የዘንድሮው 126ኛው የዓድዋ በዓል በእኔ ሚንስትርነት ዘመን በዳግማዊ ዓፄ ምንሊክ አደባባይ አይከበርም

የወቅቱ ባህልና ስፖርት ሚንስትና የአንዱ ኦነግ ክንፍ ሊቀመንበር የሆኑት ኦቦ ቀጀላ መርዳሳ የዘንድሮው 126ኛው የዓድዋ በዓል በእኔ ሚንስትርነት ዘመን በዳግማዊ ዓፄ ምንሊክ አደባባይ አይከበርም በሚለው አቋማቸው በመፅናታቸው በዓሉ እስከ ዛሬ ይከበርበት ከነበረው የምንሊክ አደባባይ ወደ አድዋ ድልድይ እንዲዛወር ተደርጓል። የኦቦ ቀጀላን ውሳኔ በመቃወም አንጋፋው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ቅሬታውን ቢያቀርብም ኦቦ ቀጀላ አሻፈረኝ ብለዋል። በዚህም መሠረት ለዓድዋ በዓል የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ከብሔራዊ ሙዚዬም ወደ አብርሆት ቤተመጻሕፍት፣ የበዓሉ ማክበሪያ ከምንሊክ አደባባይ ወደ ዓድዋ ድልድይ እንዲቀየር ተደርጓል።
ኦቦ ቀጀላ የፖለቲካ ፓርቲወን አይዲዎሎጂ እናከብራለን። ሀገርን ወክሎ መስራትና ፓርቲን ወክሎ መስራት የተለያዩ በመሆናቸው በቀሩት ሁለት ቀናት ወደ ሀገራዊ አስተሳሰባቸው ተመልሰው በዓሉ በተለመደው በምንሊክ አደባባይ ይከበር ዘንድ የግል አመለካከታቸውን ገተው ሕዝባዊ አመለካከለት ይላበሱ ዘንድ እንመክራለን
ፔጥሮስ አሸናፊ
ተጨማሪ ያንብቡ:  20 year old Thomas Hagos accuses Kobe Bryant of hurting him

5 Comments

  1. ኦቦ ቀጄላ መርዳሣ ስለ አድዋ የማክበርያ ቦታ አስመልክተው የሰጡትን አተያይ እየሰማሁ እያዘንኩ ይህን በፅሁፍ አየሁና ተሸማቅቄአለሁ። አድዋ በምንሊክ አደባባይ ቀርቶ በምንሊክ ድልድይ ይከበራል ያሉት በበኩሌ ድልድዩ ዬት እንዳለም አልሰማሁም ። ይህ ሁሉ የወያኔ ትውልድ ህፃናትን ላለማስከፋት የተደረገ ካልሆነ በቀር የአድዋ ክብር የሚያምረው በባለቤቱ በምንሊክ ፈረስ ስር ቢሆን ነበር። ድንገት ሳይፈልጉት ዖነግነቱ ባርቆባቸው ከሆነ በስህተት ፌዴራል ተቀላቅለዋልና በሚቀጥለው የብልፅግና ስብሰባ እሳቸውንም እንደ ኦቦ ዳውድ ወደ ሙዚየም መሸኘት አለባቸው። እጅግ የሚያስፈራና የሚያሳዝን ዘመን ነው። ምናልባት ከምንሊክ ችግር ያለው ፍንዳታው ችግር እንዳያመጣ ከሆነም ስለድልድዩም አላወራም ነበር ሲጀመር። ለመሆኑ ክብርት ከንቲባዋ እያለች ምን ያገባዋል የቱሪስት ሚር? የሸገር ቦታ ፈቃጅና ከልካይ ከንቲባዋ አይደሉም ነበር? ወያኔዎቹ ትውልድ ለዘመናት ገድለውብናል። አገራችን ችግር ላይ ናት። እንዲህ ቀላል አይደለም ችግራችን ሆኖም አድዋ አድዋ ነውና ችግሩን በግልፅ መጋፈጥ ነበረባቸው።

