ከለንደን እስከ እትዮጵያ የተዘረጋው የወንጀለኞች ቡድን /ስኳድ/ ዕቅድና የማስፈራራት ዘመቻ

ሃገራዊ ጥሪውን ተቀብላችሁ ወደ ውድ እናት ሃገራችሁ ኢትዮጵያ ለምትጓዙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተላለፈ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት።

በዚህ አጋጣሚ ይህን መረጃ ሳስተላልፍ የጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች በመሆናችሁ ከጉዟችሁ ፈርታችሁ እንደማትቀሩ በመተማመን ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው ትላንት ለጉዞ የሚሆነኝን ቁሳቁስ ገዝቸ ሻንጣየን ስሸካክፍ ሞባይሌ የመልዕክት መምጣትን ድምፅ ያሰማኛል።

እኔም የምጠብቀው መልዕክት ከሃገር ቤት ይህን አምጣልን፣ ስንት ሰዓት ነው የምትገባው?፣ የት ሆቴል ነው የምታርፈው?፣ ከቤተሰብህ ጋር ነው ወይ የምትመጣው? ወዘተ የሚል ነበር። ነገር ግን አንጀት የሚበጥስ ፣ ያልጠበኩትና እጅግ የሚያሳዝን መልዕክት “ ጠላት ከሩቅ አይመጣም” እንዲሉ ከወገን ተብየ አሸባሪ ርካሽ የሆነ መልዕክት ደረሰኝ።

መልዕክቱ ” Bini Man” ከሚባል በፌስ ቡክ ገፄ ይደረሰኝ የማስፈራሪያ መልዕክት እንዲህ ይነበባል “እኔ እማ ዋና የአብይ ደጋፊ ነኝ እስቲ ኢትዮጵያ ሂድ ወንድ ከሆንክ በማስረጃ ነው የማሲዝህ “ ይላል።

እራሴን መጠየቅ ጀመርኩ ፣ እኔ በሃገሬ ተምሬ፣ በሃገሬ ትልቅ ቦታ ድረስ በመመደብ በሃላፊነት የሰራሁና ይህን ይህን አደረኩ ለማለት ጀግኖች ሕይወታቸውን እየሰጡ ስለሆነ አስተዋፅኦየን ለማንሳት አልዳዳም። አንድ ነገር የደረሰብኝ የአማራ ተወላጅ በመሆኔ ተገፍቸ የምወዳትን ሃገሬን ትቸ ለመሰደድ መብቃቴን ነው።

ከዚያም ወንድሜ ሆይ ማስፈራራቱ ምንም አይደለም። ፈራጅ አምላክ ያውቀዋል ። እስኪ ማንድን ነው ምክንያቱ ንገረኝ በሞቴ አልኩት “ እገባለሁ ብትል የሚደርስብህን፣ ታውቀዋለህ” ብሎ መለሰልኝ። አሁን ከራሴ ጋር መሟገት ጀመርኩ። ሃገሬን ከለቀቅኩ ሃያ ሁለት ዓመት ሊሆነኝ ነው። ይህ ማስፈራራት የተቀነባበረው ከእነ አጂሬ ሰፈር፣ ከእነሱ ጉዳይ አስፈፃሚዎች ፣ ከጁንታው፣ ካልጠራውና ከባለተረኞቹ ከኢትዮጵያ ኢምባሲ መሆኑ ጥርጥር የለኝም።

ከዚያም አንተ ማነህ ወንድሜ ብየ ፣እኔም እኮ ኢትዮጵያዊ ነኝ ፣ ምንስና ማንስ ያበላልጠናል ፣ እኔን እንዳትሄድ ያልከኝ ብየ ስጠይቀው ‘Bini Man* እንዲህ ብሎ መለሰ” አብይ ማንን እንደሚሰማ

ኢትዮጵያ ያገናኘን ወርቅየን ጨምሮ” ብሎ ምላሽ ይሰጠኛል።

እንግዲህ የእንቁራሪቷና የዝሆኗ ተረት ፣ ተረት ትዝ አለኝ። እነዚህን ሰዎች የበለጠ ማወቅ አለብኝ ብየ የፌስ ቡክ ማንነታቸውን/Profile/ ፈለፈልኩ።

