የመግለጫ ጋጋታ ከጥቃት አያድንም፤ #ነፃነት በነፃ የለም፤ ከንግሥት ይርጋ (ጎንደር)

250414565 4626368834086232 2261487363295149205 n
ንግሥት ይርጋ (ጎንደር)
ከክልል እስከ ወረዳ ያለ አመራር በአግባቡ ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም :: ይህን ስል በእጣት የሚቆጠሩ ምሳሌ የሚሆኑትን አመራሮች አይጨምርም ::
በየግንባሩ “እያዋጋን ነው” የሚሉ አመራሮችን አሉበት በተባለው በቦታው እየተንቀሳቀስኩ አይቻለሁ :: በሕዝብ በጀት ሆቴል ተቀምጦ የምግብ እና የመጠጥ በጀት ከመፍጀት ውጪ ግንባር ገብቶ የድርሻውን ወይም ግዴታውን የሚወጣ አመራር የለንም :: አስተያየት ስንሰጥም በጥርስ ውስጥ እንገባለን ::
የሚሠሩ አመራሮችን ምሳሌ አድርገን ስንናገር ጓ-ገጭ የሚለው ብዙ ነው ::
አሻጥር አለ ለሚባለው አሉባልታ እንደ እኔ በመከላከያ ሠራዊታችን ላይ ምንም ዓይነት አሻጥር አለ ብየ አላምንም :: ወታደሩ የሚችለውን ያክል ዋጋ እየከፈለ እየተዋደቀ በዓይኔ እያየሁ ነው ::
ግን ትእዛዙ ከየት እና ለምን እንደሆነ ባናውቅም ፤ በውጊያ ስዓት ላይ “ውጊያውን አቁሙ” የሚል ትዛዝ ይሰጣል :: ወታደር ለምን ? እንዴት ? የሚባል ጥያቄ ማንሳት አይቻልም ምክንያቱም ትእዛዙን የሚሰጡት ፖለቲከኞች ናቸው ::
እንደ እኔ እይታ ሕዝባችን መሪ አልባ ነው:: መንግሥት ምን አለ ? ከማለት እና የመንግሥትን ዲስኩር እና #የመግለጫ ጋጋታ ከመጠበቅ ወጥተን ሁላችንም የምንችል ገብተን በመዋጋት ወይም ስንቅ በማቀበል አለዚያም ቁስለኛ በማንሳት እና በማገዝ ለመከላከያ ሠራዊታችን ለዐማራ ልዩ ኃይል ለፋኖ እና ለምንሻችን የኋላ ደጀን በመሆን ለነፃነታችን እንታገል::
በክልል እና በወረዳ አመራሮች ተስፋ የምታደርግ እርምህን አውጣ :: የእኛ አመራሮች መግዚትነቱን ለምደውታል :: በዚህ ስዓት የህልውና ትግል ከፊታችን ተደቅኖ ሰዎች ስለሥልጣን እከሌ ተሾመ እከሌ ተንሳፈፈ ሲሉ ነው የሚውሉ :: ለሄደ ለመጣው ማሸርገድ ልምዳቸው ነው::
እስካሁን ዋጋ እየከፈለም እየሞተም ያለ መከላከያ ወይም ልዩ ኃይል ፋኖ ምንሻ እንጅ አመራር ከተንደላቀቀ ሆቴል ወጥቶ እንደ ሕውሀት በችግር ጫካ ገብቶ የታገለና ያታገለ የለም ::
ወንድ ሆነው ማታገሉን አያታግሉ ግን የሆነ ከተማ ስጋት ላይ ሲሆን ቀድመው በመፈርጠጥ ሕዝቡን ውዥንብር ውሰጥ ከተው የሚጠፉትን ብታዩ ያሳፍራል:: ነገሩ ሲያልፍ ጠብቀው ተመልሰው አክተር (የድሉ ባለቤት ) ይሆናሉ :: ስለዚህ #ነፃነት በነፃ የለም የመጣውን ጠላት እንደ ሕዝብ መታገል ያስፈልጋል ::
በእየቤታችን ተቀምጠን የግዞትን ቀን አንጠብቅ መብትና ግዴታችን ካወቅን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ወጥተን ግዴታችን እንወጣ ሌላው ሙቶ እኔ ልኑር እሳቤአችን እናስወግድ ::
ድል ዋጋ እየከፈሉ ላሉ ጀግኖቻችን!!!

ጊዜ ለኩሉ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የደህንነቱ ሹም ሕወሓት ስቃይ የሚፈጽምባቸውን ሆቴሎች ስም ዝርዝር አጋለጡ

2 Comments

  1. የወያኔ ሴራና ደባ ላንቺ የገባሽ ቀደም ሲል ነው። ከወያኔ ጋር አሁንም ለማደር ህዝባቸውን የሚያስገድሉ ጉዶች ባሉበት ሃገር በሰው ደም ነጋዴዎችን ቀድሞ ማጥፋት አስፈላጊ ነው። እንደ ድቄት ተበተነ የተባለው ወያኔ ዛሬ የሰው ማሳ ሲያቃጥል፤ አጭዶ ሲወስድ፤ የአማራና የአፋር ህዝብን በዘፈቀደ ሲገድልና ሲደፍር ቆይቶ አሁን ደግሞ ይባስ ተብሎ የወሎን ዋና ከተማ ደሴን በመድፍ መታ መባሉ ምን ያህል ወደ ከተማይቱ እንደ ተጠጋ ነው የሚያሳየው። ልብ ላለ ሰው የወያኔን ክፋትና ተንኮል፤ ጭካኔና አረመኔነት ባለፈ መልኩ የወያኔን የእብደት ጽናት አለማድነቅ አይቻልም። ከላይ በአየር፤ ከምድር በጣምራ ጦር የሚመታው ወያኔ ትግራይን ለቆ አፋርና አማራ ክልልን ወሮ ህዝብን ሲያሸብርና ሲገድል አግርሞትን ይፈጥራል። የፌዴራል መንግስቱንም እጅን በአፍ የሚያስጭን ወሬ ማሰማቱ ቀርቶ ራሱ እጅን በአፉ እንዲጭን አስደርጎታል። ውጊያው መጠነ ሰፊ ነው። አዲስ አበባ ላይ ተቀምጠው ለወያኔ ሚስጢር የሚያቀብሉ፤ ቦታዎች ተያዙ በተባለ ቁጥር ከሃገሪቱ በዘረፉት ሃብትና ንብረት ፍሪዳ ጥለው ጮቤ የሚረግጡ ብዙ ናቸው። ወደ አማራውና ወደ አፋሩ ክልል ስንመጣ ደግሞ ክተት ማለት ብቻ በቂ አይሆንም። በጎን፤ በዙሪያ፤ በአካባቢ ያሉ የውስጥ አመላካቾችን ለይቶ ስፍራ ማስያዝ ያስፈልጋል። ዋናው ውጊያ ከመረጃ አቀባዪችና ከመንገድ መሪዎች ጋር ነው። የፊት ለፊቱ ውጊያ የሰለጠነ ሰራዊት ስለገባበት የሚሰሩትን ያውቃሉ።
    ባጭሩ ትላንትም ዛሬም በተለያየ ጊዜ መግለጫ አቁሙ፤ ዲስኩር ይቅር፤ ማቅራራት ይብቃ ብለናል። ንግሥት የምትነግረንም ይህኑ ነው። ሥራ በልብ ነው። ሁሉ ነገር ሲፈተሽ ይገኛል። ጀግንነትም ሌላው ሲናገረው ነው የሚጣፍጥ። ወያኔ ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ በቁርጠኝነት ሲፋለመን እኛም ቁርጠኛና ገሎ ለመሞት መሰለፍ ይኖርብናል። ሌላው ሁሉ ድሪቶ ወሬ ነው። በቃኝ!

  2. It is an interesting opinion ! But your belief that you do not think the very existence of dangerous conspiracy and sabotage within the military is a very naïve and misleading way of thinking. Do you think it was and is easy for TPLF to march all the way down to Dessie without the work of some elements within the high ranking military officials whose hearts and minds are full of the hatred of the Amharas? Why are you very shy of telling the very self-evident truth? I know your great work as a political activist and still I appreciate your courage . But why are afraid of telling the truth and the whole truth? Why you feel shy to tell the very hard reality even the government of EPRDF/Prosperity admitted that there are elements of sabotage and conspiracy within the military structure ? Do not mix the very hard political reality with simple morality or ethics unnecessarily!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.