እያረጋጋ በመለሳለስ
ያመኑት ፈረስ ጥሎ በደንደስ
ይረጋግጣል እስከሚጨርስ፡፡
በሌላ በኩል የፈሩት ፈረስ
እንቅስቃሴው ሳያሰኝ ደስ
ስለሚደረግ ልጓም እንዲነክስ፣
በመንሸራተት በጎን ከግላስ
ከመውደቅ የከፋ ከቆመ አጋሰስ
የባሰ ጉዳት እምብዛም አይደርስ፡፡
ከኦነግ ፈረሶች ዐብይና ጃዋር
ጦቢያን የሚገላት ጥሎ ከኦዳ ሥር፣
ሳይሆን ያልተገራው የአሩሲው ስናር
ያጋሮው ጮሌ ነው ያመነው ሙሉ አገር፡፡
ስለዚህ ጦቢያዊ አማራው በተለይ
ጦቢያን ጥሎ እንዳይገል አሙለጨላጩ ዐብይ፣
ለጃዋር ማስካካት ሳትሰጠው ጉዳይ
ሙሉ ትኩረትህን አድርግ በጮሌው ላይ፡፡
መስፍን አረጋ
[email protected]