ይህ ወርቁ ተሾመ የተባለው ሆነ የBini Man የሁለቱም የፌስቡክ ጓደኞች እነ ገረእንቼሄል፣ ገብረ፣ ተክላይ፣እነ ትብለፅ ወዘተ ሆነው ፣ የፕሮፋይላቸው አርማ የሕወአትና የኦነግ ሸኔ ሆኖ አገኘሁት። ይህ የተደራጀ ተልዕኮ እንዳለሁ ተማመንኩ።

ሌላው የተቀናጀ ሰንሰለት ያለው አሸባሪ ቡድን እንዳለ የሚያረጋግጠው የBini Man የፌስ ቡክ አድራሻ ቦሌ አዲስ አበባና በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ኑሮውን ሊያደርግ እንደገባ ያሳያል፣ የእነ ወርቁ ቡድን ግን እንግሊዝ-ለንደን መናህሪያውን ማድረጉን የፌስቡክ መገኛ አድራሻ/Profile/ ያረጋግጣል።

እንደሚታውቀው እኔ የምታውቀው ወገንን በማማከር፣ በመርዳትና የሃገሬ ልጆች በሃገረ እንግሊዝ ተላምደው እንዲኖሩና የሚገባቸውን ከሚመለከተው አካልና ከኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲያገኙ መደገፍና ማሳለጥ ነው።

ከዚህ ሌላ በአማራ ክልል በቅማንትና አማራ መካከል በሕወአት አሻጥርና አቀነባባሪነት በተቀሰቀሰው ግጭት ለተፈናቀሉት ወገኖች ታላላቅ ጉምቱ ባልሃብቶች፣የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተገኙበት ትልቅ ዝግጅት ተዘጋጅቶ ነበር።

ይህን ዝግጅት በአውራነት ባዘጋጀነው የአማራ ተወላጆች በኢምባሲው አቀነባባሪነት የደረሰብን ፈተና ቀላል አልነበረም።

ይህን ዝግጅት ብትንትኑን ለማውጣትና በኛ አዘጋጆች ላይ ጥቃት ለማድረስ ተወጥኖ የነበረው ሴራ ይዘገንናል።

የዚህ ስብሰባ መድረክ መሪ /Stage Manager/ እኔ ነበርኩ።

የዝግጅቱን ታዳሚያን ላነጋግር ወደ ስብሰባው አዳራሽ ስወርድ የጠበቀኝ ክስተት ከአንድ የሃገር ልጅ ተብየ የሚጠበቅ አልነበረም። ከላይ የተጠቀሰው እናቱ ወርቅ ብለው ስም ቢያወጡለትም “ መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ” እንዲሉ የጀግኖችን ስም ስለያዘ እያዘንኩ የቢራ ጠርሙስ አሹሎ፣ በመጠጥ የደፈረስ ዐይኑን እያጉረጠረጠና የፈሪ የተርበተበተ ድምፅ ይዞ ቀረበ፣ ከጀሌዎቹ የተሰጠውን ልማዳዊ ወንጀሉን ለመፀም። የዋዛ አይደለሁምና የመይሳው ልጅ በመሆኔ “ምን ፈልክ፣ በደህንነት ነው እያጎራደድኩ አስገፍቼ እማስወጥህ፣ የቢራውን ጠርሙስ ከውን” አልኩት”።

ይህን የሚያጓራ ድምፅ ሲሰማ እነ Bini-Man ከወርቁ ተብየ የወንጀል ፈፃሚ ሲጠጉ ፣ ፋኖ ወገኔ ከየት መጡ ሳይባል ከች አሉ።

እነ አጅሮች ፋኖ “ማን እንደሆነ ታውቀዋልህ? እናንተ ሰውን ሳታውቁ አትዳፈሩ” ሲባሉ እንደ ጉም በነኑ።

ይህ ነው እንግዲህ የነ Bini Manና የነ ወርቁ አይጡ ተልዕኮ።

እነዚህ የእንግዲህ ልጆች ወይም የሃገር ሽያጭ ልጆች እያደረጉት ያሉት በውጭ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ አማራ ካልጠራውና ከተረኛው በየኢምባሲው ከሚግተለተለው የሸኔ ቡድንና ከአንድ አንድ ውታፍ ነቃይ አድርባይ አማራ ጋር እንዲሁም የአማራን የውሸት ካባ የተላበሱ የጁንታው ዲቃላወች ይዘው እንደዚህ እያመሱንና ሰላም እያሳጡን ያሉት።

