ለፈርስት ሂጅራ ሒማም ሀጂ ሼክ ኻሊድ በህግ አምላክ!

አባት ምን ማለት ነው? መሪያቸው አቶ ጁሃር የአባቱን ስም አልጠራም የታለቁን ነቢይ ስም ማጉደፍ ነው። የሠራው ካልኩሌሽን ነው። “ Ethiopia out of Oromia” ኦሮሚያ ውስጥ ያሉትን አማራ ክርስቲያን አንገት አንገቱን በመጫና በገጀራ ” እንዳለና እንደፎከረ በትንሹ ለሶስተኛ ጊዜ ንፁሃን ሰዎችን በአርመኒያዊ ግድያ አስጨፈጨፈ። የጣሊያን መከላከያ ሚኒስትርበወረራው ጊዜ አባቶቻቸው በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ለሰሩት አረሜናዊ ተግባር በመፀፀት ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ላይ ለፈፀምንባቸቸው ፋሽሽታዌ ተግባር መካስ አለብን ሲሉ ፡ የኛው ትንሹ አርመኔ ግን መፀፀት የሚባለው የለውም።በሄደበትና ቤደሰኮረበት ቦታ ሁሉ “በጡጫ ፡ በጉልበት ፡ በሜጨ ወዘተ የማንአለብኝነት ዕብሪት ሲደነፋ በህግ አምላክ አልተባለም። በስደት እንደልቡ ይኖርበት ከነበረው አገረ አሜሪካ ተቀምጦ ሲረጭ የነበረው መርዝ ፡ ወደሃገር ከተመለሰ በኋላም ህዝብ በህዝብ ላይ እንዲነሳ ፡ በሐረሪ ባደረገው ስብሰባ የረጨው መርዝ በአደስ አበባ ጉዳይ በምርጫ የማያገኛት ከሆነ በቂ ሰራዊት እንዳለው በሰሜን ከአማራው ልዩ ኦሮምይ ዞነ፣ በደቡብ ፡ በምሥራቅ እና በምዕራብ በተደራጀ መልኩ፤ሃይል እንዳለ ፎከረ ፡ በሲዳማም አዋሳ ተገኝቶ ለሲዳማ ህዝብ ባደረገው ንግግር የክልል ጉዳይ በሠላም ካልሆነ በኃይልና በጉልበት ፡ ወዘተ… እያለ ህዝብን ለአመፅ ሲያነሳሳ ፡ ወደ አገር እንደገባ በየክልሉ እንደ አንድ ንጉሥ አየታጀበ ኢትዮጵያዊነትን ሲሸሸረሽር። አመፅ ሲያነሳሳ። እንዴ! ህግ የለም? ሰው የለም? መንግሥት የለም? በህግ አምላክ የሚል። በጉልበትህ አምላክ ሲባል ባሰበት። ለነገሩ ይህንን ለውጥ ተከትሎ ሲገባ በኢትዮጵያ ሁለት መንግስት አንዳለ አሰረግጦ ነግሮናል። በደ/ር አቢይ የሚመራውና በእሱ የሚመራው ቄሮ። ከአባቱ ትሃት በወረሰው የትግልት ስል፤ ትሃት ከትግራይ ጀምሮ እስከ ዳር ሀገር የህዝባዊ ድርጅቶችን ፡ የወጣትና የሴቶች ማህበራትን፣ የገበሬና የአምራች ህብረት ሥራ ማህበራትን ገንዘብና ባንኮችን ለድርጅትና ለግል እየዘረፉ ለሥልጣን በቅተዋል። ኦነግሞ በሰላማዊ ጥሪ ወደ ሀገረ ሲገባ በመቐለ በኩል የትግል አርማና ስልት ተቀብሎ ገባ። በአንድ ሀገር ሁለት መንግሥት። በአንድ ሀገር ሁለት መከላከያ። ኦቦ ዳዎድ ስለ ኦነግ ሰላማዊ ትግልና ትጥቅ መፍታትን አስመልክቶ “ፈቺና አስፈችውን እናያለን” ብለው ነበር። ለሽማግሌዎችና ለአባገዳዎች የማስፈታቱ አደራ ተሰ።

