በሶሻል ሚዲያ የተለያዩ ሰዎች “የተቀናበረ ነው፣ ተመሳሳይ ድምፅ ባለው ሰው የተቀዳ ቅጅ ነው!” ምንንትስ ባሉ ሰዎች ጭፍንነትና ማስተዋል አለመቻል በጣም አዘንኩ ተደነኩም፡፡ ድምፁ የአገኘሁ ለመሆኑ ፈጽሞ የሚያጠራጥር ነገር የሌለውና ከፍተኛ ጥራት ያለው የድምፅ መልእክት ነው፡፡ “ከሌሎች ንግግሮች እየተቆረጠ የመጣና የተቀናበረ ነው!” እንዳይባል የድምጹ ቶን ወጥ መሆኑና ከጀርባ የሚሰማው ድምፅ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ መኖሩ “ከሌሎች ንግግሮች ተቆራርጦ የተቀናበረ ነው!” የሚለውን ግምት ያፈርሳል!!!
“ድምፁ የአቶ አገኘሁን የሚመስል ሰው ድምፅ ነው እንጅ የአቶ አገኘሁ አይደለም!” የሚለው የጨነቃቸው ሰዎች አስተያየትም የድምፅ ቅጁ ፈጽሞ ለመለየት በማያስቸግር ደረጃ ጥርት ብሎ የሚሰማ ድምፅ በመሆኑና የአቶ አገኘሁ ድምፅ መሆኑን ለመለየት ምንም የማያስቸግር በመሆኑ ይሄ አስተያየትም የሚረባ አይደለም!!!
የገረመኝ ነገር “ተሰደብን!” ያሉ የጎጃምና የወሎ ሰዎች ቅሬታ ነው፡፡ ቆይ እንጅ እኔ የምለው በዓይናቸው በብረቱ አሻጥር ሲሠራባቸው ያዩ እና በአሻጥር ተጨፍጭፈው ከማለቅ በስተቀር በቅጥረኛው ፀረ አማራ ብአዴን ትዕዛዝ ስር ተሰልፈው ጠላትን በመደምሰስ ያሰቡትን ጀብድ መፈጸም የማይችሉ መሆናቸው የገባቸው በራያ ግንባር የተሰለፉት የጎጃምና የወሎ ፋኖዎች “ወደቤታችን መልሱን!” አሉ መባላቸው ምንድን ነው ነውሩና ስድቡ??? እኔን ይገርመኝ የነበረው ይሄንን ባይሉ ነበር እንጅ ይሄንን ማለታቸውማ ንቃታቸውንና ብስለታቸውን ነው እንጅ የሚያሳየው ፈጽሞ ፍርሐታቸውን አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሊዋጉ አልነበረም እንዴ በገዛ ፍላጎታቸው እዚያ ድረስ የሔዱት??? ቢፈሩማ ኖሮ ሲጀመርም ወደዚያ ባልሔዱ ነበር!!! ምሥጢሩ ሌላ ነው ወገኔ!!!
አንዳንድ የድምፅ መልእክትን ምንነት የማያውቁ ደናቁርት ደግሞ “በድምፅ ቅጁ ላይ የታማኝ ድምፅ ባለመሰማቱ የተቀናበረ ነው እንጅ ትክክለኛ አይደለም!” ሲሉ ተመልክቻለሁ፡፡ ቆይ እንጅ የአገኘሁ ንግግር ቅንብር ከሆነ ያቀናበሩት ሰዎች የታማኝን ድምፅ ጨምረው ማቀናበር አቅቷቸው ነው ወይ ያላካተቱት??? ሲጀመር የድምፅ ቅጁ የድምፅ መልእክት voice message ነው እንጅ የስልክ ንግግር አይደለም፡፡ ስለሆነም ታማኝ በየነ ከአቶ አገኘሁ ጋር ሲያወራ ሊሰማ አይችልም!!!
እናም የድምፅ ቅጅው ትክክለኛና እራሱ አቶ አገኘሁ ተሻገር ለታማኝ በየነ የላከው የድምፅ ቅጅ ነው፡፡ የድምፅ ቅጁን ለሶሻል ሚዲያ አሳልፎ የሰጠውና የናኘውም እራሱ አቶ አገኘሁ ተሻገር ነው፡፡ ታማኝ በየነን ብትጠይቁት እነ አገኘሁ ተሻገር “የድምፅ መልእክቱን አሳልፎ ለሶሻል ሚዲያ ሰጠ!” ብለው ታማኝን ሊወቅሱትና ሊከሱት ስለፈለጉ ይሄ ክሳቸው እውነት እንዳይመስል ሲል “የድምፅ መልእክቱ አልደረሰኝም!” ብሎ ካልዋሸ በስተቀር የድምፅ ቅጁ እንደደረሰው ይነግራቹሃል!!!
