January 8, 2022
14 mins read

ፍትህ የሌለበት ይቅርታና ምህረት በምድር ላይ ቀርቶ በሰማይ ቤትስ ይኖር ይሆን??

271608352 5136321329733017 7508973600061667832 nእነ ስባሃት ነጋ ተፈቱ፣ እነ ጀዋር ተፈቱ፣ እነ እስክንድርም ምን ያህል ጦር እንደመሩና የተኛውን እዝ እንደ አጠቁ ባናውቅም በምህረት ተፈቱ።

´የለህም አይባል ይመሻል ይነጋል
አለህ እንዳይባል ስንት ጉድ ይታያል።´ ያለችው መሪ እረምዴ ነበረች።
አሁን በህይወት ብትኖር ምን ብላ ትዘፍን ይሆን?

መጀመሪያ ላይ ቅዝት መሰለኝ፤ እውነታውን ሳረጋግጥ ደግሞ ሰማይ ከላየ ላይ የተደፋብኝ መሰለኝ። እናም መጠይቅ ጀመርኩ፤

= የሰሜን ዕዝ ሰመእዕታት ነፍስ ምን ይል ይሆን?
በወሎ፣ በጎንደር፣ በአፋርና በስሜን ሸዋ እንደከብት የታረዱት ነፍሳቸው ምን ትል ይሆን?
– ´ከአሉት በታች ከሞቱት በላይ ´ሆነው በህይወት የቀሩትስ ምን ይሉ ይሆን?
– እንደከብት የታረዱት የማይካድራ ዜጎች ነፍስና ከገጀራ የተረፋትስ ከእንግዲህ
ተስፋቸው ምን ይሆን?
– ከሰሜን ሸዋ እስከ ትግራይ ድረስ የተከፈለው መሰዋአትነት ለምን አስፈለገ?

¨´–በባቢሎን ወንዝ ዳርቻ በስደት ላይ፤ በገናችን ዛፍ ላይ ሰቅለን እየሩሳለምን ባሰብ ግዜ አለቀስን–´ ነበር ያለው ቅዱስ ዳዊት።
እኛስ ኢትዮጵያን ስናስባት ምን ተሰማን?

´ራሄል ልጆቿ ስለሞቱባት መጽናናት እንቢ አላት—´ ይላል ቅዱሱ መጸሃፍ። የ´ኛስ እናቶች ከእንግዲህ ምን መጽናኛ ይኖራቸዋል??

ቁዘማ ይሁን ቁጭት፤ ሽንፈት ይሁን ሃዘን፤ ንዴት ይሁን ግራ መጋባት፤ ብቻ ይህ ነው ከማልለው ስሜት ስነቃ ፤ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ኢትዮጵያዊያን የጠላቶቻችንን ማንነት ብቻ ሳይሆን እስክዚህ ድረስ ርቀው መሄድ እንደሚችሉ አለማወቃችን ራሴን እንድታዘብ አደረገኝ።

የማንኛውም ትግል መሰረት የጠላትን ማንነት፣ መነሻና መድረሻ ብሎም ዓላማ ማወቅ ነው። ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ ጠላቶች ኢትዮያዊነትንና አማራነትና ፤ ሲያስፍልጋቸው ነጥለው፤ ከላያ ደግሞ ጨፍልቀው ያጠቁታል። ስለዚህ ለኢትዮጵያዊነትና ለኢትዮጵያ ቁሚያለሁ ወይም እታገላለሁ የሚለው መርህና ጽናት አልባ በመሆኑ፣ እስከ አሁን መሪ ድርጅትም ሆነ መሪ ማፍራት አልቻለም። ስለዚህም የጎሰኞችን የቤት ሥራ እየተቀበለ፤ በስሜትና በሆሆታ በመንጎድ ፤ በእነሱ አዙሪት ውስጥ በመግባቱ፤ የጎሰኞች መፈንጫ በመሆን ዳግማዊ የወያኔና የኦነጋዊ ብልጽግና በኢትዮጵያዊያን ደም ጋብቻ ሲፈጽሙ ለማየት በቃን። ለዚህ ደግሞ ተጠያቂዎቹም ሆነ ለአዲስ ዙር የመከራ ገፈት ጠጭዎች እኛ ኢትዮጵያዊያኖች እንጅ ማንም ሊሆን አይችልም።

ወደድንም ጠላንም ከሰላሳ ዓመት በኋላም ተሸውደናል ወይም በቀጥታ ቋንቋ ተበልጥናል። ይሁን እንጂ በአገር ተስፋ አይቆረጥምና፤ አሁንም ለዘምናትና እስከዚህ ሰዓት ድረስ የሚፈሰው የወገኖቻችን ደም ይጠራናል። ኢትዮጵያ ደግሞ ብዙ ፈተናዎችን ተሻግራ ከዚህ የደረሰች ናትና፤ ምንም ፈተናው ቢበዛ እናፈርሳታለን ያሉ ካሃዲዎች መፈረሳቸው አይቀርም። እኛ ግን አሁን ሁሉም ነገር ገሃድ በወጣበት ሰዓት በአዲስ መንፈስ ራሳችንን ለትግልና ለመሰዋአትነት ማዘጋጀት ይጠበቅብናል።