መፍታት አይደለም የታጣቂ አይሉን ብዛት መጨመርና በከተማዎች የፋኖና የኮማንዶ ቡድን በመደራጀትና በሎጅስቲክ በመደገፍ በተከብቤአለሁ ቀጭን ትህዛዝ አዘል መልእክትና በሰኔ 22ና 23 በአዲስ አበባና በቫቨመኔ ፡ በአርሲ፣ በሃረር፣ በባሌ ወዘተ…የደረሰው የተፈጸመው አረመኒያዊ ተግባር፣ በአምላክ ቸርነትና በመንግሥት ንቃት ሳይፈጽም የተኮላሸው ዕቅዳቸው ዓብይ ምስክር ነው።

ኢትዮጵያን የማፍረስ ፅቅድ ተግባራዊ የሚሆነው የኦርቶዶክስ እምነት ማጥፋት እንደሆነ በማሰብ ፡ የእምነቱ ተከታዮችን ህይወትና ለዘመናት ያፈሩትን ንብረት አየመረጡ በተደራጀና በተጠና ሁኔታ አጠፉ ፡ አወደሙ ፡ አቃጠሉ።

ኢትዮጵያ በአለም ባሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ከፍ ብላ የምትነሳ አገር ነች። አበሽ አቢሲኒያ። ብዘዎች የመሀከለኛው ምስራቅ ሙስሊም ወንድሞቼ ስለ አገሬ ከኔ የበለጠ ክብርና ስለታሪኳ እውቀት አላቸው። የዕድሜ ወሰን ሳይወስናቸው። ትንሹም ትልቁም። የአምነቱ መጀመሪያ ስለሆነች።ቢላልን ይጠቅሶአል። በእጅ የያዙት ወርቅ …ይላሉ አበው። ታላቂቷን አገር እኔን መሠል ትናንሽ ሰዎች አነሰነ እናሳንሳታለን

ኦርቶዶክሳዊነት ምን አጠፋ? ኢትዮጵያዊነት ምንአጎደለ? ነቢዩ መሃመድ ተከታዮቻቸውን ቁርሸዎች ሲያሳድዱአቸው ሂዱ ወደእንግዳ ተቀባዩ የአበሻ ክርስቲያን ንጉሥ ብለው ነው የላኩአቸው። ንጉሱም ለሕዝቡ አውጀው ህዝቡም በእንክብካቤአስተናገዱአቸው። አኖሩአቸው። ኢትዮጵያ አንድ ነች። አትፈርስም። ታላላቆች መንግስታት እንግሊዝ፣ ፈረንሣይና ጣልያኖችም በሶስትዮሽ ስምምነት ኢትዮጵያን ለመውረር ለመቀራመት ሞክረው በብልሁ መሪ ምንሊክ ረቂቅ አያያዝ አልተሳካላቸውም።

አረ በፈጣሪ እነዚህ ንፁሃን ዜጎች ምን አደረጉ? የሰው ልጅ ሞቱ አንሶ አንዴት እንደ በግ ተበልቶ በሚንጦ ይሰቀላል? አምላክ በአምሳያው የፈጠረውን ሰው ገድሎ በሞተር ብስክሌት ሬሣውን አስሮ መጎተት የሸሪያ ህግ ነው? ሃይማኖታዊ ትውፊት ነው? እረ የአምላክ ያለህ!

ይህ ሁሉ ግፍ ለምን? በንፁሐን ላይ። አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ ይላል የሀገሬ ሰው። አላህ በሚያውቀው ለእውነት ይቁሙ። ግንማቆሚያው የት ነው?

አባታችን? ህግ የለም?ህግ አስከባሪ የለም? መንግስት የለም?ሀገር የለም?

በህግ አምላክ!!

ፈለቀ ሃይሌ

 

<div dir=”auto”></div>
<iframe src=”https://www.youtube.com/embed/j3gJ3Pj_6KE” width=”560″ height=”315″ frameborder=”0″ allowfullscreen=”allowfullscreen”></iframe>

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.