ሰሞኑን ትህነግ ወይም እነሱ ካልጠፉ ሰላም በኢትዮጵያ አይመጣም ፡፡ በማለት ዳንኤል ክብረት
በመናገሩ የአሜሪካ መንግስት የአሸባሪ ሬድዮ ጣብያ ይመስል በአባባሉ ተጠቅሞ አሉታዊ ቅስቀሳ አካሂዶበታል ፡፡ የሙአዘ ጥበባት ዳንዔልን ንግግር የተረጎመው ጌታቸው ረዳ ቢሆ ነው ፤ የአሜሪካ ባለስልጣናት እንዲህ ጩኸት የበዛበት ውግዘት ያሰሙት ፡፡ ወዳጄ የማይክል ጃክሰንን ቆዳ ያስቀየረ ዘረኛ ነጭ ዛሬም የእሱን ዘረኝነት በኢትዮጵያዊያን ያደርጉታል ብሎ ቢያስብ አይገርምም ፡፡ ዳቆን ዳንኤል በፈጣሪ የሚያምን እና የዓለም ህዝብ ሁሉ አንድ ነው ብሎ የሚያምን ነው ፡፡ አዳም ና ሄዋን የሰው መነሻ እነደሆኑ እኮ የክርስትና ኃይማኖት ስተምራል ፡፡ እስልምናም እንዲሁ ፡፡ ለዚህ ነው የአሜሪካ መንግስት ተዋደን ተጋብተን ቤተሰብ መስርተን በመላው ኢትዮጵያ በምንኖር ዜጎች መሓል ጥርጣሬና ፈርሃት እንዲነግስ ያልተገባ መግለጫ አውጥቷል የምለው ፡፡ ይኽ ድርጊቱም በወድማማቾች መካከል ፀብ እንደመዝራት ይቆጠራል ፡፡…
የአሜሪካ መንግስት እውነቱን ያውቀዋል ፡፡ ትህነግ የተባለ ቡድንን የሚመሩ ግለሰቦች ፤ ጭራቸው እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ፤ ጭንቅላታቸው ውጪ አገር ( አሜሪካም ጭምር ) እንደለ አሳምሮ ያውቃል
፡፡ እውነቱ እኮ በግልጽ የሚታወቅ ነው ፡፡ ዓለም የውሸታሞች ሆና ነው እንጂ !…
እውነት እንነጋገር ከተባለ ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ማነው “ሀ” ብሎ ዘረኝነትን የተከለው ? ትህነግ / ህወሐት አይደለም እንዴ ፡፡ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አይደለም እንዴ ፣ በዓለም የሌለ ዘረኝነትን ለ27 ዓመት አንግሶ የኢትዮጵያ ዜጎች የጎሪጥ እንዲተያዩ ያደረገው ?! ያልቋረጠ ድጋፍ በመስጠት ማነው ወደ አሜሪካ የኢትዮጵያ ሀብት እንዲሸሸ ለ27 ዓመት ሲሰራ የኖረው ? ቤት ገዝተው ንብረት አፍርተው በአሜሪካ ውስጥ እየተደላቁቁ ያሉት የትሕነግ ና ከትህነግ ጋር ንክኪ ያላቸው ከበርቴዎችን አይደሉም እንዴ ? እነዚህ ዘራፊዎችንስ የአሜሪካ መንግስት የመኖርያ ፈቃድ እንዲያገኙ አላደረገምን
? እውን የዛሬው የአሜሪካ መንግስት ፈጣሪ እንዳለ ሊያውቅ ይቅርና ተፈጥሯዊው ሞት ራሱ መኖሩንስ ያውቃል እንዴ ? …
ይህንን ቢያውቀ ኖሮማ ፤ ትህነግ / ወያኔ የሚባል አንድ የሽፍታ ስብስብ ፤በውጭ ጠላቶቻችን እየታገዘ ፣ በትግራይ ክልል የሚኖሩትን የኢትዮጵያ ዜጎች በጠመንጃ አስገዳጅነት አፋቸዉን አፍኖ ፤ በችግራቸውም እያስገደደ ፤ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ወንድሙን አማርኛ ና አፋርኛ ቋንቋ ተናጋሪውን ቀየው ድረስ ዘልቆ እንዲገለውና ሀብቱንም ቀምቶ ና ነጥቆ ፤ ዘርፎ እንዲበላ ሲያደርግ እያየ ዝም አይልም ነበር ፡፡
ዛሬ አይን ባወጣ ውሸት የአሜሪካ መንግስት እየተመራ ” እሰየው ! አንበሳዬ ! የኔ ገንጣይ ! … ቀጥል ግፋ ምንሊክ ቤተመንግስት በፍጥነት ግባ ! ” በማለትም አያበረታታውም ነበር ፡፡
የአሜሪካ መንግስት ፤ ትላንት በ18 ኛውና 19 ኘው ክፍለ ዘመን ያልተሳካውን ፤ ኢትዮጵያን በዘውግ ከፋፍሎ መግዛት ዛሬ በዘመነው ዓለም እተገብራዋለሁ ፡፡ ዕድሜ ለወያኔ በማለት አይደለ እንዴ በቀቢፀ ተስፋ ኢትዮጵያን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከወያኔ ጋር አብሮ የሚሰራው ፡፡ ይኽ ምኞቱ ለኢትዮጵያውያን ንቀት ነው ፡፡ እኛ ኢትዮጵዊያን ምንግዜም ከእውነት እና እውነትን ይዞ ከተጠቃ ወገን ጎን እንቆማለን እንጂ በሸፍጥ ሰውን አናጠቃም ፡፡በዚህም ምግባራችን ፈጣሪ ምንጊዜም ሲረዳን ይኖራል ፡፡ …