አገዛዙ የባንዳውንና የፀረ አማራውን የብአዴንን መሪ አቶ አገኘሁ ተሻገርን እንዲህ እንዲያደርግ ያደረገበት ምክንያትና ዓላማም የአማራን አንድነት ለመፈረካከስ እርስበርሱ ለማናከስና እንዲሸነፍ ለማድረግ ነው ሌላ ዓላማ የለውም!!! ይሄ የአገዛዙ ከፋፍሎ እርስበርስ የማናቆር የማባላት ሴራውም በጣም የተለመደና ሲሠራበት የቆየ አሠራሩ ነው!!!
አንዴ ምን ሆነ መሰላቹህ ወያኔ የገባ ሰሞን ነው የእኛ ታላላቅ የሆኑት የጎንደርና የጎጃም ወጣቶች “እንታገላለን እንጅ በወያኔስ አንገዛም!” ብለው ለትግል ወደ በረሃ ወጡ፡፡ ቁጥራቸው ቀላል አልነበረምና ወያኔ ፈራቸው፡፡ ከዚያ መሠሪው እባቡ ወያኔ ሊበትናቸው አሰበና ሦስት ሰርጎ ገቦችን በመላክ ምን ያደርጋል መሰላቹህ እነዚህ ሰርጎ ገቦቹ ጎጃሞቹን ሔደው “ጎንደሬዎቹ እናንተን ‘ቡዳዎች ናቸው ሰው ይበላሉ!’ ይሏቹሃል!” ይሏቸዋል፡፡ ወደ ጎንደሬዎቹ ይሔዱና ደግሞ “ጎጃሞቹ እናንተን ‘ጎንደሬ የሚለብሰው አጥቶ እራቁቱን እየተኛ መጋረጃ የሚጥል፣ ጦሙን እያደረ ለሰው ለታይታ ግን ነጭ ጤፍ ከደጁ አስጥቶ የሚታይ ባዶ ወገኛና ጉረኛ ነው!’ ይሏቹሃል!” ይሏቸዋል፡፡
ከዚያም እነዚህ ሰርጎገቦች በገቡ በሦስተኛው ቀን ጎንደሬና ጎጃሜ ተባድኖ እርስበርስ እንደጉድ ተቀጣቀጠ፡፡ መሪዎቹ የትግል ልምድ የነበራቸው ነበሩና ይሄ ሁኔታ እንደተከሰተ “ወያኔ ሰርጋ ገብታብናለች!” በማለት ችግሩን ወዲያውኑ አወቁት፡፡ ታጋዩን ሰብስበው በመመርመር እነዚያን ጸቡ እንዲፈጠር ያደረጉትን ሦስት የወያኔ ሰርጎገቦችን ለይተው አወጧቸውና እዚያው ላይ እረሸኗቸው!!!
እናም “ይሄንን የመሰለ የወያኔ/ኢሕአዴግ ከፋፋይና የሚያባላ ስልት አዲስ አይደለም አማራ አንድ እንዳይሆን ሲጠቀምበት የኖረበት ስልት ነው!” ነው እያልኳቹህ ያለሁት ወገኖቸ፡፡ የልቅየ ሌሎች ከዚህ የከፉ እርስበርስ የማባያ ሴራዎችን ጠብቁ፡፡ ለዚህ መድኃኒቱ እርስበርስ ጎጃሜ፣ ጎንደሬ፣ ሸዌ፣ መሎየ አባብሎ ለሚያናቁር ነገር ጆሮን ጥርቅም አድርጎ መድፈን አለመስማት ብቻ ነውና የፈለገ ነገር ቢወራ ፈጽሞ አትስሙ፡፡ ከተቻለም የተለያየ ነገር እያወራ ለመከፋፈል የሚጥረውን ባንዳና ሰርጎገብ ቅጥረኛን እዚያው ላይ እየረሸናቹህ መድፋት ነው!!! ለነገሩ አጠቃላይ የብአዴን አመራርና ካድሬ የወያኔ ሰርጎገብ ነው በእነዚህ ተመርተህ እንዴትና በምንስ ተአምር ነው ሴራ እየጎነጎኑ አስፈጅተው ያስጨርሱሃል እንጅ በምን ተአምር ነው ልታሸንፍ የምትችለው???
እግዚአብሔር ይሁንህ ብቻ ወገኔ ምንም ነገር እንዳታስተውል አዚም አድርገውብሃል፣ ፀረ አማራው የወያኔ አህያ ብአዴን ከቢጤው ኦሕዴድ ጋር ሆኖ ወልቃይትንና ራያን ለወያኔ ወይም ለትግሬ ማስረከብ ብቻ ሳይሆን አንተን ጨርሶ አጥፍቶ ያንተ የሆነውን ሁሉ ለማውረስ እየተሴረብህ እየተሸረበብህ ያለውን እልቂት ልትረዳ ባለመቻልህ መውጫህን ባስበው ባስበው አልታየኝ ብሏል!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው