“ የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያን አጉራሽ ጣት የሚነክሥ ፤ ቆም ብሎ የማያሥብ ህዝብ አይደለም ። በጉያው የኢትዮጵያን ጠላቶች ሸሽጎ ለመኖርም ፍላጎት የለውም ።

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ይህን ፅሑፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ፣አብዛኛው የትግራይ ኗሪ ፣ ወያኔ ከጅምሩ ካጠመቀው የጎሣ የቋንቋ መንገድ መውጣት አቅቶት ፤ ኢትዮጵያ አገሩ እንደሆነች አሥረስቶት ከአንድ ፋብሪካ እንደተሰራ አሽግ ቁሥ ወጥ የሆነ ባህሪ እንዲያሳይ ማድረጉን ያለማሥተዋሉ ነው ( እርግጥ የወያኔ በጭካኔ የተሞላ ተግባር በራሱ ዜጎች ላይ ከበረሃ ጀምሮ የታየ ነውና በፍርሃትትግራይ ያለው ኗሪ ጥቂት የማይበለው አንድ አይነት የኮኮ ጥርሙስ ሆኖ መታየቱ አያሥገርምም ፤ የሌት እና ቀን ፣ ፕሮፖጋንዳውና እሥከ ጎጆው የዘለቀው የአንድ ለአምሥት ጥርነፋ ለ30 ዓመት አደንዝዞታልና ቆም ብሎ ያለማሰቡ በጥፋት ጎዳና ቢያሥጉዘው አይገርመኝም ። ያሥገረመኝ ማሐል አገር የሚኖር ሰውነቱን የረሳ ምሁር ነኝ ባይ በሰው ቁሥል ላይ እጨት ሲሰድ ማሥተዋሌ ነው ። ( ወንድም ወንድሙን በመግደሉ መጨፈር ሰውነት አይደለም። አውሬነት እንጂ !! )

ለመሆኑ ትግራይ የትግራውያን ብቻ ነች እንዴ ? እንዲህ ከሆነማ ፤ የመላው ኢትዮጵያዊያን እናት ና አባቶች የአድዋ ና የማጨው መሰዋትነት ከቱ ነበር ያ በአደዋ ና በመቀሌ በፋሺስት ኢጣሊያ ምሽግ ላይ የፈሰሰው ደምና የተከሰከሰው አጥንት በከንቱ ለአፈር ማዳበሪያነት የዋለ ነበር ። ትላንት የወያኔንን ጨካኝ ጭፍጨፋ ለመመከት የወደቀው የኢትዮጵያ ሠራዊት መሰዋትነትም የዕቃ እቃ ጨዋታ ነበራ !

Tigrayየወያኔ ሎሌዎች ና መሰሎቻቸው በሃሺሽ ጦዞው የሚቀባጥሩት የዘረኝነት ቅሥቀሳ ግቡ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር መቅበር ነውና በባዳነት ተሰልፈው ፣ ታሪካችንን ለመደምሰስ ቢጥሩ አያሥገርምም ።

እንደጨው ዘር በመላው ኢትዮጵያ ተበታትነው ከሌሎች ቋንቋ ተናጋሪ ጋር ተጋብተው የተዋለዱት የትግሪኛ ቋንቋ ተናገሪዎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ናቸውና የሎሌውን የጌታቸውን ፕሮፖጋንዳ አጥብቀው ይቃወማሉ ።

የገንጣይ ሥም ባላቸው በህወሓት የትላንትም ሆነ የዛሬ መንገድ ላይ ከቶም አይራመድም ። የአሁኑ አፀያፊ የባንዳ ተግባር የተቀነባበረው ታሪክ ይቅር በማይለው የሐሰት ቅሥቀሣ ነው

