መንደርደርያ!
የጄ/ተፈራን አስተያየት ሰማሁት የመርዶ ያህል ። ለማን ነው ይህ ስሞታ ግን? ለኢትዮጵያ ነው? ለአማራው ጥቅም ነው? ከጄ/ አበባው ተናበዋል የተከበሩ ጄ ተፈራ? ባወጣው ባወርደው ከሰማሁበት ቀን ጀምሮ መንፈሴ ተረብሿል። የተረበሸውም በታሪኩ ብቻም ሳይሆን ባሁን ባለንበት እሣት ውስጥ የትረካው ጨብጥ ላገራችን ጥቅሙ አልታይህ ብሎ ነው። በመከላከያ ውስጥ ያለውን ውስብስብ ችግር አቢይም፣ አብዛኞች መኮንኖችም ጠቃቅሰውታል እኮ። እኔ ይቅርታ ያርጉልኝና ባሁን ሰአት እንዲህ የአገርን የውስጥ ውትድርና ጉዳይ ባደባባይ ማስጣት የጤና አይመስለኝም። በዚህ አጋጣሚ አሁንም ልደጋግመው፣ የ ጄ/አበባውን ቃለመጠይቅ አንዴ ሳይሆን ሶስቴ ስሙት። የሁሉን መልስ እዛው ታገኙታላችሁ። ታድያ ደካሞች አማራ ተነካ በሉና የጎሳ ጥብቋችሁን አልብሱኝ – ማፈርያ ሁላ። ስለኢትዮጵያ የሚናገር ባልበዛበት ዳሩስ ምን ይገርማል።
ፍሬ ነገሩ፣
ብዙ የሚታዩኝ ችግሮች አሉ። ከዬት ጀምሬ ወዴት እንደምሄድ ባላውቀውም እስቲ የሰሞኑን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲህ ልበል።
፩) ወልቃይትን በተመለከተ
ወልቃይትን እስከ ደም ጠብታ እያሉ ፊልድ ማርሻሉ፣ ጄ/አበባው ከሰአት በላይ ቆይታቸው ውስጥ አስረግጠው ነግረው፣ አቢይ ብዙ ጊዜ የማይታሰብ መሆኑን አስረግጠው፣ ምንድነው የተፈለገው? ከዚህ በላይ በተግባር የሚታየውን ምናለ ባልተፈጠረ ጉዳይ እራሳችንን ባናዳክመው?
ይልቅ ትላንት ዜና ስከታተል ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ያነሷቸው የመሰረተ ልማት ችግሮችን በተመለከተ ገንዘብ ሚኒስትሩ ማቀብ እንዳደረጉ አስረድተዋል። መለስ ብለው ደግሞ የአማራው ብልፅግና የአቅሙን እንደሚረዳ አስረድተዋል። የገንዘብ ሚር መቤት የአይኤምፍ ተፅኖ በመፍራት ይመስላል የከለከለን እንደ ዞን ብለዋል። ምናልባት ገንዘብ ሚር የወልቃይትን ድርሻ ጨምሮ ለአማራው ብልፅግና ላለመስጠቱ አረጋግጠዋል? ከሆነስ ዬትም ፍጪው እንደሚባለው ዋናው ድጎማው ላይ ማተኮሩ አይበጀንም በዚህ ሴንሲቲቭ ጊዜ? ክቡር ደመቀ የወልቃይት ጉዳይ ሳይቋጭ የነ ሲዳማው መልስ አግኝታል ብለዋል። አዎ አግኝቷል ሆኖም በሲዳማ በኩል ሊውጠን ያሰፈሰፈ ትህነግ የሚሉት ባለረጃጅም ሽንጥ ዘንዶ የለብንም ።ለዚያውም IMF ን የሚያክል እንደራሴ ያለውና እባክዎ ትንሽ ይታገሱ አንቱ ቆራጥ ወታደር። የወልቃይት ጉዳይ የሁላችንም የኢትዮጵያውያን ነውና. ወልቃይት ከተነካች በክራንችም ቢሆን ቤት የሚቀር የለም። ይህው ነው።
፪) ጦርነቱን በተመለከተና የትግራይ ጉዳይ
ሌላው ሰሞነኛው፣ ረሃብ እጅግ በትግራይ የከፋ በመሆኑና የሁዋላ ሁዋላ ችግሩ ስለማይቀርልን መፍትሄ በ ፓራለል መፈለግ መልካም ነው። ይህን በተመለከተ በተለየ ሁኔታ በውጭ ያላችሁት የትግራይ ልጆች እርቃናችሁን ለራሳችሁ ጥቅም መቅረት ከምታለቃቅሱ በፈጣሪ ብላችሁ የኤፈርት ካዝና ትግራዋይ እጅ እንዲገባ፣ እንደው ለይምሰል እንኳ እስቲ አሜሪካ ላይ አልቅሱ። እነዚህ ወገኖች ለህዝባቸው ተጨናቂ ትባሉና ክብር ታገኙ ነበር። ሁሌም ስለነ ጌታቸው ረዳ ማለቃቀስ ያስገምታል። የትግራይ ህዝባችን ዓረም እየበላ? እናንተ በኬክና ውስኪ የሚሰራችሁን እያሳጣችሁ አስፋልት ስትንከባለሉ ህዝባችን የሚላስ የሚቀመስ ይጣ? ። ይህ ጦርነት መቋጨቱ አይቀርም ግን ብዙ ብርቅዬ ህፃናት፣ አረጋውያን ሳይቀሩ ህይወት ይገብራሉ። ህዝባችንን ወደፊት እንዴት ብላችሁ ቀና ብላችሁ እንደምታዩ ሳስበው ይወረኛል። አንዲት ሄርሜላና ጋዜጠኛ አበበችና ያ ቀናሰው ጋዜጠኛ አርአያ ብቻ? ያሳዝናል!
፫) hr6600 በተመለከተ
እንዴት ዝም ይባላል? ጎበዝ በጥንካሬ ይህ ጉዳይ ሳይፀድቅ መበርታት አለብን። በደንብ ሽፋን አልተሰጠውም። ስለዩክሬንና አሜሪካ አናሊዝ የምናደርግ የሚደንቅ ነው። እባካችሁ ያቺን ሄርሜላ እንዳታስከፉብን። ዋና ጠበቃችን ልጅ ናት። ኖ-ሞሩ መፋፋም አለበትና
፬) ራሺያን በተመለከተ የኢትዮጵያ አቋም
ምስጋና ለ አባመላው አቢይ። ኒውትራል ኢትዮጵያዊ ዝምታ አዋጭ ነው። በውስጥ መስመርና ውጭ መስመርን በተመለከተ ለአቢይ አይመከርም። የጃንሆይን ኮሌክቲቭ ሴኩሪቲና ገለልተኛ ፖሊሲ እጅግ ይጠቅመናል በዛሬው ዘመን።
በተረፈ መልካም የአቢይ ፆም ለህዝበ ኦርቶዶክስ ክርስትያን ይሁንልን!!
አሜን
የጄነራሉ ሚስጢሮች የፍትህ መጽሄት ቃለ መጠየቅ
https://youtu.be/GnYCyJE9Cx8