል ጠብሶ መብላት ነው ብሎ ለልዩ ሀይላችንና ለሚኒሻችን ለፋኖዎቻችን ጁንታው በህዝባችን ለይ ሲፈጽም የነበረውን ከፍተኛ የጭካኔ ድርጊት ተንተርሰን ሁኔታው የከፋ መሆኑን የተጠቀምንበትን ቃል እነ ቆርጦ ቀጥል ዛሬ እንደ አዲስ እየቆራረጡ ሁኔታው ወደሌላ የሄደ በማስመሠል ላይ ይገኛሉ።
275747670 3150703128580823 7095846210162661297 nእኛ በተፈጥሮ ሰውን የምንረዳ ለሰው የምናዝን እንጂ የእዚህ አይነት አመለካከት የለንም።
አሁንም ይህ ወራሪ ሀይል በአማራ ክልል ለይ ግፍ ለመፈጸም ያቀዳቸው ብዙ አስከፊ ነገሮችና ሌላ ችግር ለመፍጠር ብሎም የጭካኔ ስሜት ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ለይ እንዳለ ይታወቃል።
ለምሳሌ የተለያዩ አጀንዳዎች በመስጠት እኛ በእዚህ አጀንዳ ስንሻኮት እሱ የራሱን ስራ ለመስራት ስለሆነ ይሄ ታምኖበት ከእውነት የራቀውን ውሸት ከቁም ነገር በለመቁጠር ወደ ዋናው ትኩረታችን ሄደን በክልላችን ሳንበታተን አንድ ሆነን ፣ በአንድ አስበን ፣በጥቅሻ ተግባብተን በእዚህ ወራሪ ሀይል ለዳግም ጥቃት እንዳንዳረግ አጀንዳችንን ና የአጀንዳ ማስጠያ ቃሎችን በአጠቃላይ በደላሎቻቸውና በተከፋይ ዩቲዩበሮቻቸው የሚያደርጉትን የሳይበር ጦርነት ወደ ጎን አሽቀንጥረን በመተው ዝግጅት እናድርግ።
ሀገራችን ለሁላችንም ትበቃለች። የመልማት ጸጋዋን ተጠቅመን በፍቅርና በአንድነት ተሳስበን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለሁለንተናዊ እድገት ራሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። ከዚሁ በተቃራኒ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሀሰት ታሪኮችን እውነት በማስመሰል እየተወኑ ያሉት ሀገር አፍራሽ ሀይሎች ስንቃቸው ውሸት ጥይታቸው ቅጥፈት ስለሆነ የሚሰጡትን አጀንዳ ወደ ጎን በመተው በራሳችን አጀንዳዎች ዙሪያ በርትተን እንድንሰራ ስል በአክብሮት እጠቃለሁ።

4 Comments

  1. አይ አቶ ወርቁ ይችማ ትንሿ ነች ሌላ ቢሉህ ነበር እንጅ የሚገርመው። አይዞህ ወንድማችን የማናውቀዉ የለም ሃሳብ አይግባህ ይህን የሚጽፉብህ እንደ ፍየል ጠብሰው የበሉ እንደ ከብት ሰብአዊ ፍጥረትን ያረዱ ናቸው ታዲያ ክፋት አድራጊዎች ቢጽፉቡህ ምን አስጨንቆህ? ለሀገርህ ምቾትህን ትተህ የሚገባህን አድርገሀል ይሄ ክፉ ጊዜ እስኪያልፍ ወጣ ብዬ ልምጣ ሳትል በግምባር በመገኘት የተቻለህን ሁሉ አድርገሃል ለዚህ መልካም ስራህ ያለው መንግስት ኢትዮጵያዊ ከሆነ እውቅና ሊሰጥህ በተገባ ነበር ኢትዮጵያን ከብተና ማዳንህ ስህተት ነው ብሎ ካመነ በቀጣይ የሚያደርገውን እናያለን። ሁሉም ያልፋል ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ለዘላለም ይኖራል ዳኝነት የሚሰጡትም ኢትዮጵያዉያን ናቸው። መልካም ጤንነት።

  2. The TPLF is a fascist organization and had been committing atrocities against all Ethiopian communities and has singled out the Amharas as the main enemies of the Tigrayans. Accordingly it indoctrinated and mobilized the Tigrayans young and old to invade the Amhara and Afar regions where it committed unspeakable atrocities. Typical of fascists, the TPLF targets the whole communities indiscriminately and unleashes its barbaric forces against them as witnessed in the Afar and Amhara regions. When the TPLF fascists mobilize en masse, the target communities have to use every legitimate means to defend themselves. At the same time national political plans and strategies should be prepared and devised to de-fascistize Tigray ( ridding Tigray of fascism). The experience and knowledge gained from the de-nazification of Europe can be used to rid Tigray of fascism.

  3. አቶ ወርቁ መተኪያ የሌለህ ወንድማችን እነዚህ አረመኔዎችና ተከፋዮቻቸው ብዙ ስም ሊሰጡህ ይችላሉ ሆኖም መላው ኢትዮጵያውያን ካንተ ጋር ነን ምንም ማስረጃ አያስፈልግም

  4. አቶ ወርቁ ማንነትህን በተግባር የገለጽ ጀግና ወንድማችን በመሆንህ እንኮራብሀለን ። እንዳልከውም ቆርጦ ቀጥሎቹ ሌላ የቤት ሥራ ሊሰጡን ፈልገው ነው እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምስናል ። አይዞህ በርታ አብረንህ ነን ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ስድስቱ የብልጽግና ፓርቲ ቀጣይ አቅጣጫ እና የአቋም መግለጫዎች

hewan
Next Story

እጅግ አሳዛኝ… ሄዋን ወልዴ ትባላለች የተወለደችዉ ጎንደር ከተማ ነዉ።

Latest from Blog

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የውጪ ግንኙነት የቤተክርስቲያኒቱን የሺሕ ዘመናት ታሪክ እና እሤቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርባታል!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) (ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) እንደመንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ- ባሳለፍነው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአንድ ቀን የተካሄደው፤ ‹‹የአፍሪካ  መንፈሳዊ ቀን/The African Spiritual

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |
Go toTop