ህውሃት ከጅምሩ ፣ በዘረኝነት ያበደ ጭንቅላት ሥላለው ዛሬም ከዚህ አውዳሚ የፋሺሥት ተግባር አለመላቀቁ አይገርምም ይህ ግዝፍ የነሳ የዘረኝነት ና የባንዳነት አሥተሣሠቡም ዛሬ ጎልቶ መውጣቱ ፣ ጨካኝና ግፈኛ ና ዘርፎ በል አሸባሪ ቡድንነቱን በይበልጥ አሳውቆናል ጨካኝና ግፈኛና ዘርፎ በል ብቻ ሳይሆን በሰው ደም በሰው ሞት የናጠጠ ሀብታም በመሆኑ ፣ በዘረፋ ሀብቱን አጥቶ እሥካልደኸየ ድረሥ የጥፋት ተግባሩ እሥከ መሐል አገር መቀጠሉ አይቀሬ ነው ።

በዘረኝነት ያበደ በዘረፋ የኖረ ድርጅት ነውና ፣ሠርተህ ብላ ብትለው ከቶም በጄ አይልም። እናም የአሁኑ ድንገቴ ፣ የተኩስ አቁም ሥምምነት በውሸት ቅሥቀሣው ግራ የተጋባው የትግራይ ህዝብ ይህንን የዘረፋ አሥተሳሰብ ያለውን አጥፊ ቡድን የበለጠ እንዲረዳው ና እንዲገነዘበው የማሰብያ ጊዜ ይሰጠዋል

የጥፋት ኃይሉ ማለትም አሸባሪው ቡድን በ1983 / በህዝቡ ጭቆና እርዛት በችጋር በቸነፈር መጠቃት ሰበብ ወደሥልጣን ቢመጣም ፣ ሥልጣኑንን ለግል ብልፅግናው እንጂ ፣ ሥልጣኑንን የህዝቡን ጥያቄ መለሻ አላደረገውም 1.8 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ በእርጥባን ኗሪ ነበር ። በ27 ዓመቱ የወያኔ /ኢህአዴግ የሥልጣን ዘመን ተጠቃሚዎቹ ባለሥልጣናቱ ና የትግራይ ጀነራሎቹ ነበሩ ። ንጉሣዊ ኑሮ የሚኖሩ ባለፎቅና ባለፋብሪካ መሆናቸውን የትግራይ ህዝብ አሣምሮ ያውቃል ። ይህ ምድር ላይ ያለ እውነትን የትግራይ ህዝብ በጊዜ ርዝመት የተሰወረ የድሮ ታሪክ አይደለም ። የዛሬና የአሁን ታሪክ እንጂ !

ታዲያ ለምን ከአሸባሪው በንዳ ጋር ጥቂት የማይባለው የትግራይ ህዝብ ቆመ ? ለምንሥ የመከላከያ ኃይሉን ፤ የኢትዮጵያን ፤ የገዛ አገሩን ሠራዊት ከኋላው ወጋው ? ዛሬም በእርጥባን መኖር ናፍቆት ? ዛሬም ሌሎች በእሱ ጀርባ ተንጠላጥለው እንዲበለፅጉ ፈልጎ ? አይመሥለኝም ።

በእኔም ሆነ በብዙዎች አሥተዋዮች ግምት ፣ አንደኛ ከህዝቡ ከግማሽ በላይ ዕድሜው ከ30 ዓመት በታች በመሆኑ በሥሜት ና በውሸት ለመነዳት በመቻሉ ። ሁለተኛ የሚቀምሰው ና የሚልሰው ያጣ በመብዛቱ ፣ እና የእርዳታ እህሉን ወያኔ በዋሻ በማከማቸቱ ና ሥንቅ ከእኔ ጋር ነው የምታገኙት በማለቱ ።

በሦሥተኝነት የሚጠቀሰው ፍራቻ ሲሆን ፤ ከወያኔ ጋር ያለመተባበር ደግሞ የሚያሥከፍለው ዋጋ ህይወትን በአሰቃቂ መንገድ ማጣት በመሆኑ ፤ ከመገደልና ታረዶ ለጅብ ከመሰጠት ሰሳይወድ በግዱ የጥቂት ሤጣናትን ፈቃድ ፈፃሚ ሆኗል ።

