ምን ህዝብ ቢያዉቅ በመንግስት በኩል ያልቅ – ሙላት በላይ

ቀን ሀምሌ 20 ቀን 2013 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ህዝብ ከባንዳዎች ዉጭ ሁሉም በአንድት የሀገሩን ዳር ድንበር አስከባሪ ነዉ፡፡  ምእራባዊያን ግብጽን እና ጣሊያንን እየአፈራረቁ በኢትዮጵያ ላይ በማሰለፍ እነሱም በጀርባ በእዝልእነት ተሰልፈዉ ቅኝ እንድተገዛ ተደጋጋሚ ጥረትአድርገዋል፡፡ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ ህዝብ በአሸናፊነት እስከአሁንም የቆየ ነዉ፡፡ ከአሸነፈባቸዉ ቦታዎ ች ዉስጥ በ1571 ዓ.ም ቱርኮችን ድሆኖ ላይ፡፡በ1824፣በ1826፣ በ1829፣በ1830፣በ1832 ዓ.ም ግብጾችን ትግሬ መሬትእና ባህረ ነጋሽላይ፡፡በ1867፣1868 ዓ.ም ግብጽን ጉንዳጉንድ እና ጉራዕይ ላይ፡፡በ1879፣በ1880 ዓ.ም ጣሊያንን ሰዓቲ እና ኩንፊት ላይ፡፡በ1877 ድርቡሾችንኩንፊት ላይ፡፡በ1896 ዓ፣ም ጣሊያንን አምባልጌ፣መቀሌ አድዋ ላይ፡ ከ1928 እስከ 1933 ዓ፣ም ጣለያንን በመላዉ ኢትዮጵያ ላይ ይገኙበታል፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ በዘማችነት፣ በተዋጊነት፣ በአርበኝነት ፣በአጥቂነት የሀገሩን ዳር ድንበር ፣ሉዓላዊነት እና የህዝቡን መብት አስከብሯል፡፡ እያዳበረ ይዞት በመጣዉ የአጥቂነት ልምዱ ዛሬም ነገም  ያስከብራል፡፡

ምዕራባዊያን ኢትዮጵያ የራሷን ቀዳሚ ባለቤትነት ቀይ ባህርን፣ዐባይን፣ የየብስ ወሰንን በር እና የማልማት አቅምን  በማሳጣት የዘላለም ጥገኛ ለማድረግ የራሳቸዉን ተላላኪ የመንግስት  መሬ ማስቀመጥ የዉጭ ፖሊሲያቸዉ አድርገዉ እየሰሩበት ነዉ፡፡ ለዚህም ነዉ ዛሬ ኢትዮጵያ ለዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ሥር እንዲሰድ የሚያስችሉ ነባራዊ፣ ቁሳዊ እናህሊናዊ ዝግጁነት ለዲሞክራሲያዊ አስተዳደር የሚያበቃን ዝመና ለማግኘት በህዝብ የሚመረጥ፣ ለህዝብ የሚሰራ፣ ከህዝብ የወጣ የመንግሥት ዓይነት መ መስረት ስንጀምር ከዓላማ አጋሮቻቸዉ ከባንዳ ዘር አዝርት ጋር በመሆን የሚያቅበጠብጣቸዉ፣ የሚያርበተብታቸዉ እና የሚያሯሩጣቸዉ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር የህዝብ አገዛዝ የበላይነት የሚታይበት መሆኑን በማመን ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ ችግር እና መከራ በምእራብ አዉሮፓዊያን በእቅድ እና በሴራ በባንዳዎች ዘር አዝርት ግንባር ቀደምትነት የሚሠራ መሆኑን በመገንዘብ በአንድነት መዝመት በአንድነት መመከት በአንድነት አጸፋዉን መስጠት መቻልነዉ፡፡ ይህ ዓይነቱ አሰራር ደግሞ የህዝብ አንድነት መግለጫ  ነዉ ፡፡