በምድረ ኢትዮጵያ ሲለበለቡ በውጭ ሃገር ደግሞ፣ ሌላ ጦርነት ከፍተዋል። ዲሞክራሲ ባለበት ሃገር የአዋቂዎቹን፣ ነቃ ነቃ ያሉትንና የሚገዳደራቸውን ልሳንና የሾለ ብዕር ለማዶልዶም በመሞከር ላይ ናቸው። ከዚያም ቆፍጠን ባለ ብእር አንተ “ የጉም ፣ ሽንት፣ አትዘላብድ፣ ጀግና አያወራም ፣ ውረድ እንውረድ ፣ የት ነህ? እኔ “ተዘራ ነኝ ፈሪ ያልወለደኝ ፣ ኢትዮጵያዊ ስም ያለኝ” ብየ “ ባንዳ የባንዳ ልጅ ባንዳ የሰጠህን ስም ወዲያ ትተህ ፣ኢትዮጵያዊ ከሆንክ በእውነት ስምህ ና“ ብየ ሰለው።

ይሄን መልዕክት ላከ “ ኢትዮጵያ ኤንባሲ ሄደን እናመለክታለንና ኢትዮጵያ ከሄድክ ደግሞ የዛኔ ማን ማንን እንደሚሰማ እናያለን” የሚል ስንኩል ፣ መልስ ሰጥቶ ልሳኑ ተዘጋ።

“ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ አሳደረች” እንዲሉ ኢምባሲውም በአማራ ተወላጆች ላይ፣ ከነ ሸኔ፣ ውታፍ ነቃይና የወያኔ ሽፍላዎች ጋር ሆኖ ክትትሉን እንደቀጠለ ያሳያል ።

በዚህ ታላቅ ሃገራዊ ጥሪ ወገን ልቡን ነፍቶ በነፃነት እንዳይሳተፍ፣ የተረኞች የድለቃ መድረክ እንዲሆን፣ ኢትዮጵያዊነት በሰፊው እንዳይውለበለብ የሚደረግ ሻጥር እንዳለ ያሳያል።

ከዚህ አልፎ መልካም ነገር ሲታሰብ ዐይናቸው የሚቀላ፣ ከጀርባ ወንጀልን ከማሰብ በስተቀር ሰላም፣ ቅንነትና ፍቅር እንዲያብብ የማያስቡ /Deluded/ የሆኑ ቡድኖች እንዳሉ ሊታወቅ ይገባል።