    ሌላው በዚሁ አጋጣሚ ብዙዎቻችሁ ለአማራ ያዘናችሁ የምትመስሉ እሣት አቀጣጣዮች የመስፍን አረጋ አይነቶችም እውነት ለወገን የቆማችሁ ከሆነ ቆም ብላችሁ አስተውሉ። ጫፍ ረገጥ ዛቻ፣ስድብና ማንቋሸሽ፣ ብሎም ክብሪት መጫር የወገንን ችግር አይፈታም ።እልክ ከማስገባት ውጭ የሚፈይደውም የለም። ምራቅ የዋጠ ይጥፋ? ወይስ ሁሉ ካንዳንድ መንግስት መ/ቤትም ጨምሮ የፅልመት አገልጋይ ሆኖ አረፈው? የኦቦ ቀጄላን ውሳኔ ወደጎን ብዬ በክራንችም ቢሆን ምንሊክ ሃውልት እሄዳታለሁ እንጅ ድልድይ ስር ሳከብር አልገኝም እኔ ብሆን። አሁንስ በዛ። አገሪቱ በስንቱ ትታመስ በፈጣሪ? ለሱባዔ እንኳ የማይመች ዘመን! በሉ መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ። እኔ በቅቶኛል!

  2. ኦቦ ቀጀላ ፈረንጅ ኢትዮጵያን እንዲያምሱ ከቡርኪና ፋሶ ያመጣቸው እንጅ ኢትዮጵያዊ አይመስሉኝም። ይህንን ካልን በሗላ ክቡር ቀጀላ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እድሜ ልካቸውን ከሰሩ በኋላ አሁን ጠቅላዩ የባህል ሚኒስቴር አድርጓቸዋል ።ልብ በሉ የባህል ሚኒስተር ትውልድ አስተሳሰብ ላይ የሚሰራ ነው ስለዚህ ጠቅላዩ ያዘዛቸውን ስራ በመስራታቸው ሊወቀሱ አይገባምፍ። ቀሪው አጀንዳቸው የኢትዮጵያ ባንዲራና የኢትዮጵያ ቋንቋ ይሆናል ጎበዝ ራቅ አድርገን እናስብ እንጂ።

    ጠቅላዩ የሚሰራውን ያውቃል ከትግሬዎች ጋር የተጓተተውን ጦርነት የሚመራው አብረሀም በላይ ነው አብረህም ህወአት በተዳክመበት ጊዜ ወደ ትግራይ በዶር/አብይ ተልኮ ህወአትን አጠናክሮ የወጣ የህወት ባለሟል ነው። አርከበ እቁባይ እህቱ ዋሺንግተን ዲሲ ምድር አንቀጥቀጥ ጸረ ኢትዮጵያ ሰልፍ ስትመራ ስታዘጋጅ አርከበ እቁባይ የአብይ አማካሪ ነበር። ብርሃነ ገ/ክርስቶሰም ከሀገር ወጥቶ ኢትዮጵያን እንዲያምስ አማላጅ የሆነው ይኸዉ አርክበ እቁባይ ነው ይባላል። እንግዲህ የነ ተወልደ ገ/ማርያምን አረጋዊ በርሄን እና ሌሎች ትግሪዎችን ነገር ትተን ንገሩን ስናገጣጥመው ማንኛዉም ነገር በጠቅላዩ ረቂቅ አመራር የተዘጋጀ ጥልፍልፎሺ ነው። ለመሆኑ ኦቦ ቀጀላ ለአብይስ ታማኝ ናቸው ወይ? ጊዜ ይፍታው።
    ኢትዮጵያ ፈርሶ አምሮበት የሚኖር ክልል ስለማይኖር ወደ ህሊናችን እንመለስ የያዝነው ጎሳ ስልጣን ላይ ቁጭ ብሏልና ተውት ይርገጥ የሚባል ነገር ለጎሳዉም ለኢትዮጵያም አይበጅም ተያይዞ መጥፋት ነው። ለማንኛውም በአጣዬ ያለቁት ዜጎች ጁዋርን ከፋው ተብሎ በሻሸመኔ ያለቁት ዜጎች ክዩኒቨርስቲ ተወስደው እስክ አሁን ዱካቸው ለጠፋው ዶ/ር አብይም አታንሱ ስላላቸው ወገኖች ፍጥረትና ዜጋ በመሆናችው ለቅንጣት አንርሳቸው።