ለዚህ ህዝባዊ ዘመቻ ጦርነት ለወታደራዊ ግዳጅ መሳካትም ሆነ ሽንፈት የጦር መሪዎች እና ፖለቲካዉን የሚቆጣጠረዉ አካል(ክፍል) ወሳኝነት አለዉ፡፡ በመሆኑም ጦሩ ግዳጁን መወጣት ሳያቅተዉ የፖለቲካ ዉሳኔ የሚሰጥ መሆኑን አዉቆ ህዝቡ ከመንግስት ጀርባ ተሰልፎ የዘመቻዉን መሪዎች የአፈጻጸም ሂደት  መገምገም እና መቆጣጠር ለጦርነቱ  በድል መጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለዉ ይታመናል፡፡ነፃ አዉጭ፣የጠባብ ብሄርተኞች ጽንፈኞች ፣የብሄር አክራሪዎች ፣በተተኪነት የሚያምኑ ኃይሎች፣ የአሜሪካ እና የአዉሮፓዊያን አምልኮ የበከላቸዉ እና በነሱም የሀሰት ትርክት አማኝ ለህዝብ እናዉቅልሃለን በማለት በእዉቀት ሳይሆን በእምነት የሚሰብኩ ምሁራን ነን ባይዎች ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በመሆን የሞት የሽረት  እርብርብ  እየአደረጉ የአሉበት ወሳኝ ወቅት አሁን ነዉ፡፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዘር ፍጅቱ በነፃና ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ይጣራ!!! - ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

አሚሪካ ዓለምን ለመቆጣጠር እና ለመከታተል የሚያስችለዉ ስለላን እንደ አንድ የጦር ዘዴ በመሆን አንዲያገለግል በ1874ዓ.ም  ዓለም አቀፍ እዉቅናን  አስገኝቶታል፡፡ከስለላዉ ዓላማዎቹ አንዱ ሶሥተኛ የዓለም ህዝቦችን ታሪክ እንዳይሰሩ እናድህነትን አስወግደዉ ተከብረዉ እንዳይኖሩ ማድረግ ነዉ፡፡ሲአይኤማለት የአሜሪካ መንግሥት የአሜሪካ መንግስት ማለት ደግሞ ሲአይኤመሆኑን አዉቆ ሥራዉን መከታተል ነዉ፡፡የአሜሪካ መንግሥት ለምሥራቅ አፍሪካ  በሾመዉ ልዩዲፕሎማት ጃፍሬ ፌልት ማን፣ በአንቶኒ ብሊንከን፣ሲማንት ፓወርስ፣ጀፍ ፌልትማን ዳንኤል ጣሰዉ እና መሰሎቹ እየተከተሉት የአለዉ መርህ እናዓላማቸዉ ከሀወሀትጋር በተመሳሳይ  እየሰሩበት መሆኑን እና እየተካሄደ ላለዉ ጦርነት አንድ አካል መሆኑን መንግስት ችላ ሳይለዉ አትኩሮ ቢሰራበት፡፡

