ዛሬ በኢትዮጵያ ማን ተሹሞ ማን ተሻረ?

ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩን፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙን፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ኃላፊን እና የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርን ከኃላፊነት አንስተዋል። በዛሬው ሹም ሽር እና ሽግሽግ ማን ተሹሞ ማን ተሻረ?
                          _____________________
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የመከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ደመላሽ ገብረ ሚካኤል እና የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ከኃላፊነታቸው ተነሱ። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. አዳዲስ ሹመቶች ሰጥተዋል።
ውጭ ጉዳይ ምኒስትር የነበሩት ገዱ አንዳርጋቸው ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን የጠቅላይ ምኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ ይፋ አድርጓል። በምትካቸው ደመቀ መኮንን ከምክትል ጠቅላይ ምኒስትርነታቸው በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ምኒስትርነት ሥልጣንን ደርበው እንዲሰሩ ተሾመዋል። አቶ ገዱ ከዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሆነው ተሾመዋል።
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ሲገደሉ የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ሆነው የተሾሙት ጄኔራል አደም መሐመድ ከኃላፊነት ተነስተዋል። ምክትላቸው የነበሩት ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ሆነዋል። ባለፈው ሳምንት ጥሪ ተደርጎላቸው የኢትዮጵያን ጦር የተቀላቀሉት ሌቴናል ጄኔራል አበባው ታደሰ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነዋል።
የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎትን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል ሌላው ከኃላፊነት የተነሱ ባለሥልጣን ናቸው። በኦሮሚያ ክልል እና በፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን በከፍተኛ ኃላፊነት የሠሩት ደመላሽ የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎትን እንዲመሩ የተሾሙት ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ከተፈጸመው የከፍተኛ ባለሥልጣናት ግድያ በኋላ ነበር።
በምትኩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነዋል። አዲሱ የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙት ሐምሌ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ነበር። ተመስገን ክልሉን የመምራት ኃላፊነት የተረከቡት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) በባሕር ዳር ከተማ ከተገደሉ በኋላ ነው። ከዚያ በፊት የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደሕንነት አማካሪ ሆነው አገልግለዋል።
በዛሬው ሹም ሽር እና ሽግሽግ አቶ ደመላሽ የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሾመዋል። በውሳኔው መሰረት የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ከኃላፊነት ተነስተዋል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው ስብሰባ በአቶ ተመስገን ምትክ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩትን አቶ አገኘሁ ተሻገርን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።
 
SOURCE: DW (Deutsche Welle’) Amharic 

1 Comment

 1. The former Foreign Minister Gedu Andargachew recently bluntly , courageously and publicly said “በጉራ ፈርዳ ወረዳ የተፈፀመው ጥቃት ማንነትን መሰረት ያደረገ ነው –” which got the Pro Oromo Prime Minister Abiy Ahmed uncomfortable because if anyone in his cabinet needed to say “በጉራ ፈርዳ ወረዳ የተፈፀመው ጥቃት ማንነትን መሰረት ያደረገ ነው ” it should have been the Prime Minister himself then after that maybe the other Ministers, but if the Prime Minister did not say that first, then all in his cabinet should have kept quiet according to the cabinet protocol.

  Now what the then Foreign Minister Gedu said publicly does not show the stand of the whole Ethiopian government ,it was just a stand of one high level official individual in the Ethiopian government.
  So far the Prime Minister Abiy Ahmed’s government has not officially said “በጉራ ፈርዳ ወረዳ የተፈፀመው ጥቃት ማንነትን መሰረት ያደረገ ነው ” , only the former Foreign Minister and the current National Security Advisor Gedu Andargachew said that which shows this new appointment of Gedu Andargachew as a National Security Advisor is just a tactic to quiet down Gedu Andargachew from making anymore public comments about the ongoing Amara’s extermination which is being waged against the Amaras by Abiy siding with the attackers.

  That is why rather than reshuffling the cabinet almost every month now, even at this moment where the country is at a point of a brink of a big war which Africa did not see in this millennium just shows the desperation to cling to power .

  Currently the failed Abiy’s government intentionally got things to reach to this point of failure

  1. Amaras and Tigray’s farmers lost their crops to Locust Infestation due to neglect of PP and TPLF to the issue.

  2. Abiy and TPLF Picked this hunger time to start a civil war just to get the volunteer farmers from both sides finish each other off.

  3. While Abiy is having a Defense Minister (Lemma Megerssa , “the Reform leader ” ) under house arrest, this new war is underway which shows Abiy’s personal determination to accumulate his dictatorial tyrant power.

  4. While reshuffling intelligence and top military officials once again amidst beating the drum for the war of the millennium not only internally but globally, it is being evident all along Abiy was the person who needed to be shuffled from his post all this time.

  5. While all of a sudden Abiy Ahmed is unwilling to accept nothing else but “unspecified” total defeat of TPLF leadership at whatever cost.

  6. While Capital flight illicit financial outflow through Bole International this year reached an all-time high Abiy Ahmed is busy searching for treasure in Mekele.

  If this Abiy’s government is not a failed government with all the cabinets needing to resign ASAP, then I do not know whatelse to call his government or to say what else is left for this failed Abiy’s Cabinet to possibly do to redeem itself.

  Many are currently saying the Ethiopian Amara soldiers need to take out Abiy on the way back from Mekele!!!!

  “ከባድመ መልስ ወደ መለስ” ብለው ባድመ ዘምተው ሳይመለሱ እንዳስቀራቸው እንዳይሆንብን ይታሰብበት!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.