ማጠቃለያ

እንግዲህ “ እንኳን ከተወረወረ ፣ ከታሰበው የሚከልል አምላክ ክብር ይግባው” እያልኩ

የኢትዮጵያ ጉዞየን እያዘንኩ ሰርዣለሁ። የትኬቱን ምላሽና ታሳቢ ወጭየን ለተፈናቀለው

ወገኔ እንደሁልግዜው አበረክታለሁ። ውጭ ያለው ወገኔን ግን አምላክ ሆነ መልአክታን

በክንፋቸው ከልለው ይጠብቋቸው ዘንድ ፀሎቴ ነው። በየምትሄድበት ሁለ “ አይደርስንም

ተተሽ ይደርሳልን አስብ” እንዲሉ ጥንቃቄ እንዲኖራችሁ እመክራለሁ።

በተረፈ መንግስት በዚህ ላይ ጥንቃቆ እንደሚወስድ ሙሉ እምነት አለኝ። የወንጀሉን እሳቤ

ግን ግንዛቤ ውስጥ እንዲገባ እማፀናለሁ።

ተዘራ አሰጉ

እንግሊዝ- ሎንዶን

እትዮጵያና ልጆቿን አምላክ ይጠብቅ ። አሜን።

3 Comments

  1. አይዞን አምበሳው። ወያኔ በሰዎች መንግድ ወጥመድ ማስቀመጥ ከጀመረ ቆዬ። ህዝባችን ለ 27 ዓመት ደንዝዞና በፍርፋሪ ለቃሚዎች ታፍኖ እንጂ ወያኔ በኢትዪጵያ ህዝብ ላይ የሰራው በደል እልፍ ነው። ይህ ተንኮላቸው ከከተማ እስከ ገጠር፤ ከስደተኛ ጣቢያ እስከ ትምህርት ተቋማት ከሻሂና ቡና ቤቶች እስከ ሰው ቤት የተዘረጋ የስለላና ሰውን በደቦ ሆኖ የማስፈራራት የመደባደብ እጅግ የጠለቀና ሰፊ መረብ ነው ያላቸው። በውጭ ሃገር በሥራ ስፍራ፤ በቤታቸው፤ በመንገድ ላይ የሚያስፈሯሯቸውና አልፎ ተርፎም የተደበደቡ ብዙዎች ናቸው። ከተንኮል ሌላ ምንም የሚያስቡትና የሚተነፍሱት ነገር የለም። አይ አልተረዳኝም የሚል ካለ በአፋርና በአማራ ያደረሱትን የመከራ ክምር ተመልክቶ መፍረድ ይችላል።
    እህቴ እናቴ ተደፍራለች በሚል የውሸት የወያኔ ጥሩንባ መነኩሴዎችን፤ እናቶችን፤ ህጻናትን በህብረት የደፈሩትና የገደሉት ወያኔዎች አረመኔ ለመሆናቸው አንድ ማሳያ ነው። ወንድ ልጅን አስቁሞ ሱሪውን አስወልቆ ከትግራይ ይዞ የመጣውን ቡትቶ አውልቆ የቀማውን ሱሪ ለብሶ ሰውን እርቃኑን የሚያባርር አለዚያም ተንበርከክ ብሎ በጥይት የሚደበድብ ይህ ነው የትግራይ ነጻ አውጪ ማለት። አሁን በአማራና በአፋር የሚያደርሱት መከራ በወልቃይትና በራያ ወያኔ በ 27 ዓመቱ ሲያደርስ የነበረውን መከራና ሰቆቃ ነው ሽዋ ድረስ ተሸክሞ የገባው። ልናስብ ይገባል። እነዚህ እብዶች ሮኬት ቢኖራቸው፤ ድሮኖች ቢኖራቸው በኢትዪጵያ ውስጥ የሚኖር አንድም ከተማ አይኖርም። የቀንድ ከብቶችን ተኩሶ የሚገል የትግራይ ወራሪ ሃይል ከሰው ባህሪ የወጡ በሰው ደም ዝንተ ዓለም ሲነግድ የኖሩ እብዶች ናቸው።
    በውጭ ሃገር አፍቃሪ ሃገር የሆኑ ድህረ ገጾችን በማፈን፤ የፈጠራ ወሬ በመንዛት (shaming and blaming) እያራቡ ሰውን ስቀቀን ውስጥ በመክተት፤ ነጮችን የተዛባና ከእውነት የራቁ ወሬዎችን በማቀበልና እየከፈሉ ውሸትን በማሰራጨት ቀዳሚ የላቸውም። የተሳሳቱት ለብቻቸው አይደለም። ሌላውንም ዓለም ጭምር ነው የሚያሳስቱት። አውቃለሁ እንደ አሜሪካ ያለው አይኑን በጨው ታጥቦ ሃገርን ለማፈራረስ እየተራወጡ እንደሆነ። የወያኔ ታሪክ የማፊያ ታሪክ ነው። በሃውዜን የራሱን ህዝብ አስጨርሶ በደርግ ላይ በማላከክ ኡኡታ እንዳሰማው ሁሉ ዛሬም ከCNN ና መሰል ጡሩንባ ነፊዎች ጋር በመሆን አስከሬን ወንዝ ላይ በመጣል እውነቱን በማማታት ላይ ይገኛል። ስለሆነም ለአንተ ስልክ ተደውሎ እንዲህ እና እንዲያ መባሉ የሚያስገርም አይደለም። ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እንዴት ባለ የተቀናበረ ሴራ ሞታቸውን እንዳፋጠኑት ሰው እንዴት መረዳት ያቅተዋል? ህዝባችን ግን ዛሬም ደንዝዟል። ከቀን ህልማችን መንቃት አለብን። መተባበር፤ የሃሳብ ልዪነትን ወደኋላ ጥሎ የጋራ ጠላትን መፋለም አማራጭ የማይገኝለት እርምጃ ነው። አሁን ወያኔ ሽዋ ድረስ ገብቶ እንዲያፈራርስ መንገድ ያመቻቹለት ተመልሰው እንገንባ እንዲህ እናርግ ሲሉ መስማት ያማል። መጀመሪያ መቼ የወያኔ የውስጥ አዋጊዎችና ወያኔዎች ዳግም እንዳይነሱ የሚያደርጉ ድርጊቶች ነጻ በወጡባቸው ቦታዎች ላይ ተቋቋሙና? የኢትዮጵያ ወታደር ይታደገኛል ብሎ ማመን ጭራሽ አይችልም። ቀዪን፤ ምድሩን ሃገሩን ገበሬውና ወጣቱ እንዲጠብቅ ሰልጥኖ መታጠቅ አለበት። ያለበለዚያ ወያኔ ተመልሶ መጥቶ እንደገና ዘረፋና ግድያ እንደሚፈጽም የታወቀ ነው። አንድ የተማረከ የወያኔ ወታደር በአንገቱ ላይ መስቀል ያላት የወርቅ ሃብል አድርጎ ይታያል። ወልድያ ላይ የቀማት ልጅ እሱን ስታይ እሱ ነው እኔን ደፍሮ የቀማኝ እያለች ስትጮህ ሰው ዝም በይ አሁን የማይገኝ ነገር ምን ታወሪያለሽ እንዳላት በስፍራው የነበረ ሰው አጫውቶኛል። ማጽናናት፤ በእዝ ሰንሰለት ፎቶውን አስተላልፎ ልጅ ተጠያቂ እንዲሆን ከማድረግ ይልቅ ተበዳይን ዝም በይ የምንል ከወያኔ አንሻልም። አንድ መጽሃፍ ሳነብ እንዲህ ይላል ” We should fear equally the fogs and the clears” ትልቅ ነጥብ ነው። አሁን ጦርነቱ አለቀ፤ ውጊያው ቆመ የሚሉ ሁሉ የወያኔን ሴራና ሃገር ሽያጭነት ያልገባቸው ናቸው። የሃገራችን መከራ ብዙ ነው። በቅርቡ አቶ ልደቱ አያሌው ስለ ሽግግር መንግስት ሲያወራ መስማት እንዴት ያማል? በቃለ መጠየቁ ውስጥ (ለነገሩ ራሱ ብቻ ነው የለፈለፈው) አንድም ቦታ ላይ ወያኔ ስላደረሰው መከራና ዝርፊያ አንዳች ነገር አልተነፈሰም። ግን ልክ እንደ ጌታቸው ረዳ ዶ/ር አብይ ይህን ሰርቶ ያን ብሎ በኢትዮጵያ ሰላም አይኖርም፤ ኢትዮጵያ አስጊ ሁኔታ ላይ ናት እያለ ሲያላዝን እሱ መቼ ለእኛ ጠፋን ግን ወያኔያዊ አሜሪካዊ ጥምረት ያለው ሴራ ውስጥ እንደገባ በቀላሉ መረዳት ይቻላል። የአማራና የአፋር ህዝብ ነቃ፤ ቆፍጠን በማለት የዳግም የወያኔን ወረራ ለመፋለም ዝግጅት እስካላረጋችሁ ድረስ መጠቃታችሁ የማይቀር መሆኑን ከአሁኑ እወቁት። ወያኔ የበዳይ ተበቃይ ነው። አሁን የአሜሪካ የአፍሪቃ ጉዳዪች ሃላፊ በምስራቅ አፍሪቃ የሚመላለሰው ለአህጉሯ አስቦ አይደለም። በኢትዮጵያ የመንግስት ለውጥ ለማድረግ ያደረጉት ሴራ ባለመሳካቱ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ለማስፈራራት እንጂ። ካልፉ ታሪኮች መማር አለብን። ለምሳሌ ፓናማን እንውሰድ እውቁና በህዝብ ተወዳጅ የሆነው General Omar Torrijos ማን ገደለው? ለምንስ ተገደለ ከሞተስ በህዋላ የተካው Manuel Antonio Noriega በዚህ ጀግና ሞት ድርሻው ምን ነበር? ከአመታት በህዋላስ እጅን ታስሮ ወደ እስርቤት ተግዞ በዚያው የሞተው ይህ ጄኔራል የሰራው ነገር ጸጽቶት ይሆን? ሴራው አሁን በይፋ ወጥቶ ሁሉ እያነበበውና እውቁ የኢኮኖሚ ሰላይ የነበረው John john Perkins በላቲን አሜሪካ እየተዘዋወረ ባደረጋቸው ስብሰባዎችና በጻፋቸው መጽሃፍቶች ላይ ግድያው በአሜሪካው የስለላ መረብ እንደተከናወነ ተናግሯል/ጽፏል። አሁንም የአፍሪቃ መሪዎች ጠንቀቅ ማለት ነው። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ፓሊሲ አሁንም የሚተገበረው በቀዝቃዛው ጦርነት በተቀመረው ህሳቤ ነው። ለዚህ ነው በተደጋጋሚ ኬኒያ ሱዳን ግብጽ ሌሎችም ሃገሮች በመሄድ መሪዎችን የሚያስፈራሩትና የግል ጫና እንዲያደርጉ መሪዎችን የሚያስጠነቅቁት። ነጩ ዓለም ለጥቁሩ ዓለም ጭራሽ አይገደውም። ሊገባን ይገባል? መንቃትና ብልሃተኞች መሆን አለብን። ወያኔ የአረብና የነጮች ተላላኪና ጉዳይ አስፈጻሚ ነው። ለዛ ነው ስንት ሰዎች ያስጨረሱትን የወያኔ መሪዎች ከለላ ሰጥተው አሁንም ባሉበት ቦታ ሆነው ሌሎች እንዲሞቱ ትዕዛዝና ድጋፍ የሚያረጉት። በቃኝ!

  2. ጸሀፊ ህሳብህን ግልጽ አድርገህ አልጻፍከውም ስዎቹ ትግሬዎች ከሆኑ ጁንታ ኦሮሞዎች ክሆኑ ደግሞ ሸኔ ብሎ መጻፍ ይቻልም ነበር አንተም ህዝባዊ ስብሰባው በነዚህ ሀይሎች ከተያዘም ወደሗላ ማፈግፈግ ይገባህ ነበር ካቅምህ በላይ ክሆነ ማለቴ ነው። መቅረትህ በዚህ ላይ ሌላ ነገር ነው ብቻ ግልጽ ያልሆኑ ሁኔታዎች አሉ። እንደሰማነው ለንደን ክጊዜው ጋር አብረው የሚለወጡ ጩሉሌዎች ህዝባዊ ንቅናቄውን ለማምከን ካርበኛ በላይ አርበኛ የሚሆኑ ስላሉ አምባሳደሩ እነዚህን ጩሉሌዎች የሚያጠልበት ብልሃት ካልፈጠረ ቆሎ በሚቆላ ምላሳቸው ሀገር ወዳዱን ዜጋ ከኤምባሳዊ ያርቁታል የሚል ስጋት አለኝ እኛ ዘንድ ግን አይሞከሩትም።፡ባለፈው የትግሬዎች ስብሰባ ላይ ጋሻ ጃግሬ ሁኖ ሰው ሲደባደብ የነበረ ዛሬ ዋና አስተናባሪ ሁኖ ቪዲዮው ላይ ያየሁት መሰለኝ። ለማንኛዉም ልብህ ክሀገርህ አይራቅ ሁሉንም ለመንግስት መተው ጥሩ አይደለም ባንዳ ሰታይ ባንዳ ነዉ እንዳይመጣ ብለህ ዛሬ ብትጀምር ነገ ክባነዳ የጸዳ ሰብሰባ ይካሄዳል። የኢሳት አስተባባሪ ከነበሩት ዋናዉ ሰው ኤርትራዊ ነበር አሉ ብዙ ስራ የሰራ ስራ እንበለው እንጅ ለማንኛዉም አሁን የለም መሰል። አሁን ትግሬዎች እንዲህ ወርደው ይንኮታኮታሉ ብሎ የጠረጠረ ግለሰብ ይኖራል? ስራው ረቂቅ ነው መቼም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.