  3. አባ ዊርቱ ሰብአዊ ፍጥረት ሁኖ ለአማራው ካላዘነ ሰው ለማን ይዘን? እረ የተሰራንበትና የደካሞች ትርክት አይጎትተን ከሌንጮ ለታና ከዳውድ ኢብሳ በላይ የሚያስቡ ሰው እድሉን ያገኙ ዜጋ ለነሱ ተረት የተመቻቹ አይሁኑ እንጅ። ዛሬ ይህን ጽሁፍ ሲያነቡ በወለጋ ስንት ሰው እንደሚያልቅ፤እንደሚቃጠል፤እንደሚዘረፍ፤ህጻናት መድረሻ ሲያጡ ከእኛ በላይ መረጃው ይደርሶታል በለን እንገምታለን። ምንሊክ መኖራቸውን የማያውቅ የአማራ ገበሬ በትግሬና በኦነግ ቅንብር መድረሻ ሲያጣ እንዴት አይታዘንለትም? አብይ አንድ ግለሰብ ነው ከታረደው ክተሳደደው ከተቃጠለው እንቅልፍ አጥቶ ከሚያድረው አንጻር መስፍን አብይ ላይ የሰነረው ትችት ለንጽጽር አይቀርብም ።እርሶም ብዙ ማስተማር የሚቺሉ የዘር ስበት ጎትቶት ማሰቢያዎን አጡ እንጂ አማራ ላይ የተፈጸመው ግፍ ተስፋዬ ገ/አብ ጽፎ ከሰጣቸሁ ተረት በላይ ነው። ለማንኛውም የሃጢያት ስበት የቆማችሁበትን መሰረት አንድ ቀን ጠርጎ መሄዱ ስለማይቀር እስከዛዉ መጠበቅ ነው።፡ለማንኛውም ሰብአዊነት ሀይማኖታችን፤ዜግነታችን፤ዘራችን ቢሆን መልካም ነው እላለሁ ለዛውስ በኢትዮጵያ እድሜ አንጻር ለመኖር ስንት ጊዜ ቀረን ብለው ነው።