 • አንቶኒ ብሊንከን የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዉስጣዊ እና ዉጫዊ ደንበሮች በኃይል ወይም ከህገመንግስቱ ዉጭ እንዳይቀየሩ ከኢትዮጵያ መንግሥት ማረጋገጫ እፈልጋለሁ ማለቱ፤
 • አሁንም ብሊንከን የትግራይ መሬት ሲል በገለጸዉ የዐማራዉን እርስት ከወልቃይት ጠገዴ ሁመራ ጠለምት እና ራያ የዐማራዉ ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ ሲል መጠየቁ፣
 • የአዉሮፓ ህብረት ጆሴፍ ቦሬል ድርድር ከአላደረጋችሁ  ለምርጫዉ ታዛቢ አልክም ማለቱ ፣
 • የአንግሊዝ የዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ዶሚኒክ ራብ ድርድር እንዲደረግ ጫና እንፈጥራለን ሲል መናገሩ፣
 • ፒጂ7 አገሮችም ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸዉ ማስታወቃቸዉ፣
 • ድንበር የለሽ ሀኪሞች እና ዩኒሴፍ ኢትዮጵያን የሚከስ ሪፖርት ማቅረባቸዉ፣
 • ዳንኤል ጣሰዉ የሚያዋጣዉ መደራደሩነዉ፡፡ ከአዉሮፓዊያን እና ከአሜሪካ ጋር መጣላት አያዋጣም በማለት ለማስፈራራት ሲዳዳ መሰማቱ፣የወያኔ ባለሥልጣናት በዐማራዉ የዘርማጥፋት ወንጀል እንደማይጠየቁ  እነሱ ከተጠየቁ  አሁን  የአሉትም ባለሥልጣናት መጠየቅ አለባቸዉ በማለት የአማራዉ እልቂት እንዳይነሳ፣ በመርሃ ግብር ነድፈዉ በዐማራዉ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት እና የዘርማጽዳት ወንጀል የፈጸሙበትን በህግ እንዳይጠየቁ መስበኩ ፣
 • አሜሪካ እና አዉሮፓዉያን ቁመንለታል የሚሉትን ሰባዊ መብት ፣የህግ የበላይነት እናተጠያቂነት እሴት ተጻራሪ በማድረግ ህወሀትን ማሰለፋቸዉ፤ ኢትዮጵያን በትብብር ለማጥፋት የባንዳን ዘር አዝርት በማስተባበር በሚፈልጉት ሁሉ በመርዳት መስራት እንዳለባቸዉ ዓልመዉ እና አቅደዉ የተነሱ ለመሆቸዉን ማረጋገጫ ነዉ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ግዕዝ ኦሮምኛ ጨምሮ ለሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ብቃት እንዳለው ዶ/ር አበራ ይናገራሉ

መንግሥት አሁን ገጥሞት ያለዉን የትብብር እና የከበባ ጦርነት በአጥቂነት ለመወጣት ጠላቶቹን እና  አሰላለፋቸዉን አዉቆ በተሰለፉበት አቅጣጫ ሁሉ ህዝብን እየአደራጁ ማሰለፍ ለተሰለፈዉ ሃይል ለሚፈጽመዉ እንቅስቃሴ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ መስራቱ ያለጥርጥር በአጥቂነት ያሰልፈዋል ተብሎ ይታመናል፡፡

1 በአሜሪካ እና  በአዉሮፓዊያን የሚነዛዉን የማስፈራሪያ የሥነልቦና ጦርነትን መካች ከጎሰኝነት የጸዱ ምሁራንን እና የሀይማኖት መሪዎችን የአካተተ ግብረኃይል አደራጅቶ ለወያኔ ቅስቀሳ አጸፋ መልስ እንዲሰጥ ቢደረግ፤

2 አሜሪካዊ የሆኑ በኢምባሲዉ በኩል የሚከናወኑ ክንዉኖችን ፣የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎችን ፣ በራሪዎችእና እርዳታዎች የሚንቀሳቀሱት በአሜሪካ የስለላ ድርጅት በኩል መሆኑ ታዉቆ ለመለስ ሥርዓት አሽከር ያልነበሩትን ባለሙያዎች አሰልፎ  ብርቱ ቁጥጥር እና ፍተሸ ቢካሄድ፤

