August 3, 2020
15 mins read

ለዶ/ር አብይ አህመድ የቀረበ ጥሪ – ሰርፀ ደስታ

ወቀሳዬን ረዘም ያደረኩት እንዲያስተውሉት ነው፡፡ እኔም ብዙ ተስፋ ካደረጉና ቆይቶ ግን እጅግ ካዘኑ ነኝና፡፡ ለበርካታ ወራትም እንዲህ ያለ ጽሁፍ ጽፌ አላውቅም፡፡ በሁኔታዎች እጅግ ስለተበሳጨሁ፡፡ እርሶ ወደ ስልጣን እንደመጡ ብዙዎች የናፈቁትን ኢትዮጵያዊነት ያገኙ ስለመሰላቸው ስለእርሶም ሆነ አብረዎት ለነበሩ የለውጥ መሪዎች ትልቅ ድጋፍና ብዙ ምስጋናና ዝማሬም ሁሉ ሳይቀር ከሕዝብ ዘንድ ሲቀርብልዎት ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ሁኔታ ብዙም አልቆየም፡፡ ምን አልባትም ሶስት የረባ ወራት እንኳን ሳይሆን ነበር በናፍቆት ከጠበቅንለት ኢትዮጵያዊነት ይልቅ በ27 ዓመቱ እንኳን  ወደ አላየንው እጅግ የከፋ የዘረኝነትና የሥርዓተ አልበኝነት ምልክቶችን ማየት የጀመርንው፡፡ በተለይ ደግሞ እርሶና የመሩት ቡድን አሜሪካ መጥቶ ከተመለሰበት ቀን ጀምሮ የሆነው ሁሉ ለማመንም በሚከብድ ሁኔታ እጅግ የከፋ እየሆነ መጥቶ ይሄው አሁን ያለንበት ደርሰናል፡፡

ያኔ መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ በተናገሩት የመጀመሪያው ንግግርዎና ከዛም በኋላ በተግባርም እስከሶስት ወር ገደማ ያየናቸው የመሰሉን ተስፋዎች ሁሉ ድንገት ክስም አሉ፡፡ በዛች አጭር የመጀመሪያዎቹ የሲመትዎ ቀናት ብዙ መሠረታዊ የነበሩ ጉዳዮች  ተቀይረው የተናፈቀው ማንነታቸውን ያዙ፡፡ ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ ቀደምት መሪዎች በመሪዋ አንደበት በይፋ ሲወደሱ ሰማን፣ ከ20 ዓመት በላይ የዘለቀው የኢትዮ-ኤርትራን የጦርነት ስጋት ቀርቶ ዓለም ሁሉ ተዓምር በሆነበት ሆኔታ እርሶና የኤርትራው መሪ የሁለቱ አገራት የገጠር ቀበሌዎች ሳይቀር በጋራ ተራመዳችሁ፡፡ ለ27ዓመት ተከፍላ የነበረችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን አንድ አደረጉ (በእርሶ ውሳኔ ባይሆን ላለመዋሀድ ችግር እንደነበር እናውቀለን)፣ በተመሳሳይ በሙስሊሙም እምነት ተከታዮች ተፈጥሮ የነበረውን መከፋፈል ወደ አንድ አመጡ፡፡ እነዚህን ሁሉ ነገሮች አስታውሳለሁ፡፡ በእርግጥም ያኔ በነበረዎት በቃልም በተግባርም በተገለጠው የመሪነት ቁርጠኛ የሚመስል አካሄድዎ በእርግጥም በዓመታት እንኳን ሊታሰቡ የማይችሉ ክንውኖችና ድሎች በቀናቶች ሆነዋል፡፡ ለመልካም ነገር ሲነሱ እግዚአብሔርም በብዙ እጥፍ እንደሚያከናውንም በመጽሐፍ ያነበብነው በእውን በአገራችን ሲሆን አይተን ነበር፡፡  ሆኖም ከላይ እንደጠቀስኩት ጥቂት ወራት እንኳን በዛ መቀጠል አልቻለም፡፡ የ27 ዓመቱ የዘረኝነትና ጥላቻን ዘር በገፍ ማጨድ የጀመርንው ወዲያው ነበር፡፡

