“ ጌታው የሚጥመወትን እርሰዎ ያውቃሉ” እንዳለው በግ ሻጭ ስለትህነግና የትግራይ ህዝብ (ሀዱሽ መለስ)

በአንድ ወቅት የበአል ሰሞን ገበያ ድራማ ላይ የበግ ገዥና የበግ ሻጭ እንዲህ ተነጋገሩ ፡፡
የበግ ገዥ ይህ በግ ስንት ነው?
በግ ሻጭ ዋጋው ቆንጠጥ የሚያደርግ ጥሪ ጠርቶ ‘ይህንን ያህል ነው” ይለዋል
በግ ገዥ “ለዚህ ለዚህማ በዚህ ዋጋ አህያ አልገዛም” እንዴ? ብሎ ይመልስለታል (ስለትወደደበት)
በግ ሻጭ “ጌታው የሚጥመወትን እርሰዎ ያውቃሉ” ብሎት እርፍ

ይህ አባባል አስተማሪነቱ ለሰፊው (አጋሜ) የትግራይ ህዝብ ነው፡፡ በጀግናው አሉላ አባነጋ ስም የትህነግ ርዝራዦች አሁን ላይ ባሉበት “ክብ” ውስጥ ሆነው “ዘመቻ አሉላ አባነጋ” በሚል ስም ክተት ማወጃቸው ይታወቃል፡፡
ሲጀመር የትህነግ ርዝራዦች እንኳን በአሉላ አባነጋ ስም ዘመቻ ለማወጅ ይቅርና የዚህን ታላቅ ጀግና ስም መጥራት ይችላሉ ወይ ነው ጥያቄው፡፡ ምክንያቱም ነገሩ ‘ሀ” ብሎ ሲጀመር አሉላ አባነጋ የቆሙትና የተዋደቁት ለኢትዮጵያ ሲሆን ትህነግ የቆመው በውርጃ ለተፈጠረበት መንደሩ ብቻ ስለሆነ ፈጽሞ አይገናኙም፡፡ ስለሆነም ይህንን የተከበረ የአገር አርበኛና የጦር መሪ ስም ለመጠቀም የሞራል ብቃት የላቸውም፡፡ ከትግራይ ምድር የበቀሉት አሉላ አባነጋና ታላቁ የኢትዮጵያ መሪ አጼ ዮሃንስ ስለአገራቸው ኢትዮጵያ ያሉትንና በተግባር ያደረጉትን ታሪክ በሰፊው መዝግቦ ይዞታል፡፡ ክብር ለሚገባው ክብርን የሚሰጠው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም የጦር ግንባሮች ጠላትን ድል አድርገውና ታላቅ ስራ ሰርተው ያለፉትን ጀግናው አሉላ አባነጋን ምንጊዜም አይረሳም፡፡ ሌላው ሁሉ ቢቀር አሉላ አባነጋ የጣሊያን ጦር ተሸንፎ ከአገር ሲወጣ ተሸናፊዎቹ ጣልያኖች በጫማቸው የአገራችንን አፈር ይዘው እንዳይሄዱ ጫማቸውን እያራገፉ እንድሄዱ ማስደረጋቸው ምን ያህል ለአገራቸው ቀናኢ እንደነበሩ ታሪክ ሲያስታውሳቸው ይኖራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህወሓት "ስሜን ልታጠፋ" ነው! (ከአብርሃ ደስታ)