3 ግንባር ለግንባር ለሚደረገዉ ጦርነት አሰላለፉ በወታደራዊ ሙያ ላይ ብቻ የአተኮረ ቢሆን፣

4 የወታደራዊ ሥልጠና እና  ትጥቅ ተከታታይነት ቢኖረዉ፤

5.የሀገር ሞት የእለት ቀለባቸዉ የሚያደርጉ ሆዳሞች እና የመለስ ግርፎች፤ ጦሩ በስንቅ እና በትጥቅ እጦት  እየተማረረ እንዲሸሽ ለማድረግ  አምስት፣ስድስት ጥይት፣ የማይተኩስ መሳሪያእና የማይተኮስ ጥይት በመሥጠት፤ ከህዝብ የሚዋጣዉን የሥጋ ከብት እና እራሽን ተቧድኖ በመብላት፣ ሸሽጎ በማቆየት ለጠላት ወገን በመሸጥ እና መሰል አሻጥሮችን በወረዳዎች በቀበሌዎች የሚሰሩ እንዳሉ እርግጠኛ በመሆን አሁን ኢትዮጵያን ለማጥፋት በተባባሪነት በአጋርነት የተሰለፉ ለመሆናች ሰርተዉ በተገኙቡት የአገር ማጥፋት ሥራቸዉ መረጃነት ብቻ በአፋጣኝ የዘመቻ ዉሳኔ ቢሰጣቸዉ እና በክትትል ለህዝብ ይፋ ቢደረግ ጦርነቱ በአጭር ጊዜ ዉጤታማ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

ለምሳሌ በምስራቅ ጎጃም በደብረ ኤልያስ ከተማ ሶስት መቶ ኩንታል ደረቅ እራሽን ለጦሩ የተዘጋጀዉን  በወቅቱ ሳያደርስ በቤቱ ዉሥጥ በጥቆማ ሲገኝበት አጥፊዉ እንዲያመልጥ መደረጉ የወያኔ እረዳቶች የለመዱትን የመለስን ዉርስ እየሰሩበት መሆኑን ማሳያ መረጃ በመሆኑ መንግሥት ይህን ስዉር እና ምስጢራዊ የጦርነቱን አካል እና መሰል ሥራዎችን እየተከታተለ እርምጃ እየወሰደ ለህዝብ  ይፋ ቢያደርግ፤

የጦርነቱ አካል በግንባር ተሰልፎ የሚዋጋዉ ጦር፣ በተጠባባቂነት የሚሰለፍ ደጀን ጦር፣ ለጠርነት ዘማች መፈልፈያ እና  መመልመያ ህዝብ ናቸዉ፡፡ ከነዚህ ዉስጥ በአንዱም ላይ አሻጥር ከተሰራበት ሌሎችም ሽባ በመሆን ጦርነቱን ያራዝማል የከፋ መስዋእትነት ያስከፍላል፡፡ስለዚህ በእዉነት ለኢትጵያ ህልዉና የተሰለፍን ሁሉ ጦርነቱ በግንባር ብቻ ሳይሆን በመላዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በኢኮኖሚዉ እና በጦሩ አቅርቦት ላይ መሆኑን አዉቀን የጦርነት ዘመቻችን በወረዳ ፣በቀበሌ፣በሰፈር፣በህዝብ መኪና መሳፈሪያ ቦታዎች  ፣በድርጅት ቦታዎች፣ በልመና ቦታዎች፣በገበያ ቦታዎች፣ በህወሃት ካድሬዎች በአጠቃላይ በመለስ መዋቅር ከላይ እሰከ ታች በአሉት ህሊናቢስ ሆድ አምላኪዎች የሥራ አፈጻጸም እና  እንቅስቃሴ ላይም በመዝመት የሚሰሩ አሻጥሮችን እየተከታተሉ መያዝ ለህግ ማቅረብ የኢትዮጵያዊነት መረጃ ነዉ፡፡በተለይ በመለስ ሥርዓት የተሰቃያችሁ እና ተተፍታችሁ የበራችሁ ወጣቶች እየተሰራ የአለዉን አሻጥር በመረጃ እየመዘገባችሁ ለኢትዮጵያ በእዉነት መቆሙን ለምታምኑት አካል እንድታስመዘግቡ መረጃዎችንም በጥንቃቄ በመያዝ  የእናት ሀገር ጥሪን በመናገር ሳይሁን በተግባር እንድታሳዩ የህልዉናዋ መድህን እንድትሆኗት ኢትዮጵያ እየአነባች ትጠራችኋለች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እያሸበሩ … “አሸባሪ” ፍለጋ … - በነስረዲን ኡስማን

