እኔም እላለሁ – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

“በዝጌሃር ! ሆ ሆ!ሂ ሂ!ሃ ሃ!
ሆ ሆ!ሆ ሆ ሆ!
ሄ ሄ ሄ ! ሃ ሃ ሃ !

ሐሰብን ለመግለጽ

ዳግመኛ ገብቼ በልሜ ተማሪ ቤት
እማር ይመስለኛል ንባብና ጽሕፈት፡፡
ድርሰት ነበርና የያዝሁት ሥራዬ
የኔታ ምናልባት ያስረዱኛል ብዬ
ብዬ ጠየቅኋቸው
—እንዴት አድርጎ ነው ሐሳብ አስተያየት
የሚገልጸው ሰው?
የኔታ መለሱ
—ይህ አስቸጋሪ ነው፡፡
ከመነፅር ውጪ እኔን አግድም አይተው
ተረት ስማኝ አሉ፡፡
ባነድ ቤት ሲወለድ ልጅ ከነቃጭሉ
ደስታ ያድርጋል ቤተሰብ በሙሉ፡፡
ገና ወር ሳይሞላው ልጁን እያወጡ
እዩልን ይላሉ ዕንግዶች ሲመጡ፡፡
ጥቂት ውዳሴና ምስጋና ሽተው
ያን የመሰለ ልጅ በማፍራታቸው፡፡
አንዱ ከእንግዶቹ ልጁን ካዩት መሀል
“ የህ ልጅ ከበርቴ ነው የሚሆነው“ ይላል
በዚህም ቤተሰብ ያመሰግነዋል፡፡
አንዱ “ይህ ወንድ ልጅ ታለቅ ባለ ሥልጣን
ታላቅ ሹም ይሆናል“ ሲል ያሰማል ቃሉን
ባዩም ከመስጋና ያገኛል ድርሻውን፡፡
አንዱ “ይህ ልጅ ይላል “ አይቀርም መሞቱ “
ዱላ ያጠግቡታል ይህን በማለቱ፡፡
ልጁ ሰው ነውና እርግጥ ነው ይሞታል፡፡
ትልቅ ሹም ይሆናል ከበርቴ ይሆናል
ማለት ግና ሐሰት ለመሆን ይችላል፡፡
ሆኖም ሲያስመሰግን ሲያስወድድ ሐሰት
የማይቀረውን ሞት አይቀርም ማለት
የበትር መዓት ነው ያተረፈው ምርት፡፡
አልፈልግም እኔ ውሸት መናገር
አያምረኝም ደግሞ ዱላና በትር፡፡
ጠባይህ ከሆነ እነደዘህ እንደልከው
“ሃሃሃ !አያችሁት ያንን ልጅ?“ ማለት ነው
ማለት ነው “በዝጌሃር ! ሆ ሆ!ሂ ሂ!ሃ ሃ!
ሆ ሆ!ሆ ሆ ሆ!
ሄ ሄ ሄ ! ሃ ሃ ሃ ! “

(መንግስቱ ለማ ከቻይናው ደራሲ ከሉሕሡን ሃሰቡን ወስዶ እነደጻፈው)

በሆሆ ! በሃሃሃ! በሄሄሄ! እንደዋዛ የሚያልፍ ዓለም ነው ፤ይህ ዓለም፡፡የህ ዓለም በከንቱ ውዳሴ የተሞላ
ነው፡፡ከእውነታ ይበልጥ ተረት ተረት የሰው ልጅን ማህበራዊ ኑሮ ጠፍንጎ ይዞታል፡፡ ሰው የኔ ነው የሚለውን ነገር
ሁሉ እነድታጣጥልበት ከቶም አይፈልግም፡፡በተለይ ባለው ቁሳዊ ሀብት ራሱን ከማህበረሰቡ የኑሮ ደረጃ አግዝፎ
የሚያይ ሰው ፣ሥለ እንከኑ አንዳች ብታወራ አይታገስህም፡፡በማህበራዊ መስተጋብራችን ውስጥ አብዛኛው ሰው ከራሱ
ጋር ጭምር የተጣላ መሆኑ ትዕግስት አልባ አኗኗሩ ይመሰክራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሻለቃ ኃይሌ አፍሪካን እንደሰቀላት አውርዶ ፈጠፈጣት?

በአደባባይ የሚያወራውና በግሉ የሚኖረው ኑሮ ጫማና ኮፍያ ናቸው፡፡ብዙው ሰው ህይወቱ ጫማና ኮፍያ መሆኑን
አሳምሮ ያወቀዋል፡፡በውሸትና በተረት ተረት የተሞላ መሆኑንንም በገባው ደረጃ ይገነዘባል።ሰው ሁሌም እውነትን
እነደሸሻት እና ተረትተረት ውስጥ ተደብቆ እንደኖረ ነው፡፡ ኑሮ ራሷ ከውሸት ጋር ፍቅር ይዞታል። በዘጠና ዘጠኝ
እብዶች መካከል አንድ ጤነኛ ቢገኝ መፈጠሩን ይረግማል።…
እውነትን የሙጥኝ ብለን እንኑር ካልን፣ኢየሱስን የሰቀለው የውሸት መንፈስ ከቶም አያኖረንም።ደሞም ዓለምን
በአሁኑ ገፅታዋ ያገኘናት ውሸት በምድራችን በመንሰራፋቱ ነው።

ሰው ፣ፖለቲካን፣ኃይማኖትን፣ ባስ ሲል ዘሩን፣ና ጎሳውን ፣ወዘተ በማመካኘት፣ ለግሉ ብልፅግና ሲል ፣
አምሳያውን ያለርህራዬ፣”እያሶገደ” ለዘመናት ኖሯል። ሰው እኩይ ድርጊቱን ፣በልቡ ሰውሮ ፣ሌላ በይፋ የሚነገር
፣ፖለቲካዊ፣ኃይማኖታዊ እና ዘራዊ ሰበብ በመፍጠር በሥሩ መሰሎቹን አሰባስቦ ፣ ፣እንደ ኔሮ.
ሂትለር፣ሞሶሎኒ፣ስታሊን፣ፒኖቼ ፣ቦካሳ፣ኢዲያሚን ( ሌሎች የአፍሪካ አምባገነን መሪዎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡)
በሚሊዮን የሚቀጠሩ ሰዎችን ፣እንደ እንስሳ በመቁጠር ፣በአብዮት፣ በፈጣሪ ፣ ተጨቋኝ በሚለው ህዝብ ሥም ፣በግልፅ
በአደባባይ ሰውን እየሳቀ ይገድላል፡፡ለህዝብ ጥቅም ሲል፡፡
ይህን እኩይ ድርጊት ለራሱና ለመሰሎቹ ፣ምቾትና ድሎት እንደፈፀመ እንዳይታወቅበትም በራሱ ታሪክ ፀሐፊዎች
አማከኝነት ነው ለህዝብ ጥቅም በግፍ ሰው መጨፍጨፉ ተዋዝቶ የሚቀርብለት፡፡ሥለትክክለኛ ጦርነቱ ፤ሐሰተኛ ታሪክ
የሚፃፍለት ፡፡ በከያንያኑም (በአዘማሪዎቻቸው) የሚዘመርለት፡፡

ጦርነቱ  ምክንያታዊ እንዳልሆነ፣ሰውን ያለህግ ያውም ምንም ወንጅል ሳይሰራ ፣ጥቅም፣ ሆድን፤ ሥግብግብነትን
ወዘተ፡፡ ሸሽጎ፤ በህዝብ ሥም፣ በቋንቋ ሥም፣በዘር ሥም፣በብሔር እና በብሔረሰብ ሥም ፣  “የሙጃሌ መውጫ መርፌ
ያልሰራ ” እበላባይ፣ደልቃቄ ፖለቲከኛ ሁላ፣  ለደሃ ቆሚያለሁ ብሎ ፣ደሃን እርስ በእርሱ እንዲተላለቅ ጩቤ
ማቀበል ተገቢ ነውን?

ይህ አስቀያሚ እውነት ከእትየጵያ ምድር ሊወገድ ይገባል፡፡በሀገሬ ላይ በህዝብ ሥም፤ በብሄርና ብሄረሰቦች
ሥም፤በቋንቋ ሥም ከኢትዮጵያ ጠላቶች የሚያገኙትን ገንዘብ እየረጩ እና እነሱም እየተደላቀቁ፣ ምስኪኑን ዜጋ
ባልገባውና ባለወቀው ጉዳይ በቸገረው ዳቦ እየገዙት ፣አትየጵያን የሚበታትን የጥፋት ኃይል ለማደርግ ፣የጥፋት
መንገዶችን በመቀያየር በታላቅ ሚሥጥር የሚሸርቡት ሴራ   በቃ መባል ይኖርበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግልጽ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን!

ሀገሬ የሰው ሀገር እንጂ የቋንቋ ሀገር አይደለችም፡፡እንኳን ከራሱ ዜጋ ጋር ይቅርና ከሌሎች ዓለም ህዝቦች
ገር በፍቅር የሚኖር.ፍቅር የሚገዘው ህዝብ ወይም ባለሀገር የሚኖርባት ወርቅ የሆነች የወርቅ ህዝብ ሀገር ናት
ሀገሬ፡፡ቋንቋዎቾ ውበቶቿ እንጂ የመታራረጃ ቢላዎች እንዳደሉም ባላገሩ አሳምሮ ያውቃል፡፡

ይህ ወርቅ ህዝብም እጅግ ሀይማኖተኛ  መሆኑኑ አትዘንጉ፡፡ራቁቱን እንደተወለደና ነገም ምንም ነገር ከዘህ
ዓለም ሳይዝ ራቁቱን ወደ መቃብር እንደሚወርድም አስቀድሞ የተገነዘበ አስተዋይ ህዝብ ነው፡፡፡ግብዝ ፖለቲከኞቻችን
ብቻ ናቸው ይህንን እውነት  በምቾት ባህር ሰምጠው የዘነጉት፡፡….

“በዝጌሃር ! ሆ ሆ!ሂ ሂ!ሃ ሃ!
ሆ ሆ!ሆ ሆ ሆ!
ሄ ሄ ሄ ! ሃ ሃ ሃ ! “.. አሉ አብዬ መንግስቱ፡፡ሆኖም ግን በግጥማቸው እውነትን ተናግረዋል፡፡

1 Comment

  1. ድጋፍ ያለመ በክምር ቢሊዮንዎች ተበድረው ከአገር ተሸከመው የጠፉ የውጭ አገር ተበዳሪ ኩባንያዎችን በሚጠቁም ባለሙያ ያሳየና::

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share