ነፋስ ሰውን ነዳው! – በላይነህ አባተ

ገዳዩ ጨፍጫፊው ደም አፍሳሹ ብሎ፣
ትናንትና ማታ ሲጮህበት አድሮ፣
አቀፈና ሳመው ዛሬ አብዬ ብሎ!

አጥንቱ ውልክፋ የዛሬ ዘመን ሰው፣
ቀጥ ብሎ እማይቆም እንደ ሊጥ ልምሾ ነው፡፡

እስተ ቀራኒዮ ብሎ ማዩ ሁሉ፣
ሲሶ መንገድ ሳይደርስ ይሰበራል ቃሉ፡፡

የሰው የበግ መንጋን ምንድን ይለያቸው፣
አሳራጅ እረኛ እኩል ተነዳቸው?

ይብላኝ ለሞተ እንጅ ቋሚንስ ደልቶታል፣
ገዳዩ ሲዘፍን እስክስታ ያወርዳል፡፡

ላባ የሚከብደው የነፋስ ሽውታ፣
ምን ያህል ቢቀለው የሰውነት ገላ፣
አንስቶ አንሳፈፈው እንደ በጋ ትቢያ!

ጣምራ እጅ አያነሳው ሲባል የነበረው፣
የቀጣፊ ትንፋሽ ሲጠርገው አየነው፡፡

እየቀላቀለ ነፋስ ስልነዳው፣
ከባድና ቀላል እኩል ሆነ ዋጋው፡፡

የዚህ ዘመን ነፋስ ከዛር የከፋ ነው፣
እንኳን ገለባውን አለቱን አነሳው፡፡

ታጋዩ በሰለ አፈራ ስንለው፣
ትል የወጋው ዱባ ክፍት ሆኖ አገኘነው፡፡

በአልፎ ሃጂ ነፋስ የተወሰደ ሰው፣
ሰማዩ ሲሰክን ስካሩ ሲለቀው፣
በየ ቁጥቋጦው ሥር ወድቆ እሚገኝ ነው፣
ብርሃን ሲነጋ ወጥቶ መመልከት ነው፡፡

እባክህ ነፋሱ እረፍ አደብ ግዛ፣
በሰማዕት መቃብር አረምን አትዝራ!

እባክህ መለኮት ለሰው ክብደት ስጠው፣
እንደ ገብስ ገለባ ነፋስ እንዳይጠርግው፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ህዳር ሰላሳ ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

ተጨማሪ ያንብቡ:  ተሳጥናኤል ጋራ ሽምግልና ሲሉ!

2 Comments

  1. አቶ በላይነህ
    አንተ እኮ እንደው በአማራ ስም ትነግዳለህ እንጂ ድሮም ጉዳይህ ከአቢይ እንደሆነ ግልጽ ነበር፤፤ በአቢይ ላይ እንዲህ የታወረ ጥላቻ ሊያሳድርብህ የሚችል አንድ ሌላ ምክንያት ብዬ የምጠረጥረው አለኝ፤ ግን ለጊዜው ይቆይ፤፤ በግልጽ አቢይ የወሰደውን የመከላከል እና ህግ የማስከበር እርምጃ እቃወማለሁ ላለማለት፤ “ለምን አቢይን ደገፋችሁት” ብለህ በስታየል እየነገርከን ነው፤፤ እንዴት ዓይነት ንቅተ ነው አያ? ሰው “እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ” ሲል አይታወቀውም ማለት ነው? ሌላው ሁሉ “ቂል” ነው ብሎ ነው የሚያስበው ማለት ነው? ህመም መሆን አለበት!
    ይህ “ጦርነት” ከብልጽግና፤ ክህወሃትና ከአቢይ በላይ መሆኑ እስካሁን አልገባህም፤፤ እረ በናትህ ግጥም የመጻፍ አራራ ካለብህ ሌላ አርዕስት ፈልግ፤፤
    “You are either with US or your are with THEM!’
    Ethiopia Shall Prevail!

  2. ተጋደልን አሉን ጀምረን ጦርነት

    እስክስ ሲሉ አድረው ከበው ርችት

    ኢህአዴግ ኢንሳ ጀርባዬን እከክልኝ በመባባል

    ተጋደልን አሉን ሊያሞኙን እንደ ጅል

    እስቲ መስክር የአረብ ሸማች ያየኸውን

    ኢሳያስ ሲያሻሽጥ የኢትዮጵያን መትረየስ ባዙቃን

    ወያኔ እና ሻዕቢያ ደለቁ ከበሮ ተመሳጥረው

    ጦር መሳሪያችንን በግብጽ ሲያዘርፉን አማራን አሳርደው

    ኦነግ ሸኔ አባ ቶርቤ ገለመሌ

    ነው የአብይ እና የደብረጽዮን ጀሌ

    አማራ ሞኞ አትታለል ሳይኖርህ የሚያዝንልህ መሪ

    ገዳይህን የሚሸልም ነው ተብዬው ህግ አስከባሪ

    አንድ አይንህን ከፍተህ እደር አማራ

    ጣትህን ከቃታህ አድርገህ ለመትረፍ ከሞት መከራ

    እንኳን ሰንኮፍህን ሊያስነቅል

    አልሞከረም ሊያስከፍል ካሳ እንደገባው ቃል

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share