እናም ለመጭው ትግላችን ግንዛቤ እንዲሆን፤ ወደ ኋላ ልመልሳችሁ።

እንደ ምሳሌ ግራዚያን ለሙሰለኒ የጻፈው ደብዳቤ፣…

” ለእኛ ለጣሊያኖች ኢትዮጵያን እዳንገዛ የሚታገሉን ።

1/ ምሁራን => ልብ ካለህ… ልብ አድርግ… እንደ አሁኑ ምሁር ዘር የለውም፡፡ እንደ አሁኑ በገንዝብ የተሸመተ የምስክር ወረቀት የለውም።

2/አማራ => ልብ ካለህ …ልብ አድርግ ።መለስ ዜናዊ የሰጠህን ክልልና ስም ሳትቀበል፣ በዘመኑ አልገዛም ያለና መንግሥታዊ አስተዳደር ላይ ያለው ሁሉ ዜጋ አማራ ነው።

3/ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት => ልብ አድርግ፤ምንም ዓይነት ዕምነት ቢኖርህ በኢትዮጵያዊነትህ የማትደራደር ክሆነ ”ኦርቶዶክሳዊ” ነው ይሉሃል።

ታዲያ የጣሊያንን ወረራ የቀለበሰውና ጠራርጎ ሙጃ እያስበላ ያባረረው እንደ አንተ ” አማራ ታርደ! አማራ ተሳደደ! ኢትዮጵያን አፈረሷት! ኦርቶዶክስ ተቃጠለ! የሚያደራጀን አጣን! ወዘተ —–” እያለ እያላዘነ ሳይሆን፤ መንግሥት በሌለበት፣ ራሱን በራሱ አደራጅቶ፣ መሪና ተመሪ ሆኖ፣ ቤት ንብራቴ፣ ልጀ-ሚስቴ ሳይል፣ ለህይወቱ ሳይሳሳ፣ በዱር በገደሉ ስለተጋደለና ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞትን ስለመረጠ ነው።

አንተ አሁን ፤ እንደከብት ከልለው፣ የአካባቢህን ሆድ አደር ሰዎች በምስለኔ ሹመው፣ እያረዱና እያሳረዱ ሲቀረመቱህና ሲያሳድዱህ የምታላዝነው ለማን ነው?
ከዚህ ሁሉ መሰዋአትነትነት በኋላ´ አማራንና ኦርቶዶክስን ሰብረነዋል´ ያሉትን መልሰው ወደ መበራቸው እያመጡልህ ነው።
ማርቲን ሉተር ነበር ”አንተ ካልተጎነበስክ ማንም ከጀርባህ ላይ አይወጣም” ያለው።

አዎ!ኢትዮዮጵያዊ ነኝ ፣ አማራ ነኝ ያለ ሁሉ ዜጋ፤ ትላንትም ሆነ ዛሬ እንደ ከበት ይታርዳል፣ እንደ አውሬ ይታደናል፣ አከላቱ እየተበለት ይበላል፣ ይጠበሳል፤ እናት ሆዷ እየተቀደደ ጽንሷ ይበለታል። እና ማን እንዲያስጥለህ ነው የምትፈልገው?

ምዕራቡና ዕረቡ ዓለም? የገንዛ ወገኖችህ በገዛ አገራቸውና ወገናቸው ላይ በጠላትነት እንዲነሱና በባዳነት እንዲያድሩ፤ ከጽንሰት እስከ ትውልድ፤ ከትውልድ እስከ እድገት፤ ከእድገት እስከ እርጅና የሚነከባከቧቸው፤ የሚመሯቸው፤ እነሱ መሆናቸውን በዚህ ሰዓት እንደ ጅል ልናገር እንዴ?

ጠላቶችህ ወያኔዎችም ሆኑ ኦነጋዊያን እኮ እንደ አንተ ሰው ናቸው፤ እንደ አንተ የመኖር ፍላጎት አላቸው። ልዮነቱ እነሱ ለ’ርኩስ ኣላማቸው ፤ ጸንተው፤ ተደራጅተውና አደራጅተ፤ ቤተ መንግሥትን ተቆጣጥረው፤ አንተንም ሆነ ለዘመናት በደምና በአጥንት በምሊዮኖች መሰዋትነት የተገውነባችውን አገርህን ሲያፈርሱ ፤ እስከዚች ሰዓት ድረስ ያለምንቃትህን ምክንያት ራስህን ጠይቅ።