በነዚህና በሌሎችም የፍራቻ ና ህይወትን የማሥቀጠል ምክንያቶች ፣ ግፈኛውን አሸባሪ ቡድን የትግራይ ህዝብ ፈርቶታል። ገሚሱም ፣ እንደማይፈታው አውቆ ጎመን በጤና በማለት አድብቷል ሰው ፍርሐትን እሥካልገደለ ድረሥ የህይወት ድንክ ሆኖ መኖሩ ደግሞ እርግጥ ነው የትግራይ ህዝብ ከፍርሐት ይወጣ ዘንድ ከእውነተኛ ጠላቱ ጋር ማፋጠጡ ተገቢ እርምጃ ነው ።በዲህ አይነት የእውነት ፍለጋ ነው ፣የትግራይ ህዝብ ወያኔ 1983 / ሰኔ ወር ጀምሮ የፈፀመውን ሥህተት መገንዘብ የሚቻለው

ወያኔ ራሱን ኢህአዴግ የተሰኘ ካባ አልብሶ ከሽግግር መንግሥቱ ጀምሮ የብሔርተኝነት ሥሜትን በእጅጉ በማጉላት ከፍተኛ ሥህተት ፈፅሟል ለሁሉም ባህሎች ነፃነት መሥጠት አክብሮት ማሳየት አንድ ነገር ሲሆን ሰዎችን በብሔር ና በቋንቋ ፖለቲካ እንዲደራጁ በማድረግ ነበርአራት ኪሎ ቤተመንግሥትን ሲቆጣጠር ተቀዳሚ ሥራው ያደረገው በብሔር ፖለቲካ ላይ የተመሠረተ መደራጀት አደገኛ የሆነ መቃቃርን በህዝቦች መካከል እንደሚፈጥር እያወቀ ይህንን በዓለም መንግሥታት ውሥጥ የሌለ ርዕዮት አብዮታዊ ዴሞክራሲ ካባ ፈጥሯ እውን አደረገው

መንግሥታት ግን በሣይንሥ በተረጋገጠ በታወቁ ርዕዮት ነው የሚመሩት የታወቀ የፖለቲካ መሰመር ባላቸው ሊሂቃንም ነው የሚመሩት ሊሂቃኑ በርዕዮት_ ዓለም በአመለካከት በመደብ በይዘት ወዘተ የዳበረ ህሊና ያላቸው ናቸው ሰዎችን በብሔር ለመለያየትም ከቶም አይፈልጉም ።ሰዎችን በብሔራቸው መግፋት ጨቆኝነት ነው

ወያኔ ግን ፣ ኢትዮጵያውያን ፣ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ክደው በብሔራቸው እንዲምሉ ለ27 ዓመት ሠርቷል ። ሰውነትንን እና ዜግነትን እና ፈጣሪን አሥክዷል ።ዜጎች በቋንቋዊ አመራር ነፃነታቸውን አጥተው ፣ በብሔራቸው መታወቂያ እንዲሰጣቸው አድርጎ ነበር ።

በኢትዮጵያዊነት ለመታወቅ የሚፈልጉ ከሁለት ቋንቋ ተናጋሪ የተወለዱትን ከፖለቲካዊና የቋንቋ ፖለቲካው ከሚያሥገኘው ጥቅም እንዲገለሉ አድርጎ ነበር እነዚህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች የመምረጥ እንጂ የመመረጥ መብት አልነበራቸውም

