ወቅታዊ ማሳሰቢያ በተለይ ለአማራ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ! – አምባቸው ደጀኔ

አዲስ ነገር አይደለም፡፡ አንድ ነገር ይጀመራል፤ ያልቃልም፡፡ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ነገር ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡

ፀሐይ ጧት ትወጣለች፤ ሙቀቷ ለብ እያለ፣ ሞቅ እያለና እያቃጠለ ይሄድና ልክ እንዳነሳሷ ኃይሏ እየቀዘቀዘ ሄዶ በምዕራብ እንደወጣች በምሥራቅ ገብታ ትሰወራለች፡፡ ልጅም ይፀነሳል፤ ይወለዳል፤ ያድጋል፤ ያረጃል፤ በመጨረሻም ይሞታል – እርግጥ ነው – ይህን ዑደት ለማግኘትም መታደልን ይጠይቃል፡፡ አለበለዚያ ከጽንሰቱ ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት በሕይወት የመቆየት ዕድሉ ሊቋረጥ ይችላል፡፡

ሁልጊዜ ፋሲካ የለም፡፡ በፋሲካ እንደገባች ገረድ ሁሌም ፋሲካ የሚመስላቸው ወያኔና መሰሎቹ ብቻ ናቸው፡፡ ሁልጊዜ አሸናፊነትም ሆነ ተሸናፊነት የለም፡፡ እንዳማሩ መሞትም መቼም ኖሮ አያውቅም፡፡ ሁልጊዜ መደሰትም ሆነ ሁልጊዜ ማልቀስና ማዘን በጤናማ ማኅበራዊ ተራክቦ የተለመደ አይደለም – የልቅሶ ድንኳ በተደኮነበትና የልቅሶ ዋይታ በተሰማበት ግቢ በወር ተራው የሠርግ ዳስ ተጥሎ አሼሼ ገዳሜ ይባልበታል፡፡ ብዙ ተቃራኒ ነገሮች ተፈራራቂ ናቸው፡፡ ልደትን ሞት ይሸፍነዋል፤ ቁንጅናን ፉንጋነት ያጎላዋል፡፡ ውፍረትን ቅጥነት፣ ረጂምትን አጭርነት፣ በሽተኛነትን ጤንነት፣ ጀግንነትን ፍርሀት … ያጠይመዋል፡፡ ሀብታምነት በድህነት ይሸነፋል፤ ወጣትነት በእርጅና ይረታል፡፡ ሥልጣንና ሹመትን ጊዜ ይሽራቸውና ዘብጥያ ሊያወርዱ ይችላሉ፡፡ የአንጻራዊነትን ህግ ማስታወሱም ተገቢ ነው – እዚህ ላይ፡፡

ሕወሓት አሁን መግቢያ ያጣች ይመስላል፡፡ ግን ልክ እንደሙኣማር ጋዳፊ አእምሮዋ በሁልጊዜ አሸናፊነት የሥነ ልቦና ደዌ ስለተመረዘ ሞታምና እየሞተችም ቢሆን ሽንፈቷን መቀበል አትፈልግም፡፡ ሞኣማር ጋዳፊ ተሸንፎ ከተደበቀበት የቆሻሻ ቱቦ ውስጥ ሲያስወጡት የሊቢያ መሪነቱን እንዳጣ አላወቀም ነበርና የያዙትንና በመቀመጫው ሣንጃቸውን የቀበቀቡበትን ወታደሮች ሊያዛቸው ይቃጣው ነበር፡፡

ወደኛ ጉዳይ ስንመጣ በመሠረቱ ሕወሓት የሞተችው ገና ስትፈጠር ነው፡፡ ስንኩል ዓላማ ይዞ ለተወሰነ ጊዜ በጥፋት ጎዳና መትመም ይቻላል፡፡ እየተመሰገኑና እየተወደሱ በሕዝብ ተወዶና ተፈቅሮ ብዙ ርቀት ለመጓዝ ግን እውነትና ፍትኅን አስተካክሎ መያዝ ይገባል፡፡

