‹‹መንግሥት ለአገር ሕልውና የተጋደሉና ጀብድ የሠሩ ፋኖዎችን ያደራጃል እንጂ ትጥቅ አያስፈታም›› አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

gizachew

መንግሥት ለአገር ሕልውናና ለሕዝብ ነጻነት የተጋደሉና ጀብድ የሠሩ ፋኖዎችን የበለጠ ያደራጃል እንጂ ትጥቅ አያስፈታም ሲሉ የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ተናገሩ፡፡

አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአማራ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ የአማራን ሕዝብ ከጠላት የሚከላከል፣ ከውርደት የሚታደጉና በልማትና በፖለቲካው መስክ ተጠቃሚ እንዲሆን ዋጋ የሚከፍሉ ሁሉ ፋኖዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም መንግሥት ለአገር ሕልውናና ለሕዝብ ነጻነት የተጋደሉና ጀብድ የሠሩ ፋኖዎችን የበለጠ ያደራጃል እንጂ ትጥቅ አያስፈታም ብለዋል፡፡
የአሸባሪው ሕወሓት ቡድንን ወረራ ለመቀልበስ ፋኖዎች ትልቅ ጀብድ ፈጽመዋል፤ የሕይወት መስዋዕትነትም ከፍለዋል ያሉት ቢሮ ኃላፊው፤ መንግሥት ለእነዚህ ሰዎች እውቅና ሰጥቶ ይሸልማል እንጂ ትጥቅ የሚያስፈታበት ምክንያት እንደሌለው ገልጸዋል፡፡
የመንግሥት ሃሳብ ለአገሩ ሲዋደቅ ጉዳት የደረሰበትን ፋኖ ለሌሎች ኃይሎች በሚደረገው አግባብ እንዲታገዝ ፣ ለአገር ክብር ለተሰዋውም ለሌላው እንደተደረገው ማድረግ እንጂ..
ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል በሰሜን አሜሪካ ነገ በሜሪላንድ በድምቀት ይጀመራል

1 Comment

  1. እየተባለ ያለው እኮ ሸፍጠኛውና ሴረኛው ብልፅግና ድሮውንም በስሜታዊነት በመነዳት ወይንም አንዳች አይነት ጥቅም ማግኘት ይቻል ይሆናል በሚል እጅግ ወራዳ እሳቤ ፋኖ የሚባለውን ንቅናቄ የተቀላቀሉ ግለሰቦችን አደራጅቶ የራሱ እኩይ ዓላማ አስፈፃሚ ሊያደርጋቸው አይችልም አይደለም ።
    ድሮውንም ትክክለኛ እና ዘላቂ የነፃነትና የፍትህ ሥርዓትን እውን ለማድረግ በሚያስችል ዓላማ ፣ መርህና ግብ ላይ ያልተመሠረተ ንቅናቄ ወይም ስብስብ የብልፅግና ቁማር መጫወቻ አይሆንም ማለት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከምር ያለመረዳት ችግር ነው ።
    ቀድሞውንም ቢሆን ድርጅታዊ ቁመና እና አሠራር ያልነበረው የጅምላ (amorphous) እንቅስቃሴ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሸፍጠኛና የሴረኛ ገዥ ቡድን ሰለባ ከመሆን ከቶ አያመልጥምና ከላይ ምስሉን የምናየው የአማራ ብልፅግና (የብልግና ማለት ይሻላል) ባለሥልጣን እየነገረን ያለው ይህንኑ ርካሽ ግን አደገኛ የፖለቲካ ቁማር ጨዋታ ነው። ”የብልፅግና ፋኖን” የማደራጀት ፖለቲካ ቁማር !
    አዎ! ቀደምት ትውልዶች (አያቶችና ቅድመ አያቶች) በተጠቀሙበትና በወቅቱ ድል ባስመዘገቡበት የፋኖነት (የአርበኝነት – ጥልቅ የአገር ፍቅር) ንቅናቄ በመጠቀም የዚህ ክፍለ ዘመን እጅግ እኩይ፣ ሸፍጠኛ፧ ሴረኛ ፣ፈሪና ጨካኝ ገዥ ቡድኖችን ድል ነስቶ ልኡላዊነቷና አንድነቷ የተጠበቀ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን ማለት ፈፅሞ አሳማኝነት የለውም።
    እናም ፋኖ እያልን የምንጠራውን ንቅናቄን ከዚህ መሪር እውነታ አንፃር ቃኝቶ ከተዋጊነት ንቅናቄ በመሠረታዊና ዘላቂ መርህ፣ ዓላማ፣ ግብ ላይ ወደ ተደራጀ ዴሞክራሲያዊ ሃይል (ንቅናቄ) ከፍ ማድረግ የግድ ነው። ያለዚያ ስሜታዊነት በተጫነው፣ በክስተቶች ላይ በሚንተራስ እና ጅምላዊ በሆነ የአገር መውደድ ዘመቻ ውስጥ የሰውና የማቴሪያል ሃብትን እያባከኑ እና የሸፍጠኛና ሴረኛ ገዥ ቡድን (የብልፅግና) ሰለባ እየሆኑ ፋኖ ነኝ/ነን ማለት የትም አያደርስም።
    መቸም የሰበብ አስባብ ድሪቶ በመደረት ከገንዛ ራሳችን ፈታኝ እውነታ መሸሽ ክፉ ልማድ (ልክፍት) ሆኖብን እየተቸገርን ነው እንጅ ግዙፉና መሪሩ እውነታ ይኸው ነው!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share