፲፩ኛ ስዓት፡ ዕድል እና ገደል= ገድል + ድል

አበዉ እንደሚሉት የጨዉ ክምር ሲናድ ብልህ ያለቅሳል ፤ሞኝ ይስቃል እንዲሉ ዛሬ የክፍለ ዘመኑ አገር የማፍረስ ፤ህዝብ የማፍለስ የጠላት ሴራ በኢትዮጵያ እና ነባር ህዝቦች ላይ የተጠመደዉ የጥፋት ወጥመድ ፲፩ኛ ሠኣትላይ ሆኖ ያለዉን የነጻነት እና ህልዉና ተጋድሎ እና ትንቅንቅ በድንገት እንደተፈጠረ እና የተወሰኑ ኢትዮጵያዉያን ( ዓማራ ፣ አፋር) ዐድርጎ የመመልከት አባዜ እና አዚም የተጫነዉ በቁጥር ትንሽ ሆኖ አይገመትም ፡፡

ያን ያህል ባይሆንም ለአንድ ክ/ዘመን ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራ ቀድሞ የገባቻዉ ጥቂት ኢትዮጵጵያዉያን ለአለፉት ረጅም የጥልመት እና ሞት የመከራ ዓመታት ሞቶ ላለማለፍ ኖረዉ ለህዝብ እና ለአገር ነጻነት እና ሉዓላዊነት ኑረዉ ያለፉ በበጎ ሥራቸዉ እና በተጋድሏቸዉ ትዉልድ የሚዘክራቸዉ ዕልፍ አዕላፍ ጀግኖች ያኔ የጨዉ ክምር ሲናድ የምር አልቅሰዉ እና አይቀሬዉን መራር የነፃነት እና ብሄራዊ አርነት ተጋድሎ አድርገዉ ገድል ሠርተዉ አልፈዋል ፡፡

ዛሬም በ፲፩ ኛዉ ወሳኝ የህልዉና ፣ ነጻነት እና ሉዓላዊነት ተጋድሎ ሠዓት ከ፴ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ጣራ ሲናድ እና ምሶዉ ሲነድ የሠቁ ዛሬም በዚህ በመጨረሻዉ የሞት ሽረት ትግል ሠዓት ቢኖሩ የሚጠበቅ ሲሆን የቀደሙት የቁርጥ ቀን ልጆች ታሪክ በአብሪ ታሪክ ለማደስ እና ለማንገስ ዐሁን ላይ በታሪክ እና ጊዜ አጋጣሚ የሚገኝ ዕድል በገደል እና ድል ለማድመቅ ከፍተኛዉን ተጋድሎ በህብረት እና አንድነት እያከናወኑ ይገኛሉ ፡፡

ሆኖም በጎ አጋጣሚ( ዕድል) ገደል መስሎ የሚታያቸዉ የኢትዮጵያ ጥንተ ባላንጣዎች ከዉጭም ፤ ከዉስጥም ፤ ከሩቅ እና ቅርብ ፣ ከጥንት አስከ ጥዋት ኢትዮጵያ የምትባል ጥንተ ታሪክ አከር ለማክሰም ዋናኛ እና የመጨረሻ መጀመሪያ(አልፋ) ፤ የመጨረሻ ተቀዳሚ የጥፋት ሠይፍ የመዘዙበት እንዲሁም የመወጊያ ዘገር የነቀነቁበት “ሞት ለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት” እያሉ የኖሩበት የአንድ ክ/ዘመን የጥላቻ ዉላጂ አፍራሽ ተልዕኮ ትብብር ይኸዉና ፲፩ኛ ዉ የጥፋት ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ፤ ይገኛሉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለአገሬ ሕዝቦችና መሪዎች፣ እግዚአብሔር ለሕዝቦቹ የሚናገረው በሽማግሌዎች አንደብት ነው - ጆቢር ሔይኢ

በዚህ የአንድ ክ/ዘመን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን የማዋራድ ፣የማሳደድ ፣የመግደል እና የመደለል የተደራጀ እና ህቡዕ የጠላት ሴራ ሴራ ኢትዮጵያን ወይም ኢትዮጵያዉያንን ማኮስመን እና ማክሰም ሲባል በተለይም በታሪክ እና ፣ ስነ ልቦና ፣ ማንነት እና መገለጫዎች ተያይዞ ኢትዮጵያዊነትን በአስተሳሰብ እና ተግባር የሚያስቀድም በተለይም በታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያዊነት ከዓማራ ጋር አብዝቶ የማያያዝ የጥላቻ እና ጥፋት አባዜ የተጠናወተዉ አጥፍቶ ጠፊ ዓማራን የማጥፋት ስልት የመጨረሻዉ መጀመሪያ ምዕራፍ 11ኛዉ ሠዓት ላይ ይገኛል ፡፡

