ይህችም ቀን ታልፋለች (ዘ-ጌርሣም)

እንዳለፉት ጊዜያት
ለረዥም ዘመናት
ሰው እንደኖረበት
ኖሮ እንዳለፈበት
ገድል አስመዝግቦ
ታሪክን አድልቦ
ደጉንም
ክፉንም
ጥላቻን
ፍቅርን
ማግኘትን
ማጣትን
መጥገብን
መራብን
ከአገር መሰደድን
ተዋርዶ መኖርን
መታመም መሞትን
ታሞ ማገገምን
ሁሉንም በቅጡ
እንድየ አመጣጡ
እንዳስተናገደው
በአግባቡ እንደሸኘው
ይህችም ቀን ታልፋለች
አክብረን ካልያዝናት ታስተዛዝባለች
ትዕግሥቷ ሲሟጠጥ
ስንገፋት ያለቅጥ

መገንዘብ አቅቶን
ስንጋብዝ መከራን
ለጠላት በማገዝ
አገርን ስናወግዝ
በዓይናችን እያየን
ሲያልቅብን ሕዝባችን
ዙሪያውን ተከበን
በጠላቶቻችን
ምጡ ጨክኖባት
የአገራችን ጩኸት
አዋላጅ በማጣት
ድረሱልኝ ብላ ስትጮኽ እያየን
ጆሮ ዳባ ልበስ አልሰማነም ብለን
ጦር አውርድ በማለት መከራ እንጠራለን
ይህችም ቀን ታልፋለች
አክብረን ካልያዝናት ታስተዘዝባለች
ትዕግሥቷ ሲሟጠጥ
ስንገፋት ያለቅጥ
ጨለማው ይበራል
ድፍርሱም ይጠራል
የአገር ጠላት ያፍራል
ጀግኖችን ያኮራል
በጊዜ ዳኝነት
ፍርዱን ቆሞ ማየት
የማይቀር ሐቅ ነው
በቅርብ የምናየው
ሕዝባችን እንደሆን
ለምዶታል መከራን
መፍትሄው አንድ ነው
አማራጭ የሌለው
እንደ አባቶቻችን
እንደ እናቶቻችን
በጋራ አብረው ቆመው
ጠላትን መክተው
መቁሰልን
መሞትን
የመጣውን ሁሉ
የኔ ነው ሳይሉ
እንደየ አመጣጡ ሁሉን አጣጥመው
ክፉ ቀንን ሳይቀር አብረው አሳልፈው
ለእኛ ሲሉ ሞተው
አገር አቆይተው
ትውልድን ተክተው
ለአስረከቡን ሀገር
ልንሆን ይገባናል ጨፈቃና ማገር
የጊዜው ግርግር የትም ላያደርሰን
በታሪክ ተወቃሽ ቆይቶ እንዳያደርገን
ማሰብ ይገባናል መልሰን መላልሰን
ማፈስ ስለሚከብድ የፈሰሰ ውሃን
የእግር እሣት ሆኖ እንዳያቃጥለን
እናስተውል ከልብ መልሰን መላልሰን
ይህችም ቀን ታልፋለች
አክብረን ካልያዝናት ታስተዛዝባለች
ትዕግሥቷ ሲሟጠጥ
ስንገፋት ያለቅጥ

4 Comments

 1. Lock him up ! Al Mariam , political stooge of PP party, is advocating for genociders! put him behind bars!

  Dismantle mahibrekidusan , mouse in the church . We just propose you to replace this business and political organization with other devout church members ! We are not inciting a violence !They are concrend only for their future as businessmen if they are retaken by other ethnic members !We know they were supporting the government via Daniel Kibret and others . Now, they start to oppose as soon as the amahara people in Bahirdar and other towns start to stand against the ruling party,PP! The excutive staff are mostly from Amahara and they have many members in INSA, working with Temsegen Tiruneh.Mahibrekidysan brainwash every student while he or she is freshman in colleges and they facilitate the process of collecting teaxes from every student when he land a job and work for this political organizations disguised as religious entity as a spy wherever they work . Simply saying, they have members in any public organizations because they delude them in the name of religion and bible lesson.

  They claim youth will be taken by protestants if mahibrekidusan take care of them which is false. We have priests, pastors and church scholars , but mahibrekidyasn twist them to work them by bribing them and defame the strong church leaders and scholars and prevent them from getting accepted by the entire laity of EOTC.

  Dismantle the gathering of mahibrekidusan and replace it by a newly formed association. Mahibrekidusan donot want to talk about the killings of priests , monks, mothers, children and buring of monasteries and churches and chose to play with words and strived to hide its evil nature with words like “natural right, church is in exile , church is under serious condition since 1950, etc we are not asking them to tell us the history of the church since 1950 they must have determined to adresss the current burning and deadly case resulting in an unmaginable atrocities on our church leaders and the laity!

  We want to see mahibrekidysan get destroyed and dissolved. However, I am referring only only to the instition a,nd gathering but not violence on any person. I dnot care if you misunderstood and misinterprete it. They must be destroyed because they are one of those who support the war on Tigray and plan of the ruling party!

  Dissolve mahibrekidusan like PJDF(Higdef):they are a threat for our country , laity of EOTC(EOTC=Ethiopian Orthodox Tewahedo Church) our church leaders:mahibrekidusan is a pure political organization. Deacon Engineer Abayeneh kasse affirmed this fact saying: we delayed presenting our recent statement since we have members who bear diffrent political, socio-environmental stance which is ridiculous pretext to take into consideration when it comes to deal with serious matter that the church is facing and unacceptable to see soccaled religious organization to bring political issue at the table and decide critical matter being driven by political motive while gathering under the name of the church whose hhead is the crucified Christ!

  EOTC is in exile because they made this exile, killings of our people by taking part in the campaign against Tigray in the guise of destroying a handful TPLF leaders!
  ማህበረ ቅድሳን ተብየዎቹ እኛ ከሌለን ወጣቱ ሁሉ ጴንጤ ይሆናል ቤተክርስቲያን ጉግማንጉግ ይወራታል፥ትግራዋይ ኦርቶዶክስ የሆነ ሁሉ አንድ ሆኖ ቤተክርስቲያንን ማዳን አለበት ወዘተ የሚሉ አጀንዳዎችን ያራግባሉ፥፥የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ስም በማጠልሸት ና ከቤተክርስቲያን እንዲርቁ በማድረግ እኛ አለንላቹ እያሉ ከበርበሬ፥ሽሮ እንጀራ እስከ አስመጨና ላኪ በመሰማራት ቤተክርስቲያን ስም እየነገዱ የፖለቲካ አላማቸውን በስውር ያራምዳሉ፥፥እኛ በዚህ ጊዜ ናሰዓት የ ቤተክርስቲያን ታሪክ አስተምሩን አላልናቸውም ቤተክርስቲያን ስደት ላይ ናት፥ ተፈጥሯዊ መብታቸው ነው የሚል የቃላት ጨዋታ በዘመናችን ለሚፈፀመው ና እየተፈፀመ ላለው የ ወገናችን ዕልቂት ይመጥነውም፥፥ጅምላ ዕልቂት ፈፃሚዎቹ እንኳ ኢሳያስና አቢይ ባደባባይ ባመኑበት ወቅት ቤተክርስቲያን ስደት ላይ ናት የሚል የፈሪ ና የ ንፍገት ከ ሀላፊነት የመሸሽ፥ ጎጠኝነትን ለመደበቅና አዛኝ ቅቤ አንጓች ስሜትን የሚገልፁ ቃላትን ማሽቀንጠር የቤተክርስቲያን ስርዓት አይደለም፥፥በደብዳቤያቸው (መግለጫም ማላገጫም በሉት እንደአረዳዳቹ)፭ኛ ቁጥር ላይ በአንጻሩ ሌሎች አካላት በቤተ ክርስቲያኒቱ ይዞታዎች ላይ ያለአግባብ ለሚያነሱት ጥያቄ መልስ ለመስጠት በሚያደርገው ሂደት ረጅም ርቀት በመሄድ ይቅርታ ሲጠይቅ ይታያል)በዚህ አረፍተ ገር ማህበሩ በሌሎች ብሄር አባላት የሚነሳን ጥያቄ አለመቀበላቸውንና ሀሳባቸውን በአሽሙር መልክ ለመግለፅ ተጠቅመውበታል፥፥ይንቀላቸው፥ማህበሩ መፍረስ አለበት እንርሱ ሲደግፉት የነበረ ፓርቲ ሕዝባችንን እየገደለ ያለው፥አሁን መግቢያ መውጫ ስለጠበባቸው አማራ በብዛት እየተገደለ ስላለና በአማራ ክልል የሚባለው አብዛኛው ሕዝብ መቃወም ስለጀመረ የለኮሰው እሳት እቤቱ ስለገባ ነው፥፥ስደት ላይ ናት ኳይት ቬግ ስቴትመንት በአካል ምዕመናን ሲሰደዱ ስደት ላይናት ይባላል አሁን ግን እየታረዱ እየተቃጠሉ ነው የከፋ ሰቆቃ ላይ ናቸው፥፥

 2. You smell like a PP cadre and your language use, be it English or Amharic, is poor. Next time, try to write better.

  • meseret tesfaye you sound mahibrekidusan buchila !! PP is your master and still helping you killing nonamhara

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.