የህልዉና እና ነፃነት ትግል ታሪካዊ ይዘት እና ምንነት !

የእናት አገር ኢትዮጵያን የግዛት አንድነት በመናድ ኢትዮጵያዊነትን በማሳከር(Historical Distortion ) ጠላተቿ የሰሯት የ21ኛዉ ክ/ዘመን አዲስ ዓለም ለማድረግ ሲኳትኑ ያሁኑ የመጨረሻዉ ቀዳሚ የጥፋት ምዕራፍ ነዉ፡፡

1983 .ም በፊት የነበረዉን ትተተን በዚሁ ዓመት ኢትዮጵያን በማጥፋት ታላቋን የትግራይ ትግሬ ሪፓፕሊክ ለማልማት ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን የጥፋት እና ክስመት የመጨረሻዉ መጀመሪያ የጥፋት ዕሳት የተለኮሰዉ ግንቦት ፳ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሶስት መሆኑን አለማወቅ ወይም መርሳት ራስን ከማታለል እና ከማዘናጋት ብርቱ ወጥመድ ከመጠለፍ አይለይም ፡፡

በኢትዮጵያ ከሽግግር መንግስት ምስረታ ፣ህገ መንግስት ማፅደቅ እና ፌደራል አስተዳደር ምስረታ ምክክር ላይ ኢትዮጵያዉያንን በተለይም ዓማራን መደለል፣ማግለል ፣ መበደል ፣ መግደል እና ማስገደል ሀሁ ……..ጅምር ያኔ እና ይህ ነዉ ፡፡

በተለያየ ጊዜ እና የአገሪቷ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በተለይም ዓማራ ማህበረሰብ በተፈጥሮ እና ሠዉ በመሆን ያላቸዉን የመኖር አንጡራ መብት /ህልዉና እና ነፃነት እንዲያጡ የማድረግ ሴራ በስፋት እና በይፋ ተከናዉኗል ፡፡

በመላዉ የአገሪቷ ክፍለ ሀገራት ዓማራን እና ኢትዮጵያ ማንነትን በማዛባት ታሪካዊ ይዘት እና ትዉፊት ለጥፋት ማዘጋጀት ይህን በድርጊት ማስኬድ ተጀምሮ አስካሁን ቀጥሏል፡፡

በሁሉም ክልሎች በሚባል ሁኔታ የዓማራን ማህበረሰብ ማክሰም ኢትዮጵያን ለማዉደም መግቢያ ፣መንደርደርደሪያ እና መሻገሪያ መሆኑን በማመን በአርባ ገጉ፣ በሀረር፣ በጉራ ፈረዳ ፣ በሜጢ፣ በወለጋ ፣ መተከል…. መፃተኛ እና ስደተኛ ብሎ ማሳደድ እና መግደል የሠባዊ መብት አስኳል በህይወት የመኖር / ህልዉና እና በነፃነት ሠዉ የመሆን መብት በይፋ የተገሰሰዉ ያን ጊዜ ጀምሮ አስካሁን የቀጠለዉ የህልዉና እና ነፃነት ጉዳይ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከህወሓት በኋላ:ለተጋሩ ብቻ (አብርሃም ደስታ –ከመቀሌ)

የዓማራ ህዝብ እና የኢትዮጵያን መፃኢ የህልዉና እና ነፃነት ጉዳይ ያሳሰባቸዉ ኢትዮጵያዉያን እና ጠበብት የህልዉና እና ነፃነት ጥያቄ ቀርቧል፡፡

በቅርቡም በሁለት ሽ አስራ ሶስት ዓ.. በመላዉ የዓማራ ክልል በነቂስ የተደረገዉ ህዝባዊ ብሶት እና በህይዎት የመኖር እና ራስን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብት ለማስከበር መደራጀት እና መዘጋጀት የህልዉና እና የነፃነት ጥያቄ ነበር ፡፡

በአፀፋዉ ጥያቄ የቀረበለት እና በባለቤትነት ሊቀበለዉ እና ሊያስተናግድ የሚገባዉ የመንግስት አካል በጊዜዉ ያሳሰበዉ የህዝብ እና አገር ህልዉና ሳይሆን የግል እና የቡድን ጥቅም ነበር ፡፡

ከዚህ በፊት ሆነ በኌላ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ኢትዮጵያን እና ዜገቿን ጠል ቅስቀሳ እና ወቀሳ (ፕሮፖጋንዳ) የሚያራምዱ ሁሉ በኢትዮጵያዉያን ላይ በግናባር ቀደም በዓማራ በሁሉም የዓማራ ክልል እና በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች ያቀረቧቸዉ እሮረዎች፣ አቤቱታዎች እና አገራዊ ፋይዳ ያላቸዉ ጥቆማወች ሰሚ ይጡ እንጂ የህልዉና እና ነጻነት ትግል ፋና ወጊዎች ነበሩ ናቸዉ ፡፡

የወልቃይት የማንነት እና የድንበር ጥያቄ ፣ የመተከል መካለል እና የዜጎች ደመከል ፣ የተለያዩ በማንነትሞት እና ስደት እንዲያስተናግዱ የተደረጉት ያልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል ህልዉና እና ነፃነት የማስከበር እና የማንበር እንጂ የከሳ እና የመብት ጉዳይ አልነበረም ፤አይደለም ፡፡

የህልዉና እና በራስ አገር በነፃነት የመኖር ፤አለመኖር ግብግብ ዛሬም በሁሉም አካባቢ በተለይም በወለጋ የሆነዉ እና እየሆነ ያለዉ ከህልዉና እና ነፃነት ማዕቀፍ ዉጭ የት ሊመደብ ይችላል፡፡

ህልዉና እና ነፃነት በተፈጥሮ የሚገኝ በህይዎት የመኖር ሠዉ የመሆን አንጡራ ሀብት እና ፀጋ ከሆነ ለህልዉና እና ነፃነት የሚደረገዉ ትግል እና ተጋድሎ ስረ መሰረት እና ምንጭ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከማጥላላት እና ከማጥፋት ሲጀምር የግለሰብ ህልዉና ነፃነት ከማስከበር የሚነሳ ትግል መሆን አለበት ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በዘንድው ሃጅ ጸሎት የተወገዱት ሰው ሰራሽ አደጋዎች !