በዚህ ኢትዮጵያን የማጥፋት የመጨረሻ ሠዓት መባቻ የ፲፩ ኛ ሠዓት ዕድል እና ድል ዉጤት የሚወሰንበት እና የሚረጋገጥበት የመጨረሻ መነሻ እና መዳረሻ ጊዜ እና ሠዓት ነዉ ፡፡

ይህም ለዓማራ እና ኢትዮጵያ ህልዉና እና ዓርነት ወይም ሞት እና ባርነት የመጨረሻ መዳረሻ መባቻ ወሳኝ ሠዓት በመሆኑ ከአሁን የላቀ አኩሪ እና አብሪ ታሪክ የሚቀመርበት ፣ የሚረጋገጥበት ፣የሚበሰርበት እና የሚደጎስበት በመሆኑ እየሞቱ ከመኖር ሞቶ መኖር ምርጫ አይደለም በተለይም የዘመናት ሞት እና ስደት ለታወጀበት ህዝብ ዓማራ እና ታላቋ ኢትዮጵያ ፤ኢትዮጵያዉያን ብቸኛ የመጀመሪያዉም ፤የመጨረሻዉም አማራጭ አንድ ነዉ እርሱም ህልዉና ከ ሞት ፤ነፃነት ከባርነት የማረጋገጫ ሠዓት አሁን እና አሁን ነዉ ፡፡

ይህ ፲፩ ኛ ሠዓት ላይ የተገኘዉን በሞት እና በህይወት መካከል የሚገኘዉን ዕድል ወደ ድል ለመቀየር የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ነፃነት እና ህልዉና በቀኝ እጁ ፤ ሞት እና ባርነት በግራ እጁ የሚገኘዉ የመከራ ገፈት ግንባር ቀደም የጭቆና(ባርነት) እና ሞት ቀንበር በጫንቃዉ የተሸከመዉ ኢትዮጵያዊ ዓማራ ሁሉ አለኝታዉ እና አወንታዉ ቀኝ እጁ ላይ የሚገኘዉን ወርቃማ አጋጣሚ ( ዕድል) ወደ ድል ፍሬ ለመቀየር መራራዉን ተጋድሎ ለማድረግ በአብሮነት እና ዕምቢተኝነት ( ዕምቢ ለነጻነት ፣ለማንነት እና ሉዓላዊ አንድነት እና ህብረት….) ለራሱ እና ለአገሩ ዘብ ሊቆም ይገባል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ሕዝብና የአጭቤ ዜናው አባት አማራጠሉ ቢቢሲ

መልካሙን አጋጣሚ(ዕድል) ለበጎ ነገር ከማዋል ለኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያ ገደል ለሚያስብ ጠላት ሁሉ ይህን በህዝባዊ ታግድሎ ወደ አኩሪ ገድል እና ድል በመቀየር በበርቱ አንድነት እና ፅኑ ዓላማ የማሳያ ጊዜዉ ይህ ፲፩ ኛዉ የመጨረሻዉ መባቻ ሠዓት ነዉ ፡፡

የህልዉና እና ነፃነት ድል ለኢትዮጵያ !!!

“ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አንድነት መሠረት የዓማራ ህዝባዊ አንድነት እና ህብረት ወሳኝ ነዉ !”

“ኢትዮጵያን ለመታደግ ህዝባዊ የዓማራ ነፃነት ኃይል / ሠራዊት (Amhara People’s public Liberty eagle/Apple -Force ) የድል ታሪክ የምስራች በታላቋ ኢትዮጵያ በታላቅ ህዝባዊ ተጋድሎ ሩቅ አይሆንም፡፡”

“ታላቋን ትግራይ ለመቀለስ ኢትዮጵያዉያንን(ዓማራ) ማስለቀስ እና ኢትዮጵያን ማፍረስ ቅዠት ለመጨረሻ ጊዜ በ፲፩ ኛ ሠዓት በህዝባዊ ዕምቢተኝነት እና ህብረት መሬት ላይ መደምሰስ አለበት ፡፡”

“ዉድቀት እና ሞት በጥላቻ እና ክህደት የብሄራዊ ነፃነት እና ህልዉና መጋኞች ፡፡”

“ታላቁን እና ብዙኃኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እና ታላቋን አገር በጥላቻ እና ክህደት በጠላትነት የሚፈርጂ ሁነኛ እና ዋና ጠላት ነዉ ፡፡ ”

የ፲፩ኛ የድል መባቻ ዕድል ወደ መጨረሻዉ እና ፲፪ ኛዉ ምዕራፍ በህዝባዊ አንድነት ተጋድሎ ገድል እና ድል ዕዉን ይሆናል ፡፡

“ያለነፃነት ህልዉና ፤ ያለ ህልዉና ሠወዉነት ዉኃ የሌለበት ወንዝ / ጅረት ነዉ ፡፡”

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

ማላጂ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share