  4. ሁሉም እባብ መርዝ አይተፋም። ግን እባብ ምን ጊዜም እባብ ነው። መርዛምነቱ የሚታወቀው በአዋቂና በተነደፈ ሰው ብቻ ነው። የሃበሻው ፓለቲካ በዘር ሰካራሞች የተሞላ ነው። አሁን ማን ይሙት የአድዋ ድል እዚህ ሥፍራ እንጂ እዚያ ስፍራ አይከበርም ማለት ምን ማለት ነው? የእነዚህ ጠባብ ብሄርተኞች ጥላቻ ከወያኔ ክፋት ቢከፋ እንጂ አያንስም። በበጎች መካካል እንዳለ ተኩላ ሁሌ የሚተፉት ሃገር አፍራሽ፤ አዋኪና ከፋፋይ ሃሳብን ብቻ ነው። አቦ ቀጄላ ሰከን ያሉና ሚዛናዊ የሆኑ ሰው ይመስሉኝ ነበር። አሁን ያነሱት ሃሳብ ግን የልጆች ጫወታ ነው። ግን ምንጩ ለዘመናት ራሳቸውን ግተው ሌላውንም ከጋቱት የውስልትና ፓለቲካ የተቀዳ ውሃ በመሆኑ ጥላቻቸው ከየት እንደመጣ ቁልጭ ብሎ ይታየኛል። በዚህ እዚህ አይከበርም እዚያ ይከበር በሚለው እሰጣ ገባ አንድ ነገር ሰው ሊያስተውል ይገባል። በወለጋና በሌሎች አካባቢዎች ዘር ተኮር ጥቃትና መፈናቀል የሚፈጽሙት እዚያው ቤተመንግስት ሥር ቁጭ ብለው የመንግስት ደመወዝ፤ የመንግስት መኪና እያሽከረከሩ የሚያናኩሩን ጎዶች ናቸው። ሲጀመር አቦ ቀጄላ የአድዋ በዓል የት ሊከበር እንደሚገባ የመወሰን ስልጣንም የለውም። ለኮታ ተብሎ የተቀመጠ ጉድ እንጂ በራሳቸው አስበው ለሃገርና ለወገን ደህንነት ተሻጋሪ ሃሳብ ያመጣሉ ተብሎ ስልጣን የተሰጣቸው አይደሉም። 60 ዓመት ሙሉ የዘር ፓለቲካ ስታመነዥክ ኑረህ አሁን ጥርስህን አሳየኝ ማለት ፓለቲካ ሳይሆን ምህታታዊ እይታ ነው። ስንቱን የነከሱበትን፤ ምን የሚታይ ጥርስ አለ ወይቦና ጠቁሮ! እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ የሚጓዘው የሃበሻ ፓለቲካ በሃሳብ መዣለጥና የቆመን ማፍረስ ልማድ ነው። ለሃገሬ፤ ለወገኔ ወይም ለጎሳና ለዘሬ ወይም ለሃይማኖቴ የሚባለው የየጊዜው እሰጣ ገባ ሁሉ የመኖሪያ ብልሃት ፍለጋ እንጂ ለጭቁኑ ህዝብ የወጣለት ተምቦላ ዛሬም የለም፤ በፊትም አልነበረም ወደፊትም አይኖርም። ባዶ እንዘጥ እንዘጥ። መሬት ላራሹ ብለው ደማቸው የፈሰሰው፤ አካላቸው የጎደለው፤ ሃገር ጥለው የሸሹት ዛሬ በህይወት ያሉ የዚያ ዘመን ትውልዶች ምድሪቱን አሁን ሲያዪ ምን ይሉ ይሆን? መሬት ላራሹ መሆኑ ቀርቶ መሬት ለባለሃብት፤ በዘሩ ለተሰለፈ፤ በክልል ፓለቲካው የክልሉን አርማ ያነሳ አራጊ ፈጣሪ የሆኑበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ገበሬውና አራሹ ደሃ ደግሞ ልክ እንደሚገፋው አፈር ተገፍቶ እዳሪ ተጥሏል። የጦቢያ ፓለቲካ እውነቱ ይህን ነው። እየገደሉ ሞተብን፤ እየሞተብን ገደልን፤ እየተረታን አሸነፍን፤ እየተሸነፍን ደመሰስናቸው ጉራና ቱልቱላ ብቻ። ኦቦ ቀጄላ መርዳሣ እንዲህ ያለ ስንኩል ሃሳብ ማንሳታቸው ያው ከእሳት ላይ ነዳጅ ለማርከፍከፍ እንጂ ለኦሮሞ ህዝብ አንዳች ፓለቲካዊ ፍጆታ የለውም። ዋ ተው በሁለት ቢለዋ መብላት። በህዋላ ይህን ህዝብ የባሰ መከራ ትከቱታላችሁ። ሊከፋፍለውና ሊያገዳድለው የሚችሉትን ቅራኔዎች እንደማጥበብ እንዲህ መቦጫረቅና በደፈረሰ የፓለቲካ ውሃ ውስጥ መዋኘት ምን የሚሉት ብልሃት ነው? አታድርስ። በቃኝ!

  5. አባዊርቱ፣
    “እሣት አቀጣጣዮች የመስፍን አረጋ አይነቶች” ናቸው! ምሥጢሩን አግኝተኸዋል!
    ከላይ ኦቦ ቀጄላ ተናገሩ ስለ ተባለው “ፔጥሮስ” (ስሙን አስተካክሎ እንኳ መጥቀስ የማይችል) ለምን ምንጩን አልጠቀሰም?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share