የህልዉና ትግልም እና አድማሱ ከግለሰብ እና ቡድን ጥቅም እና የነዚህ ማስከበሪያ መሳሪያዎች ( ፖለቲካ ፣ ህግ…….) በላይ የአገር እና የሠዉ ልጂ ተፈጥሯዊ ሠባዊ መብት ስለሚቀድም ሁለንተናዊ እና ልባዊ መሆን አለበት ፡፡

የአገርን እና ህዝብን ህልዉና ከግለሰብ ነፃነት ጋር ለማረጋገጥ ለጥላቻ ዘመቻ ፣ለዜጎች እና ሠባዊ ፍጡር መሞቻ መንስዔ የሞት ግድግዳዎች መናድ አለባቸዉ ፡፡

የጥላቻ መጋረጃ ሳይቀደድ ስለ ህልዉና እና የዜጎች ነጻነት መስበክም የአዞ ዕንባ ከመሆን እና ከምር እና በምር ስለ ራሳቸዉ ፣ ህዝባቸዉ እና አገራቸዉ ህልዉና እና ነፃነት ከትናንት አስከ ዛሬ የሚደክሙትን ዕዉነተኛ የቁርጥ ቀን የህዝብ ልጆች ተምሳሌታዊ ተጋድሎ ግለት ላይ ዉኃ እንደመቸለስ እንዳይሆን ሊታወቅ ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እና ጥቂት የቁርጥ ቀን ልጆች ከጥንት አስካሁን ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለዜጎች ህልዉና በተግባር አንድኛ ህይዎታቸዉን አስከ መስጠት ቤዛ የሆኑት እምቢ ለህልዉና፤ ዕምቢ ለነጻፃነት በማለት ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያን በማጥፋት ታላቋን ትግራይ መመስረት እና ማልማት ዛሬ የሚነገር ሳይሆን ጥንት የነበር መሆኑን በመገንዘብ በምንም ነገር መዘናጋት እና ጊዜ ማጥፋት ተያይዞ ሞት ነዉ ፡፡

የዛረዎች የዉስጥ እና ዉጭ ከቅርብ እና ሩቅ ሆነዉ ኢትዮጵያን ማጥፋት ወይም ሞት ለሚሉት እና ቆርጠዉ ለተነሱት ዛሬ መዳረሻቸዉ እንጂ መነሻቸዉ አለመሆኑን የጋራ የጥፋት ህብረት እና ደባ ገምደዉ “ኢትዮጵያዉያንን ማጥፋት የሚያስችል ማንኛዉም የጥፋት እና ሞት አማራጭ አስከ ሲዖል ” ያሉትን አለመረዳት ወይም መዘንጋት ከበድንነት ዉጭ ሌላ ሊባል አይችልም ፡፡

ለኢትዮጵያዉያን እና አገራችን ሞት በዕብሪት ለሚራኮቱት ሁሉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት “ከሳጥናኤል ጋር አስከ ሲኦል ” ምኞት በድንገት እና በስሜት አለመሆኑን ተገንዝበን መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ስደት ፣ ዕንግልት እና ሞት ቀንበር ለተጫነብህ ዓማራ ኢትዮጵያዊ ነኝ የምትል ይህ አስከ ሲዖል …የጥፋት ትብብር ያንተን ህልዉና እና ነፃነት ለመግደል የተደረገ የመጨረሻዉ የአጥፍቶ መጥፋት የጥፋት ደዎል መሆኑን ዕወቅ ፤ አሳዉቅ ፣ተጠንቅቅ ፣ታጠቅ ራስህን ፣ አገርህን እና ዳር ድንበርህን ጠብቅ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአቶ ተኮላ ጽሁፍ ትችት ወይንስ ሽሙጥ ከሳᎀኤል ሽፈራው/ዳላስ

በዕዉቀት እና በብቃት ከመተባበር እና በዓላማ ከመኖር ዉጭ ያንተን ህልዉና እና ነጻነት እንዲያስጠብቅ ከማንም ምንም አጠበቅ ፡፡

የሆነዉ እና እየሆነ ያለዉ ሆነ የሚሆነዉ ሁሉ ድንገተኛ ደራሽ ዉኃ አድርጎ መቁጠር እና መደናቆር ጊዜ በመግደል የመከራ እና በደል ጊዜ በማራዘም አማሟትን መምረጥ ይሆናል ፡፡

የነፃነት እና ህልዉና ቀዉስ ጥያቄ እና መልስ ታሪካዊ ሂደት ጅምር ዛሬ አለመሆኑን ተረድተን በዚህ ላይ የምናጠፋዉ ጊዜ ለጥፋት እና ሞት መስዋዕት እንደመሆን ተረድተን አማራጭ ወደ ሌለዉ የመጨረሻ መፍትሄ የነፃነት ተጋድሎ ዉሎ ላይ መተባበር እና መኖር ላይ ማትኮር ይገባል፡፡

ማላጂ

አንድነት ኃይል ነዉ ”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share