ከዚህ ምርጫ ውጤት በኋላ በሚቋቋመው መንግሥት ፣ ዜጎች ፣ ለቀያቸው እትብታቸው ለተቀበረባቸው ቦታዎች ሁሉ ባይተዋር እንደማይሆኑ አሥባለሁ ከአምሥት ዓመት በኋላ ቋንቋ አወቁም አላወቁም በተወለዱበት እና በኖሩበት አካባቢ ገጠር ይሁን ከተማ በምርጫ የመወዳደር መብት ይኖራቸዋል የሚል እምነትም አለኝ ይህ እምነቴ የመነጨው 21 ኛውን / በቅጡ ከተረዳው ከብልፅግና ፖርቲ መሪ ከደ/ አብይ አህመድ በብልሐት በጥበብ የተመራ ለውጥ ጉዞ ነው

የኢትዮጵያ መንግሥት የአሸባሪውን ጥቂት ቡድን የህወሓትንእኔ ከሞት ሰርዶ አይብቀል። የሚል አካሄድን በመረዳት የተኩሥ አቁም በተናጥል ማድረጉ ፤ ዓለምን በውሸት ፕሮፖጋንዳ ያጭበረበረውን ፣ የአብዬን ወደ እምዬ የማላከክ የአሻጥር ጫወታ የሚጫወተውን ፣ ለአገር እና ለህዝብ ደንታ የሌለውን አሸባሪ ቡድን የሚያጋልጥ በመሆኑ የሚደገፍ ነው

ከበርቴዎቹ ህወሃትዎች የመንግሥትን እጅ ለመጠምዘዝም ሆነ እኔ ከሞት ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው እንሥሣ አገርን በማያባራ ጦርነት ውሥጥ ለመክተት ያላቸውን ብርና ዶላር በሰፊው መርጨታቸውና ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ሽፍቶችንና በየአገሪቱ ማሠማራታቸውን እሥከዕለተ ሞታቸው ለመቀጠል ፍላጎት ያላቸው መሆኑንን ተረድቶ ለትግራይ ህዝብ ፈረሱም ሜዳውም ይኸውልህ የተቀረውን አንተ ጨርሥ ብሎ ከመላው የትግራይ ከተማ ጦሩን ማሶጣቱ ተገቢ እርምጃ ነው።

ሲጀመር ህውሃትዎች በግንባር ቀደምትነት ይህንን እኩይ ተግባራቸውን የሚፈፅምላቸው የእኔ ነው የሚሉት አንድ ቋንቋ ተናጋሪ በፕሮፖጋንዳቸው የሠከረ በዕለት ጉርስ እጦት የተቸገረ የሰው ኃይል አላቸው በቋንቋው ላም አለህ በሰማይ…” ይሉታል ነገ ተዋግተን ድል ሥናደርግ የተቀናጣ ኑሮ ትኖራለህ በርታ ጀግን ይሉታል በአማላይ ቃላት እየሰበኩ ሰው መሆኑንን ዘንግቶ በካናቢስ ጦዞ ወንድሙን እንዲያርድ ቢላ ያቀብሉታል ።ከዛ በኋላማ ራሱን እንደ አንድ ልእለ ሰብ ይቆጥራል ፈሪኃ እግዛብሔር የሌለው ፍፁም ዳቢሎስ ይሆናል በተግባር እንዲህ አይነቱ ዳቢሎስም እንዲበዛ ይፈልጋሉ በዳቢሎሶች ተጠቅመውም ህዝብን በሽብርና በፍርሃት በመያዝ ከጎናቸው ያሰልፉታል ሰዋዊ ምሽግም ያደርጉታል ይህንን በግልፅ የታየ ሁነት ለመቀልበሥ ለራሱ ለትግራይ ህዝብ የቤት ሥራውን መሥጠት ተገቢ ነው

ፈረሱም ይኸውልህ ። ሜዳውም ያንተው ነው ። ከጭቆና እና ከግፍ አገዛዝ ለመላቀቅ በወጉ ፣ በሥርዓት ና በህግ አግባብ በሜዳው ላይ ለመጋለብ የሚችል ። አቀበትና ቁልቁለቱን ከደሃው ህዝብ ጋር በመጎዝ ወደ ብልፅግና የሚወሥድ መሪ የመምረጥ ፣ ዳቢሎሶችን የማወገዝና የማሶገድ ሥራ ያንተ ነው ። በዚህ ዕድል መጠቀም የአንተ ነው ። ብሎ ለአፍታ ዞር ማለት የተወናበደው ህዝብ ቀልቡን እንዲገዛ ያደርገዋል ።

ይህንን ዳቢሎሥ ከህዝብ ለመነጠል የግድ ቆም ብሎ የትግራይ ህዝብ ማሰብ አለበት በሰው ደም የሚነገግዱ የሤጣን ደቀመዝሙሮችን ከእንግዲህ በቃችሁ ማለት መቻሉንም በተግባር ማሳየት የሚችልበት ጊዜ አሁን ነው

ዛሬ እና አሁን በመላው ኢትዮጵያ የምንኖር ዜጎች ከትግራይ ወገናችን ጎን መቆም ይኖርብናል የጥፋት ኃይሉን ወይም በአሸባሪነት የተፈረጀውን ህውሃትን በፍርሃት በእጦቱ ምክንያት ምርጫ በማጣት እንዲሁም ተገዶ አብሮት የተሰለፈውን ከዳቢሎሥ ሠራዊት ለይተን ማየት ይኖርብናል ።

ማጠቃለያ

ትላንት በተቀነባበረ የውጪ ኃይሎች ሴራ በዘመነ ደርግ በኤርትራም ሆነ በትግራይ በረሃ ያለቁት ኢትዮጵያውያን ናቸው ያለቁበት መሣሪያም ከምዕራቡና ከምሥራቁ ( ከቀኙ ከግራው ) የተሸመተ እና ሻጮቹን አትራፊ ያደረገ ነው ዛሬም በሰው ደም ለማትረፍ ሁሌም የሚያሴሩ የሞት ነጋዴዎች በሥውር እጃቸው ኢትዮጵያ የምትታረድበትን ቢላዋ እያቀበሉ ነው

ኢትዮጵያዊያን በእነዚህ የውጪ ኃይሎች ሴራ እየሞትን ነው በሤረኞቹ ቢላዋ እየተራረድን ነው አማራጭ አጥቶ ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሰልፎ የሚሞተውም ሆነ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እና የህዝቡን ሠላም ለማሥከበር ሲል የሚሰዋው ኢትዮጵያዊ ነው ።የወያኔን ቱጃሮች ጥቅም የሚሰዋው ዓላማ ቢስ ነው ። ሞቱም የውሻ ሞት ነው ። የኢትዮጵያ ሠራዊት ግን ለዘላለም የሁለቱምየሚታወስ የሀገር ውድ ጀግና ልጅ ነው ።ከቤተሰቡ ከዘመድ አዝማዱ ጎን መንግሥትና የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ይቆማል ። የደግፋል ።

የዜጎች ሞት ሁሉ ለኢትዮጵያ ጉዳት ነው ለኢትዮጵያ ሐዘን ነው ልጅ ልጅ ነውና የሁለቱም ሞት ያሳዝናታል ምንም እንኳን አንዱ ዓላማ ቢስ እና አሣፋሪ የባንዳነት ተግባር ላይ ተሠማርቶ መሞቱ ቢያበሣጫትም ?!

ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ሐዘን ማብቃት አለበት የትግራይ ህዝብ የአሸባሪውን ቡድን የጥፋት ተልኮ ይበቃል ! ” በማለት የኢትዮጵያን እንባ ለማበሥ ቆም ብሎ ማሰብ አለበት ልጆቹ የካናቢስ ሰለባ በመሆን ህሊናቸውን አጥተው የደቢሎስ ደቀመዝሙር ሲሆኑ ዝም ብሎ መመልከት የለበትም ነገ በእነዚህ የሃሺሽ ሰለባዎች እጅግ ዘግናኝ ሥቃይ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ና መፈጠሩን የሚረግምበት ቀን እንደሚመጣም ከወዲሁ መገንዘብ አለበት ።

