የመግለጫዎቹን ሙሉ ቃል በአማርኛ አዳመጥኩት!!! – ወንድይራድ ሀይለገብርኤል

ታደሰ ወረደም ደብረፅዮንም የሰጡት የሰሞኑ መግለጫ “”ዕቅድ 2″” በማለት ያስቀመጡትን የጥፋት ተልዕኮ ያስተጋባል።

ዕቅድ 2— “”ወልቃይትን ተቆጣጥረን ከሱዳን ጋር የምንገናኝበትን ኮሪዶር ማስከፈት ካልቻልን ባጭር ጊዜ ውስጥ ከምድረ ገፅ እንጠፋለን”” የተሰኘ አስደንጋጭ ግምገማ ከወሰዱ በኋላ የደረሱበት ድምዳሜ ነው።

“”በዕቅድ አንድ”” ሚሌን በመቆጣጠር ጁቡቲ ወደብ ላይ በአሜሪካኖቹ ተዘጋጅቶ ይጠብቃቸው የነበረውን ድሮኖችን ጨምሮ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የመቀበል ህልማቸው ረገፈና- ነው ወደ “”ዕቅድ ሁለት”” የተመለሱት።

 

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከአሜሪካኖቹ ጋር ሊያደርጉት የነበረው የዱላ ቅብብል ሩጫ እጃቸው ባቲ ላይ ተቆርጦ ቀረና ውሀ በላው።

አሁን ደግሞ አሜሪካኖቹ በሱዳን ጀርባ ተሰልፈው ለወራሪው ሀይል የጥፋት ተልዕኮ ክንድ ለመሆን በዕቅድ ሁለት ሊሞክሩ ነው።

ሊሳካ አይችልም። እንደ እውነቱ ከሆነ መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተን ግምገማ ስንወስድ ለወራሪው ሀይል ሁመራን ከመያዝ ይልቅ አስመራን መያዝ ይቀላል። ሁመራ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የኤርትራም የህልውና ማረጋገጫ የድነት ባፈር ዞን ነች።

ቢሆንም ግን መሰራት ከሚገባቸው ቀዳሚ ጉዳዮች አንዱ በመቶ ሽዎች የሚገመተውን የጎንደር አማራ የፋኖ እና ህዝባዊ ሰራዊት ሀይል በአንድ የዕዝ ሰንሰለት ስር እንዲደራጅ ማድረግ ነው።

በአንድ ግንባር ብቻ እስከ 20 የሚደርሱ የፋኖ አደረጃጀቶች መኖራቸው ለብዙ መሰናክሎች እና አደጋዎች ሊያጋልጡ እንደሚችሉ ከወዲሁ ተረድተው የጎንደር፡ ደብረታቦርና ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ከታዋቂና አዋቂ ወገኖች ጋር ተባብረው ለፋኖ መልክና ስርዓት ያለው ተቋማዊ አደረጃጀት ለመፍጠር ቢሞክሩ መልካም ይሆናል። ተቋማዊ በሆነ አግባብ በስርዓት ያልተያዘ አፈሙዝ ይባርቃል።

ይህንን ማድረግ ከተቻለ ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት ህወሀትን አፈር ለማስጋጥ አርማጭሆ በቂ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰበር የደስታ ዜና 7ግዜ ጠርምሶnየወጣ ጀግና - እንኳንም አተረፈህ

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!!

https://amharic.zehabesha.com/biden-has-abandoned-tplf-but-is-still-dreaming-of-invading-ethiopia-through-sudan/

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share