በነገራችን ላይ ፤ የ27 ዓመቱ የወያኔ የዘውግ ሥርዓት እኮ ፤ የትላንትናዎቹ ፋሺስቶቹ ፤ የነ ሞሶሎኒ ሥርዓት ነበር ፡፡ ወያኔ ፤ አሜሪካኖች እና ብዙ የአውሮፓ አገራት የሚስተዳደሩበትን ፤ በዓለም ቅቡልነት ያለውን ፌደራላዊ ስርአት መቼ ተገበረና ነው ፤ ዛሬ የአሜሪካ ባለስልጣናት ፣” ወያኔ ወይም ሞት ! ” የሚሉን ? ለበዝባዢ ቱጆሮቻቸው ፍላጎት ሲሉ እኝን አገር አልባ ለማድረግ መጣር በራሱ የሴጣን ተግባር እንደሆነ መቼም ይጠፋቸዋል ብዬ አላስብም ፡፡
የአሜሪካ መንግስት ለብዝበዛ ሲል ፤ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት በዴሞክረሲና በፍትህ ሥም ይሸቅጣል እንጂ ፤ ኽ እውነት አይጠፋውም ፡፡ሆኖም ይህ ሴጣናዊ ድርጊቱ ለአሜሪካን ዜጎች የሚያሰፍር ነው ፡፡ በእውነት ይህ ድርጊት ከ3000 ዘመን በላይ ባላት አገር ላይ በዚህ በዘመነኛ ዓለም መፈጸሙን ስናስተውል ፤ ” እነ ጆርጅ ዋሽንግተን ፤ እነ አብርሃም ሊንከን ፤ እነ ቶማስ ጄፈርሰን…ብልሆቹ የአሜሪካ መሪዎች በሞላ ፤ እንኳን የዛሬውን የአሜሪካንን መንግስት ሸፍጥ ፤ በዴሞክራሲ እና በፍትህ ሥም ማላገጥ ፤ ሳያዩ ሞቱ ፡፡ ” ለማለት እንገደዳለን ፡፡ህሊና ላለው አሜሪካዊ ዜጋ ፤ አሜሪካ እንዲህ ወርዳ ማየት በእጅጉ ያሰፍራል ፡፡ ያስቆጫልም ፡፡
አሜሪካ ና ህዝቧ ክብር ይገባቸዋል ፡፡ ለምሳሌ የጠቀስኳቸውም የቀደሙት የአሜሪካ መሪዎች የተባረኩ ነበሩ ፡፡ ” እኛ ብቻ እናውቃለን እና እናውቅላችኋለንን ፡፡ ” አያቀነቅኑም ነበር ፡፡ግብዝ ስላልነበሩ አሜሪካንን በሁሉም ረገድ ታላቅ አድርገዋታል ፡፡ የዛሬዎቹ መሪዎች በተለይም ትራፕና ባይደን ለአሜሪካ ህዝብ የማይመጥኑ መሪዎች ናቸው ፡፡ ትራፕም ሆነ ባይደን ከጎናቸው ያሰለፏቸው ባለስልጣናት ግብዞች ናቸው ፡፡ ለብዝበዛ ሲሉ ብቻ ፤ በሐሰት የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውንን ክብር ለማዋረድ ሌት ተቀን መጣራቸው ደግሞ ግብዘነታቸውን ያረጋግጥልናል ፡፡
በምድር ላይ ያለውን እውነት እያወቁ ዛሬም በጋሃዱ ዓለም በእግዛብሔር የዋህ ፍጡር በሆኑ ሰዎች ተጠቅሞ ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር ( ትህነግ ) በማለት ፤ ከኢንተር ሃሙዬ ከተሰኘው የሩዋዳ ጨፍጫፊ ቡድን በግብር አንድ አይነት የሆነ ጭፍጨፋ እየፈጸመ እያዩ ፤ የአሸባሪ ቡድን ተባባሪ መሆናቸው በእጅጉ ያስገርማል ፡፡
ህውሓት እኮ ፤ ለ27 ዓመት ኢትዮጵያን ሲገዛ ስሙ ከዛሬው ትህነግ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡ ዛሬም ያው ነው ፡፡ የአሸባሪነት ና የጭካ ተግባሩም ዛሬም አብሮት ነው ፡፡ ትላንትም አሲንባ ላይ “ለዓላማዬ እንቅፋት ናቸው ፡፡ ” ያላቸውን በተኙበት አርዷል ፡፡ በ1983 ዓ/ም አዲስ አበባ እንደገባ የኦነግን ሠራዊት ጨፍጭፏል ፡፡ ስልጣንም ይዞ በስውር አያሌ ንፁሀንን በስውር ገድሏል ፡፡ እራሱ ገድሎ እራሱ አፈላላጊ በመሆን ድራማ ይሰራ ነበር ፡፡ የአዞ እንባ በሚያነባለት በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀውን በደል ደግሞ አንድ ቀን ፣ የምናመልከው ድንቅ ኣምላክ ፤ እግዛብሔር ይፋ በማውጣት ዓለምን ጉድ ያሰኛል
፡፡
በመጨረሻም ፤ የአሜሪካን ባለሥልጣነት ሆይ በወድማማቿች መካከል ጠብ መዝራታችሁን አቁሙ
፡፡ እላለሁ ፡፡ ይህንን በፈጣሪ የተወገዘ ሥራ የማታቆሙ ከሆነ ግን ለእናንተ የመጣው ጥፋት ለአሜሪካንም ህዝብ ይተርፋል በማለት አስጠነቅቃችኋለሁ ፡፡ እግዚአብሔር ሲቀጣ ብትር እንደማይቆርጥም ከወዲሁ ብታወቁ መልካም ነው ፡፡