“ፋኖ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን እያርበደበደ ነው” የፋኖ ብርጌድ ምክትል አዛዥ ሻለቃ አራጋው እንዳለ

259557163 1685635908278063 3314049233801351470 nፋኖ በሁሉም ግንባሮች ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን እያርበደበደ፣ ጋራ ሸንተረሩን እንደ ቀትር እባብ እየተስፈነጠረበት ለጠላት እሳት ሆኖበታል፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያነጋገረው የአማራ ብሎም የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ፋኖ ሻለቃ አራጋው እንዳለ ለሀገሩ ሉዓላዊነትና ለሕዝቡ ነፃነት መታገል እድል እንደኾነ ተናግሯል። ስለኾነም ለሀገሩ ያለውን ፍቅር በተግባር ለመግለጽ በ1991 .ም የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል የሚጠበቅበትን ኹሉ በስኬታማነት ለመወጣት በቅቷል።

ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል በሥልጣን ዘመኑ በአማራ እንዲኹም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን አሥተዳደራዊ በደል፣ ማንነትን ለማሳጣት የሚያደርገው ጥረት፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል የመረረው ሻለቃ አራጋው በጥፋት ቡድኑ ላይ ጠንካራ ክንዱን ለማሳረፍ በ2008 .ም ፋኖ አርበኛ ሕዝባዊ ሠራዊት አባልና መስራች ለመኾን በቃ።

2008 .ም ጀምሮ በየአካባቢው በመዘዋወር በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰዉን ግፍ አጥብቀው ለመታገል ሲጓጉ የነበሩትን የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ማደራጀት፣ ማስተማርና ማሠልጠን ጀመረ። የአማራ መደራጀት የራስ ምታት የሚኾንበት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በ2009 .ም ሻለቃ አራጋውን በማሰር የተለያየ እንግልት ሲያደረስበት ቆየ። ከለውጡ በኋላ የተፈታው ሻለቃ አራጋው የትግሉን ሕይወት የበለጠ ለማቀጣጠል እድሉን አገኘ። የሱን አርአያ የሚከተሉ ሺህዎች ፋኖዎችን በማፍራት የአማራን ሕዝብ እምባ ለማበስም የበኩሉን ግዴታ ተወጣ፤ እየተወጣም ይገኛል።

በቅርቡ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ወረራ በፈጸመበት አካባቢ ፋኖ፣ የአካባቢው ሚሊሻና ኅብረተሰቡን በማስተባበር ጠላትን ክፉኛ በመቀጥቀጥ የራሳቸውን ሀገራዊ አስተዋጽዖ ማድረጋቸውን ሻለቃ አራጋው ተናግሯል። በዚኽም በተለይ ከጭና እስከ ቆላ ወገራ አጅሬ ድረስ ጠላት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ስለደረሰበት ዳግም የአካባቢው ስጋት እንዳይኾን መደረጉን ነው ሻለቃው የተናገረው።

በዚኽ ግንባር ብቻ ሳይኾን ፋኖ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ጎን በመሰለፍ ጠላትን በመደምሰስ ሂደት ላይ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን አስረድቷል። ፋኖ ከአኹን በፊት ባደረገው መራራ ትግል የጠላትን ምሽግ በመደረማመስ በርካታ የቡድን መሳሪያዎችን በመማረክ ለመንግሥት ማስረከቡን አስታውሷል።

የፋኖ ዓላማ የአባቶቹን ታሪክ በመድገም የሕዝብን ነፃነት ማስጠበቅ ነው። ይህን ለማድረግም ፋኖ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን እያርበደበደ ነውብሏል። ኾኖም አኹን ላይ ፋኖ ለሕዝብ ነፃነት እንደሚታገል ስለተረጋገጠ ሕዝቡም ኾነ መንግሥት ድጋፍ እያደረገላቸው እንደኾነ ጠቁሟል። እንደተለመደው ኹሉ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ፋኖ በግንባር እየተፋለ መሆኑን እና ድል እየተጎናጸፈ መሆኑን ተናግሯል፤ ሻለቃ አራጋው፡፡

ሻለቃው አኹንም ኹሉንም ብሔር ለባርነት ለመዳረግ እየጣረ ስለኾነ ኹሉም በአንድነት ተረባርቦ ሊያጠፋው ይገባል ብሏል። የሽብር ቡድኑ ለሕዝብ ቢያዝን ኖሮ ንጹሃንን አይገድልም፣ አያፈናቅልም፣ አይደፍርም፣ ሃብትና ንብረትን አያወድምም፣ አይዘርፍም ነበር ሲል ነው የአሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል የጥፋት ተልዕኮ ያስረዳው። ሁሉም ዘመቻው የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመረዳት አሸባሪው የትግራይን ወራሪ ኃይልን ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ

ባሕር ዳር፡ ሕዳር 15/2014 .(አሚኮ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.