መጀመሪያ በብዙ ቦታዎች መንገጫገጩን ይረጋጋል ብለን ስንጠብቅ ጭራሽ ኢትዮጵያን በይፋ እናፈርሳለን እያሉ ከራሳችን ከተማ ከአዲስ አበባ የሚፎክሩብን በተግባርም ራሳቸውን ሲያደራጁና ኢትዮጵያዊነትን በፍጥነት ለመደምሰስ ሲዘጋጁ አየን፡፡  እዚህ ውስጥ ነበር የእርሶም ማንነት በብዙዎች ዘንድ ጥያቄ ውስጥ የገባው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነገሩን በእርጋታ ተጠባበቀ፡፡ ምንም የለም፡፡ በግልጽ በ27 ዓመት በኦነጋውያን፣ ኦሮሞ ምሁራ ነን በሚሉና በወያኔ በአንድነት የኦሮሞን ወጣት ከኢትዮጵያዊነት ሙልጭ አድርገው አውጥተው የእነሱ አስተሳሰብ ባሪያ እንዲሆን እንዳደረጉት ታዘብን፡፡ ብዙ ጊዜ ስለዚህ ነገር እኔ አስታውሼ ነበር፡፡ ጥንቃቄ ካልተደረገ አደጋ እንዳለ፡፡ በአይኑ ሲገድሉትና፣ ብዙ ግፍ ሲያደርሱበት የነበሩት ጠላቶቹን ፍጹም እንዳይመለከት ሆኖ ጠላቶቹ በሰበኩት በጥላቻ ትርክት ተጠመቀ፡፡ የኦሮሞን ማህበረሰብ በከፍተኛ የአገሪቱ የታሪክ ማማ ላይ ያስቀመጠውን የሚኒሊክን ሥርዓት ጭራቅ ተመስሎ ተተረከለት፡፡ ይህ ሥርዓት ደግሞ በእርግጥም ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አፍሪካ በሙሉና የተጨቆኑ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ሳይቀር ቀና ብለው እንዲሄዱ ምልክት የሆነላቸው ነበር፡፡ ኦሮሞ ከታላቁ ጎበና ዳጬ ይልቅ ወሮበላውና ከማንነቱ አውጥቶ ለጠላቶቹ እየገበረ የሚነግድበት ጀዋር ጀግናው ሆነ፡፡ አዝናለሁ!  የሚኒሊክ ታሪክ ምን ዓልባትም ከ80 በመቶ የሚሆነው አመራር የነበረው ከዚሁ ማህበረሰብ ከወጡ አባቶች ነበር፡፡ ይገርማል፡፡ እንግዲህ እነዚህ ታላላቅ አባቶች ደምና አጥንታቸውን ገብረው አገር ሰርተውና ጠብቀው ያስረከቡትን አገር አፈርሳለሁ እያለ መደንፋት ቀጠለ፡፡ ውጤቱ ለወራዳ አስተሳሰብ ባሪያ መሆን ሆነ፡፡  ከዚህ የአእምሮ መታወክ እስካልተፈወሰ ድረስ ይቀጥላል፡፡ ቀጥሎ ይሄው የዛሬው ትውልደ ኦሮሞ ነፍጠኛን (አማራን) መጥላት መሠረታዊ እምነቱ አደረገ፡፡ ውጤቱንም አየነው፡፡

ይሄ በኦሮሞ ልጆች ላይ የተፈጸመው የጥላቻና ዘረኝነት መርዝ ወደሌሎችም በፍጥነት እንዲዘልቅ ተደረገ በዚቸው እረሶ በመሩባት ሁለት ዓመታት፡፡ ከእኛው ከተማ ይሄው ትዕዛዝ ይሰራጭ ጀመር፡፡ በድብቅ ሳይሆን በይፋ፡፡ ይሄ ሁሉ ሲሆን የእርሶ አስተዳደር ነገሮችን ሕግና ሥርዓት ከማስያዝ ይልቅ ለኢትዮጵያ ጠላቶች ከለላ ሰጭ ሆኖ አይተናል፡፡ አዝናለሁ በጥላቻና ዘረኝነት የተመረዘው ኦሮሞነት ከዛም ለዘመነታ ሲሸምቅ የነበረው የእስላማዊ ጸረ-ኢትዮጵያ ኦሮሞነት በኢትዮጵያውያን ሁሉ ላይ ጥላውን አጠላ፡፡ ኦሮሞነትንም በይፋ አዋረደ፡፡ የአባቶቹን ታሪክ ክዶ የወረበሎችን የጥላቻና ዘረኝነት ትርክት ሲጋት የኖረው ትውልድን ለማስነሳት አሳማኝ ጉዳይ ማንሳት አይጠበቅም ነፍጠኛ፣ ሚኒሊክ፣ የመሳሰሉት ማለት ብቻ ነው፡፡ በግልጽ ይሄው አየንው ወጤቱን፡፡ በነገራችን ላይ ሰሞኑን መንግስት የማያውቀው ሳተላይት የተባለው ነገር አሁንም ባይድበሰበስ እላለሁ፡፡ እኔ መንግስት መዋቅር ውስጥ አደለሁም፡፡ ግን ስለዚህ ጉዳይ ቀደም ብሎ አውቅ ነበር፡፡ ያወቅኩትም በይፋ ከወጣ በዛው በአዲስ አበባ በሚኖሩ ዲፖሎማቲክ ጽ/ቤጾች ነው፡፡ የጥቅምቱ ወር 86 ሰዎች (መንግስት ያመነው) ከተጨፈጨፉበት ቀደም ብሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የተንቀሳቃሽ ስልክ በሕገወጥ ወደ እነዛ ጭፍጨፋ ወደተደረገባቸው ቦታዎች እንደገባ የአንዳንድ መንግስታት የደህንነት ተቋማት ጠቁመው ነበር፡፡  መረጃውም ወጥቶ የነበረው ከደህንነት ጋር በተያያዘ ነበር፡፡ ይሄን ግን የእርሶ መንግስት አልተናገረም፡፡ ዛሬ ሳተላይት አገኘን ስትሉ እነዛ ሞባይሎችም ከቴሌ ውጭ በሆነ መስመር ሲሰሩ እንደነበር አሁን ነው የገባኝ፡፡ በወቅቱ የደህንነት ስጋት እንዴት ሊሆን እንደቻለና መረጃውን ያወጡት እንደተናገሩ ብዙም ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር፡፡