በውሸት የቆረበችው ወያኔ ከማን ጋር እንደተጣላች ራሱ አልገባትም፡፡ እነአቢይ ሥልጣን የያዙት በአጋጣሚ ነው፡፡ ዋናው የወያኔ ገፍታሪ አምላከ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ እርግማን ናቸው፡፡ የሕዝብን ዕንባና ደም መናቅ ከቶውንም አይቻልም፡፡ እንጦርጦስ ይከታል፡፡ ይህን ነባራዊ ዕውነት አለመረዳት ነፈዝነት ነው፡፡ ብዙዎች ታሪካቸውን የሚያበላሹት አስተሳሰባቸው ድውይ በመሆኑ ነው፡፡

ዝንጀሮዎቹ እነአቢይ በአጋጣሚ እጃቸው የገባውን ሥልጣን አለመላው እየተጠቀሙ ዕድላቸውን እያባከኑት ነው፡፡ በተለይ የዘመኑ ኢትዮጵያውያን ወርቃማ ዕድልን በማበላሸት ረገድ የሚስተካከለን የለም፤ በዚህ በኩል ድንቁርናችን ድንበር የለውም፡፡ ወያኔ ያልጠቀማትን ዘረኝነትና አግላይነት እነሱም ተረክበው እስከጥግ ሥራ ላይ እያዋሉት ናቸው፡፡ የአበራሽን ጠባሳ ያዬ ለምን በእሳት መጫወትን እንደሚመርጥ በፍጹም አይገባኝም፡፡ በመጨረሻ ግን እነሱም የወያኔን ዕጣ እንደሚያገኙ ማወቅ አለባቸው፡፡ ለምን ዝንጀሮ እንዳልኳቸው ልናገር፡፡

ዝንጀሮ የአባቱ ተቀናቃኝ ነው፡፡ ወጣት ዝንጀሮ ተሳቅቆ ነው የሚያድገው፡፡ የሚታዘለውም በእናቱ ሆድ እንጅ እንደሴት ሕጻናትና ታዳጊ ዝንጀሮዎች በጀርባ ተቀማጥሎ አይደለም፡፡ ወንዱ ወጣት ዝንጀሮ ከአባቱ ኋላ እየተከተለ እርምጃውን ይቆጣጠራል፤ ልክ እንዳባቱ ያህል ሲራመድ ከጎን ሆኖ ይሄዳል፡፡ ያኔ በጉልበትም በብልጠትም ከአባቱ እንደማይተናነስ ማኅበረ ዝንጀሮ ሁሉ ይረዳልና ጎልማሣው ዝንጀሮ ከዚያን ጊዜ በኋላ የአባቱን ሚስት ማለትም እናቱን ከአባቱ ቀምቶ ሊያገባ ሁሉ ይችላል፡፡ እነአቢይም ያደረጉት ይህንን ነው፡፡ አንድ ባለጌ ሰው እናቱን ሲያገባ የሚያደርገውን ሁሉ ጠያፍ ተግባር ነው እነሽመልስ አብዲሣ በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያሉት፡፡ የሰንበት ጽንሶቹ ወያኔዎችም ያደረጉት ይህንኑ ነው፡፡ እነዚህ በዕውቀትም በትምህርትም በግብረ ገብም እጅግ የተበደሉ ሰዎች የባለጌነትንና የዋልጌነትን ዕኩይ ምግባራት ከባሕርይ አባታቸው ከሰይጣን ዕጥፍ ድርብ በሚያስከነዳ ሁኔታ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸሙ ናቸው፡፡ ዋጋቸውም ያንኑ ያህል ነው፡፡

አሁን ለወያኔ ጊዜው ጥሩ አይደለም፡፡ የመጨረሻቸው ይመስላል፡፡ ፍርዱም ከላይም እንጂ ከታች ብቻ አይደለም፡፡ ኦህዲድ (ማለትም አቢይ) ከዚህ በኋላ ቢያፈገፍግ የራሱም መጨረሻ ይሆናል፡፡ የነብርን ጅራት አይዙም …፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን መጠንቀቅ አለባቸው፡፡ የሁለት ወገን ጭዳ እንዳይሆኑ የብልጦች ወጥመድ ውስጥ ዘለው መግባት የለባቸውም፡፡ አቢይ ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት አማራውን እየተጠቀመ ነው፡፡ በመቶና ሁለት መቶ ሽዎች የሚገመተው የኦሮሚያ ወታደር የት እንደተደበቀ ካለመታወቁም ባሻገር ለምን ዓላማ በሥውር ቦታ እንደተቀመጠ ከግምት ባለፈ አናውቅም፡፡ የፈረደበት አማራ ግን ደሴ ላይ አንድ ወቅት በአቢይ አሽሙራዊ ለበጣ የተወቀሰበትን ያሉትን ጥቂት የልዩ ኃይልና የሚሊሺያ አባላት ይሄው አቢይ በጦርነት ካስጨረሰ በኋላ እሱና የቆመለት ድርጅት ኦህዲድ/ኦነግ እንደልባቸው የሚፈነጩባት አዲስ ኢትዮጵያ ለመመሥረት ዕቅድና ፍላጎት ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ ህልማቸው እውን የመሆን ዕድሉ የመነመነ መሆኑ የታመነ ቢሆንም መጠንቀቅ ግን ከተጨማሪ ጉዳት ይታደጋልና የነዚህን ብልጣብልጦች ግልጽ ስድነት መከታተል፣ ራስን ከዕልቂት ለመከላከል መጣርና ዙሪያ ገባን ማማተር  ተገቢ ነው፡፡ አጭበርባሪ ቁጭ በሉዎች መሆናቸውን ተረድቶ ራስን የማዳኛ ብልኃት ከአሁኑ መተለም እጅግ ወሳኝ ነው፡፡

በዚያ ላይ ሽመልስና አቢይ እየተመሳጠሩ በተለይ አማራውንና ኦርቶዶክሱን በልዩ ሥልት እያስፈጁት ነው፡፡ እያስፈጁትም የዓዞ ዕንባ ያነባሉ – ከነሱ ያልጠበቅሁት አስገራሚ ብልጥነት ነው፤ ወያኔ በደምብ ነው ያሰለጠነቻቸው፡፡ መከላከያን ያለተተኪ ኃይል ከየአካባቢዎቹ በማስወጣት አማራን በኦነግ ሸኔ በግላጭ ማስጨፍጨፍን አሁን ሀገር ከወያኔ ጋር ጦርነት በገጠመችበት አስጨናቂ ወቅት ሳይቀር ሥራየ ብለው ተያይዘውታል፡፡ አክራሪ ኦሮሞዎች ብልጥ ቢሆኑ ኖሮ ቢያንስ በዚህን ወቅት ማንንም መንካት አልነበረባውም – የነሱን ሥልጣን ለማስጠበቅ አማራው በጦር ግምባ,ር እየተፋለመ ባለበት ወቅት በጓዳ ያልታጠቁ ሕጻናትና ሴቶች አማሮችን በያሉበት መምታት ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ ሽመልስ ይሉኝታንና ሀፍረትን በማያውቀው ንግግሩም ሆነ በግልጽ በሚታይ ተግባሩ አማራን ካልጨረሰና በአማራ ከርሰ መቃብር ላይ የኦሮሙማን አበባ ካልተከለ የኅሊና ዕረፍት እንደሌለው ተረድተናል፡፡  በተለይ አማራንም ሆነ ኢትዮጵያን በአጠቃላይ የሚጠብቀው ፈጣሪ መሆኑ በጄን እንጂ እንደእስካሁኑ አካሄዳቸው ወያኔዎችና ተተኪዎቹ ኦህዲድ/ኦነጎች እስካሁንም ቢሆን አማራን ከምድረ ገጽ ባጠፉት ነበር፡፡ በተበላ ዕቁብ የምትጃጃሉ አማሮች ተጠንቀቁ፡፡ አቢይን ማመን ጉም መዝገን መሆኑን ተገንዘቡ፡፡ ሥልጣን ወዳድን ሰው ማመን ቀብሮ ነውና እርሱን ከጉድ ካወጣችሁት በኋላ ጉዳዩ ሲሞላ እናንተን መቀመቅ እንዳይከታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ ከነአምባቸውና አሣምነው ጽጌም ተማሩ፡፡ አምባገነኖች ዐውሬ ናቸው፤ አምባገነኖች ጨካኞች ናቸው፤ አምባገነኖች በሥልጣን ላይ ለአንዲት ቀንም ቢሆን ለመቆየት ሲሉ የትዳ ርአጋራቸውንና የአብራክ ክፋያቸውን ሳይቀር ለሰይጣን እስከመገበር ይደርሳሉና አቢይ ሳቀልን ብላችሁ ጉድ እንዳትሠሩ መጠንቀቅ ያለባችሁ ሰዎች ምን ጊዜም ጥንቃቄ አይለያችሁ፡፡ ይህ ሰው በጥርሱ ገዳይ ነው፤ ይህ ሰው እየሸነገለ ወደ መቃብር የሚሸኝ የጥልቁ ጨለማ ገዢ ወኪል ነው፤ ከምላሴ ፀጉር ይነቀል!

ወያኔን በማጥፋተ ረገድ አባታቸው ሰይጣንን ጨምሮ ሁሉም ቢረባረብና እነዚህን ጉግ ማንጉጎች አርቆ ቢቀብራቸው ለኢትዮጵያ ትንሣኤ አንድ እርምጃ ወደፊት እንደመራመድ ይቆጠራል፡፡ ቀሪው … ስለቀሪው ወደፊት እንነጋገራለን፡፡ የነገ ሰው ይበለን፡፡

[email protected]

3 Comments

 1. What you said is realistically and powerfully true !!! Appreciated !!
  It is absolutely essential to get rid of these deadly ethnocentric ruling elites of both the so called Prosperity and their former mindmaster ,TPLF !
  Yes, it is absolutely compelling to have a well matured and rational understand about these political elites who are now in a very dangerously bloody war that is causing and would cause an incalculable damages not only between themselves but most dangerously to the people in general!
  True, it is quite necessary to think and act in such a way that these politicians of EPRDF/PROSPERITY/TPLF should be challenged and forced to get out of the very bloody political business as if what they did for a quarter of a century and during the last more than two years of “change” was/is not enough!
  It must be clear that there would be no any relatively significant sense of peace and stability leave alone democratic transition that would lead us to the establishment of a true democratic system !!

 2. አውሮፕላን ልኮ ቦምብ መጣል ጀግንነት ከተባለማ መንግስቱ ኃይለማርያምም ጀግና ነበር በሉን። አብይ ተዋርዶ ይሸነፋል በጦርነት ።ተደማሪ ከብቶች እንደ ከብት መታገዳችሁን ትታችሁ እራሳችሁን ጠብቁ አለበለዛ ውርድ ከተጋሩ ብለናል። አብይን ሰምታችሁ ትግራይን ለመውረር ያሰፈሰፋችሁ ዝግ ብላችሁ አስቡበት ከአሁኑ በጊዜ ። አይናችሁ እያየ ወደ እሳት አትማገዱለት። እንደ ሰው አመዛዝኑ እና ሕሊናችሁን አሰሩት።ማን ከብት እንደሆነ ማን ሰው እንድሆን መለያው አዕምሮአችንን ተጠቅመን ዛሬ የምናደርጋቸው ነገሮች እንክርዳድ እና ስንዴው የሚለይበት መሆኑን መገንዘብ መቻላችን ነው ። የትም አታመልጡም ተጋሩ የገባችሁበት ገብቶ የዋጋችሁን እንደሚሰጣችሁ አትጠራጠሩ።

  CALMLY USE YOUR HEAD , DO NOT FALL FOR THE PEER MEDEMER PRESSURE, DO NOT BELIEVE THE HYPE.
  THE CURRENT TALK ABOUT THIS MEDEMER FREAKS BATTLING IN A CIVIL WAR AGAINST TPLF IS JUST A HYPE NOTHINGELSE !!

 3. አለም ሰት ልታጠፋን ነዉ ማለት ነዉ? የገባንበት ገብተህ? እንዲህ አይነት ልብ ካለህ ታዲያ አማርኛ መንገድ ላይ ማዉራት ምነዉ ፈራህ? እነደዉ ጠቅላላ ቱሪናፋ ናችሁ ማለት ነዉ? በዚህ አፍህ ኢትዮጵያን ሁለተኛ ታያታለህ እዛዉ ስታለቅስ ጥልያን ካዘነ እንደገና ይገዛሀል መቼም ላንተ ክብር ነዉ። እንዳንተዉ ተስፋና ዘርአ ያእቆብ የሚባሉ የከሰሩ ትግሬዎች አሉ እየመጡ የሚላቀሱ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ አትምጡ እዛዉ ተጋሩ ተላቀሱ ለኢትዮጵያዊነት ክብር አትመጥኑም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.