በበኩሌ የኢትዮጵያ መንግሥት የትግራይ ህዝብ በሰቆቃ እንዳይኖር የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ያቀረበውን የተኩስ አቁም ጥሪ በአወንታዊነት መቀበሉን አደንቃለሁ የሰላም ጥሪ ወይም የተኩሥ ሥምምነት በማድረግ የምህረት አዋጅ በማወጅ ተደናግረው የዕለት ጉርስ አጥተው ወደበረሃ የገቡትን ዜጎች በሰላም እጅ ሰጥተው ሰላማዊ ኑሮን እንዲኖሩም መደገፍ ያለበት የክልሉ መንግሥት ነው ይህንን አሸባሪው ህውሐት አልቀበልም ካለ ና ህዝቡም ካልተቃወመው እጣ ፈንታው ጥርሥ ማፋጨት ነው ። ከእንግዲህ ወዲያ ለጨካኞቹ በሃሺሽሽ ለሚቅበዘበዙት ለዳቢሎሶቹ መንግሥት ና የኢትዮጵያ ህዝብ እሣት እንጂ ውሃ አያቀርቡላቸውም ።

ልብ በሉ ከተጨባጭ ነበራዊ እውነት አንፃር በትግራይ ክልል በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ገበሬው ጥይት ሳይጮኽበት የግብርና ሥራውን እንዲሰራ ለማሥቻል ፣ መንግሥት ተኩሥ ማቆምን አትዘንጉ ገበሬው ነፃ ማዳበሪያ ዘር ሊፈልግ ይችላልና ለዚህም ከወዲሁ መዘጋጀት ያሥፈልጋል

የመንግሥትንም ቀናነትን በአወንታዊነት መመልከቱ ተገቢ ነው ኢትዮጵያዊው ዜጋ የትግራይ ሰው በማያሳምኑ በሥሜት በተሞሉ በሐሰት ትርክት በደለበ ፕሮፖጋንዳ ምክንያትነት ከጥፋት ኃይሉ ጋር ሊተባበር መሣሪያ አንግቦ ሊሰለፍ ችሎል ይህ ሁኔታ ግን ለኢትዮጵያን ወዳዱ የትግራይ ህዝብ የሚመጥን እንዳይደለ ተገንዝቦ የመንግሥትን የሠላም ፍላጎት በቅንነት ተገንዝቦ ንሥሐ ሊገባ ና ያባንዳነት ተልዕኮውን ለመወጣት በሃሺሽ ናውዞ ኢትዮጵያን የሚያደማና የሚያቆሥለውን ማውጎዝ ይጠበቅበታል

በዚህና በዛም የሚሥተጋቡ ገድሎ የመፎከር አባዜ ሊቆሙ ይገባዋል በዚህ በበኩል የኢትዮጵያ መንግሥት እጅግ የሚመሰገን ነው ። ገበሬ የምሥኪን የከተማ ኗሪ ልጅ በከንቱ አልፎ የሚፎክሩ የግል ሚዲያዎች ከዚህ ሤጣናዊ ድርጊት ሊቆጠቡ ይገባቸዋል ። ቀዳዳው እና ባንዳው ጌታቸው ረዳ ግን መበጥረቁን ይቀጥል ።( እኔ ለእንደዚህ ዓይነቱ ምግባረ ብልሹ በሰው አምሳል ለሚንቀሳቀሥ ሤጣን ክብር የለኝም ። )

በመጨረሻ በሃሺሽ ለደነዘዙት ሤጣናት የውሸት አባቶች የማሥተላልፈው መልዕክት አለኝ መቼም እናንተ በጭካኔ እና በውሸት የሚወዳደራችው የለምና እኛ ድል ሥላደረግን እና በሺ የሚቆጠሩ ምርኮኞች ሥለያዝን መንግሥት ተኩስ እናቁም ሲል በትግራይ ክልልላዊ መንግሥት በኩል ጠየቀን …’ በማለት ለድርድር የማይሆን ጥያቄ ማቅረባችሁ አይቀርም ፤ ሆኖም መንግሥት ያላችሁ ፣ለአርሶ አደሩ በማሰብ አምርቶ እንደሚገብ እናሥብለት ለከተማ ኗሪውም እንዘንለት እና የጥፋት ኃይሉ ሰዋዊ ጋሻ ከመሆን ይልቅ እርሱን ለብቻው ትተነው ወደ ሠላም ጓዳና በመምጣት የጥፋት ኃይሉን እርቃኑንን በማሥቀረት ለፍርድ እናቅርበው እንጂ ነፍሰ በላና አራጁ የጥፋት ኃይል በደም ከተጨማለቀ እጁ ጋር ከሠላማዊው ሰው ጋር ተቀላቅሎ በሰላም ይኑር እንደልሆነ ከወዲሂ በትረዱት መልካም ነው በማለት ትሁት ምክሬን እለግሳችኋለሁ ። ይህንን የሠላም ጥሪ ችላ በማለት ዛሬም ሰው መሆናችሁን ክዳችው በተግባር ዳቢሎስ መሆኑንን ካረጋገጠው ቡድን ጋር ከተሰለፋችሁ የተራዘመ ሰቆቃ ውሥጥ የምትኖሩት ራሳችሁ መሆናችሁን እወቁት ። በተአምር ህውሐት ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ተመልሶ አይመጣም ።

የትግራይ ህዝብ ሰው ሰራሽ የጦር መሣሪያ አለመሆኑን እና የፈጣሪ ፍጡር ሰው መሆኑንን በዚህ በጥሞና ጊዜ ይረዳል ብዬ አሥባለሁ ።

በዚህ በጥሞና ጊዜ ፣ የትግራይ አጎራባች ክልሎች ሁሉ ግን ከሽብርተኛው ቡድን ሤጣናዊ ተግባር እንደተማሩ ና እጃቸውን አጣምረው ለመታረድ ዝግጁ ሆነው እንደማይቀመጡ በሥሜት የሚነዳው የትግራይ ወጣት ቢገነዘብ መልካም ነው ። ሽብርተኛው ቡድን ምሽግ እንዳደረገውም ቢረዳ መልካም ነው። ጀግና ና ፈሪ ህዝብ ብሎ ነገር እንደሌለ ይገንዘብ ። ማንም ሰው በቢላዋ ቀልድ የለም ማለቱ የተረጋገጠ ነው ። ደግሞም ፤ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለአገሩ ለመሞት ወደኋላ አይልም ። ትላንትም አደዋ ሄዶ የሞተው ትግራይ ሀገሬ ህዝቡም ወንድምና እህቴ ነው ብሎ ነው ። ዛሬ በብዝበዛው በአጥንቱ ያሥቀረውን ወዶ ያጎረሰውን የሚነክሥ በአጠቃላይ እንደ ህዝብ አለ ብዬ ለማመን ይቸግረኛል ። እናም ህዝቡ እናቱን ኢትዮጵያን ወንድምና እህቶቹን ኢትዮጵያዊያንን አክብሮ የአሸባሪውን እጅ ይዞ ለኢትዮጵያ መንግሥት በመሥጠት ፣ ጳጉሜ አምሥት 2013 /ም በዴሞክራሲያዊ መንገድ አሥተዳዳሪዎቹን እንደሚመርጥ ተሥፋ አደርጋለሁ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

merlin 169160205 f43eb8f7 4dff 42b6 b013 f05fa9c496ea articleLarge
Previous Story

“ ጆሮ ያለው ይሥማ ! የማይሰማ አይስማ ! “ መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Next Story

የትግራይ ህዝብ የወያኔን ሂትለራዊ ተግባር እንዲረዳ ፣ መከላከያው ለጊዜው ፣ ገለል ማለቱ ተገቢ ነው ፡፡

Go toTop