ለዚህ ታላቅ ሰው በድንቁርናው እንጅ በኢትዮጵያዊነቱ የማይታማው የደርግ ወታደራዊ አስተዳደር ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪካቸውን ከወደቀበት ትቢያ አንስቶ በኢትዮጵያ የአርበኝነት ታሪክ ውስጥ በይፋና በታላቅ ክብር ቦታቸውን እንዲይዙ አድርጓል፡፡ በስማቸውም ትምህርት ቤት አሰርቶላቸዋል፡፡ ከትግራይ በውርጃ የተፈጠረውና ባንዳው የትህነግ ስብስብ ለዚህ ታላቅ አርበኛ ለኢትዮጵያ ስለቆሙ ብቻ ሲነሳ ጀምሮ ካደረበት ጥላቻ አንጻ ምን አደረገላቸው ብለን እንጠይቅ፡፡ ደርግ በስማቸው አሰርቶት የነበረውን ትምህርት ቤት የመለስ ዜናዊ ትምህርት ቤት ብሎ ስሙን በመቀየር የታሪክ ዱካቸውን ከማጥፋትና ከመካድ ውጭ ምንም ነገር አላደረገላቸውም፡፡ አሁንስ?? አሁንማ መርዘኛው መሪያቸው መለስ ዜናዊ ስላለፈና አብዛኛውም ቀንደኛ የትህነግ ስብስብ በመሪነት ደረጃ በዚህም ሆነ በዚያ ምክንያት አሁን ከመሪነት ስለተወገደ ተራፊው የባንዳው ርዝራዥ ቡድን አሁን ላይ ቆሞ ሲያሰላስል የአሉላ አባነጋን የጀግንንነት ታሪክ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ስለሚያውቅ ሊጠቀምበት ተመኝቶ በጭንቅ ላይ ስለሆነ በስማቸው ዘመቻን አወጀ፡፤ አይ ውርደት!! ለትግራይ አጠቃላይ ችግር፣ ሰቆቃና እልቂት መንስኤው የአድዋ ባንዳ ውላጆች ስብስብ መንሰራፋት ነው፡፤እየሆነ ያለው እውነታም የሚያስረዳው ይህንኑ ነው፡ ትህነግ በዝርፊያ፣ በውሸት፣ በሴራ፣ በጀብደኝነት፤ ህዝብን በዘር መርዘኛ ፖለቲካው በማናከስ፣ በተለይም አማራን በማጥፋት መሬቶቹን በመመኘት ፍጹምና የማይሳካ ቅዠትን በመመገብ ጭዳ የሚሆኑ የትግራይ ወጣቶችን እንዲያልቁ በማድረግ ወደር የሌለው የከሀዲ ማፊያ ስብስብ መሆኑን ነው፡፡፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አጼ ዮሀንስ ምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት በሆኑት ሀይሎች ማለትም አሁን ላይ ግን በውርጃ በትግራይ ምድር ለተፈጠረውና ለባንዳው ትህነግ ወዳጅ በሆኑት ሀይሎች ህይወታቸው ያለፈ መሪ ናቸው፡፡ እንደሚታወቀው ንጉሱ ከእነዚህ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር መተማ ላይ ውጊያ ገጥመው አንገታቸው በሰይፍ ተቆርጦ ህይወታቸውን ለኢትዮጵያ የሰጡ ታላቅ ንጉስ ነበሩ፡፡ እኚህ ንጉስ ለአገራቸው በተግባር የከፈሉት ሁሉ እንዳለ ሆኖ ስለኢትዮጵያ የመከሩት ምክር ዘለአለም ሲጠቀስ ይኖራል፡፡ ያሉትም እንዲህ ነበረ፦
የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ፣ ልብ አድርገህ ተመልከት፡፡
ኢትዮጵያ የተባለችው :-
አንደኛ እናትህ ናት፡፡
ሁለተኛ ክብርህ ናት፡፡
ሶስተኛም ሚስትህ ናት፡፡
አራተኛም ልጅህ ናት፡፡
አምስተኛም መቃብርህ ናት፡፡
እንግድህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ ፣የመቃብር ከባዲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሳ፡፡
ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ሆይ፦ እየሆነ ያለውንና ለምንስ እንዲህ ሆነ ብለህ ጭምር ቆም ብለህ አስብ፡፡
የትህነግ የውርጃ ቡድን ከውስጥህ በውርጃ ተፈጥሮ የራሱን ጓዶች ሲሸማገል ውሎ አዳሩን ተማምነው በተኙበት አርዶ የበላ ማፊያ ቡድን ለመሆኑ ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ፡፡ ከአፓርታይድ ሰፈር ጀምሮ በየክተሞችህ የተደረገውንም አትረሳውም፡፡ በዚህ ቡድን ሴራ ያለፈላቸው ጥቂቶች ነበሩ፡፡ አንተም አሁን ላይ የት እንዳለህ እራስህ ታውቀዋለህ፡፤ ነገህንም ጭምር ታውቃለህ፡፡ እነዚያም ጥቂቶች አሁን ላይ ወደአልነበሩነት እየተቀየሩ ነው፡ ምክንያቱስ?? ምክንያቱማ አላግባብ ዘግይቶና አላግባብ ተጎድቶም ቢሆን አሁን ላይ ተነቃ!! አለቀ፡፡ጉዳቱና ቀውሱ ለምን መጣ ብለህ አስተውልና አርቀህም አስብ፡፡ ቀውሱም ተፈትቶ ከገባህበት ችግሮች መላቀቅ ትችል ዘንድ የሚጥምህን ምረጥ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወያኔ ጠላቴ ነዉ ያለዉ አማራን እንጅ ኢትዮጵያን አይደለም::አንተ ከዬት አምጥተህ ነዉ ወያኔ የኢትዮጵያም ጠላት ነዉ እያልክ የምትጽፈዉ?  - ሸንቁጥ አየለ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share