መንግሥትም ለኢትዮጵያ ህልዉና የቆሙ፣ በህዝብ በኩል ተቀባይነት የአላቸዉ፣ በጉቦ እና በሙስና የማይጠረጠሩ፣ ለቆሙለት ዓላማ መስዋእት ለመሆን የተዘጋጁ በየወረዳዉ አስማርቶ የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮችን እየተከታተለ የሚቆጣጠር ከህዝብ ጥቆማ እየተቀበለ የሚጠይቅ  የዘመቻ ግብረ ኃይል ቢያዘጋጅ፡፡

አሜሪካኖች አገርን ለማጥፋት  በሰላይዎቻቸዉ ከሚጠቀሙባቸዉ  ሥልቶች ወስጥ በሀሰት ቅስቀሳ፡- አቅጣጫን በማሳት፣የህዝብን ስሜት በማናጋት ፣ፍርሀት በመፍጠር፣ በብዛት ገንዘብ በመበተን ሆደሞችን በመግዛት፣ ቅርስን በማጥፋት እና በማዋረድ፣ እስከ መገንጠል በማመቻቸት፣ በሚችሉት ሁሉ አገር ወዳድን በማስፈራራት አስወግዶ የራሳቸዉን አሽከር መሪ ማስቀመጥ ነዉ፡፡ ይ ሁሉ ካልተቻለ  በመንግሥት ግልበጣ እና በግደያ አስወግዶ የራሳቸዉን አሻንጉሊት ማስቀመጥ የጦርነቱ ዋነኛ አካል መሆኑን መንግሥት አያዉቀዉም ባይባልም በአንድ ሰዉ እእምሮ ዉሥጥ የሚፈካከሩት ፍርሀት እና መተማመን ሰለማይጠፉ ፍርሃትን እና እምነትን አስወግዶ በአስተማማኝነት አዳዲስ ልምዶችን እና ሃሳቦችን በማፍለቅ ህዝብ ሊከተለዉ የሚፈለልገዉ መሪ ሁኖ መገኘትን የሚጠይቅበት እና ሆኖ የመገኛ ጊዜዉ አሁን በዛሬዉ እለት ነዉ፡፡

የተሳካላቸዉ መሪዎች በራስ መተማመናቸዉ የሚመነጨዉ ማድረግ የአለባቸዉን  እና ማድረግ የለለባቸዉን ጠንቅቀዉ የሚያዉቁ ከመሆናቸዉ ላይነዉ፡፡ የህዝብን ችግር ለመፍታት ደግሞ ህዝብን በማማከር የህዝብን አስተያየት እየአነጠሩ በመቀበል እና በመሪዉ እይታ ሳይሆን በህዝብ እይታ ዓልሞ መሥራት ሲቻል ብቻ ነዉ፡፡ምክንያቱም ሥልጣን የህዝብ መሆኑን አዉቆ ማሳወቅ እንጂ በሥልጣን ህዝቡን መተካት የህዝቡን ሥልጣን መንጠቅ ሰለሚሆን ነዉ፡፡

ኢትዮጵያ በህዝቧ አንድነት የመለስን ቡድንከነአስተሳሰቡ ከቆፈረዉ ጉድጓድ ትቀብራለች!!

ሙላት በላይ

1 Comment

 1. እውቁ አልጀሪያዊ/ፈረንሳያዊ የመብት ተሟጋችና ፈላስፋ Albert Camus the Human Crisis በተሰኘው ጽሁፉ ላይ እንዲህ ይለናል። No Cause justifies the murder of the innocent. ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሰው ደም ማፍሰስ ብቻ ሳይሆን ሊያስቡ የሚችሉ የራሱን ወገኖችም በመግደል የሚያምን የጀርመን ናዚ አይነት አስተሳሰብ ያለው ቡድን ነው። ከተደበቁበት ዋሽ ተመልሰው መቀሌ ከገቡ በህዋላ ያለምንም ርህራሄ የጨፈጨፏቸው የትግራይ ተወላጆች ደም ልክ እንደ በፊቱ ዛሬም ለፍትህ ይጮሃል። ሰሚ ግን የለም። በለው እና እንበልህ በሚል የሽኩቻ ዓለም ማን አጥርቶ ነገርን ያይ እና! ግን አንዳንድ ተስፋ ሰጪ ነገሮች በትግራይ ልጆች ላይ እየታየ ነው። በጭፍን የወያኔን የውሸት ፕሮፓጋንዳ እንደበፊቱ ከመጋት አልፎ አልፎ ጥያቄ የሚያነሱና ለይቶላቸውም ወያኔን የሚቃወሙ ብቅ ብቅ ማለት ጀመረዋል። ለምሳሌ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ በትግራይ ህዝብ ስም የተዋጣውን ገንዘብ ለወያኔ አናስረክብም እኛ በእኛ ለህዝባችን መድረሱን እናያለን እያሉ በመሆኑ ወያኔ ግራ ተጋብቷል፡ በትግራይ በህቡዕና በገሃድ የወያኔን ውሸትና የገድል ጡሩንባ እየተፋለሙ ባለስልጣናትን ሳይቀር መግደል ጀመረዋል። ለዚህ ነው የትግራይን ህዝብ ከወያኔ ነጻ የሚያወጣው ያው የትግራይ ህዝብ እንጂ ከውጭ የሚመጣ ሌላ ሃይል አይሆንም የምለው። ድጋፍ መስጠት ግን ይችል ይሆናል። በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዪ ከተሞች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችም የጠበቀ ጥያቄ በወያኔ አመራር ላይ ማንሳት ለመጀመራቸው በአዲስ አበባ የተደረገው ስብሰባ አመላካች ነው።
  በዚህ ሁሉ ግን በወያኔ የውሸት ፓለቲካ ጢንቢራቸው የሰከረ አወናባጅና የውሸት ዜና በታኞች የሉም እያልኩ አይደለም። እድሜ ለዪቱቭ ለፍርፋሪ ሳንቲም ውሸትን መለጠፍ ሙያ ሆኗል። እነዚህ ወገኖች በሃገርም በውጭም ሞልተዋል። ረጋ ብሎ እውነቱን ለፈተሸ ግን እውነት አይኗን አፍጣ አፍንጫው ላይ እንደ ቆመች ማየት ይችላል። በለው፤ ጀጋኑ ገለ መሌ ከማለት ይልቅ ተው ሃገርና ወገንን ትጨርሳላችሁ እብደታችን ይብቃ የሚል የለም። ሰላም ይሻላል የሚሉ ድምጾች በወያኔ ደጋፊዎች በኩል አለመሰማታቸው የስካራቸውን ጣራ ላይ መውጣት ያሳያል። ከአመራሩ ተነስተን ምሳሌ እንስጥ። ዶ/ር ደብረጽዪን ጭራሽ የተማታበት ሰው ነው። ሌላው ሥራ አስፈጻሚ አባል እየተባለ የወያኔ አፈ ቀላጤ የሆነው ጌታቸው ረዳ በእውነት እንደታመመ በቅርቡ ጋዜጠኛ ተብየዋ ጋር ያደረገው ዲስኩር አስረግጦ ያሳያል። አይ ጋዜጠኝነት ለመኖር አሃ እያሉ ማለፍ። ማፈሪያ። ሌላው ጄ/ጻድቃን ነው። ይህ ሰው ሻቢያን ፈርቶ አዲስ አበባን ጥሎ በመቀሌ የሴራው ተካፋይ ከሆነ ጀመሮ የሚናገራቸው ሁሉ አምታች ናቸው። ለወያኔው ቱልቱላ የሆነው የእንግሊዙ ቢቢሲ ጋር ያደረገው የእንግሊዝኛ ቃለ ምልልስ እግዚኦ ያሰኛል። እነዚህና የመሳሰሉት የወያኔ ጭፍራዎች አልታመሙም የሚለን ካለ ራሱ የታመመ ነው። ህጻናት በጦር ሜዳ ሲረግፉ እያየን ዝም ማለት ራስን የቁም ሟች ማድረግ ነው። አልጄሪያዊው የሰው ልጆች የመብት ተሟጋች Tahar Djaout ከዘመናት በፊት እንዲህ ብሎን ነበር፡ Silence is death, if you speak you die, and if you remain silent you die. So speak out and die. ሞት ለጉረኛውም፤ ለፈሪውም፤ ጀግና ለተባለውም፤ ለድሃና ሃብታሙም አይቀርም። በጊዜው በሩን ያንኳኳል። የቀን ተቀን ተስፋ የሚሆነን የተቆረጠልንን ጊዜ ስለማናውቅ ብቻ ነው። ልቤ ንድድ የሚለው የጌታቸው ረዳን ውፋሪና የትግራይ ገበሬዎችን ክሳት ስመለከት ነው። ማን እየበላ ማን ጦሙን ያድራል? ጉዳዪ ግልጽ ነው።
  ወያኔ መሽቶበታል። ለእራት ጠርቶ ካቴና በእጃቸው ያስገባባቸው ወታደራዊ መኮንኖች፤ በመኪና ከመደፍጠጥ የተረፉ ወታደሮችና ሲቪሎች፤ የጓዳቸው ጡት ሲቆረጥ አይናቸው ያየ ሴትና ወንድ ወታደሮች፤ በ 27 ዓመቱ አገዛዝ ወገናቸው በወያኔ የተገደለባቸው፤ ሃብት ንብረታቸው የተዘረፈባቸው፤ ባጭሩ በወያኔ የግፍ ጽዋ ቀማሽ ሆነው የተረፉና ቆመው የመሰከሩ ሁሉ አንድ ሆነው ወያኔን ለማጥፋት ተነስተዋል። ወያኔ ጭንቅ ላይ ነው። ለዚህም ነው የመከላከያ ሰራዊቱም ሆነ ሌሎች ወያኔን የሚፋለሙ ሃሎች ድልና መስዋዕትነታቸውን በመረጃ መዝግቦ መያዝ እንጂ የተገኘውን ነገር ለዜና ማብቃት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል የምንለው። በሌላ ጎን ለወያኔ ህጻናትና ሴቶች እንዲሁም አዛውንት ስመ ተጋዳላይ በድምጽ ማጉያ ተው አንተላለቅ እኛ ወያኔ እንደሚያናፋው ትግራይን ለማጥፋት አይደለም የቆምነው ወገኖቻቹህ ነን መሳሪያቹሁን ይዛችሁ ተቀላቀሉንና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወያኔን እናስወግድ ቢሏቸው ያለምንም ማቅማማት እንደሚቀላቀሉ እርግጠኛ ነኝ። ከመንገድ እየታፈነ ወደ ውጊያ የገባው ወጣት የወያኔን ሴራ ይረዳል ባይ ነኝ። ይህም ከመተላለቅ ብዙዎችን ያድናል። በተረፈ በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን ውስጥ ያለው የውጭና የውስጥ ፍልሚያ በመንግስት በኩል ማለቁን ጊዜ ያሳየናል። ያ ቀን እስኪመጣ ግን እርስ በእርስ መገዳደላችን ቢቆም ወይም ቢቀንስ መልካም ነው እላለሁ። በቃኝ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.