ከላይ የጻፍኩትን ለማስታወስ ያህል ነው፡፡ በእነዛ ትቂት መልካምና ተስፋ በመሰሉን ወራት ብዙዎቻችን ኢትዮጵያን በአለን አቅም ሁሉ በመረባረብ አገራችን አሁን  ካለችበት የኑሮ ምስቅልቅል አውጥተን ሌሎች የደረሱበት እናደርሳለን የሚል ትልቅ እንቅስቃሴ ጀምረን ነበር፡፡ እርሶ ያሉት ከዲያስፖራ የሚሰበሰብ በቀን አንድ ዶላር ማለቴ ሳይሆን በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር በተማሩ ኢትዮጵያውየን ወደ አገራችን ለማስገባት ብዙ ተስፋ አድርገን ነበር፡፡ ሐሳባችንም በተለያየ ዘርፍ ኢትዮጵያን ሊያለሙና በቴክኖሎጂ ሊያበለጽጉ የሚችሉ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

ያ አልፏል አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ይሄን አጀንዳ መነጋገር ጀምረናል፡፡ ከብዙ ነገር አንጻር፡፡  ትውልድን፣ ሕዝብን፣ አገርን ወደተሻለ መቀየር እንችላለን፡፡ እንችላለን ስል አዎ እንችላለን! ለዚህ የምንፈልገው የኢትዮጵያ መንግስትን ቁርጠኝነት ብቻ ነው፡፡  በእልህና ቁጭት ነው ብዙዎች የተነሳሱት፡፡ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን እንጂ የወሮበሎች መፈንጫ ሆና ማየት አንፈልግም፡፡ ዛሬ እውቀትና ጥበብ የማይፈልግ ነገር ቢሆን ፖለቲካና አክቲቪስትነት ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ሌላ ቀርቶ ገበሬው ሳይቀር የፖለቲካ ተንታኝ እየሆነ መጥቷል፡፡ ፖለቲካም ሆነ ሌላ የጥቂቶች እንጂ የ100 ምናምን ሚሊየን ሕዝብ ጉዳይ ሆኖ አገር ከመጥፋት አትድንም፡፡ ያ በአመጽና ሕዝብን ሁሉ ወደ ራሱ ገበያ ለመሳብ በሴራ መርዘኛ ሐሳቦችን ወደሕዝብ እየዘራ እርስ በእርሱ ሲጫረስ የኖረ የ60ዎቹ ትውልድ ያመጣብን ችግር ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የምንፈልገው ጥቂት በውዴታቸው እዛው ፖለቲካቸው ላይ ቀርተው ሌላውን ሕዝባችንን ወደ አገሩ መመለስ ነው፡፡ ወደ አገሩ ስል ወደ ኢትዮጵያዊነት፣ በቁጭትና በሚደርስበት ራዕይ ማሰማራት፣ ማዘመን፡፡ ይሄን ለማድረግ ብዙዎች እየተሰባሰብን ነው፡፡ ይሄን የምለው አሁንም ይሰመርበት በስሜት አደለም፡፡ የምናውቀው የሚቻል ነገር ስላለ እንጂ፡፡ በዚህ ሂደት የነበሩ የአስተሳሰብ ጋሬጦች እንቅፋት እንዳይሆኑ ግን መንግስት ቁርጠኝነቱን ያሳይ፡፡ ይሄ ጥሪዬ ከብዙ ወራት በኋላ ነው፡፡ ክብር የሚሆነው ሕዝባችንንና አገራችንን የምንለውጠበት ሥራ ነው፡፡ ኦሮሞነት፣ አማራነት ወይም ሌላ አደለም፡፡ እኔ እነዚህ ቃላቶች የምጠቀመው ሰው በዚህ ስለለመደው እንጂ ዛሬ ኦሮሞ፣ አማራ ወይም ሌላ የተባለውን ሕዝብ ማንነቱን አውቀዋለሁ፡፡  አሁን የምጠይቅዎት የኢትዮጵያውያን (በዋናነት የምሁራን) አገራችንን ለማልማትና የሕዝባችንን ኑሮ ለመቀየር የእርሶ አስተዳደር ቁርጠኝነቱን ሊያሳየን ይችላል? ሐሳብ ሰጥተን ዞሮ ለማለት አደለም በተግባር ራሳችን ሰርተን ለማሰራት እንጂ፡፡ ትውልድንና አገርን ማዳን ግዴታችን ነው፡፡

አመሰግናለሁ!

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ! አሜን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop