የጋሸናና የሸዋሮቢት ሁኔታ – ግርማ ካሳ

የሕወሃትና የኦነግ መሪዎች እጅግ በጣም ጨካኖች ናቸው። እነ ጀነራል ጻድቃን እድሚያቸው ከስድሳ አምስት በላይ ላይ ነው። ወደ ሰባውም ሊጠጉ ይችላሉ። ልጆቻቸውን ከሕዝብ በተዘረፈ ገንዘብ፣ ወደ ውጭ በመላክ፣ በጥሩ ትምህርት ቤቶች እያስተማሩ ፣ እያስመረቁ ደህና ኑሮ እንዲኖሩ ያደረጉ ናቸው። ነገር ግን የድሃው የትግራይ ወጣትን ሕይወት፣ የትንኝ ሕይወት ይመስል፣ አላስፈላጊና ውጤት አልባ ባልሆነ ጦርነት እየማገዱ ነው። በነዚህ ልጆች ሕይወት፣ እንደፈለጉ ካርታ፣ ቁማር እየተጫወቱ ነው።

260418923 10226313089804380 3670546171788065334 nዶር አብይ አህመድ ከትግራይ የወጣነው የትግራይ ገበሬ እንዲያርስ፣ የትግራይ ህዝብ የጥሞና ጊዜ እንዲኖረው ነው በሚል የተኩስ አቁም አውጆ ነበር። እነ ጀነራል ጻድቃን ደግሞ መከላከያ ከትግራይ የወጣው ተሸንፎ ይላሉ። ዶር አብይ ትክክል ይሁን እነ ጀነራል ጻድቃን፣ በዚህ ይሁን በዚያ፣ ትግራይ ሙሉ ለሙሉ በእጃቸው ሆናለች። ያን አጋጣሚ በመጠቀም ለሕዝብ የሚጠቅም ስራ መስራት ሲገባቸው፣ በበቀልና በጥላቻ ተሞልተው፣ የአማራንና የአፋር ክልልን በመውረር ጦረነቱን አስቀጠሉ። ይህ ውሳኔያቸው ፡

1ኛ በአማርና አፋር ክልል ብዙ ሰላማዊ ዜጎች ሕይወታቸው እንዲያልፍ፣ በመቶ ሺሆች እንዲፈናቀሉና ከፍተኛ ውድመት እንዲፈጠር አድርገዋል።

2ኛ ሕዝብንና አገርን ለመከላከል የተሰለፉ. ክብር የሚገባቸው ከትውልድ እስከ ትዉልድ የሚዘከሩ፣ ብዙ የወገን ጦር አባላት ሰማዕታት ሆነዋል።

3ኛ ምን እንኳን ለአሸባሪዎች የተሰለፉ ቢሆኑም፣ ኢትዮጵያዊያ የሆኑ፣ እጅግ በጣም ቀላል የማይባሉ፣ የትግራይ ወጣቶች እንዲሁም በተወሰነ መልኩ ለኦነግ የተሰለፉ የኦሮሞ ልጆች፣ እንደ ቅጠል ረግፈዋል።

4ኛ የአገር ኢኮኖሚ ዳሽቋል።

5ኛ በትግራይ በስቃይ፣ በረሃብና በችግር ላይ ያለው ከ4.5 ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ተጋሩዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታና የሰብአዊ ድጋፍ እንዳያገኙ ነገሮች ተወሳስበዋል።

የነዚህ ጸረ ህዝብና ጨካኝ ኃይሎችን መመከት ብቻ ሳይሆን በቶሎ መቆጣጠርና መደምሰስ ካልተቻለ የሕዝብ መከራ ይቀጥላል። የአገርም ሕልውና አደጋ ውስጥ ይገባል። ከዚህም የተነሳ ሕዝብ በነቂስ ራሱንና አገሩን ለማዳን ተንቀሳቅሷል። ህዝብን ማሸነፍ ስለማይቻል በተለያዩ ግንባሮች ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት የነዚህ ቡድኖች መጨረሻ መዳረሱን የሚያሳዩ ምልክቶችን እያየን ነው።

ጦርነት ከሚደረግባቸው እጅግ በጣም ወሳኝ ከሆኑት ከተሞች መካከል ስለሁለቱ አንዳንድ ወቅታዊ መረጃዎችን እንደሚከተለው ላቀብላችሁ፡

ጋሸና ማለት መቀሌ ማለት ነው ነበር ያሉት ሕወሃቶች የጋሸናን ቁልፍ ስትራቴጂካዊነት ለመግልጽ።

ለሁለት ወር የወገን ጦር ዝግጁ ሆኖ፣ ከጋሸና ጥቂት ኪሎሜትሮች በምትገኘዋ በአርቢት ትእዛዝ ሲጠብቅ ነበር።

የማጥቃት ዘመቻ ትእዛዝ ከተሰጠ በኋላ፣ ላለፉት ሁለት ቀናት ጋሸናን ለመያዝ ከፍተኛ ዉጊያ እየተደረገ ነበር። ወያኔ ከ20 ሺህ በላይ ታጣቂዎችን በዚያ እንዳሰማራች ነው የሚነገረው።

አንዳንድ ወገኖች ጋሸና ነጻ ወጣች እያሉ ሲናገሩ ይሰማሉ። እርግጥ ነው የወገን ጦር በካታ ምሽጎችን በመስበር ጋሸና ገብቷል። ሆኖም ገና ጋሸናን ሙሉ ለሙሉ ገና አልተቆጣጠረም።

ሌላ እጅግ በጣም ቁልፍ የሆነችዋና፣ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ወያኔና ኦነግ እያደረጉት ያለው ጦርነት ማዕከል የሆነችዋ የሸዋ ሮቢት ከተማም ነጻ ወጣት የሚል አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። ልክ እንደጋሸና የወገን ጦር ሸዋ ሮቢት ገብቷል። ሆኖም ግን ሸዋ ሮቢት ገና መሉ ለሙሉ ነጻ አላወጣችም።

በርካታ የኦነግና የወያኔ ታጣቂዎች በደብረ ሲና፣ ሸዋ ሮቢት፣ ሞላሌ. ሰላ ድንጋይ መዘዞና መሃል ሜዳ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በደብረሲናና በሸዋ ሮቢት መካከል ከሮቢት ቀረብ ብሎ አርማኒያ በሚባል ቦታ፣ ከደብረ ሲና ሽሽት ላይ ያሉ ወደ 70 የሚጠጉ የኦነግ ታጣቂዎች መገደላቸውን ወታደራዊ ምንጮቹን በመግለጽ ኢትይ251 ዘግቧል።

በአሁኑ ወቅት ኦነጎችና ሕወሃቶች ከሸዋ ሮቢት ወደ ሰንበቴ መስመር ወደ ጀኸዋ ሽሽት ላይ መሆናቸውም እየተሰማ ሲሆን፣ ከከሚሴ በስተሰሜን ከኮምቦቻ በስተደቡብ ባለችው የሃርቦ ከተማ መከላከያ ስለገባ፣ ከሸዋ ሮቢት የሸሹት እጅ ከመስጠት ውጭ ሌላ አማራጭ አይኖራቸውም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.