አስቸኳይ ጥቆማ ለኢትዮጵያ መንግስትና ኢትዮ-ቴሌኮም (እውነቱ ቢሆን)

telecomጉዳዩ፦ በወያኔ ተይዘው በነበሩ የአፋርና የአማራ ክልሎች ስለተዘረፉ በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠሩ የእጅ ስልኮች በኢትዮ-ቴሌኮም እንደአዲስ በወያኔና ተባባሪወቹ እየተመዘገቡ በስራ ላይ መዋላቸውን ስለማገድ ፦

ወደጉዳዬ ከመግባቴ በፊት አንባቢወች ሆይ እባካችሁ ለተሸናፊው የትግራይ ወያኔ መንጋ ሰራዊት “አልበንናዶን” ለአሸናፊው የኢትዮጵያ  ጦር ደግሞ የአብነት አጎናፍርን ”አያውቁንም ” ዘፈኖችን አሰሙልኝ፡፡ በተለይ የአብነት “አያውቁንም ”የተሰኘው ዘፈን የውጮቹን የወያኔ አጨብጫቢወች በሚገባ  ያስፋራልና አሰሟቸው፡፡

አሁን ወደተነሳሁበት ጉዳይ ልግባ፡፡

የወያኔ ወራሪ ሰራዊት በአማራና አፋር ክልሎች በየደረሱባቸው ከተሞች ከምግብ ቀጥሎ ህዝቡን አምጡ እያሉ የሚያስጨንቁት የእጅ ስልኮችን ነው፡፡ በዚሁ ዘረፋም በብዙ መቶ ሽህወች ምናልባትም ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስልኮችን ዘርፈዋል፡፡ በዚህ መልክ ከዘረፏቸው ስልኮች ውስጥ በሚገርም ሁኔታ የተውሰኑት የእጅ ስልኮች በሽያጭም በሉት በሌላ መንገድ በአፋጣኝ ቅብብሎሽ በአሁኑ ሰአት አዲስ አበባ ገብተው በወያኔ አባላትና የህወሀት ደጋፊወች በሆኑ የትግራይ ተወላጆች እጅ ተይዘው አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡ የሚገርመው ካለው ጥብቅ የደህንነት አሰራርና ፍተሻ አንጻር በዚህ ፍጥነት ስልኮቹ አዲስ አበባ መግባታቸው ሲሆን ይባስ ብሎም በኢትዮ-ቴሌኮም በኩል ባለቤቶች ላልሆኑ ሰወች ስልኮቹ እንደ አዲስ ተመዝግበውና የመጠቀሚያ ስልክ ቁጥሮች ተስጥቷቸው በአገልግሎት ላይ መዋላቸው ነው፡

በቴሌ በኩል ባለው ቴክኒካዊ አሰራር እነዚህን ስልኮች ከዘራፊወቹ በግዥ፣ በስጦታ፣ በለውጥም ሆነ በሌላ ማናቸውም መንገድ ወደ እጃቸው ያስገቡ ሰወች ስልኮቹን በአዲስ አበባም ሆነ በአገሪቱ ውስጥ የትም ቦታ እንዳይጠቀሙባቸው ማድረግ አስፈላጊና ወቅታዊ ሲሆን አፈጻጸሙም በጣም ቀላል ነው፡፡ምክንያቱም እነዚህን የተዘረፉ ስልኮች ጨምሮ በአለም ላይ ሁሉም ስልኮች ገና ሲመረቱ ልዩ የሆኑ ባለ15 አሀዞች የየራሳቸው መለያ ቁጥሮችን የያዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ስልክን ከስልክ ለመለየት የሚጠቅሙት በስልኮቹ አምራቾቹ የሚሰጡ መለያወች ሲሆኑ በአህጽሮት አጠራራቸውም I.M.E.I – International Mobile Equipment Identity ተብለው ይታወቃሉ፡፡ የየግላቸው መለያ ቁጥሮች ያላቸውን እነዚህን ስልኮች ኢትዮ-ቴሌኮም በመለያ ቁጥሮቻቸው ከመረጃ ቋቱ በማውጣትና ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ምሳሌ፦በዚሁ ማጣሪያ አማካይነት መጀመሪያ ላይ በቴሌ መረጃ ቋት ውስጥ ተሰጥቷቸው የነበሩት የስልክ ቁጥሮች ለእነማን እንደነበረ፣ መቼ ቴሌ ውስጥ ተመዝግበው ጥቅም ላይ ዉለው እንደነበረ (የቴሌ ዞን ፣ክልል፣ከተማ ወዘተ መለያ በማድረግ)፣መጀመሪያ ላይ የየስልኮቹ ባለቤቶች ለነበሩት (የአሁኑ ተዘራፊዎች ማለት ነው) መቼ፣ የትና የትኛው የመገልገያ ስልክ ቁጥሮችስ ተሰጥተዋቸው እንደነበረ …. ወዘተ ማጣራትና የመሳሰሉ ብዙ ማሳያወችን አገናዝቦ ማወቅ ይቻላል፡፡

እንደ መነሻ ከኢትዮ-ቴሌኮም መረጃ ቋት በተለይ ክሰኔ ወር 2013 ጀምሮ በዚህ መልክ ጥያቄ ውስጥ የሚገቡ ስልኮችን የተዘረፉ መሆን አለመሆናቸውን ለማጣራት የቴሌ የስራ ዞኖችንና ወቅቶችን መነሻ በማድረግ ቴሌ ስራውን መጀመር ይችላል፡፡ ኢትዮ-ቴሌኮም ይህንን እንዲያደርግ በመንግስትም መታዘዝ አለበት፡፡አለበለዚያ ከዘራፊ ወንጀለኞች መተባበር ማለት ስለሆነ በህግ ያስጠይቃል፡፡ ስለሆነም ኢትዮ-ቴሌኮም ከዘረፋው ጋር ተያይዞ እጅግ በጣም ብዙ ስልኮች ወደትግራይ ገና ተላልፈው አላለቁም፡፤ያኔ ምናልባትም እያንዳንዱ የመቀሌ ነዋሪ አምስት አምስትና ከዚያም በላይ የእጅ ስልክ ሊኖረው ይችል ይሆናል፡፡

ስልኮቹ አገግሎት እንዳይሰጡ ሲታገድ በተለይ አሁን ላይ ከትግራይ ውጭ ባሉ ከተሞች የሚገኙ አንዳንድ የስልኮቹ የአሁን ባለቤት ነን ባዮች በተለይም ከግለሰብ ገዝተናቸው ነው ባዮች ወደ ኢትዮ-ቴሌኮም ለአቤቱታ እንደሚመጡ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ለዚህም ኢትዮ-ቴሌኮም እነዚህ ስልኮች በጦርነቱ ከእነዚህ አካባቢወች የተዘረፉ መሆናቸውን በቴክኒካል አሰራሩ ማረጋገጡን በማስረዳት እነዚህ መሰሎቹ ስልኮች በመላ አገሪቱ ውስጥ የቴሌ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ አለበት፡፡ያኔ ሌላው ቀርቶ ሊጥ ሲሰርቅ የነበረው የወያኔ መንጋ ስልኮቹን ሰርቆ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይጠቀምባቸው መደረጉን ሲረዳ ቢፈልግ ገዢ ካገኘ ሱዳን ወይንም ግብጽ ወስዶ ሊሸጣቸው ይችላል፡፡አለበለዚያም በመስፍን ኢንጂነሪንግ አቅልጦ ጠመንጃ ይስራና ወደፊት ከፋኖ ጋር ይዋጋባቸው፡፡

ለነገሩ ከእንግዲህ እነዚህ የምድር ጉዶች ከበቀሉበት አካባቢ ማለትም ከትግራይ ጋር ሊኖር የሚችለው ጉርብትና  ምን ሊመስል እንደሚችል መገመት እጅግ አዳጋች ነው፡፤ ተስፋ የምናደርገው የወልቃይትና ራያ ለም የአማራ መሬቶችን ቅዠት ትተው ተገንጥለው ሄደው ይሞክሩታል፤ ይሄውም እሰየው ነው ብለን  ነው የምንጠብቀው፡፤ ይህም ሆነ አልሆነ አማራው መጥፎ ጎረቤትን በሩቅ እንዲሉ ከኮረም እስከ ሁመራ አጥር ማጠር ሊያስፈልገው ይችል ይሆናል፡፤ ምክንያቱም ወራሪወቹ የወያኔ መንጋወች በአማራ ህዝብ ላይ የሰሯቸው  እጅግ እንሰሳዊና አረመኔያዊ ድርጊቶች ይህንንም ከማስባልና ከማሰብ አልፎ ሄዷልና፡፡ ከህሊና በላይ እጅግ ሰቅጣጭ ድርጊቶች በአማራ ሚስቶች፣ እናቶች፣ እህቶች፣ ወጣቶች …  ህዝብ ላይ ተፈጽሟል፡፤ በወረራው ሰበብ የተሰራው ስራ መቼም ቢሆን መቼ ሊረሳ የማይችል የዘለአለም ጠባሳና የበቀል፣ የእልህና የቁጭት ስሜት በድፍን አማራ ህዝብ ልብና አእምሮ  ውስጥ ትቷል፡፡ ስለሆነም ከህንግዲህም ያልታሰበው ሊከሰት ስለሚችል ‘ከአጋም እንደተጠጋ ቁልቋል’ በድንበር ላይ ያለው አማራ በሙሉ ታጥቆ ሁልጊዜም ንቁና ዝግጁ መሆን አለበት፡፤ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የክልሉም ሆነ የፌደራሉ መንግስት  ከወያኔ ድምሰሳ ማግስት ጀምሮ አሁኑኑ ይህንን ህዝበ ከ-እስከ ማስታጠቅ ግድ ይላቸዋል፡፡

 

1 Comment

  1. የወያኔ ስብስብ በአለም ላይ በሌብነትና በውሸት ወደር የሌለው ድርጅት ነው፡፤ የእጅ ስልክ ይቅርና የእገሪቱን መርከብ የሰረቀ የባንዳወች ጥርቅም ነው፡፤ ምን መገለጫ እንድሚመጥነው አላውቅም፡፡ ሌባ፣ ምቀኛ ማፊያ፣ ባንዳ፣ ዱርዬ፣ ቀማኛ፣ ከንቱ፣ ቅዠታም ….ወዘተ የሚሉት መገለቻወችወይንም ሁሉም ተደምረው እርሱን አይገልጹትም፡፡ ያንሱበታል፡፤ እቡይ ድርጅት ነው፡፤
    አገሪቱንና የትግራይን ታላቅ ህዝብ ለዚህ ውርደት ዳርጓቸዋል፡፤ ራሱ በጫረው ጦርነት በመቶ ሽህወች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶችን አስጨርሷል፡፤ እርሱ ራሱም በአማራና አፋር ክልልሎች ውስጥ ገብቶና ከኦሮሙማ ጦር አዛዦች ጋር በገንዘብም በሴራም ተመሳጥሮ በብዙ አስር ሽህወች የሚቆጠሩ ንጹሀንን ራሱ ጨፍጭፏል፡፤ ይህ ትግራይንም ሆነ በወረራ ይዟቸው ከፍተና ውድመት የደረሰባቸውን ሁሉ ልማት እንድወድም አድርጎ ብዙ አመት ወድኋላ መልሷቸዋል፡፤
    አገሪቱን ለማፍረስ በውጭእንደ አህያ ከሚጭኑት ከጠላቶቿ ጋር ሆኖ ከውስጥም ከቢጤወቹ ኦነጎች ጋር ሆኖ ብዙ ጥረት አድርጓል፡፡ ወያኔ በከሀዲነቱ አገሪቱንና ራሱ የበቀለበትን የትግራይ ህዝብ ለእንደዚህ አይነት ውርደት፣ ጉዳትና ስቃይ መዳረጉ፣ ለወያኔ ምን አመጣለት? ከንግዲህ በኋላስ ምን ያመጣለታል?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.