ለመሆኑ ጠላቶችህን አውቀሃቸዋል ወይ?—— ለጠላቶችህ በሆዳቸው አስበው፣ ለሆዳቸው የሸጡህ፣ የሚያሳርዱህና የሚያሳድዱህ እኮ ከጎንህ፣ ያውም ከጉያህ ፣ በደምህ የሚነግዱት የባንዳ – ባንዳዎቹ የገዛ ወገኖችህ ናቸው። ያለፈውን ወደ ጎን እንተወውና፤ እንወክልሃለን የሚሉህ ዛሬስ እነ አቶ ስብሃት ወደ ቤተ-መንግሥት ዳግመኛ እንዲመጡ ሲደረጉ ምን እርምጃ ወሰዱ? ከዚህ በላይስ የቁም ሞት አለወይ?

የክልሌ ፕሪዚዳንት የምትለው የት ነው የሚውለው? ለማን ነው የሚታዘዘው? ማንን ነው የክብር በርኖስ የሚሸልመው? ምክትል ጠቅላይ ሚንስተር የምትለው የጠላቶችህን ጉዳይ ሲያስፈጽምና ሲያጎበድድ ዕሩብ ምት-ዓመት አለፈ እኮ ? ባህርዳር እስከ አራት ኪሎ ድረስ ያለቱ ሆድ አደሮቹ ገዥዎችህ ፤ ” የሰው ልጅ በማንነቱ ሲታረድ፣ በጅምላ በግሪደር ሲቀበር፣ ሙሉ ከተማ ሲወድም ፣ ምን እያደረጋችሁ ነው?” ብለህ ጠይቀህ የወሰድከው እርምጃ አለ ወይ?

እሁንስ ” የአማራ ብልጽግና ” የተባለውን የወያኔን ወራሽ አይደለም ወይ ለኦነጋዊ ብልጽግና አድሮ በስምህና በማንነትህ ላይ እየተረማመደ የሚያስጨርስህ? ሲያርዱህና ሲያሳርዱህ የነበሩትን ወያኔዎችና እነ አቶ ጃዋር ያለ አማራ ብልጽግና የተፈጸመ ይመስልሃል?

ወያኔ ከተንቤን ተንስቶ ሰሜን ሸዋ ደርሶ ያን ሁል ግፍ ሲፈጽም፤ የክልል ገዥዎችህ ከማንም በፊት ተጠያቂዎች ብቻ ሳይሆኑ ስልጣናቸውን መልቀቅና ለፍርድ ማቅረብ ሲገባህ፤ ‘ጣትህን ኦነጋዊ ብልጽግና ላይ ትቀስራለህ። እነሱ ምን ያደርጉህ? አንተ ለመኖር እንደምትፍጨረጨረው ሁሉ፤ እነሱ ደግሞ አንተን ለማጥፋት ከአንተ በላይ ተደራጅተና ”መንግሥት” ሆነው እየሰሩ መሆናቸው መቸ ነው የሚገልጽልህ??

በተለይም ላለፋት 3 ዓመታት በወለጋ፣ በመተከልና በስሜን ሸዋ እንዲሁም በሃረርና በሻሸመኔ እንደ ቅጠል ለረገፈው ወገንህን አሁንም እየረገፈ ላላው ፤ እንተን እንወክላለን የሚሉት ገዥዎችህ ምን አደረጉ? አንተስ ምን አደረክ? ጠ/ ሚኒስተር አብይን የሚሰማቸው የለም እንጂ፤ እንዲህ ብለው ነግረውህ ነበር”—-ከአሁን በኋላ ኦሮሞን ፤ ኦሮሞ አይገለውም—”

አሁን ደግሞ ´ ኦሮሞ ትግሬን፤ ትግሬን ኦሮሞ አይገለውም –¨ እያሉህ ነው።

-ጦርንርቱን ከትግራይ አውጥተው በአንተ ምድር ላይ ለምን እንደ አደረጉት ተገለጸልህ?
– ጦርነቱ ሳይጠናቀቅ ልምን በእለህበት ቁም እንደተባልክ አሁንስ አልተገልጸልህም??

መጸሃፍ ¨—ክረምቱም አለፈ፤ መከሩም አለቀ፣ እኛ ግን አልዳንም–¨ ይላል።
እንግዲህ አማራን ማጥፋት ኢትዮጵያን ማጥፋት የሚለው ከጣሊያን የወረራ ዘመን ጀምሮ የነበና አሁን በወያኔንና በኦነጋዎ ብልጽግና እየተቀላጠፈ ነው። በልመና የመጣ ነጽነትም ሆነ አንድነት አለመኖሩ ዛሬም ሆነ ነገ መታዎወቅ አለበት። እናም ለማይቀረው ትግል መዘጋጀት የግድ ይላል። ምርጫው የመኖርና ያለመኖር ነውና።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!
———-//——–ፊልጵስ
ታህሳስ 29/2014

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop